ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
1.03K subscribers
2.92K photos
44 videos
102 files
787 links
ይኽ በፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች የሚለቀቁበት ሚዲያ ነው።
https://linktr.ee/kaletsidkizm
Download Telegram
✝️ የቅዱሳን ህይወት

#እግዚአብሔር በወደዱት በቅዱሳን ህይወት ላይ በተመስጦ የምትቆዩ ከሆናችሁ እናንተም እነርሱን እንደወደዱት ትወዱታላችሁ፡፡
በተለይም በእነርሱና #በእግዚአብሔር መካከል ባለው አስደናቂ መመሳሰል ላይ ተመስጦ የምንቆይ ከሆነ፥እርሱ ለእነርሱ እንዴት ከፍ ያለ ስልጣን እንደሰጣቸውና በራሱ ምስጢራት ላይ ተካፋይ የሚሆኑ ታማኝ ባልንጀራዎቹ እንዳደረጋቸው ለማወቅ በተመስጦ ብትቆዩ እንደ እነርሱ ትወዱታላችሁ፡፡

#የቅዱሳን_ሕይወት_አንባቢውን_ሰው_ወደ_ከፍተኛ_መንፈሳዊ_ደረጃ_ከፍ_ከፍ_ያደርገዋል፡፡
ይህ ደረጃ ከቁሳዊ እና ከዓለማዊው እንዲሁም ለስጋና ከኋጢአት በላይ ከፍ ያለ ደረጃ ነው። ስለሆነም እግዚአብሔር በውስጡ ይኖር ዘንድ ዓለምን ከሰው ልብ ያስወጣል። ማር ይስሓቅ ይህን አስመልክቶ ሲናገር " አዲስ የተተከለ ተክል ውኋ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የቅዱሳንም ሕይወት ያን ያህል አስፈላጊ ነው።" ብሏል።

#የቅዱሳን_ሕይወት_ነፍስን_ስለሚነካ_ሰውን_እነርሱን_እንዲመስል_ይጠራዋል
በቅዱስ አትናቴዎስ አማካይነት ለሮማ ሰዎች የተጻፈው የቅዱስ እንጦንስ ሕይወት በሰዎች ላይ ጥልቅ የሆነ ውጤት ስላመጣ ብዙዎች ዓለምን በመተው #ከእግዚአብሔር ጋር የንቸኝነት ሕይወት ለመኖር ናፍቀዋል። ሌላም ቢቀር በቅዱስ አውግስጦስ ሕይወት ላይ አስደናቂ ውጤት ስላመጣ ወደ ንሰሓና ወደ ምናኔ መርቶታል። ይህ ሕይወት #እግዚአብሔርን አጥብቆ የሚወድ ታላቅ ቅዱስ ሰው አድርጎ ቀይሮታል። ይህ ፍቅር ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ በመጡት ተመስጦዎቹ ውስጥ ታይተዋል።

በምድረበዳ ውስጥ የሚኖሩ ቅዱሳን መነኮሳት ሕይወትም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመንና በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ እነዚህን መነኮሳት የጎበኙ ሰዎች የጻፏቸው ጹሑፎች ይህን ያረጋግጣል። በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ ምንኩስና ሕይወት የመራ እና በእነዚህ ሰዎች ነፍሳት ላይ ታላቅ ውጤት ያመጣ ይህ ሕይወት ምንኛ ድንቅ ነው! እነዚህ መነኮሳት ሕይወታቸውን የሰጡት #ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎታቸው አማካይነት በምሥጢር ለመነጋገር ነው። እነርሱ በበረሃ ውስጥ የኖሩት ያለ ምንም ባልንጀራ ወይም መደላደል ነው፥ #ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ወዳጅነትና ፍቅር በመንፈሳዊ ደስታቸው ይረኩ ነበርና።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
https://t.me/kaletsidkzm
ሁል ጊዜ ሕሊናህን በመንፈሳዊ ነገሮች ሙላ !!

ይህን የምታደርግ ከሆነ ዲያብሎስ መጥፎ አሳብ ሊያስተዋውቅህ ሲመጣ እንኳን ደህና መጣህ የሚለው ሕሊና አያገኝም። እንደ መከላከያ መፍትሔ ይሆንህ ዘንድ ዘወትር ራስህን በሥራ ባተሌ አድርግ። ዲያብሎስ ወደ እርሱ ገብቶ የወደደውን ዘር እንዳይዘራበት ሕሊናህን ባዶ አታድርገው።

መንፈሳዊ ንባብ ሕሊናን በሥራ ለመጥመድና መጥፎ አሳቦችን ለማራቅ ብቻ ሳይሆን ሌላም ታላቅ ጥቅም አለው። ንባብ ሕሊናን በተመስጦ ሊሞላ የሚችል መንፈሳዊ ዘዴ ከመስጠቱም በላይ ተቃዋሚ አሳቦችን የሚያጠፋውንና #እግዚአብሔርን መውደድ የሚያስችለውን ስሜት በልብ ውስጥ ያጎናጽፋል።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
✝️በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ #እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!
#እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል ። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና ። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው ።
በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው ።
በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ #እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት #እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችሗል ።
እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ #ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል ። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል ። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት ። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል ።
በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ #ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል ። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ ።

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
#እግዚአብሔርን_ተስፋ_አድርግ

ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ #እግዚአብሔርም በፍጥረታቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር በዝምታ ይሠራል። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው #የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሰራ አድርገው ያስባሉ። እነርሱ #እግዚአብሔር አይሰራም በሚያስቡበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ በጥልቅ እየሰራ ነው። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ #የእግዚአብሔርን ሥራና የስራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይነቻቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል።" #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ በርታ ልብህም ይጽና #እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፡፡" መዝ 26 ፥ 14።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ጓደኛ ያበዛ ፣ መከራ አበዛ

ለወጣቶች መልክት ነው

ሁሉን ሰው መውደድ እንጂ ሁሉን ጓደኛ ማድረግ አይቻልም ፤ ደግሞም ተገቢ አይደለም ። #ሁሉን ሰው በእኩል ማየት እንጂ ለሁሉ ሰው ጓዳን መግለጥ ተገቢ አይደለም ፤ ደግሞም ጎጂ ነው ።

#በሚጠሉህ መሐል ወዳጅህን እንደምታገኘው ፤ ከሚወዱህ መሐልም የሚጠላህን ታገኘዋለህ ። ሁሉ ይወደኛል ብሎ የሚያስብ ጅል ብቻ ነው ። ሁሉ ይጠላኛል ብሎ የሚያስብም ትላንትን ያልረሳ ነው ።

#አንተ ቀድሞ ትጠላቸው የነበሩትን አሁን በጣም ትወዳቸዋለህ ፣ ቀድሞ በጣም ትወዳቸው የነበሩትን አሁን ባሰብካቸው ቊጥር ትታመማለህ ። ሰዎችም እንዳንተ ናቸው ።

#ሳያውቁህ ሊጠሉህ ይችላሉ ፣ ጥላቻ ስሜት ነውና ስሜቱ ሲሄድ እንደገና ይወዱሃል ። ይወዱህ የነበሩም ከዓይናቸው ጆሮአቸውን አምነው ሊርቁህ ይችላሉ ። #የሄደው ይመጣል ፣ የመጣውም ይሄዳል ። በዚህ ዓለም ላይና በሚመጣው ዓለም ቋሚው #መንግሥተ #ሥላሴ #ብቻ ነው ።

#እግዚአብሔርን ከማያምኑና እናምናለን ከሚሉ ግብዞች ተጠንቀቅ ። #ክርስቲያን ሁነው ጭካኔን የሚለማመዱ እንደ አርዮስ በልብ ክደው በአፍ የሚያምኑ ናቸው ። የእነዚህ ሰዎች ወዳጅነት እንደ ፍግ እሳት ነው ፣ ውስጥ ውስጡን ሂዶ መጨረሻ ላይ ያቃጥላል ።

ጻድቅ ለመምሰል ከሚሞክሩ ስጦም ውያለሁ ፣ #ስጸልይ አድሬአለሁ ከሚሉ ፣ ለወሬ እየነቁ ለቃለ እግዚአብሔር ከሚተኙ ፣ ሌሎችን ሲኰንኑ ከሚውሉ ፣ ለመናገር እንጂ ለመስማት የተፈጠሩ ከማይመስላቸው ሰዎች ጋር ያለህን ወዳጅነት እንደገና መርምረው ። #እነዚህ ሰዎች አንተን በተለያየ ነገር ተገዥአቸው ሊያደርጉህ ይፈልጋሉ ። ድራማቸውን ከነቃህበት እንደ ጠላት ያዩሃል ።

እንባ ሊያበዙ ፣ ተጎዳሁ የሚል ድርሰት ሊያነቡልህ ይችላሉ ። የሚናገሩት የተጠና የመከራ ታሪክ አላቸው ፤ ተሳስተው ከሚጎዱህ አልመው የሚጎዱህ እነዚህ ናቸውና ተጠንቀቅ። የአየር ትራፊክ ሠራተኛ ብዙ አውሮፕላኖችን አየር ላይ ደርድሮ አንዱ አንዱን ሳያይ ሲያሳርፍና ሲያስነሣ እንደሚውል እነዚህ ሰዎችም የተለያዩ ወገኖችን ለተለያየ ጥቅም የሚጠቀሙ ስልታዊ ናቸው ።

የሚደልሉላቸው ብዙ ሠራተኞች ፣ ጽድቃቸውን እያወሩ የሚከፈላቸው ሎሌዎች አሉአቸውና ተጠንቀቅ ።

#የታወቁ ሰዎችን ለማወቅ አትጣር ። ከሹም ጋር ለመታየት ጥረት አታድርግ። ከባለጠጎች ጋርም ጊዜ ለማጥፋት አትሻ ። ዝነኞችንም በቤትህ ለመጋበዝ አትከጅል ።

እነዚህ ሁሉ የነፋስ ጎረቤቶች ናቸውና ሲጠረጉ አብረህ ትጠረጋለህ ። በእነዚህ መንደር ስላደረጉት ጀብዱ ስለሚፈጽሙት በቀል እንጂ ስለ ሕይወት አይወራምና ወዳጅነታቸውን አትውደደው ። ደግሞም በሩቅም በቅርብም ውብ #እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን አትዘንጋ ።

በሥራ ሰነፎች የሆኑ ፣ በየቤቱ እየዞሩ በጸሎት ስም አድማ የሚረጩ ሰዎች አብረውህ ቢቆዩ እንኳ ስለ ሆዳቸው እንጂ ስለ ፍቅር አይደለምና ወዳጆችህን የሚያጠፉብህ እነዚህ ስለሆኑ በቶሎ ሸኛቸው ።

#አለዝዘው የሚገድሉ ረጅም ሞት ማለት እነዚህ ናቸው ። እምነት የሚመስል ግዴለሽነት ፣ ትዕግሥት የሚመስል ስንፍና እንዳላቸው ልብ በል ። #ሥራ ስትላቸው ዋናው ጸሎት ነው የሚሉና ጸሎትን የስንፍና መጋረጃ ያደረጉ ናቸውና ከእነዚህ ዘባቾች ጋር ከቻልህ ጎረቤት አትሁን ።

ገለባ እንደማይበቅል ሰነፍም ወዳጅ አይሆንም ። አፈ ቅቤ የሆኑትን ተጠንቀቅ ። #እግዚአብሔር ተናጋሪውን አሮንን ሳይሆን ኮልታፋውን ሙሴን እንደ መረጠ እወቅ ። ተናጋሪ ሰው መጨረሻው ጥፋት ነው ።

የሚያቆላምጡህን አትውደድ ፣ የስምህም ጥገኛ ሁነህ የሚያሞካሹህን አትጋብዝ ። እነዚህ ሰዎች አዝማሪ ናቸውና ለሞቀበት የሚዘፍኑ ናቸው ።

እኔ ብቻ ነኝ ያንተ ወዳጅ የሚሉህንም አትመን ። እነዚህ ሰዎች አንተን በማምለክና አንተን የፈጠሩህ በሚመስል ስሜት ያበዱ ናቸው ።

#በማምለክ ስሜታቸው ያለ አንተ የሚኖሩ አይመስላቸውም ፣ በመፍጠር ስሜታቸው እነርሱ ሳያውቁ ማንንም እንድትወድ አይፈቅዱም ። እነዚህ ሰዎች ፍቅር በሚመስል ነገር በቅኝ የሚገዙህ ናቸውና ተጠንቀቅ ።

ራስህን ነጻ ያወጣህ ቀን ለእኔ ካልሆነ ለማንም አይሁን በሚል ስሜት ሊያጠፉህ ይነሣሉ ። የጅል ጠብ ማብቂያ የለውምና እባክህ ተጠንቀቅ ።

#ለሚያደርሱብህ ጉዳትም ጸጸት አይሰማቸውም ። ምክንያቱም በፈጠሩት ላይ የፈለጉትን የማድረግ ስሜት ስለሚሰማቸው ነው ። ቆንጥር እንደያዘው ልብስ ቀስ ብለህ ተላቀቅ ።

ሌሎችን የሚያዋርዱ ሰዎች አንተን እያከበሩህ ቢቀርቡ አትመናቸው ። #ኃይለኛ ውሻ እንኳ የሚወድህ ለሌላ ውሻ ደግነት ስታደርግ ሲያይህ ነው ። ይህ ሰው የእኛ ወዳጅ ነው ብሎ አላስቀርብ ያለ ውሻ ይቀርብሃል ።

ይለዝብልሃል ። ውሻ እንኳ በሌላ ውሻ ከለካህ አንተም ሰውን በሰው ለካው ። #ባለጌ የሚሰድበውን ሲጨርስ ወዳንተ ይዞራል ። ስድብ ሥራው ነውና ። #በተሾምህበት ስፍራ አብሮ አደጎችህን ይዘህ አትሂድ ።

በር ዘግተህ ካልሆነም ከአብሮ አደጎች ጋር አትጫወት ። #ልክና ዕረፍት ያጣ ወዳጅነትን ተጠንቀቅ። እሳትን የሚያነደው እፍ እንደሆነ ሁሉ የሚያጠፋውም እፍ ነው ። ያበዱለት ወዳጅነት አድራሻው እስኪጠፋ ብን ይላል ። ሁሉን በልክ አድርገው ። የዓመቱን በዕለት አትሥራው ።

አሰቃቂ ነገርን በራሳቸው ላይ የሚናገሩትን ፣ ራሴን አጠፋለሁ የሚሉትን ሰዎች በጥንቃቄ ተመልከት ። #አንዳንዶች ኑሮ ከፍቶባቸው እንዲህ ይላሉና እዘንላቸው ።

ሌላውን እስረኛ ለማድረግና ሌላው ሲጨነቅ በመስተዋት እያዩ ለመሳቅ ፣ ሌላውን አንቅተው እነርሱ ለመተኛት እንዲህ የሚሉ ሰውን የኅሊና እስረኛ በማድረግ የሚረኩ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጋ ።

#ርኅራኄህን ካገኙት በኋላ ያሰቃዩሃል ። እነዚህ ሰዎች በጣም ራስ ወዳድ ናቸውና ሁሉን ነገርህን እንዳያራቁቱብህ ተጠንቀቅ ።

#አበድ አበድ የሚሉ ሰዎችን እብደት መታወቂያ እንዲሆንላቸው የሚፈልጉ ሰዎችን ገስሥ እንጂ አትደንግጥላቸው። እብደት ለአንዳንድ ሰው የኑሮ ቄንጥ እንደሆነ እወቅ ።

#እነዚህ ሰዎች አንድ ቀን ቀድመው ባስመዘገቡት እብደት ቤትህንና ኑሮህን ሊያወድሙ ይችላሉ ።

#ለወዳጆችህ እኩል ፊት አሳይ ፣ ለአንዱ ትንሽ ለሌላው ብዙ ነገር አታድርግ። ፍቅር አነሰብኝ የሚለው ጠላትህ ይሆናልና ።

ቢቻልህ እስከ ሞት ድረስ ወዳጅ ሁን ። #ሰዎች ከተንሸራተቱብህ ግን ዛሬ ባገኘኸው ሰው ደስ ይበልህ ።

#እግዚአብሔር ከሌለበት ወዳጅነት እግዚአብሔር ያለበት በረሃ የተሻለ ነው ። ስሜትህን ሁሉ አትግለጥ ። ሁሉ በልቡ ይንቅሃል ፣ ወይም እንደ እብድ ያይሃል ።

#ከልክ በላይም ድብቅ አትሁን ። አንዳንድ ምሥጢር ሲገለጥ የነፋስ እርግዝና ነው ። ነፋስ ሲያረግዙት ያስጨንቃል ፣ ሲወለድ ግን አይጨበጥም ። #በሆንከው ደስ ይበልህ ። ዕድገትህን ኑሮህን ቀባብተህ አታቅርብ ።

እንደውም ተደስተህ ተርከው ። የራቀህን ወዳጅ ምክንያቱን ባወቅሁት አትበል ። እርሱ የጨረሰበት ምክንያት አንተን ቂም ያስጀምርሃልና ። ደንበኛ እንኳ ሲሄድ አመስግኖ ነው ። ይህ ከደንበኛ ያነሰ ነውና ተወዉ ።

#የበታችነት ከሚሰማቸው ሰዎች ጋር አትዋል ። ምልክታቸው የበላይነት ስሜት ይሰማቸዋል ። ዓለም እየታመሰ ያለው በእነዚህ ሰዎች ነው ። ዘሬ ፣ ክብሬ ፣ ስሜ የሚሉ እነዚህ ሰዎች ናቸው ።

#ጓደኛ አታብዛ መከራህ እንዳይበዛ !!



እግዚአብሔር የሚስፈልገን ጓደኛ ይስጠን
ህዳር 29/2016 #ፃድቁ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ #እጨጌ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት አመታዊ የልደት በአል መታሠቢያ ክብረ በአላቸውእንኳን አደረሰን

👉ኅዳር ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ዘጠገሮ ልደታቸው ነው ፃድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ

👉አባታቸው #ድላሶር እናታቸው #እምነ_ፅዮን ይባላሉ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል ወላጆቻቸውም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ   

👉አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ #እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ በምን አውቀኸኝ ነው ብላ አቅፋ ሳመችውና ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ #መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 አመት ትኖራለህ ብላ ባርካው ተሰወረች

👉ከዚያችም ቀን ጀምሮ  አባ ዮሐንስ #ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኋላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ #በቅዱስ_ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ #ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም #ከአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በፆምና በጸሎት በተጋድሎ ኖረዋል 

👉ከዚኽም በኋላ #አባ_ዮሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር #በቅዱስ_ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኋላ ይገኛል

👉ሕዝቡ በተለምዶ #እጨ_ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው #እጨጌ_ዮሐንስ ነው #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ፀበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ፀበሉ ይወርዳል

👉እዛው ቆይቶ #መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው

👉የፃድቁ አባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል

👉የአባታችን ፀሎትና ልመና ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ሁሉ ይሠዉርልን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸው ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤️ 💒