መነሷህ መልቲ ሚድያ️
9.97K subscribers
306 photos
62 videos
3 files
100 links
አሰላሙ አለይኩም በዚህ ቻናል አስተማሪ የሆኑ ኢስላማዊ ግጥሞች ፣ጥቅሶች ፣አባባሎች ፣ ታሪኮች ፣ሀዲስ እና ኢስላማዊ አባባሎችን ወደናንተ ጀባ እንላለን
Download Telegram
Q1

የዑመር ረ.ዐ ልጅ እና የረሱል ሰ.ዐ.ወ ባልተቤት ማን ትባላለች?

YELA
🤔71👏1
ማሻአላህ ስዊት (@fira1117)🦋 ነበር😅



ቀጣይ ጥያቄ ready
👍161
Q2…ትክሻውን ያዝ አድርገው "በዱንያ ስትኖር ልክ እንደ እንግዳ ወይም መንገድ አላፊ ሆነህ ኑር!" አሉት ረሱላችን ሰአወ ይህ ሰሀቢይ ማን ይባላል…
🥰41
የፀሀይናየጨረቃ ግርዶሽ
        ምክንያትና ህግጋቱ


ፀሀይና ጨረቃ አላህ የፈጠራቸው ግዙፍ ፍጥረታትና ትልቅ የአላህ ተዓምራትም ናቸው።ሙሉ በሙሉም ይሁን በከፊል መጋረዳቸው የአላህን ቁድራ/ሀያልነት የሚያሳይ ተግባር ነው።
የሰው ልጆች ከፀሀይና ከጨረቃ የሚያገኟቸው ፀጋዎችን የሆነ ጊዜ በጊዜያዊነት እንዲያጡ መደረጉም የአላህን ጸጋ እንዲያስታውሱ ያደርጋል። ነገር ግን በዘመናችን እንዲህ አይነት ክስተቶች በቴክኖሎጂና ሶሻል ሚዲያ መስፋፋት ምክንያት እነደቀላል ነገርና እንደመዝናኛ ይቆጠራሉ እንጂ በነቢዩ* ዘመን እንዲህ አይነት ነገር ሲፈጠር ደንግጠው በፍጥነት ወደ መስጂድ በመሄድ ጌታቸውን ነበር የሚማጸኑት!።
ከግርዶሽ መፈጠር ምክኒያት አንዱ  አላህ ባሮቹን ማስጠንቀቅና ማስፈራራት ነው።ይህም የሚሆነው ፀሀይና ጨረቃ ብርኃናቸውን ማጣታቸው ቂያማን እንድናስታውስ በማድረጉ ነው።
ቂያማ ሲቆም ፀሀይና ጨረቃ ብርኃናቸውን ያጣሉ።
إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ.. ،  وَخَسَفَ الْقَمَرُ...
የሚሉ አንቀፆች ይህን በግልጽ ያሳያሉ። ቂያማ ሲቆም ፀሀይና ጨረቃ ይወገዳሉ ፣ ብርኃናቸውንም  ያጣሉ።
ይህ እንዳለ  ሆኖ የተወሰኑ ኡለሞች  የዚህ አይነት ግርዶሽ መፈጠሩ ምድር የሆነ አካባቢ ላይ የሚቀጡ ሰዎች እንዳሉ የሚያሳይ ምልክትም ሊሆን ይችላል ብለዋል።

ግርዶሽ ሲከሰት የተለያዩ በሸሪዓህ የተደነገጉና መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ።እነዚህ ነገሮች ግን የሚደረጉት ፀሀይና ጨረቃ መጋረዳቸውን ስናይና ስናውቅ ብቻ ነው እንጂ በባለ-ሙያዎች አስቀድሞ ስለተነገረ ተከስቶ ሳይታይ አይደረጉም።
አስቀድሞ ማወቅና መነገር እንደሸሪዓህ ይቻላል። ጘይብ/የሩቅ ምስጥር ከማወቅ ውስጥ አይገባም።ምክንያቱም ጘይብ ቢሆን  ሰዎች ሊያውቁት አይችሉም ነበር።
ወቅትና ሁኔታውን አስቀድሞ ማወቅ የሚቻልበት እራሱን የቻለ እውቀትም አለው። ይህንንም ከጥንት ጀምሮ የሽርሪዓህ ምሁራን ተናግረዋል።ሆኖም ሁሌም ልክ እንደተባለው ሊሆን ይችላል ብሎ በሙሉ እርግጠኝነት ከመናገር ይልቅ "በአላህ ፍቃድ... ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል..." መባሉ በላጭ ነው።

ግርዶሽ ሲፈጠር: የሚደረጉ የተለያዩ ወደ አላህ የምንቃረብባቸው መልካም ስራዎች አሉ- በነቢዩ ዘመን ግርዶሽ ተከስቶ ፈጥነው ወደ መስጂድ ሄደው ቀጥሎ የሚጠቀሱ ነገሮችን አድርገዋል።

1/ሰላት መስገድ፣
2/ዱዓእ፣ ዚክርና ኢስቲግፋር ማብዛት፣
3/ሰደቃ መስጠት፣
4/ከቀብር ቅጣት እንዲጠብቀን አላህን መለመንና መማፀን

እነዚህ ሁሉ በሰሒሕ ሐዲሦች ተነግረዋል።
ሰላቱን በሱናው መሰረት መስገድ፣ዱዓና ኢስቲጝፋርን ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ማብዛት ተገቢና አንገብጋቢ ነው።
ሰላተል ኩሱፍ/የግርዶሽ ሰላት አፈፃፀሙ ከሌሎች ሰላቶች ይለያል፤
አንዱ ረከኣ ውስጥ ሁለት ሩኩእ ሁለት ሱጁድ  ያለበት ሰላት ነው።
ሰላተል ኩሱፍ ላይ አንዴ በቆምንበት በአንድ ረከኣ ውስጥ ሁለት ሩኩዓ ነው የምናደርገው።
ሰላተል ኩሱፍ ፈርደል-ኪፋያህ ነው ማለትም፣ግርዶሹ በተከሰበት ሀገር ላይ ያሉ ሰዎች በከፊል የመስገድ ግዴታ አለባቸው ማለት ነው፣እንደተለመዱ ፈርድ ሰላቶች ሁሉም ግለሰብ በነፍሰ-ወከፍ የመስገድ ግዴታ የለበትም ነገር ግን በየአካባቢው የተወሰኑ ሰዎች የመስገድ ግዴታ አለባቸው።ሁሉም ቢሰግድ ሱናና ተመራጭ ነው።
በመሰረቱ ሰለተል ኩሱፍን በአካባቢው ላይ ባለው ትልቁ የጁሙዓህ መስጂድ ላይ ተሰባስቦ መስገዱ ተመራጭ ነው።
ሆኖም፣ በየሰፈሩ ባሉ መስጂዶች ላይ መስገድ ይቻላል።እቤት ውስጥም በጀማዓም ይሁን በተናጠል መስገድም ይቻላል።እንደ ጁሙዓ መስጂድ መሄድ በጀመዓ ተሰብስቦ መስገድ ለሰላተል ኩሱፍ(ኹሱፍ) ግዴታ/ ሽርጥ አይደለም።

የግርዶሽ ሰላት የተገደበ ወቅት የለውም።ግርዶሹ በተከሰተበት ሰዓት ላይ ይሰግዳል።
እየተሰገደ ሳለ ችግሩ ቢቀረፍ (ግርዶሹ ቢወገድ):-ሰላቱን አጠር አጠር  አድርጎ ማጠናቀቅ ይችላል፤ እንጅ ችግሩ ተወግዷል ተብሎም ሰላቱ አይቋረጥም፣ችግሩ ተወግዶ እያለም ረዘም ተደርጎ አይስገድም።

💥የአሰጋገዱን ዝርዝር ሁኔታ ስናይ:

-
ሰላተል ኩሱፍ ሁለት (2)ረክዓህ ብቻ ነው።በያንዳንዱ ረከኣ ላይ ሁለት ሩኩእ ሁለት ሱጁድ አለ ይህም እንደሚከተለው ነው
በመጀመሪያ ኒያ ይደረጋል የትኛውም ሰላት ላይ በምላስ የሚደረግ ኒያ የለም
ውዱእ አድርገን  የምንሰግደውን ሰላት በልባችን ለይተን አውቀን አላሁ አክበር ካልን በኋላ፣ ፋቲሓ  ይቀራል፣ከዚያም ረጅም ሱራ ይቀራል የፀሀይም ይሁን የጨረቃ ግርዶሽ ሲከሰት በቀንም ይሁን በማታ የሚሰገድ ሰላት የሚቀራው ድምፅን ጮኽ ተደርጎ ነው።
ከዚያም ሩኩእ ይደረጋል ፣ሩኩኡም ረዘም ይደረጋል፣ ከዚያም ከሩኩእ ተነስቶ በድጋሚ ፋቲሓ ይቀራል፣አሁንም ሱራ ወይም አንቀፆች ይቀራሉ  ከመጀመሪያው ትንሽ አጠር ያለ በመቀጠል ሩኩእ ማድረግ፣ከዚያም ከሩኩእ ተነስቶ ኢዕቲዳል አድርጎ(ቀጥ ብሎ ቆሞ) ከዚያ ሱጁድ ይወረዳል።
ይህ አንድ ሙሉ ረክዓህ ሆነ ማለት ነው።ሁለተኛው ረክዓህ ላይም ይኸው እራሱ ነው የሚደረገው።
ሩኩዕና ሱጁድ ላይ ዘውትር የተለመደው ዚክርና ዱዓ እራሱ ነው የሚደረገው።
ተሸሁድ/አተሒያቱውም እራሱ ነው።
  ይህ ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት የነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የኩሱፍ አሰጋገድ ነው።በሒፍዙ አስረዝሞ መቅራት ያልቻለ ሰው ቁርኣን ይዞ ቢቀራ ምንም ችግር የለውም።እንዲሁም የሚችላቸውን አጫጭር ሱራዎች አያይዞ እየደጋገመ እየቀራ የማስረዘሙን ሱና ተግባራዊ ማድረግም ይቻላል።
ሰላቱ ካለቀና ከተጠናቀቀ በኃላ በጀመዓህ ከሆነ የተሰገደው አብረውን ሰዎች ካሉ ሰዎችን መምከርና መገሰፅ ተወዳጅ ይሆናል።ነቢያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰለም ሰሀቦቻቸውን ከሰላቱ በኋላ መክረዋል ፣ገስፀዋል፣ከቀብር ቅጣት እንዲጠብቃቸው ዱዓ አድርገዋል።

ሰላተል ኩሱፍን በጀመዓ እየሰገዱ ከአንዱ ረክዓህ ውስጥ የመጀመሪያው ሩኩእ ያለፈው ሰው አንድ ረክዓህ ተነስቶ ቀዷ ማውጣት አለበት።ሁለተኛው ረክዓህ ላይ መድረሱ የፊተኛውን ረክዓህ አግኝቻለሁ እንዲሉ አያደርግም።ጀመዓ ከማግኜት አንፃር የሚቆጠረው የመጀመርያው ሩኩዕ ነው።
ይህ ላይ ያልደረሰ ሰው ኢማሙ ባለበት ከሱ ጋር ገብቶ ተከትሎት ሰግዶ ኢማሙ ሲጨርስ ከላይ በተብራራው የሰላተል ኩሱፍ አሰጋገድ መሰረት አንድ ሙሉ ረክዓህ መጨመር ይኖርበታል።

የኩሱፍ ሰላት በተደጋጋሚ አይሰገድም
የፀሀይ (የጨረቃ) ግርዶሽ ተከስቶ ሰዎች አንዴ ከሰገዱ ከዚያ በኃላ ችግሩ እንኳ ባይቀረፍ ደጋግሞ መስገድ አይቻልም።ይልቅ የሚደረገው፣ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ ዚክር፣ ኢስቲጝፋርና ዱዓእ ማድረግ ፣ቁርኣን መቅራት፣ ተውበት አድርጎ ወደ አላህ መመለስ ነው።
"አላህ ይቅር ይበለን፣ ቁጣውንም ያንሳልም" ኣሚን

ትናንትና/ቅዳሜ የተላለፈውን የድምፅ ማብራሪያ መሰረት በማድረግ ወደ ፅሁፍ የተቀየረ።


©ዛዱል መ

ዓድ
3
ወማሻአሏህ አይደን @NARZMM_6 ቀጣይ የላ
👍1👏1
ከመላኢኮች ለዝናብ የተወከለው መላኢካ ማን ነው…?
🥰2
ባረከላሁፊኩም

N🦋


4ርዝ ሬዲ😘
👍8💯1
#ክብር

አላህ ሴትን ሲፈጥር አክብሮ እና አልቆ ነው የፈጠራት ላከበረውም ነገር ዱንያ ላይ መሰተርን ወይም #መሸፈንን አዘዘ

#ወንድን ደግሞ እንዲከበር አድርጎ ፈጠረው ወንድ ልጅ በተፈጥሮ የበላይነት ፈላጊ ነው ለዛም ነው ታላላቆቻችን ትዳር ለመያዝ መንገድ ስንጀምር ሴት ልጅ ባሏን እንድታከበር ደጋግመው ሚያስጠነቅቁት

ነገር ግን ተፈጥሮን ያላወቁ አዋቂ ነን ባዮች በየራሳቸው ፈርጅ ውሳኔ እየሰጡ የሴቶች እኩልነት ብለው የወንድን ክብር አቅለው እኛ ፌሚኒስት ነን ብለው መቀየር ለማይችሉት ነገር ሲፍጨረጨሩ የምናየው

ሌላኛዋም በስመ ሙስሊም ነኝ ባይ አለባበሷን ቀይራ እራሷን ያከበረች መስሏት ክብራን ምታሳጠው
በዱንያም ሆነ በጀነት መሸለምን የሻ ሰው ደግሞ ክብሩን  አውቆ አክባሪውን ያከብራል
👍3
Q4የነቢዩ ሰአወ ልጅና ባልተቤት ተመሳሳይ ስም ያላቸው ማን ይባላል
የጀነት ጠባቂ መለክ ማን ይባላል
ማሻአላህ ነበር ሃባይቢ ጥያቄዎቹ ካሁን በኋላ ይቀጥላሉ ኢንሻአላህ

about last quesion ዛሬ በኔ ቦታ
ሪድዋን ለሚባል
ሰው ዱኣ አድርጉልኝ ባለውለታችን ናቸው🦋


ኹዝ የመጨረሻው ክፍል👇

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ
👍6
🦋ኹዝ…

prt-11

ጽሁፍ- አምረን(ቢንትሳፊያ🦋)


የመጨረሻው ክፍል



ቋጨሁት! የእድሜዬን ብንክነት በመኖር አደስኩት። ያመለጡኝን ትላንቶች በዛሬ ላካክስ ሀ አልኩ። አረፈደም ዛሬ ሁሉም ቦታውን ሊይዝ አዲስ ህይወት ለመጀመር ዛሬም አረፈደም።


ከአህመድ በተፋጠጥንበት ረዩ እና ከድር ተከታትለው ገቡ።

"ሰርፕራዝማ ሲደነገጥም አይደል " አህመዲን ፈገግ ብሎ እኔ ግን አልተረጋጋውም ባለቤቴ ተረጋግቶ ሳይቀመጥ የምጥ ጅራፍ ይልጠኝ ጀመር። አህመዲን ለሁሉም ነገር ተፀፅቶና ለአላህ ብሎ ተዛምዶናል… "መን ተረከ ሊላሂ ሸይአን አወደሁላሁ ሚኑ ኸይራ…" አለኝ አልሃምዱሊላህ…





አራት ሰአት ከፈጀ ምጥ በኋላ ወንድ ልጅ ተገላገልኩ። ኡሚ በእልልታ አቀለጠችው። ረዩ ከዶ ትክሻውን ደግፎት ወደውስጥ ገቡ። ረዩን ሳየው ልቤ ጥፍት ትላለች… ዛሬ ልክ ያኔ ከአጥሩ ስር ስሰማው ሚሰማኝ መራድና መቁነጥነጥ አለ… ዛሬም ሞገሱ እጅ ያስነሳኛል… ዛሬ ቃሉ ለኔ ማር ነው ሲወጣ ሰላም የሚሰጥ… ምን ልላቹ ነው… ካደለኝ አላህ ባለቤቴን መሪዬ ማድረግ እችልበታለሁ። ሳስበው ግን የሴትነት ባህሪ ነው ዘመን እኩልነት አስመስሎ በሰጠን አጉል ኩራት ገፍተነው እንጂ! …ምን ይላል መሰላችሁ… (የንግግሩን ባለቤት አላስታወስኩም አፍወን) ሴት ልጅ ከወንድ አትበልጥም እኩልም አይደለችም! ይሄ ክብሯን ያሳንሳል ማለት ግን አይደለም ለፍቃዱ ይሁን ማለት ያስከብራል እንጂ ሌላ አይደለም። ባሌ መሪዬ ነው ግን ደግሞ ረዩን አይነት ሰው ስለሆነ ነው ለመሪነት የበቃ ስለሆነ የተሾመኝ…! ከኔ ሌላ ቀና እንዳይል ማድረግ እችላለሁ ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም እንዴት ለፍቅር መረታትና መርታት እንዳለብኝ አውቃለሁ… ረዩ ምን ያክል ይኑረው ሀብታም ይሁን አይሁን ስመኘው አላውቅም ነበር ረዩን በአካልም አላውቀውም ነበር ያሸፈተኝ ማንነቱ ነው ወንዳዊ ባህሪው ከጌታው ጋር ሊኖረው ሚችለውን ቅርርብ ሳስብ ማለልኩ በኢማኑ ነው የረታኝ በባህሪው በሃያኡ በሚያምሩ አይኖቹ አነበረም ፂሞቹንም አይቼ አልዛልኩም። ዛሬ ላይ አይስቡኝም ማለቴ ግን አይደለም… ያስቀደምኩት ሌላ ነበር አላሳፈረኝም ! አልሃምዱሊላህ

ረዩ ልጃችንን አቅፎ አዛን ያደርግ ጀመር!

አላሁ አክበር አላሁ አክበር!

እውነትም አላሁ አክበር ለውለታህ ክበርልኝ የኔ ጌታ ስለስጦታህ ምስጋና ነውና አቅሜ አልሃምዱሊላህ ስለቸርነትህ ያለኝ ሁሉ ምስክር ነው ከክብር በላይ የተከበርከው ከመላቅ በላይ የላቅከው ከንግስና በላይ የነገስከው ከሚያማሩህ ነገር ሁሉ ጥራት ይገባህ!


ስንወጣ የሰፈር ሰው በሙሉ አጀበን ቅልጥ ያለ ድግስ የተደገሰ ነበር ሚመስለው።… ስንት አለፍኩ ግን የኔው ያልከበደ በመሰጠት ያማረ ነበርና አልከበደኝም አልሃምዱሊላህ… ምኞቴ ልጄን ረዩን አስመስዬ ማሳደግ ነው ሀፊዝ አይደለሁም ግን የሀፊዝ እናት እና ሚስት ነኝ… ሷሊህ ነኝ ልል አልደፍርም ግን የሷሊህ ሰው ሚስት ነኝ ካልጠፋኝ ጥበቡ ከቆየ ከእቅፌ የሷሊህ እናትም እሆናለው!
ረዩ ባንዱ እጁ አቀፍ አድርጎኝ በሌላ እጁ ልጃችን ሷሊህን እንደያዘ ቀና ብዬ አየሁት። ጠጋ ብዬ ሽቶውን ማግኩት! ናፍቆት ፍቅር በሀላሉ ሀቅ ናቸዋ😁 ዝቅ ብሎ አይቶኝ ፈገግ አለ… አልሃምዱሊላህ…



ከ3ወር በኋላ


"ረዩ… "

"ወዬ… የሷሊሄ እናት…"

"እስኪ ንገረኝ…"

"ምን ልንገርሽ… "

"ፍቅር ይዞህ ያውቃል…?!"


"አይ አይ አንቺን ልጠይቅሽ… ፍቅር ይዞሽ ያውቃል…? "


"አዎ! "



"ምናይነት ሰው አፈቀርሽ…?"


"ጠይም… ጥርሶቹ ሚያምሩ ፂማም ወጣት…"


"ሀሀ… ተይንጂ ታዲያ ምን ተፈጠረ…"



"አገባሁታ… " ጆሮውን ጎተት እያደረግኩ
አንተስ…?



"ታውቂያለሽ… አሁን ድረስ እንደማፈቅራት አሁን ድረስ እንደማፍራት አሁን ድረስ አይኖቿን ደፍሬ ሳይ ልቤ እንደምትመታ ታውቂያለሽ አቆላምጣ ስትጠራኝ እንደምዝል… እያት እያት እንደሚለኝ ሳያት ደስ እንደሚለኝ የልጄ እናት መሆኗን ሳውቅ ከራስህ ለራስህ ስረቃት እንደሚለኝ ሰኑዬ ምን መሰለሽ ላብድ ነው😅 በቃ😂 በጣም ነው ማፈቅርሽ እኮ በአላህ… "


"በጣም ነው እንዴ ያበድከው😂😂…"


"አንቺ ምች! 😁 እኔ እኮ ከልቤ ነበር ሙድ ያዝሻ ቆይ… "



"ረዩዬ… "

"እህ…"

"እ🙄 ረዩ…"

"ወዬ እሺ እንዲ እንድል ነው…"


"በጣም ነው እሺ… (ይሄን ገምቱና ሙሉትአልችልም🫠😁)


"እሺ… አሁን ልጄን ቀስቅሺልኝ… "b


"ተወው እሱን… "


"ምን😳 ምን ማለትሽ ነው?! "


"😌it's my time…"


"okay agree😎… "


"ቲሽ አመድ😁…"

አልሃምዱሊላህ!!!

** *
* * * *
* * ** * * * * *
* * * * *
** * * * * * * *
*-*----*-****


🦋እና ምን ልላቹ ነው ዝንት አለም በድሎት ሊያኖራችሁ የሚችለውን የተቅዋ ስንቅ የሰነቀውን ምረጡ !

ሰላሙላሂ አለይኩም አምሩ ነበርኩ አትጥፉ ደግሞ በጥሩ ፖስቶች አለን🥰
👏4117👍2🔥1🥰1
#ክብር

አላህ ሴትን ሲፈጥር አክብሮ እና አልቆ ነው የፈጠራት ላከበረውም ነገር ዱንያ ላይ መሰተርን ወይም #መሸፈንን አዘዘ

#ወንድን ደግሞ እንዲከበር አድርጎ ፈጠረው ወንድ ልጅ በተፈጥሮ የበላይነት ፈላጊ ነው ለዛም ነው ታላላቆቻችን ትዳር ለመያዝ መንገድ ስንጀምር ሴት ልጅ ባሏን እንድታከበር ደጋግመው ሚያስጠነቅቁት

ነገር ግን ተፈጥሮን ያላወቁ አዋቂ ነን ባዮች በየራሳቸው ፈርጅ ውሳኔ እየሰጡ የሴቶች እኩልነት ብለው የወንድን ክብር አቅለው እኛ ፌሚኒስት ነን ብለው መቀየር ለማይችሉት ነገር ሲፍጨረጨሩ የምናየው

ሌላኛዋም በስመ ሙስሊም ነኝ ባይ አለባበሷን ቀይራ እራሷን ያከበረች መስሏት ክብራን ምታሳጠው
በዱንያም ሆነ በጀነት መሸለምን የሻ ሰው ደግሞ ክብሩን  አውቆ አክባሪውን ያከብራል
👍51💯1
ለምን አታዝኝም.....?

🧕ለምን አታዝኚም አሏት...የደስታ ምንጭ በሆነውﷲ ላይ እርግጠኛ ነኝ አለች🤌

እስካሁን ባለመውለድሽ እንዴት አታለቅሺም አሏት...

የነብዩላህ ዘከርያን ናፍቆት የካሰው ይክሰኛል አለች🫶

የምትተማመኚበት ምን አለሽ አሏት... አልወዱድ አለኝ አለች🥹🫶

ተስፋ እዳትቆርጭ ምን አደረገሽ አሏት !

የተዉበት በር ከፍቶ የሚጠብቀኝ ጌታየ አለቻቼዉ،🫶

💔ከስብራትሽ ምን አሻረሽ አሏት !

የነብዩሏሂ ኢብራሂምን ዱአ የሰማዉ ጌታ አለቻቸዉ 🫰

❤️ልብሽን ምን ሀሴት ሰጠዉ አሏት !

የረሱል ﷺ ኡመት ያደረገኝ ጌታ  አለቻቸዉ🥹🫶

ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለሏህ🫶

ከጀሊሉ በስተቀር ከጠየቁት  በላይ የሚሰጥ ማን አለ የኔ ሴት ጥንከር በይ🧕 😊
8
                     فَإِذَا بَرِقَ الْبَصَرُ
                    ዓይንም በዋለለ ጊዜ፡፡

                           وَخَسَفَ الْقَمَرُ
               ጨረቃም በጨለመ ጊዜ፡፡

                             وَجُمِعَ الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ
ፀሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፡፡


                يَقُولُ الْإِنسَانُ يَوْمَئِذٍ أَيْنَ الْمَفَرُّ
«ሰው በዚያ ቀን መሸሻው የት ነው?» ይላል፡፡

                                     كَلَّا لَا وَزَرَ
ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም፡፡

                       إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمُسْتَقَرُّ
በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
Copied
😢118
Forwarded from susu
አሁን እየቀነሰች ነው የጨረቃ ግርዶሽ ኢንሻ አላህ በዱአ እንበርታ🥰🥰
5
የኛ ውዱ ነብይ  ሰ.ዐ.ወ 🤍
እንዲህ ይላሉ.....
ዓሊም ባትሆንም ከዓሊሞች ጎን አትጥፋ
ምክንያቱም ባትሰራ እንኳን ከመጥፎ ስራ
ትርቃለህና።😊
5👍2
Forwarded from HudHud Promotion🕊
⚡️በቴሌግራም ምን አይነት እስላምክ
ቻናል ስፈልጉ ነበር፤ስለድናችን ሁሉን
አቃፍ የሆና ቻናል ይፈልጋሉ
📖🙋
🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲🐲
🤩እንደ ምርጫው መርጦ ይቀላቀሉ🤩

🤩ሀዲስ እና ቁርኣን JOIN🅰️ይንኩ
▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁ ▁
🤩የነብዩ(ሶ.ዐ.ወ)ታሪክJOIN🅰️ይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩የሰሃቦች (ረ.ዐ)ታሪክ JOIN🅰️ይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩የደጋግ ሰለፎች ታሪክJOIN🔤ይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩 ኢስላማዊ ብይንJOIN🔤ይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩ጥያቄዎችእናመልሶችJOINይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩እስላማዊ ህይወት JOIN 🔤ይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩እስላማዊአስተምህሮJOINይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩ሴቶች በእስልምናን JOIN🅰ይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🤩 ማራክ ንግግሮች JOIN🅰️ይንኩ
━━━━━━━━━━━━━━━━━

💥🥶🥶🥶 📌 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🟠
        🪶🪶🪶🪶🪶
🅰️🅰️🅰️🅰️  :-@HudHud_waver🇵🇸
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM