Ismaiil Nuru
1.95K subscribers
162 photos
5 videos
103 files
100 links
ዘመንን እናሰልማለን እንጅ ኢስላምን አናዘምንም!
ሀሳብ/አስተያየት፦ @Ismaiilnuru_Bot
Download Telegram
ሀማስ ከኢራን ጋር የሚያደርገውን አጋርነት ለማውገዝ "የዑመርና የአቡበክር ሰዳቢዎች ጋር እየተሞዳሞደ" እያሉ ሲያወግዙ የነበሩ «ሰለፍዮች»

ቢን ሰልማን በዚህ አመት ለቀጢፍ ሺዐዎች በይፋ ሰሃቦች የሚሰደቡበት፣ ሑሰይኒያ ተእዚያ የሚከበርበትና አላህ ላይ በግልፅ ሽርክ የሚፈፀምበትን መድረክ ሲፈቅድና በወጠኒያ ወንድማማችነት ስሌት ከለላና ጥበቃ ሲያደርግ ቢያዩም ማውገዝ አይደለም ማመን አልፈለጉም።

እዛ ሰፈር ሐቅ በዞረበት እንዞራለን ማለት ይህ ነው!

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru
•••ሙገሳ በኢስላም•••

ሙገሳ የሰውን መልካም ስራ የሚያበላሽ የአንደበት ጠንቅ ነው። የሰው ልጅ መልካም ስራዎቹ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸው ዘንድ በኢኽላስ ሊሰራ ግድ ይለዋል። በሰራው መልካም መደነቅ ላይ ሲደርስ ስራው ምንዳ አልባ ይሆናል።ይህን የመደነቅ ስሜት የሚፈጥረው ደግሞ ሙገሳ የተባለ ያልተገባ ውዳሴ ነው።

ለዚህም ሲባል ኢስላም ሰውን ከፊቱ ማሞገስን ከልክሏል።ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዐ) እንደተላለፈው " የአላህ መልእክተኛ ﷺ አንድን ሰው ሲያሞግስ ሰሙት ።እርሳቸውም "አጠፋችሁት!ወይም የልጁን ወገብ ቆረጣችሁት!" አሉ።
[ቡኻሪና ሙስሊም]

ከአቡ በክረህ (ረዐ) እንደተላለፈው አንድ ሰው በመልእክተኛው ﷺ ዘንድ ስሙ ተነሳ ።ሌላ ሰውም ስለርሱ መልካምን ተናገረ። ነብዩም ﷺ እንዲህ አሉ " ወየውልህ!የጓደኛህን አንገት ቆረጥከው! " ደጋገሙት። (ቀጥለውም) አንዳችሁ ከማሞገስ ቅሮታ ከሌለው ‘እገሌን እንዲህ እንዲህ ነው ብየ አስበዋለሁ ፤ ማንነቱን የሚያውቀው አላህ ነው ፤ በአላህ ላይ ማንንም አላጠራም’ ይበል አሉ። "

[ቡኻሪና ሙስሊም]

ከነዚህ ሐዲሶች እንደምንረዳው ሰውን ማሞገስ የርሱን ስራ ማበላሸት ነው።እርግጥ ነው ሰውን የምናሞግሰው ስለምንወደው ነው።ቢሆንም የኛ ሙገሳ የርሱን ስራ የሚያበላሽ ከሆነ መተው ግዴታችን ነው። በተለይ ደግሞ የምናሞግሰው በተሞጋሹ ፊት ከሆነ ከባድ ፈተና ነው።

ሀማም ኢብኑል ሓሪስ ከሚቅዳድ (ረዐ) እንዳስተላለፉት "አንድ ሰው ዑሥማንን ማሞገስ ጀመረ ።ሚቅዳድም በጉልበቱ ተንበርክኮ በአሞጋሹ ፊት ላይ አሸዋ ይበትንበት ጀመር። ዑሥማንም "ምን ሆነህ ነው? አለው። እርሱም "የአላህ መልእክተኛ ﷺ አሞጋሾችን ስትመለከቱ በፊቶቻቸው ላይ አፈርን በትኑባቸው ብለዋል" አለው።
[ሙስሊም ዘግበውታል ]

መልእክተኛው ﷺ ሰውን ያሞገሱባቸውን ሁኔታዎች ስናይ ደግሞ፦

ረሱል ﷺ ሽርጥን በኩራት ስለሚያስረዝሙ ሰዎች ቅጣት ሲናገሩ አቡበክር "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሽርጤ ከአንድ ጉኑ ይወርድብኛል አሉ። እርሳቸውም "አንተ ከነርሱ አይደለህም" አሏቸው።
[ቡኻሪይ ዘግበውታል ]

እንዲሁም መልእክተኛው ﷺ ለዑመር (ረዐ) እንዲህ ብለዋቸዋል። " ሸይጧን አንድን መንገድ ስትገባው አያይም ካንተ መንገድ ውጭ በሌላ መንገድ የሄደ ቢሆን እንጂ" [ቡኻሪና ሙስሊም]

እነዚህን ሐዲሶች በመሰብሰብ የኢስላም ምሁራን አንድን ሰው በፊቱ ለማሞገስ ሰውየው ኢማኑ ሙሉ፣ ነፍሱ የፀዳች፣ የማይፈተን ፣ነፍስያው የማትጫወትበት መሆኑን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል።ይህን ማረጋገጥ ካልቻልን ደግሞ ማሞገስ የተወገዘና ሲበዛ የተጠላ ነው።

ስለሆነም ሰውን ማሞገስ ካለብን ተሞጋሹ በሌለበት መሆን አለበት። በአካል አጠገባችን ባይሆንም መሞገሱ ከደረሰው ካጠገባችን እንዳለ ይቆጠራል። በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ሙገሳው እርሱ ዘንድ የሚደርስ ከሆነ ያው ነው። ምሳሌ ፌስቡክ የሚጠቀምን ግለሰብ በፌስቡክ እንደማሞገስ።

አላሁ አዕለም!

@ismaiilnuru
tesfa-mequrex.png
818.7 KB
በየቀኑ መታገል ያለብን ነገር «ተስፋ መቁረጥ» እና «በአላህ ላይ መጥፎ ጥርጣሬ» ወደ ቀልባችን እንዳይገቡ መታገል ነው።

በአላህ ላይ ተስፋ የቆረጠ እንዴት ጌታው ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኖረዋል? በጌታው ላይ መጥፎን የጠረጠረስ ምን ተስፋ ይኖረዋል?

አላህ ባይኖርህም እያኖረህ ነው!
ብትወነጅልም መሃሪ ነው!
ባትሰራም ረዛቂ ነው!

ሁሌም የአላህ ስራ ሁለት አስኳሎች አሉት።ሒክማና ረሕማ! ለኛ መጥፎ የመሰለን በውስጡ የአላህ እዝነት አለበት። ለኛ መልካም ያልመሰለን ጥበቡ ከኛ ሩቅ ነው።

ሀብት ባይሰጥህ ሰብር አጥተህ በርሱ የምትከፍር ባሪያ ልትሆን ትችል ስለሆነ ይሆናል። ስለዚህ ሰጥቶ አመስጋኝ አደረገህ። ድሀ በመሆንህ ምናልባትም ሀብት ቢሰጥህ አመፀኛ ባሪያ ሆነህ እንዳትከፍር ይሆናል። ስለዚህ አሳጥቶ ታጋሽ አደረገህ!

ፀጋውን ብትቆጥር አትዘልቀውም! ላንተ ያልታየህ ስንት ፀጋ ዙሪያህን ከቦሃል! አልታይ ብሎህ እንጅ አልጎደለብህም! ታድያ በዚህ አምላክ ላይ እንዴት መጥፎን ትጠረጥራለህ! ?

«በየትኛው የጌታችሁ ፀጋ ታስተባብላላችሁ?»
(ሱረቱ ረሕማን)
ጋዛ-ዳግማዊት-ባጉዝ (2).png
1.3 MB
ሀስቡነላሁ ወኒዕመል ወኪል!
ምእራባውያን.png
119.6 KB
ምእራባውያን ፦
•ቁጥር ስፍር ከሌላቸው ሴቶች ጋር ይዘሙታሉ
•ከእንስሳት ጋር ይዘሙታሉ
•ከቤተሰብ አባል ጋር ይዘሙታሉ (ወልዒያዙ ቢላህ)
•ሶዶማዊነትን ይፈፅማሉ
(ይህ ሁሉ አልበቃ ብሏቸው ደግሞ )
•ፆታ አስቀይረው ይዘሙታሉ

ነገር ግን!
ዛሬም በሴሰኝነት የሚወነጅሉት በንፅህና አራት ሚስቶችን የፈቀደን ኢስላም ነው!

«እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው።»
(አል አዕራፍ 179)

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru
እንደተለመደው መምህሩ ገብቶ ታዳጊ ተማሪዎቹን ስለ አላማቸው ይጠይቃል። ምን መሆን ትፈልጋለህ?
ከፊሉ ዶክተር፣ ከፊሉ ፓይለት ፣ ከፊሉ ካፕቴን ወዘተ ። አብዛኞቹ ተመሳሳይ ነበሩ። መምህሩ ጥያቄውን ቀጠለ ...... ወደ አንዱ ቀረብ አለና «ያንተስ?» አለው።

ተማሪውም፦ «ዑመር ኢብኑል ኸጣብ» ሲል መለሰ ። መምህሩ ምናልባት ጆሮዬ ይሆናል ብሎ «ምን?» ሲል ደግሞ ጠየቀው ። ልጁም «ዑመር ኢብኑል ኸጣብ» ሲል ዳግም መለሰለት። ለመምህሩ አዲስ ነገር ነበር። ሰምቶት የማያውቀው የሙያ ዘርፍና ሰምቶት የማያውቀው ስም።

ልጁ ጤነኛ ለመሆኑና የአእምሮ ዝግመት ያለበት ላለመሆኑ ይህን አላማውን ሲናገር በሙሉ የራስ መተማመን (ኮንፊደንስ) መሆኑ ምስክር ነው።

መምህሩ ተማሪውን ወላጅ እንዲያመጣ ነግሮ ከክፍል አስወጣው ። ተማሪውም በቀጣይ ወላጅ ይዞ መጣ። መምህሩም ለወላጅ የነበረውን አሳወቀው። ስለተናገረው ነገር እንዲያብራራለትም ጠየቀው። ለልጁ የበቃ ወላጅ ምን ይቸግረዋል?ስለ ሰይዳችን ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) አጥግቦ አስረዳው።

"የጥፋተኛ” ተማሪ ወላጅ ሄዶ ጥፋተኛ መምህርን አረመ።ለመምህሩም ጥሩ የአእምሮ የቤት ስራ ሰጠው። ራሱን እንዲመረምርና ወደ ኢስላም እንዲሳብ ሆነ። በመጨረሻም ኢስላምን ተቀበለ።

ተርቢያን ስናውቀው ይህ ነበር

ልጅ የሚያወራው የቤትን ነው። ሐቂቃ የኛም ልጆች የነርሱም ልጆች ተመሳሳይ ነገር ካወሩ ቤታችን ውስጥ ያለው ተርቢያ አደጋ ላይ ነው። ይህን ስል ሀኪምነትን ፓይለትነትን መመኘት የለባቸውም እያልኩ አይደለም።

ግን በሶላቱ ተደራድሮ አምስቱን ባንድ ሰብስቦ የሚሰግድ ፓይለት፣ በፂሙ ተደራድሮ የሚያክም ዶክተር፣ በሒጃቧ ተደራድራ በታይት የምታስተናግድ ዶክተር ለኢስላም ምኑ ናቸው?

ታድያ የዲንን ዋጋ ሳያውቁ የዱንያ ሙያ ጥቅም ቢነገራቸው ምኑ ነው ተርቢያህ!?

ሰው የማያውቀውን ህይወት ሊኖርበት አይችልም ።ዛሬ ላይ በዲን ሳትኮተኩተው ነገ ሙስሊሙን ታደግ ብትለው ስላቅ ነው የሚሆነው።ዛሬ በልጅነቱ ከወላጆቹ ጋር ቁጭ ብሎ በቲቪ የአየር መንገድ ማስታወቂያን የሚመለከት ልጅ ነገ አድጎ ከሴቶች ጋር ፎቶ የሚነሳ ቢሆን ምን ይደንቃል?

ቢላሂ ዐለይኩም አሁን ይህ ክስተት አሁን ላይ ባሉ ኬጂዎች ውስጥ ቢሆን የተማሪዎች መሳለቂያ አይሆንም? ይህ በራሱኮ ምን ያህል በኢስላም ከአስተምህሮቶቹ የምንሸማቀቅ እንደሆነና ራሳችን ተርቢያህ እንደሚያስፈልገን ማረጋገጫ ነው።

ከጅምሩ አንድን ልጅ ስታድግ ፓይለት ዶክተር ወዘተ ትሆናለህ ብሎ ማስተማር በራሱ ተርቢያ አይደለም!

ፍትህ ሲጠፋ ፍትሕ የሚያሰፍኑ ትውልዶች የሚመጡት እነ ዑመርን የሚያውቅ ተተኪ ሲፈጠር ብቻ ነው።

(ይህ ታሪክ ድሮ ፈላ ሳለን የአቡ ቁዳማን ታሪክ የሚነግሩን ኡስታዞች በነበሩበት ጊዜ የሰማሁት ነው)
አሁን አቡ ቁዳማም ተረስቷል።ስለርሱ አፋችንን አስከፍተው ዳዕዋ ሲያደርጉልን የነበሩ ዳዒዎችም ጠፍተዋል አላህ ይመልሳቸውና!

ወማ አድራኩም መን አቡ ቁዳማህ?
አቡ ቁዳማህ ማን እንደሆነ ምን አሳወቃችሁ?

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru
formula.png
834.6 KB
አጫጭር ፎርሙላዎች

ሰሓቦች የማያውቁት ዒባዳ ሁሉ ቢድዐህ ይባላል።

ባልን ክብር የሌለው ፍጡር አድርጋ የምትመለከትና ለቢሮ አለቃዋ አክብሮት ያላት ሴት ፌሚኒስት ትባላለች።

የአላህ ብቸኛ ስልጣን በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሌላን አካል ማጣመር ሺርክ ይባላል።

አላህ በሰው ልጆች ፖለቲካ አያገባውም የሚል ሰው ሙልሒድ ይባላል።

በሁሉ ነገሯ ላይ ባሏን የምታስፈቅድ ሴት መልካም ሚስት ትባላለች ።

ዲን በፖለቲካ ውስጥ አይገባም የሚል ሰው ዐልማኒይ (ሴኩላሪስት) ይባላል።

ከኢስላም ጋር ተጋጭቶ ሰዎች የሚከተሉት አስተሳሰብ ሁሉ ጣጙት ይባላል።
ከቀናት ጁሙዐን መረጠ
ከሰዎች ሙሐመድን!

{ጌታህም የፈለገውን ይፈጥራል ፤ይመርጣልም } አልቀሰስ:68

ጁሙዐ ነው በውዱ ነብይ ላይ ሰለዋት አንርሳ!
@ismaiilnuru
እንደዚህ ዘመን ግን ኒፋቅ በአደባባይ የጎላበት ዘመን የት ይገኛል?

ሰው ሲገደል ብቻ ሸሪዐ ትዝ የሚለው ትውልድ ግን እንዴት ተፈጠረ በአላህ?

ህግ የሚኖረው ስርአት (System) ሲኖር መሆኑን ሁሉም ቀልቡ ያውቀዋል! አመቱን ሙሉ ሸሪዐዊ መንግስትን ለማቋቋም የሚታገሉ ሙጃሂዶችን በሽብር ሲከስና ሲዘልፍ ይከርምና ህፃናት በጭካኔ ሲደፈሩ /ሲገደሉ ሸሪዐ ትዝ ይለውና ስለ ፍትህ ይፅፋል!

ፍትህን ለማስፈን የሚታገሉትን እየወረፉ ሸሪዐ ቢኖር ፍትህ ይኖር ነበር ብሎ መደስኮር ኒፋቅ አይደለም!?
ለመሆኑ በዲሞክራሲ መቼ ነው የገደለ የሚገደል ሆኖ ሰውየው ይገደልልን የምትሉት? ከምራችሁ ነው ወይስ ለስላቅ?

ታሰማ ነበር ህያው ብትጣራ፣
ነገር ግን ነገሩ ሆኖ የደንጋራ፣
ተጠሪው በድን ነው ሩሕ አልባ ተራ!

ትንፋሽ ብትዘራ በእሳቱ ፍም ላይ ፣
ግልፅ እውነታ ነው ብርሃኑን ልታይ ፤

ትንፋሽህ አቅጣጫው ሆነና አመዱ ላይ ፣
ከጥቁሩ ብናኝ ውጭ የለም ከቶ ‘ሚታይ።

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru
ህፃን ፌቨን የፕሬዝደንት ወይም የጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ ብትሆን ገዳይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ይሆንበት ነበር።

በዚህች ሀገር ላይ እስካሁን ተፈፃሚ ሆኖ ያየነው የሞት ቅጣት አንድ ጀነራልን የገደለ ግለሰብ ነው።ጉዳዩ ታይቶ ፖለቲካዊ ጥቅም ያስገኛል ሲባል ፍርዱ ተፈፀመበት።

ከዚያ ውጭ ያሉ ሰቅጣጭ ግድያዎች ላይ የሞት ቅጣት ተፈፃሚ ሆኖ አልታየም።የህፃን ፌቨን ጉዳይ ሰቅጣጭነቱ ተሰምቶ የማያውቅ ከመሆኑ ጋር ግን  የሞት ቅጣት ቢበየን እንኳን ፕሬዝደንት አይፈርምም።

ምክንያቱም የባለስልጣን ልጅ ወይም ፖለቲካዊ ጥቅም የሚሰላበት ስላልሆነ ።

የሁሉም ነፍስ ዋጋ በእኩል ሚዛን የሚመዘነው በኢስላም ህግ ስር ብቻ ነው። የኸሊፋ ልጅ ሆንክ የነብይ ልጅ፥ ከገደልክ ትገደላለህ ከሰረቅክ ትቆረጣለህ! 

አንድ የመሪን ልጅ የገደለና በደሳሳ ጎጆ የሚኖር ሰው ልጅን የገደለ ሰው በኢስላም ብይናቸው እኩል ነው። 

«የማይማንን ፍርድ ይፈልጋሉን? ፍርድን ከአላህ የበለጠ አሳማሪ ማነው?፤ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች»
(አልማኢዳህ 50)

በዚህ አንቀፅ መሰረት ከአላህ ሸሪዐ ውጭ ፍትህን የሚሻ ሰው የአላህን ፍትሀዊነት አላረጋገጠም ማለት ነው።
(የኢብኑ ከሲርን ተፍሲር ይመልከቱ)

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/ismaiilnuru

#ህፃን_ፌቨን
#ሸሪዐህ
#የኢስላም_ፍትህ
Caution-line.png
1 MB
ማንም ሰው በመንገድ ላይ የአደጋ ክልል መስመር (Caution line) ተደርጎ ሲመለከት «የመንቀሳቀስ ነፃነቴ ተነፈገ»፣ «ለምን ተከለከልኩ?» ብሎ አይጮህም!

ይልቁንም ይህ እርሱን ከአደጋ ለመታደግ የተቀመጠ የክልከላ መስመር መሆኑን አውቆ መንገድ ቀይሮ በጤናማው መንገድ ይጓዛል። እንደውም «ይህ ምልክት ባይኖር ዛሬ ጉድ ሆኜ ነበር» በማለት ምልክቱን ያስቀመጠውን አካል ያመሰግናል።

አላህ ሸሪዐን ሲያስቀምጥ ጥበቡ ይህ ነው! በክልከላዎቹ ውስጥ እኛን ከአደጋ የመታደግ ጥበብ አለበት! ሆኖም ግን ሙልሒዶች የአላህ ክልከላዎች «ነፃነትን መንፈግ» እንደሆኑ አድርገው ለሰዎች ይጣራሉ! ሸሪዐ ማለት ጭቆና እንደሆነ ሊያስረዱን ይቋምጣሉ!

«ይህች የአላህ ሕግጋት ናት፤ አትተላለፏትም፡፡ የአላህንም ሕግጋት የሚተላለፉ እነዚያ እነርሱ በዳዮች ናቸው፡፡» (አልበቀራህ 229)
አስገድዶ መድፈር
ቅጣቱ በኢስላም

የኢስላም ሸሪዐ  ከቆመባቸው  አምስቱ ግቦች አንዱ የሰውን ልጅ ዘር መጠበቅ ነው። ለዚህም አላህ ዝሙትን እርምና ፀያፍ ወንጀል አድርጎታል።የወንጀለኛ መቅጫ ህግ (ሐድ)ም ተዘጋጅቶለታል።

     ስለሆነም የትኛውም በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ዝሙት አግብተው ለማያውቁ፥ ግርፋትና የአንድ አመት መባረር ሲያስቀጣ አግብተው ለሚያውቁ ደግሞ በመወገር የሚያስገድል እርኩስ ወንጀል ነው።

አስገድዶ መድፈር ባንዱ ፆታ አስገዳጅነት የሚፈፀም ዝሙት ነው። ተገዳጁ ፈልጎ ያደረገው ስላልሆነ ጥፋተኛ አይሆንም ። የዱንያም የአኺራም ቅጣት የሚይዘው አይሆንም!

አስገድዶ መድፈር ሁለት ወንጀሎችን አብሮ ይይዛል። አንዱ ዝሙትን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዝርፊያ ወንጀልን ነው። በዐረብኛው «ሒራባህ» ይባላል።

ሒራባህ ሀይልና መሳሪያን ተጠቅሞ የሰዎችን ንብረት መቀማት፣ ሽፍትነትንና ግድያን አቅፎ የያዘን ወንጀል የሚገልፅ ቃል ነው። ቁርኣን «በምድር ላይ ጥፋትን የሚያስፋፉ» በማለት በቀጥታ ገልጿቸዋል ።

አስገድዶ ደፋሪ ሀይልና ጉልበት የሚጠቀም ዘራፊ መሆኑ ግልፅ ነው።በመሆኑም ቅጣቱ የሚበየነው በሒራባህ አንቀፅ ነው። ስለሆነም ደፋሪ ቅጣቱ፦

1) በሰይፍ ይገደላል
2) ወይም  ይሰቀላል
3) ወይም እጅና እግሩን በማፈራረቅ ይቆረጣል (ቀኝ እጅ  ከግራ እግሩ ጋር ወይም ግራ እጁን ከቀኝ እግሩ ጋር)
4)  ወይም ከሀገር ይባረራል

አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦

«የእነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚዋጉ በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት መገደል ወይም መሰቀል ወይም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቆረጥ ወይም ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ በነሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው፡፡ በመጨረሻይቱም ለእነርሱ ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡»  (አል ማኢዳህ: 33)

እነዚህን ቅጣቶች በምርጫ እንዲፈፅም ለኢስላማዊ መንግስቱ መሪ መብት ተሰጥቶታል።ለህዝብና ሀገር አስተማሪ ያለውን ይተገብራል! 

በሰሞነኛው የህፃኗ አስገድዶ መደፈር ጉዳይ ላይ አብዛኞች «የገደለ ይገደል»የሚል መፈክር ሲያስተጋቡ ተስተውሏል።ነገር ግን ይህ ኢስላምን ካለማወቅ የመጣ እንጅ ግለሰቡ ህፃኗን መግደሉ ከፈፀማቸው ግፎች ምናልባትም ትንሹ ሊሆን ይችላል። በሸሪዐ ህግ ቢሆን ግለሰቡ በዚና፣በመድፈር፣ሰውነትን በማቁሰል፣እና ነፍስ በማጥፋት ተጠያቂ ይሆን ነበር።

አስገድዶ ደፋሪ ግንኙነቱን ሳይፈፅም ራሱ እጅ ከፍንጅ ቢያዝ ስላልፈፀመባት ተብሎ አይተውም።ይልቁንም ሀይል ተጠቅሞ ተደፋሪን ማፈኑ በሒራባ አንቀፅ ያስቀጣዋል ። አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው! 

የቴሌግራም ቻናል ፦ t.me/ismaiilnuru
anes.png
1.4 MB
صلوات ربي وسلامه عليه!