🕋ISLAMIC ZONE🕋
14.7K subscribers
1.53K photos
167 videos
1 file
535 links
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ሌላኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ @hanif_tube
Download Telegram
Forwarded from 🕋ISLAMIC ZONE🕋 (Ã/Š)
ህይወትህን መቀየር ፈልገህ ነገር ግን ከየት መጀመር እንዳለብህ ካላወቅ

በረሱል ﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድ ጀምር

ሸይኽ ሀቢብ ዑመር

😍😍 اللهم صلِ و سلم و بارك على سيدنا محمد ﷺ 💚🤍صلوت 😘


@Islamic_zonee
●○●○●○●○●○●○●○●○●○●○

◾️የጁመዓ ቀን ሱናዎች


♦️ገላን መታጠብ
♦️ሽቶ መቀባት ለወንዶች
♦️ሲዋክ መጠቀም
♦️ጥሩ ልብስ መልበስ
♦️ሱረቱ ከህፍን መቅራት
♦️በጧት ለጁመዓ ሶላት መሄድ
♦️በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት


اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد

http://t.me/islamic_zonee

●□●□●□●□●□●□●□●□●□●□
■ከአንተ ሁሉም ነገር ይገለልና አላህ ብቻ ከአንተ ጋር ይቀራል።
□ ሁሉም ነገር ከአንተ ጋር ይሆን ዘንድ አንተ ከአላህ ጋር ሁን።



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
አንድ ነገር ከተሰበረ በኋላ ቢጠገን እንኳ እንደ መጀመሪያው ላይሆን ይችላል። በተለይም የሰው ቀልብ! ስለዚህ እንዳማረበት ሳትሰብር ያዘው።



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ማስታወሻ፦

ነገ ሰኞ የወርሃ ሸዋል 13ኛ ቀን ነው። ከዚያም 14ኛውና 15ኛው ተከታታይ የአያመ-ል-ቢዽ ቀናቶች ናቸው። የሸዋልን ፆም የምትፆሙ ሁለቱንም ነይታችሁ ብትፆሙ በሁለቱም ትመነዳላችሁ። ነገ ደግሞ ሰኞ ስለሆነ ሸዋላችሁንም፣ አያመ-ል-ቢዻችሁንም፣ ሰኟችሁንም (በአንድ ቀን 3 ምንዳ) ታፍሳላችሁ። ኒያችሁን አሳምሩ



🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
🌟የ ወንድ ልጅ ግርማ ሞገሱ አዛን ሲሰማ ወደ መስጂድ 🕌 መቻኮሉ ነው 🌟ህይወት ከአላህ ጋር ውብ ናት !


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
በአላህ ላይ እውነተኛ መመካትን እንመካ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لو أنَّكم توَكَّلتم على اللهِ حقَّ توَكُّلِهِ، لرزقَكم كما يرزقُ الطَّيرَ، تغدو خماصًا، وتروحُ بطانًا.﴾

“እናንተ በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነ መመካትን ብትመኩ ኖሮ ወፎችን እንደሚመግበው ይመግባችሁ ነበር። ሆዷ ባዶ ሆኖ ጠዋት ትወጣና ከሰዐት በኋላ ሆዷን ሞልታ ትመለሳለች።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 2344

"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

https://t.me/islamic_zonee ☑️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጁምአ ቀን ዱአ


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
5 አውቃት ሰላት

🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ከፈጅር በኋላ

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ 

“የፈጅርን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት የሰገደ። ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 6346


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ፕሮፋይልን ፎቶ ማድረግ

➛ሙስሊም መሆን ማለት በመሰረቱ ሙሉ ስሜትን ለአላህ ብቻ ተገዥ ማድረግ ማለት ነው።

➛የሰው ልጅ ደስ ያለውን ሁሉ ያለ ምንም ገደብ ባደረገ ቁጥር ወደ ስሜት አምላኪነት ይጠጋል።

➛በመሰረቱ ያለ በቂ ምክንያት ፎቶ ማንሳትም ይሁን መነሳት በጥብቅ የተከለከለ ነው! ከከባባድ ወንጀሎችም መካከል አንዱ ነው።ሳንገደድና ለመሰረታዊ ነገሮች በጥብቅ ሳያስፈልግ ፎቶ መነሳት ክልክል ከመሆኑ ጋር እንዲሁ ያለምክንያት ሚዲያዎች ላይ ለመለጠፍ መነሳት ይቻላል ማለት በዚህ ዙሪያ የተነገሩ በርካታ ነቢያዊ ሐዲሦችን ትርጉም ማሳጣት ነው የሚሆነው።

➛ፎቶ ግራፍን ሐዲሡ አይመለከተውም የሚለው አስተያየት ተቀባይነት የሌለው ፎቶ/ምስል የተከለከለበትን ዓላማም የዘነጋ አስተያየት ነው።

➛ፎቶ ሐራም የሆነው ከአላህ ጋር መፎካከር ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ ፎቶ ግራፍ ላይ ይበልጥ ጎልቶ ነው የሚታየው።

➛ይህ እንዳለ ሆኖ ሚዲያ ላይ የሚለቀቀው ፎቶ የሴት ልጅ ፎቶ ሲሆን ደግሞ አደጋው እጅጉን የከፋ ይሆናል።ባዕድ ሴትን ማየት የዓይን ዝሙት በመሆኑ ሌሎችን ለወንጀል/ለሀጢያት ይገፋፋል።

➛ብዙዎች በትዳር አጋራቸው እንዳይደሰቱም ያደርጋል። በተለይ ውበታቸውን ለማሳየት ብለው ተውበው ፎቶ የሚለቁ ሲኖሩ!ለዚህና ለመሰል መጥፎ አላማ ፎቶን የሚለቁ (ምድር ላይ መጥፎ ነገር እንዲስፋፋ በመውደድ ወንጀል አላህ ዘንድ ልዩ ምርመራና አሳማሚ ቃጣት እንደሚጠብቃቸው ቁርኣን ላይ ተነግሯል) ችግሩ በዚህ ብቻም አያበቃም፣ሚዲያ ላይ ፎቶዋን የምትለጥፍ ሴት አላህን የማይፈሩ ሰዎች ፎቶዋን ከዛ ላይ አንስተው በተለያየ መልኩ አቀናብረው ክብሯ ላይም ችግር ሊያደርሱባት ይችላል!
ስለዚህ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ !አስበሽ ተራመጂ! በስሜት አትነጂ! ሚዲያን ለመልካም ዓላማ እንጂ አትጠቀሚ!

ሐያእ የ አንድ ሙስሊም ትልቁ መለያ ነው


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
አንድ አባት ሴት ልጁን ውድ በሆነ ሆቴል ራት ጋበዛት....

ከሆቴሉ ባልተቤት ጋር በመነጋገር  ከፊት ለፊታቸው የተለያዩ  ያማሩና ጣፍጭ ምግቦች እንዲያስቀምጥ ነገረው ።

ከትንሽ ደይቃ ብኋላ የሆቴሉ ባልተቤት የተለያዩ ጣፍጭ ምግቦችንና
የተሸፈነ ምግብ ይዞ መጣ..

ልጂቱም ከፊት ለፊቶ የተቀመጡትን ምግቦች
መመልከት ጀመረች  በእቃ የተሸፈነው  ምግብ
ይበልጥ ሳባትና ልትከፍተው ስትል አባቷ ከለከላት ....!

አባቷም ከፊት ለፊትሽ በርካታ ጣፍጭና የሚያማምሩ ምግቦች እያሉ የተሸፈነውን ለምን መክፈት ፈለግሽ ሲል ጠየቃት...?

ልጂቱም የተሸፈነ ስለሆነ በውስጥ ያለው ያማረና የተሻለ ጥፍጥና ይኖረዋል  ብየ ስላሰብኩ ነው ስትል መለሰች

አባቷም ፈገግ አለና እንዲህ አላት
በሒጃብ ለምን እንደምሸፍንሽ አወቅሽ!

ልጂቱም ወደ መሬት እየተመለከተች አባቷ ያላት ገባት !

ከዛ ብኋላ ምርጥ የተሸፈነ ምግብ ሆነች!

ሒጃብ ነገራቶች ለማክበድ ሳይሆን በአጭሩ
መደበቅ ያለበት ተደብቆ ማየት ያለበት እንዲያይ ነው ።


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ(33)

"ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?!"
ሱረቱል ፉሲለት; 33


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ሁላቹም ማንበብ ያለባቹ ነገርነው እንዳያመልጣቹ አህባቢ ገራሚ የቀብር ዝግጅት😭😭



በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ።

እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት።

እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል።

እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት....

ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?!

ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው

ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ።

አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?!

ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።"

ዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ ናቸው የፃፉት ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር ብታደርጉላቸው እና ከእነሱ ውስጥ አንድ ሰው ቢለወጥ የአጅሩ ተካፋይ ናቹ ባረከላሁ ፊኩም


🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
በሀሜት ለተጠመዳችሁ❗️

ከክፉ መጨረሻ ተጠንቀቁ! ሞት  በድንገት ይመጣልና።
ምናልባት በሰዎች መካከል መለያየትና መነታረክ እንዲፈጠር ወሬ በማቀባበል  እየተሯሯጣችሁ ፍጻሜያችሁ ይሆናል። በሞታችሁበት ነገር ላይ ደግሞ የውመል ቂያማ ትቀሰቀሳላችሁ።

🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋
ሰበር ዜና ! ተክቢር አላሁ አክበር!!!


እንደ የዓለም ዑለማዎች ህብረት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ዘገባ የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ጀምሮ ሌሎች የዓለማችን ሀገራቶችን ሳይጨምር በፈረንሳይ ብቻ 17 ሺህ ሰዎች ኢስላምን መቀበላቸውን አስታውቀዋል።

"እርሱ ያ መልዕክተኛውን በቀጥተኛው መንገድና በእውነተኛው ሀይማኖት ላይ የላከው ከሀይማኖቶች ሁሉ በላይ ይፋ ይሆን ዘንድ ነው፣ ከሀዲያን ቢጠሉም እንኳን፤"




🕋🕌@islamic_zonee🕌🕋