Intrance result.neaea.gov.et
1.35K subscribers
544 photos
29 videos
301 files
549 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች ይወስዳሉ - የትምህርት ሚኒስቴር

የዘንድሮ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 701 ሺሕ 489 ተማሪዎች እንደሚወስዱ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ዘንድሮ በሚሰጠው ድብልቅ የ12ኛ ክፍል መልቂያያ ፈተና ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ፈተናው በወረቀት እና በኦንላይን እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን እንደሀገር የአቅም ችግር በመኖሩ ምክንያት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት አለመቻሉን ተገልጿል።

በመሆኑም የዘንድሮ የፈተና አሰጣጥ በትምህርት ቤቶች አቅም የሚወሰን ይሆናል ነው የተባለው።

የኦንላይን ፈተና ውጤትን በቶሎ በማሳወቅ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፈተናን ለመስጠት፣ ስህተትን በመቀነስ እና በሌሎችም ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል።

ከኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ያሉ ስጋቶችን ለመቀነስ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር በመስራትና የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር ጀነሬተሮችን በፈተና መስጫ ተቋማት ማሟላት መቻሉ ተገልጿል።

ተማሪዎች ለኦንላይን ፈተና የመፈተኛ ኮምፒውተር እንዲያመጡ ተገደዋል የሚባለው ወሬ እውነትነት የሌለውና ከትምህርት ሚኒስቴር እውቅና ውጪ እንደሆነም በመግለጫው ተነስቷል።

#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የሰኔ_2016_ዓም_የፈታኞች_ምደባ_240609_204745.pdf
116.1 KB
የመውጫ ፈተና ፈታኞች ምደባ ‼️

በዚህ ወር የ 2016 የመውጫ ፈተና በሁሉም ግቢዎች ይሰጣል። በዚህም የተነሳ የፈታኞች ምደባን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
Forwarded from ዩኒቨርስት info
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመውጫ ፈተና (Exit Exam)  የተመለከተ አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል ሲሆን የይለፍ ቃል(Password) እንዴት እንቀይራለን የሚለውን ጨምሮ በፈተና ወቅት መከተል ያሉብንን መሰረታዊ ነጥቦች ይዳስሳል።

መልካም እድል እንዲገጥማችሁ እና እንዲገጥመን እየተመኘን በፈተና ወቅት በመረጋጋት የተሰጠንን ፈተና በፍፁም ጨዋነትና መልካም ስነ ምግባር እንድንጨርስ ከወዲሁ አደራ ለማለት እንወዳለን።

❤️

#Milestone #ThankYou #OnwardAndUpward #crypto #btc #memetoken #memecoin #hamster #hamsterkombat #taptap #clicker #game #p2e


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ከባለድረሻ አከላት ጋር መክሯል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የትምህርት ሥርዓቱ ን ለማሻሻል በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለ ምንም ችግር እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፌዴራል እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ፈተናው የተሳካ እንዲሆንም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው÷የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ተቋሙ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከክልል የትምህርት ቢሮዎችና የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን÷በቀጣይ ሁሉንም ተማሪዎች በኦንላይን ለመፈተን ሙከራ ይደረጋል መባሉን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC
#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የዘንድሮ የ 12ኛ ክፍል ፈተና ችግር እንዳይገጥመው ካሁኑ ጥንቃቄ ማደረግ እንደሚያስፈልግ እየተነገረ ነው።

የ 2016 የ 12ኛ ክፍል ፈተና ከነሃሴ 3 ጀምሮ በ Online እና በወረቀት ይሰጣል። ዘንድሮ በአዲስ አሰራር የሚሰጠው ይህ ፈተና ለችግሮች እንዳይጋለጥ እና ፈተናው እንቅፋት እንዳይገጥመው በጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ተጠቁሟል።

ለፈተናው 20 ቀን የቀራ ስሆን ቤተሰቦች እና ተፈታኞች ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቁ ተብሏል።

ስለ ፈተናው አዲስ መረጃ የምትፈልጉ እና ፈተናው ከተሰራ ቡሃላ መረጃዎችን የምታገኙበት ቻናል👇

#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ(

ከሐምሌ 3-5 /11/2016 ዓ.ም ለማህበራዊ ሳይንስ

ከሐምሌ 9 -11/11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ

በቅደም ተከተል ይሰጣል!!

⛔️ተፈታኞች በቀሪ ቀናት አስፈላጊውን የስነ ልቦና ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባችኃል‼️


ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇

#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ማጠቃለያ ONLINE ፈተና

የትምህርት ሚኒስቴር ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ(online) የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወረቀት አልባ በማድረግ የዲጂታል ጉዞውን አንድ ምዕራፍ መጀመሩን ገልጿል፡፡ ይህንንም ጉዞ የተሳካ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አስታውቋል፡፡

ለተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ (URL) ከፈተናው በፊት ገብተው የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው እለት ደግሞ መፈተኛ መሆኑ ተገልጿል።
ስለሆነም ተፈታኞች ከዚህ በታች በሚፈተኑበት የፈተና ክላስተር ፊትለፊት በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመግባት መለማምድ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

እስካሁን username እና password ያለገኘ ተፈታኝ ካለ፣ ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች ስለተላከ፣ ከየትምህርት ቤቱ አስተባባሪዎች ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

ክላስተር አንድ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር፡ https://c2.exam.et 
ሲዳማ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et
ትግራይ ብሄራዊ ክልል፡ https://c2.exam.et

ክላስተር ሁለት
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et
ጋምቤላ ህዝቦች ክልል፡ https://c3.exam.et
አማራ ብሄራዊ ክልል፡ https://c3.exam.et

ክላስተር ሶስት

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
ሀረሪ ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
አፋር ብሔራዊ ክልል: https://c4.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 1
• አዳማ ከተማ: https://c4.exam.et
• አጋሮ ከተማ: https://c4.exam.et
• አምቦ ከተማ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ አርሲ: https://c4.exam.et
• ምዕራብ አርሲ: https://c4.exam.et
• አሰላ ከተማ: https://c4.exam.et
• ባሌ: https://c4.exam.et
• ባቱ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቤሾፍቱ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቦረና: https://c4.exam.et
• ቡሌ ሆራ ከተማ: https://c4.exam.et
• ቡኖ በደሌ: https://c4.exam.et
• ዶዶላ ከተማ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ባሌ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ቦረና: https://c4.exam.et
• ጉጂ: https://c4.exam.et
• ምሥራቅ ሐረርጌ: https://c4.exam.et
• ምዕራብ ሐረርጌ: https://c4.exam.et
• ሆለታ ከተማ: https://c4.exam.et
• ሆሮ ጉዱሩ: https://c4.exam.et
• ኢሉባቦር: https://c4.exam.et

ክላስተር አራት
ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2
• ጅማ: https://c5.exam.et
• ጅማ ከተማ: https://c5.exam.et
• ቄለም ወለጋ: https://c5.exam.et
• ማያ ከተማ: https://c5.exam.et
• መቱ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሞጆ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሞያሌ ከተማ: https://c5.exam.et
• ነጆ ከተማ: https://c5.exam.et
• ነቀምት ከተማ: https://c5.exam.et
• ሮቤ ከተማ አስተዳደር: https://c5.exam.et
• ሰንዳፋ በኬ: https://c5.exam.et
• ሻኪሶ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሻሸመኔ ከተማ: https://c5.exam.et
• ሸገር ከተማ: https://c5.exam.et
• ሸኖ ከተማ: https://c5.exam.et
• ምስራቅ ሸዋ: https://c5.exam.et
• ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ): https://c5.exam.et
• ደቡብ ምዕራብ ሸዋ: https://c5.exam.et
• መዕራብ ሸዋ፡ https://c5.exam.et
• ምስራቅ ወለጋ፡ https://c5.exam.et
• መዕራብ ወለጋ፡ https://c5.exam.et
• መዕራብ ጉጂ፡ https://c5.exam.et
• ወሊሶ ከተማ፡ https://c5.exam.et


ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇

#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይንና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይህንኑ የትምህርት ሚኒስቴርን ማሳሰቢያ አጋርቷል።

ተማሪዎች ከፈተናው ጋር በተያያዘ ማንኛውም መረጃ በቀጥታ ከትምህርት ሚኒስቴር #ብቻ መቀበል እንደሚገባ እያሳሰብን ተፈታኞች ከየትኛውም ያልተረጋገጠ መረጃ ታቅባቹህ ሙሉ ትኩረታችሁን የፈተና ዝግጅት ላይ ታደርጉ ዘንድ እንመክራለን።

#MoE

#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ግዴታ እና የተከለከሉ ነገሮች

1. ማንኛውም ተፈታኝ አጤሬራ፣ ስልክ፣ ሃርድ/ፍላሽ ድስክ፣ ስማርት ሰዓት፣ የጌጥ መነጽር፣ ጌጠኛ ቀለበት፣ ማጂክ ጃኬት፣ ቁልፍ ወይም ምንም ዓይነት ድምጽና ምስል
የሚቀዱ/የሚቀርጹ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡ 

2. ፈተና በሚሰጥባቸው ኮምፕዩተሮች ላይ በሚመለከተው አካል ደህንነቱ ያልተረጋገጠ የትኛውንም ዓይነት መተግበሪያ መጫን ወይም ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም  የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖ ሲገኝም የፈተና ውጤት ከመሰረዝ በተጨማሪ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ  ያደርጋል፡፡

3. ፈተና እየተሰጠ ባለበት ወቅት በማንኛውም አማራጭ የመፈተኛ ኮምፕዩተሮችን በመጠቀም የኤሌክትሮኒክ መልዕክት ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን መላክም ሆነ መቀበል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖም ሲገኝ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፈተናው የሚሰረዝ ይሆናል፡፡ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

4. ማንኛውም ተፈታኝ ከመፈተኛ ክፍል ውጭ ሆኖና ለፈተና ሥራ ተለይቶ እውቅና ከተሰጠው ኮምፕዩተር ውጭ ለመፈተን መሞከር ወይም መፈተን በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ሆኖ ከተገኘ የፈተና ውጤቱ ሙሉ በሙሉ ይሰረዛል፤ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡  

5. ለፈተና ሥራ የሚያገለግሉ የይለፍ ቀሎችን (Password) በማንኛውም ሁኔታ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ወይም ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መያዝ ወይም በቀላሉ ተገማች ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ዓይነ ስውራን ተፈታኞች ለአንባቢዎቻቸው ወይም የአካል ጉዳት ያለባቸው ተፈታኞች ለረዳቶቻቸው ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ 

6. ማንኛውም ተፈታኝ ወደ መፈተኛ አዳራሽ መግቢያ ካርድ እና ማንነቱን በግልጽ ለመለየት የሚያስችል የትምህርት ቤት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ወይም የወሳኝ ኩነት ምስክር ወረቀት ይዞ የመገኘትና ሲጠየቅም የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡ ወደ መፈተኛ አዳራሽ መግቢያ ካርድ ሳይዙ መፈተን የተከለከለ ነው፡፡

7. ተፈታኞች በሐኪም ከታዘዘ መድኃኒት ውጭ ወደ መፈተኛ ክፍል ምንም ዓይነት መድኃኒትና መድኃኒት መውሰጃዎችን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

8. ተፈታኞች ወደመፈተኛ አዳራሽ ምግብና ውሃ ይዘው መግባት የጠከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን አስቀምጠው ለፈታኝ መምህር እያሳወቁ ሲፈቀድላቸው መጠቀም ይችላሉ፡፡  
ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡ በጤና ምክንያት የግዴታ መጠቀም ያለባቸው ሲሆኑ ከመፍተኛ ከፍል ውጪ (በር አካባቢ) አስቀምጠው ለፈታኝ መምህር እያሳወቁ ሲፈቀድላቸው መጠቀም ይችላሉ፡፡

9. ተፈታኞች የተሟላ አካላዊ ፍተሻ ተደርጎና ማንነታቸው በግልጽ ተለይቶ ወደ መፈተኛ አዳራሽ የሚገቡ ይሆናል፡፡ ለዚህም የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡  

10. አካላዊ ፍተሻ ሳይደረጉ ፈተና ወዳለበት ሰርቨር እና ኮምፕዩተሮች አካባቢ ወይም ክፍሎች ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡

11. በግልጽ ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ሰው ወደ መፈተኛ ክፍሎች ይዞ መግባት እና ፈተና የሚሰራባቸውን ኮምፕዩተሮች እንዲነካካ ወይም እንዲጠቀምባቸው መፍቀድ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡



#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
Grade 12 social male students dorm placement.pdf
996.5 KB
#WachamoUniversity #Grade12

የ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ማደርያ ዶርም 👏


ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
#NationalExam

የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች መግባት ጀምረዋል።

ተፈታኞች ከትናንት ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ናቸው።

ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ይሰጣል።

በትግራይ ክልል ፈተናው ከሐምሌ 2 እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

በትግራይ በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው ተፈታኞች ናቸው ፈተናቸውን የሚወስዱት።

ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን ብሔራዊ ፈተና በወረቀት እንዲሁም የተመረጡ ተማሪዎች ደግሞ በኦንላይን እንደሚወስዱት አሳውቋል።

ዘንድሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተናው ይቀመጣሉ።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች በመስከረም ወር 2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ፈተና ይዘጋጅላቸዋል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
ስለ ዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም ” - ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪ ወላጆችና ከተማሪዎች ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ስለተጠየቀበት የበየነ መረብ (ኦንላይን) የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱን ጠይቋል።

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን አሉ ?

“ ፈተና በሁለት አይነት መልኩ (በኦንላይንና በወረቀት) ይሰጣል።

በኦን ላይን የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲ ላይ ተመድበው የነበሩ አብርሆት ላይብረሪና ሁለት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይሆናሉ።

የተቀሩት ግን በሁሉም በግልም በመንግስም መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩ ት/ቤቶች ሆኖ በተመደቡበት (ድልድል የወጣላቸው ት/ቤቶች ያውቃሉ) መሠረት ፈተናውን በወረቀት ይወስዳሉ።

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱት፦
- በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ 
- በሲቪል ሰርቪስ
- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 
- በአዲስ አበባ ሳይንሰና ቴክኖሎጂ
- በጳውሎስ ሚሊኒየም የተመደቡ በዚያ ይወስዳሉ።


እንዲሁም፣ በአብርሆት ላይብረሪ ላይ የተመደቡ ተማሪዎች፣ የሁለቱ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኦንላይን ይወስዳሉ።

የቀሩት ግን በሌላ መፈተኛ ጣቢያ ተመድበው የነበሩት ስለታጠፈ በወረቀት ይወስዳሉ።

በወረቀት የሚወስዱት ዩኒቨርሲቲ ነው የሚገኙት በባለፉት ሁለት አመታት እንደተሰጠው ማደሪያቸውም፣ መዋያቸውም፣ መፈተኛቸውም እዛው ይሆናል። አድረው ሲጨርሱ ነው የሚወጡት።

በኦንላይን የተመደቡት ግን ውሎ ገብ ነው። ተፈትነው ወደ ቤታቸው ሂደው አድረው ተመልሰው በጠዋት መጥተው ይፈተናሉ። ” ብለዋል።

የተፈጠረው ውዝግብ ምንድን ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፥ “ የተፈጠረ ነገር የለም። በድብልቅ መንገድ እንደምንጥ ታሳቦ ነበረ። እሱን ነበር ስንለማመድ የነበረው ” ነው ያሉት።

“ አሁን More እርግጠኛ በተኮነበት መፈተኛ ጣቢያ (ከላይ በተገለጹት) ብቻ ይሰጣል። ” ሲሉ አክለዋል።

ትምህርት ቤቶች “ ቀርቷል ” ሲሉ ተስተውለዋል፤ ታዲያ መረጃውን ከየት አግኝተውት ነው ? ቢሮው ትዕዛዝ አውርዶ ነበር ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል።

ዶ/ር ዘላለም ፥ “ በዩኒቨርሲቲዎችና በሌሎች ጣቢያቸዎች እንደሚሰጥ ነገር ግን ሌሎች ጣቢያዎች የነበሩት፣ በእነርሱ ላይ ካልሆነ በስተቀር ' ቀርቷል ' ተብሎ የተሰጠ መግለጫ አልነበረም ” ብለዋል።

አክለው፣ “ ለሙከራ ስንሞክርባቸው የነበሩ እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ተማሪዎችና ቤተሰብ ላይ እንግልት እንዳይሆን እርግጠኛ ያልሆንባቸውን ቀንሰናል ” ያሉት ኃላፊው፣ “ በእርግጠኝነት ሊፈጸሙባቸው ተብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ የተወሰኑት ላይ ግን ተወስኗል ” ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የበየነ መረብ (ኦንላይን) ፈተናው እንደቀረ ያስተላለፈው መልዕክት ነበር ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ “ ትምህርት ሚኒስቴር እኮ በገጹ ላይ አስታውቋል እንዳልቀረ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በሙከራ ላይ እኛ ያጠፍናቸው ጣቢያዎች አሉ እንጂ ፈተና ይቀራል ብለን የሰጠነው መግለጫ የለም። በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተይዘው የነበሩት በተለያዩ ምክንያቶች ተቀንሰዋል ” ብለዋል።

ቢሮዎ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ጻፈው ተብሎ ሲሰራጭ የነበረው ደብዳቤ (ከላይ ተያይዟል) የቢሮ ነው ? ለሚለው ጥያቄ ፥ “አዎ። ትክክል ነው !! ” ብለዋል።

“ አሁን ባልናቸው ጣቢያዎች ማለት ነው። በፊት በ153 ጣቢያዎች ብለን ነበር ይዘን የነበረው አሁን ግን በእርግጠኝነት ይሳካል የተባለበት ቦታ ከላይ የተጠቀሱት ጣቢያዎች ብቻ ናቸው ” ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በተቀመጠው መርሀ ግብር መሠረት ተማሪዎች ከምንም አይነት ውዢምብር ራሳቸውን ጠብቀው ከቢሮውና ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወርዱ መመሪያዎች ብቻ ተረጋግተው እንዲፈተኑ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopia


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና መርሃግብር

መልካም እድል


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ከቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደሚፈተኑበት ተቋማት ገብተዋል።

ዛሬ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኞች ገለፃ ሲሰጡ የዋሉ ሲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነገ ኦረንቴሽን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ይሰጣል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በትግራይ ክልል በወረቀትና በበይነ መረብ እየተሰጠ ያለው ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና ተጀምሯል።

ፈተናው በክልሉ በሁለት ዙር ከሐምሌ 2-12/2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ራያ፣ አዲግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ፈተና ከሐምሌ 2-5/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ከ31 ሺህ በላይ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዚህ ዙር ለፈተና እንደሚቀመጡ ይጠበቃል፡፡

ተፈታኞች በአጠቃላይ የፈተና ዲሲፕሊን ዙሪያ ገለፃ በተቋማቱ ተደርጎላቸዋል፡፡


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
የ 2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል::

ተማሪዎች ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ፡፡

https://aa.ministry.et/account#/student-result

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219  በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸው ተገልጿል።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
#ማለፊያ_ነጥብ

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9% ያህሉ 50% እና በላይ ማምጣታቸው ተገልጿል።

ውጤት ለመመልከት👇
https://aa.ministry.et/account#/student-result


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በወረቀትና በኦንላይ የሚሰጠውን የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀምረዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ይሆናል።

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ ከ 9-11/ 2016 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት በበይነ መረብ (Online) እና በወረቀት ፈተናው ይሰጣቸዋል።

ፈተናውን የምትወስዱ የሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በሙሉ መልካም እድልን እንመኝላችኋለን።


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
#shere & #join
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor