Intrance result.neaea.gov.et
1.3K subscribers
512 photos
29 videos
299 files
534 links
መረጃዎች ምንጫቸውን ሳንጠቅስ አናጋራም!

ወቅታዊ ፈጣንና ታማኝነት ያላቸውን ት/ተዊ ቴክኖሎጂ፤ ፋሽንን ጨምሮ የመዝናኛ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ለማግኘት፤ ዛሬውኑ በመቀላቀል ራሶን ከዘመኑ ጋር ያዘምኑ፤ የአዋቂ ማህበረሰብ አካል ይሁኑ።

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
@intrancresult
ሀሳብ @TheRsultBot
Download Telegram
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ #ኢፕድ


ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ! 👇 👇 👇
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞችን በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በክልሉ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለሚወስዱ ከ53 ሺህ በላይ ተማሪዎች የቲቶሪያል ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ጥራት ኤጀንሲ ገልጿል፡፡

በክልሉ በሁለት ኮዶች የሚሰጠው የ2016 ዓ.ም ፈተና፤ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና ዘንድሮ ትምህርታቸውን ተከታትለው የሚፈተኑትንም ያካተተ መሆኑን የኤጀንሲው ዳይሬክተር ታደሰ ካሕሳይ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ከ53 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ ተፈታኞችን በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ለመፈተን ከተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ በክልሉ ለሚሰጠው የስምንተኛ ክፍል ፈተና 123 ሺህ ተፈታኞች በሁለት ባች ተከፍለው ከሰኔ 11-13/2016 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ጠቁመዋል፡፡ #ኢፕድ


#MoE
ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግ
ኘት
ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
👇 👇 👇🙏🙏🙏☘️☘️
https://t.me/intrancresult
https://t.me/education_stor