Intrance result.neaea.gov.et
2.79K subscribers
601 photos
32 videos
302 files
649 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
ስለ ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም ” - ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪ ወላጆችና ከተማሪዎች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ስለተጠየቀበት የበየነ መረብ (ኦንላይን) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን ጠይቋል።

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን አሉ ?

“ ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) ይሰጣል።

በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ።

የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ።

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦
- በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ 
- በሲቪል ሰርቪስ
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 
- በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ
- በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ።


እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ።

የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ።

በወረቀት የሚወስዱት ዩኒቨርሲቲ ነው የሚገኙት በባለፉት ሁለት አመታት እንደተሰጠው ማደሪያቸውም፣ መዋያቸውም፣ መፈተኛቸውም እዛው ይሆናል። አድረው ሲጨርሱ ነው የሚወጡት።

በኦንላይን የተመደቡት ግን ውሎ ገብ ነው። ተፈትነው ወደ ቤታቸው ሂደው አድረው ተመልሰው በጠዋት መጥተው ይፈተናሉ። ” ብለዋል።

የተፈጠረው ውዝግብ ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ “ የተፈጠረ ነገር የለም። በድብልቅ መንገድ እንደምንጥ ታሳቦ ነበረ። እሱን ነበር ስንለማመድ የነበረው ” ነው ያሉት።

“ አሁን More እርግጠኛ በተኮነበት መፈተኛ ጣቢያ (ከላይ በተገለጹት) ብቻ ይሰጣል። ” ሲሉ አክለዋል።

ትምህርት ቤቶች “ ቀርቷል ” ሲሉ ተስተውለዋል፤ ታዲያ መረጃውን ከየት አግኝተውት ነው ? ቢሮው ትዕዛዝ አውርዶ ነበር ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል።

ዶ/ር ዘላለም ፥ “ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ጣቢያቸዎች እንደሚሰጥ ነገር ግን ሌሎች ጣቢያዎች የነበሩት፣ በእነርሱ ላይ ካልሆነ በስተቀር ' ቀርቷል ' ተብሎ የተሰጠ መግለጫ አልነበረም ” ብለዋል።

አክለው፣ “ ለሙከራ ስንሞክርባቸው የነበሩ እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ተማሪዎችና ቤተሰብ ላይ እንግልት እንዳይሆን እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ቀንሰናል ” ያሉት ኃላፊው፣ “ በእርግጠኝነት ሊፈጸሙባቸው ተብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተወሰኑት ላይ ግን ተወስኗል ” ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው እንደቀረ ያስተላለፈው መልዕክት ነበር ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር እኮ በገጹ ላይ አስታውቋል እንዳልቀረ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም። በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተይዘው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ተቀንሰዋል ” ብለዋል።

ቢሮዎ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጻፈው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ደብዳቤ (ከላይ ተያይዟል) የቢሮ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፥ “አዎ። ትክክል ነው !! ” ብለዋል።

“ አሁን ባልናቸው ጣቢያዎች ማለት ነው። በፊት በ153 ጣቢያዎች ብለን ነበር ይዘን የነበረው አሁን ግን በእርግጠኝነት ይሳካል የተባለበት ቦታ ከላይ የተጠቀሱት ጣቢያዎች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት ተማሪዎች ከምንም አይነት ውዢምብር ራሳቸውን ጠብቀው ከቢሮውና ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወርዱ መመሪያዎች ብቻ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopia


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መርሃግብር

መልካም እድል


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ከቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደሚፈተኑበት ተቋማት ገብተዋል።

ዛሬ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኞች ገለፃ ሲሰጡ የዋሉ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነገ ኦረንቴሽን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ይሰጣል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በትግራይ ክልል በወረቀትና በበይነ መረብ እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ተጀምሯል።

ፈተናው በክልሉ በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 2-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ከ31 ሺህ በላይ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ዙር ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡

ተፈታኞች በአጠቃላይ የፈተና ዲሲፕሊን ዙሪያ ገለፃ በተቋማቱ ተደርጎላቸዋል፡፡


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ 2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል::

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

https://aa.ministry.et/account#/student-result

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219  በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸው ተገልጿል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
#ማለፊያ_ነጥብ

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸው ተገልጿል።

ውጤት ለመመልከት👇
https://aa.ministry.et/account#/student-result


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በወረቀትና በኦንላይ የሚሰጠውን የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ይሆናል።

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ ከ 9-11/ 2016 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በበይነ መረብ (Online) እና በወረቀት ፈተናው ይሰጣቸዋል።

ፈተናውን የምትወስዱ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በሙሉ መልካም እድልን እንመኝላችኋለን።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
1 ሰው invite ስታደርጉ 75 Star ማግኘት ይፈልጋሉ?

100 Star የ 112.99 ብር ነው 🔥🔥🔥

ቴሌግራም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል አዲስ Telegram Stars የተሰኘ Gift Coin አምጥቷል።

ከስር የተቀመጠውን ሊንክ ተጭናቹ ስታርት ስትሉት 3 የሚሰሩ task አሉ ስራውን ስትሰሩት 170 star በቀላሉ ታገኛላቹ። 

አሁኑኑ ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት Start በማለት ስራውን ይጀምሩት👇👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/major/start?startapp=1584418890

👑Help me to become best of the best in @Major and get some Stars!
75⭐️ invite bonus for you
200⭐️ if you are Premium Major