Intrance result.neaea.gov.et
2.81K subscribers
610 photos
33 videos
302 files
658 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ መሰረትም ፦

- ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣

- የተማሪዎች ምረቃ በዓል፣

- የሪሜዲያል ፈተና ውጤት አያያዝ በተመለከተ ቅያሪ መደረጉን ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የተላከውን ደብዳቤ #ትክክለኝነት ከሚመለከታቸው አካላት አረጋግጧል።

በዚህም ፦

- በ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ፤ ተቋማት ፊተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 30 ከመቶ፣ #በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 70 ከመቶ) ተደምሮ በድምሩ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

- በ2015 ዓ/ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃንና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡት ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማእከላት ውስጥ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 8 ባሉት ቀናት ተሰጥቶ ውጤት ሐምሌ 10 ቀን የሚገልጽ ይሆናል ተብሏል።

- የተማሪዎችን ምረቃ በተመለከተ ከሐምሌ 11 እስከ ሐምሌ 16 ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ማካሄድ የሚቻል መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የሚሳተፉት የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች #ብቻ ናቸው ብሏል።

- የ2015 የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 16 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ሥራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ ‼️
↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️ ↘️
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#NationalExam

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።

ተቋማቱ አጠቃላይ ያሉበትን ደረጃ እየገመገሙ ናቸው።

ፈተናው የተሳለጠ እንዲሆን ተቋማት በዚህ ሳምንት ተመራቂ ተማሪዎቻቸውን በማስመረቅ በቶሎ ይሸኟቸዋል።

ከሐምሌ 16 ጀምሮ ተቋማት ለ12ኛ ክፍል ፈተና #ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቡ አይዘነጋም።

ከትምህርት ምዘናና ፋተናዎች አገልግሎት ባገኘነው መረጃ መሰረት ፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሐምሌ 16 -17 / 2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ፤ ሐምሌ 18 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣቸዋል፤  ከሐምሌ ከ19 - 21/2015 ፈተናው ለ 3ት ቀናት ይሰጣቸዋል ፤ ሐምሌ 22-23/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ሐምሌ 22 -23/2015 ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ፤ ሐምሌ 24/2015 የፈተና ኦረንቴሽን ይሰጣል ፤ ከሐምሌ 25 -28/2015 ፈተናው ለአራት ቀናት ይወስዳሉ ሐምሌ 29-30/2015 ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።


➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
#Share  #share🙏🙏🙏🙏🙏
Share & Support Us
👇👇👇👇👇👇👇👍
https://t.me/intrancresult
https://t.me/intrancresult
#Result ከ ጥዋቱ 1 ሰዓት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡ 
    
👉 በዌብ ሳይት፡- eaes.et
👉 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
👉 ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ፤ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎቹ እና ወላጆች በማመሳሰል ውጤት እንገልጻለን ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተለልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

እንዴት ውጤት ልመልከት ?

በዌብ ሳይት ለማየት ፦

1. eaes.et ብለው ብሮውዘር ላይ ይጻፉ
2. በመቀጠልም በሚመጣው ገጽ ላይ የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) እና የመጀመሪያ ስም ይጻፉ
3. Check Result የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማግኘት ይችላሉ።

በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ፦

1. 6284 የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ብቻ ጽፎ አንዴ ብቻ በመላክ መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ።

በቴሌግራም ቦት ፦

1. @eaesbot ይፈልጉ

2. የሚመጡ አማራጮችን በመከተል የአድሚሽን ቁጥር (ሬጅስትሬሽን ቁጥር) ያስገቡ በመቀጠልም መልስ እስኪያገኙ ይጠብቁ፡፡

ላልሰሙ JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇👇🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
@TheRsultBot
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፈተና መቼ ይሰጣል ?

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል።

ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው።

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው።

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል።

በሌላ በኩል ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሬሜዲያ ተማሪዎች ከታህሳስ ወር ጀምሮ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።

ተማሪዎቹ የትምህርት ጊዜያቸው እያለፈ እንደሆነና አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፉ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅሬታ አቅርበዋል።

70% ፈተናው በሰኔ ወር ይሰጣ መባሉ ደግሞ እንዳስጨነቃቸው ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
- የነዚህ ልጆች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?
- ከዚህ በኃላ መቼ ተጠርተው ተምረው ለፈተና ይቀርባሉ ?
- ለምን ምቹ ሁኔታ ከሌለ ቀደም ብሎ ሌላ ግቢ አይመደቡም ነበር ?
-  አሁን መፍትሄ ምንድነው ? የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች በተደጋጋሚ በድምጽ እና በፅሁፍ ለማናገር ጥረት ቢያደርግም #ቁርጥ ያለ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

በቀጣይም ጥረቱን ይቀጥላል።

ዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ካገኘ ያቀርባል።


ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
👇 👇 👇🙏🙏🙏☘️☘️
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
ትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ 12ተኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በኦንላይንና በወረቀት እንደሚሰጥ መግለጹ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይህንኑ የትምህርት ሚኒስቴርን ማሳሰቢያ አጋርቷል።

ተማሪዎች ከፈተናው ጋር በተያያዘ ማንኛውም መረጃ በቀጥታ ከትምህርት ሚኒስቴር #ብቻ መቀበል እንደሚገባ እያሳሰብን ተፈታኞች ከየትኛውም ያልተረጋገጠ መረጃ ታቅባቹህ ሙሉ ትኩረታችሁን የፈተና ዝግጅት ላይ ታደርጉ ዘንድ እንመክራለን።

#MoE

#MoE
ተጨማሪ ትምህርታ መረጃ 👇👇👇👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor