Ismaiil Nuru
2.02K subscribers
181 photos
11 videos
120 files
118 links
ዘመንን እናሰልማለን እንጅ ኢስላምን አናዘምንም!
ሀሳብ/አስተያየት፦ @Ismaiilnuru_Bot
Download Telegram
ህፃን ፌቨን የፕሬዝደንት ወይም የጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ ብትሆን ገዳይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ይሆንበት ነበር።

በዚህች ሀገር ላይ እስካሁን ተፈፃሚ ሆኖ ያየነው የሞት ቅጣት አንድ ጀነራልን የገደለ ግለሰብ ነው።ጉዳዩ ታይቶ ፖለቲካዊ ጥቅም ያስገኛል ሲባል ፍርዱ ተፈፀመበት።

ከዚያ ውጭ ያሉ ሰቅጣጭ ግድያዎች ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሆኖ አልታየም።የህፃን ፌቨን ጉዳይ ሰቅጣጭነቱ ተሰምቶ የማያውቅ ከመሆኑ ጋር ግን  የሞት ቅጣት ቢበየን እንኳን ፕሬዝደንት አይፈርምም።

ምክንያቱም የባለስልጣን ልጅ ወይም ፖለቲካዊ ጥቅም የሚሰላበት ስላልሆነ ።

የሁሉም ነፍስ ዋጋ በእኩል ሚዛን የሚመዘነው በኢስላም ህግ ስር ብቻ ነው። የኸሊፋ ልጅ ሆንክ የነብይ ልጅ፥ ከገደልክ ትገደላለህ ከሰረቅክ ትቆረጣለህ! 

አንድ የመሪን ልጅ የገደለና በደሳሳ ጎጆ የሚኖር ሰው ልጅን የገደለ ሰው በኢስላም ብይናቸው እኩል ነው። 

«የማይማንን ፍርድ ይፈልጋሉን? ፍርድን ከአላህ የበለጠ አሳማሪ ማነው?፤ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች»
(አልማኢዳህ 50)

በዚህ አንቀፅ መሰረት ከአላህ ሸሪዐ ውጭ ፍትህን የሚሻ ሰው የአላህን ፍትሀዊነት አላረጋገጠም ማለት ነው።
(የኢብኑ ከሲርን ተፍሲር ይመልከቱ)

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru

#ህፃን_ፌቨን
#ሸሪዐህ
#የኢስላም_ፍትህ