La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ከ̎ነ̎ብ̎ዩ̎ ﷺ̎ የተነገሩ ለሰው ልጅ መድሃኒት የሆኑ 30 ንግግሮች
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""'"'''''''''''
1// " [ፀሐይ በመግቢዋ እስከምትወጣ ድረስ ወደ አላህ
የተመለሰ (የተፀፀተ) አላህ ይቀበላዋል ]
.
2// " [እውቀትን ፈልጎ መንገድን የገባ ሰው፤ አላህ ወደ
ጀነት የሚወስደውን መንገድ ያገራለታል]
.
3// " [ከመልካም ነገር ምንንም አትናቅ፤ ወንድምህን
በፈገግታ ፊት መገናኘት እንኳን ቢሆን]
.
4// " [ ከኔ አንድንም አንቀፅ ብትሆን አድርሱ]
.
5// " [ ወደ መልካም የተጣራ የተከተሉት ሰዎች ምንዳ
ሳይቀነስ የነሱንም ምንዳ ለሱ ይሆንለታል ፤ ወደ ጥመት
የተጣራ የተከተሉት ሰዎች ወንጅል ሳይቀነስ የነሱን
ወንጀልም በሱ ላይ ይሆናል]
.
6// " [ ከእናንተ መካከል መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይር፣
ያልቻለ በምላሱ ፣ ያልቻለ በልቡ , ይህም የእምነት
ደካማው ደረጃ ነው]
.
7// " [ ከእናንተ በላጫችሁ ቁርአን የተማረና ያስተማረ ነው]
.
8// " [ ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው እስካላመናችሁ ጀነት
አትገቡም፣ እስካልተዋደዳችሁ ድረስ አታምኑም ።
ብትሰሩት የምትዋደዱበት የሆነን ነገር ላመላክታችሁን?
በመካከላችሁ ሰላምታን አብዙ ]
.
9// " [ ከተቸገረ ሰው ላይ ችግሩን ያቀለለ አላህ በዱንያም
በአኼራም ያቀለለታል ]
.
10// " [ ሲሸጥ ፣ ሲገዛ ሆነ ሲፈርድ ይቅር ያለ አላህ
ይዘንለት]
.
11//" አንድ ባሪያ አንድን ባሪያ በዱንያ ላይ ገመናውን
አይደብቅለትም አላህ በአኼራ የደበቀለት ቢሆን እጂ]
.
12// " [ ዝምድና ከዓርሽ ተንጠልጥላ፥ የቀጠለኝ አላህ
ይቀጥለው የቆረጠኝ አላህ ይቁረጠው ;ትላለች]
.
13// " [ በእውነት ላይ አደራ ፤ እውነት ወደ መልካም
ይመራል መልካምም ወደ ጀነት ይመራል ]
.
14// " [ እኔና የቲሞችን የሚንከባከብ በጀነት ውስጥ
እንደዚህ ነን ፥ -መካከለኛዋን እና ጠቋሚ ጣታቸውን
አጣምረው እያመላከቱ]
.
15// "[ እሱ የሚወሳበትን የአላህን ቤት ያስገነባ ሰው አላህ
ለሱ በጀነት ውስጥ ቤትን ይገነባለታል]
.
16// "[ ህዝቦቼን አስቸግራለሁ ብየ ባልሰጋ ኖሮ፥ ከሁሉም
ሰላት (በፊት) በሲዋክ ባዘዝኳቸው ነበር]
.
17// "[ ሁለት ብርዳማ ሳላቶችን የሰገደ ጀነት ገባ ;
(የፈጅር እና ዓስር ሰላት)]
.
18// "[ አንድ ሰው ወንጀል ሰርቶ;ከዚያም ታጥቦ ሰላት ሰግዶ
ምህረትን አይጠይቅም ምህረት የተደረገለት ቢሆን እንጂ]
.
19// " [ አንድ ባሪያ ለአላህ ብሎ አንድ ቀን አይፆምም
አላህ ሰባ አመታትን ከጀሃነም ያራቀው ቢሆን እንጂ]
.
20// " [ ምፅዋት ስህተትን ታጠፋለች ውሃ እሳትን
እንደምታጠፋው]
.
21// " [ ከዑምራ እስከ ዑምራ በመካከላቸው ያለውን
ያስምራል; 'ትክክለኛ' ሐጅም ምንዳው ጀነት ነው]
.
22// " [በሁለት እግሮቹና በሁለት ፂሞቹ (ከንፈሮቹ) መካከል
ያሉትን ዋስትና የሚሰጠኝ ጀነትን ዋስትና እስጠዋለው]
.
23// " [ አንድ ሰው የተጠማን ውሻ አይቶ ከመጣማቱ
የተነሳ አፈር ሲልስ ተመልክቶ በጫማው ውሃ በመቅዳት
አጠጣው አላህም ስራውን ወደደለት ጀነትም አስገባው]
.
24// " [ ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሰላቷን ከሰገደች ፣
ረመዳንን ከፆመች ብለቷን ከጠበቀችና ባሏን ከታዘዘች
በፈለገችበት የጀነት በር ግቢ ትባላለች]
.
25// " ከልቡ 'ላ ኢላሃ ኢለላህ ' (ከአላህ ውጭ በእውነት
የሚመለክ አምላክ የለም ) ያለ ጀነት ገባ]
.
26// " [በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን
ያክብር ፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን
ያክብር ፤ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን
ይናገር አልያም ዝም ይበል ]
.
27// "[ ከሰዎች ሁሉ በላጩ ይበልጥ ለሰዎች ጠቃሚው
ነው]
.
28// " [ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆነህ አላህን ፍራ፥
ከመጥፎ ስራ በኃላም መልካምን አስከትል ታብሳታለች ፤
ሰዎችንም በመልካም ስነምግባር ተኗኗር]

29// " [ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሳይሆን በቁጣ ጊዜ
ነፍሱን የሚቆጣጠር ነው ]
.
30// " [ በኔ ላይ አንድን ሰላት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ
አስርን ያወርዳል ]

#SHARE
https://t.me/+MUyBNk7bHkM0Y2M0
La tehzen
🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌸🌹🌸🌹🌸🌹 🌹🌸ሁረል = ዐይን🌺🌹 ~ ክፍል ሁለት የጀነቷ አበባ ======== የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል… ‹ከጀነት እንስቶች መካከል አንዲት ሀውራ ወደ ምድር ብትመለከት ከምስራቅ እስከ ምእራብ ብርሃኗ ያንፀባርቃል ፣ ባማረ ሽታም ምድርን ባወደች ነበር። በጭንቅላቷ ላይ የምታደርገው ከዱኒያና ከውስጧ ካለ ሁሉ የተሻለ ነው› ቡኻሪ ዘግበውታል ሻሾ ከዱኒያና በውስጦ…
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

🌹ሑረል ዓይን🌹

~ ክፍል ሶስት (3)

የጀነቱ ሙሽራ የልቡ በር ተከፍቶ በሰፊ ደረቱ ላይ አስተኝቶት ንግግሯና ጨዋታዋ አስደስቶት ይስማታል። ከሑረል ዐይኗ ጋር በመሆኑ እርካታ ተሰምቶታል።


አንድ ለሊት በጀነት ውስጥ

በአላህ የእዝነት ስረገላ ላይ እየጋለብን ጉዞአችንን ቀጥለናል። የጀነቱ ሙሽራ ከወርቅ የተሰሩ ደረጃዎችን እየረገጠ ወደተዘጋጀለት ፎቅ አመራ። በፎቁም ውስጥ ከውጪ ውስጡ ከሚታይ ከውስጡ ውጩ የሚታይ ዙሪያው በከበረ ድንገይ ያሸበረቀ ጣራው በአልማዝ ያጌጠ ልዩ ወደሆነ ክፍል አቀና። በክፍሉ ውስጥ ክንፍ ያለው አልጋ አለ። ሰባት መቶ ፍራሽ ተደራርቦበታል። የብርሃኑም አንሶላ ከፍራሹ ላይ ተነጥፎበታል።


በወርቅ የተንቆጠቆጡ ካባና ጫማውን ለብሶ… በለሰለሰ የሀር ምንጣፍ ላይ እግሮቹን ዘርግቶ አናቱን ከለሰለሰ ትራስ ላይ አሳርፎ በተኛበት ቆንጆዋ ሚስቱ ሑረል አይን ዳሌዋን እያወዛወዘች መጣች። ወደሶው ሲዞር ፊቱን በጉንጮቹ ላይ እንደመስታወት ተመለከተ። ከመስታወትም የበለጠ ንፁህ ነበር። መዳፏን ሲዳብስ ከሀር የበለጠ ለስላሳ ሆኖ አገኘው። የባቷ መቅኔ ከአጥንቷና ስጋዋ በላይ ይታያል።


የውድ ሚስቱን ደረት ተደግፎ ዝርግትግት ብሎ ተኛቶል። ጣፋጭ ከሆነ አንደበቷ ማራኪ ዘፈኗን በጆሮው ስታንቆረቁረው ልቡ ጠፍቶ በደስታ ያዳምጣል።

በአልጋው ላይ አንገት ለአንገት ተቃቅፈወወ አርባ አመት ካስቆጠሩ በኃላ ጭንቅላቱን ወደ ላይ ከፍ ሲያደርግ ሌላኛዋ የጀነት ሚስቱ በፈገግታ ታጅባ ‹አንተ የአላህ ወዳጅ ለኛስ ተራ አይደረሰንምን› በማለት ትጠይቃለች። ከፍ ባለ ድምፆ ትጣራለች። እሱም ማንነቷን ይጠይቃል። እንዲህ ስትልም ትመልሳለች።

እኔ ማለት አላህ እንዲህ በማለት ከጠቀሳቸው እንስቶች መካከል ነኝ።

…وَلَدَيْنَا مَزِيدٌ

…እኛም ዘንድ ጭማሪ አልለ፡፡
[ቃፍ 35]

አልጋው በክንፎቹ ወደ እርሶ ይበራል። እዚያ እንደደረሰም መጀመሪያ እንደተመለከታት በመቶ ሺህ እጥፍ አምራ ያገኛታል። ዞማ ጸጉር ፣ ቀይ መልከ መልካም ቁመናዋ የሚማርክ በተለይ አይኗ! ዓይኖቹ ዓይኖቿን ሲመለከቱ ፈዘው ቀሩ። ከኮቡም በላይ ያምራሉ። የሚሰማው ድምፆ በደም ስሩ ሰርፆ መንፈሱን አድሶታል። ከሶ ጋርም ተቃቅፈው አርባ አመትን ያስቆጥራሉ። ከአርባ አመት ቡሃላ ጭንቅላቱን ወደ ላይ ሲያቀና የቤቱን ጣራ ሰንጥቆ የሚገባን ብርሃን ይመለከታል። በእይታው ባገኘው ብርሃን ተገርሞና ተደንቆ ጠባቂውን መላኢካ ይጠይቀዋል። መላኢካውም። ‹የዱኒያ ሚስትህ ከጀነቷ ሑረል ዐይን ጋር ተቃቅፈህ ስትመለከት ፈገግ አለች። የምታየውን ወደ ውስጥ ሰርፆ የገባው ብርሃን የፊት ለፊት ጥርሷ ያመነጨው ነው። ከአንተ ጋር በድሎት ሀገር አብራህ ትኖራለች።› በማለት ይመልስለታል።

እርሷ ወዳለችበት አቅጣጫ ያቀናል። ቀልበን በሚሰነጥቅ አንደበቷ ‹አንተ የአላህ ወዳጅ የኔ ተራ አልደረሰምን? ትለዋለች። እሱም ማንነቷን ይጠይቃታል።።እሷም ትመልሳለች ‹እኔማ አላህ እንዲህ ብሎ ከገለፃቸው መካከል አንዷ ነኝ…


ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡
[ሱጃዳህ 17]

አልጋው በሮ ያለችበት ቦታ እንደደረሰም ከመጀመሪያ ቁንጅናዋ መቶ ሺህ እጥፍ አምራ ያገኛታል።

ውጫዊ ውበቷ ይቅር……

የፊቷ ውበት ሲገለፅ ምህዋሯን ለቃ ትሄዳለች ፤ ፈገግታዋ እንደመብረቅ ብልጭታ ያበራል› ከባሏ ጋር ስትተቃቀፍ ፀሀይና ጨረቃ በጋራ ለምድር የሰጡትን ብርሃን ይመስላል።…


ጣፋጭ ህልም… ሁሁሁ

ወፍቅና ያረብ አሚን አትሉም ወይ ያ ጀምዓ…

ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ወደ ሐጅ በማድረግ ላይ ነኝ። በመንገዴ ላይ ያጋጠሙኝን ውጣ ውጣውረዶች አልፌ መካ ገባሁኝ። የአላህን ቤት በመዞር ላይ ሳለሁ አንድ ሰው ቀልቤን ሳበው። ወደ እርሱም ቀረብኩና የሚያደርገውን ዱዓ ለመስማት ጆሮዮን ቀሰርኩኝ።

«ጌታዮ ሆይ! የጓደኞቼን ሀጃ ፈፅመሃልና የኔን ጉዳይ ፈፅምልኝ። እያለ በለቅሶ ጌታውን ይለምናል። ከዚህ ውጭ ሌላ ዱዓን አይጨምርም። ምክንያቱ ምን አደሆነ ለማወቅ ብዮ ጠያቅኩት። እሱም «ከሩሞች ጋር ለመዋጋት ሰባት ጓደኛሞች ሆነን ከሀገራችን ወጣን። ሁላችን በጥላቶቻችን ተማረክን። ስለመሸ አንድ ክፍል ውስጥ አስረውን በሩን ቆልፈው ሄዱ።


በህልሜ የሰባቱ ሰማይ በሮች ተከፍተው በራፍ ላይ በእጃቸው ፎጣን የያዙ እንስቶች ቆመዋል። የጓደኞቼ አንገት ተራ በተራ በሰይፍ ሲቀላ የጀነት እንቡጥ ፅጌረዳ እንስቶች ተራ በተራ እየወረዱ በያዙት ፎጣ አንገታቸው ላይ ያለውን ደም ጠርገው ይመለሳሉ። በሩም ይዘጋል። አንድ የሰማይ በር ብቻ እንደተከፈተ ቀርቷል።


በእድሜ ከሌሎቹ አነስተኛ ስለነበርኩኝ አንድ የሮም ጦር አዛዥ አዝኖ አስለቀቀኝ። ክፋቱ የሰማይ በር ላይ ፎጣ ይዛ የምትጠባበቀኝ እንስትም እንዲህ ስትል ሰማኃት… ምነኛ ምርጥ ነገር ነው ያመለጠህ አይኔ እያየ በሩ ተዘጋ። በህልሜ ያየሁት ክስተት ጠዋት በእውን ተፈፀመ። የምታየው ዱኣም ባመለጠኝ እድል ቁጭት የተነሳ ዘወትር የሚደረገው ነው። በማለት መለሰለኝ።

ይቀጥላ ውድ የኢስላም ልጆች በአላህ መልካም መገጠም ከሆነ…

እናም ውዶቼ የመልካም ስራ ትንሽ የለውምና በመልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ይኖርብናል!!

ውድ ስጦታ ከጀነቱ ሙሽራ…

ለውድ ሚስቱ ለቆንጆዋ ንግስት ሑረል ዓይን ስጦታን ሊያበረክትላት አስቧል። ከምንም በላይ ያማረና እሷን በጣም የሚያስውባትን ውድ ጌጥ ሊሰጣት ፈልጓል።

ውድ ነገሮች ሁሉ ለውዶቻችን የተገቡ ናቸው አይደል እናማ ተከተሎኝ…

ሁለት እርምጃ እንደተራመደ አገልጋዩ ያሰበውን ከአእምሮው አንብቦ የጌጣጌጥ ማስቀመጫ የሆኑ ብዛት ያላቸው ካዝናዎችን እየከፋፈተ የሚፈልገውን እንዲመርጥ በታላቅ ትህትና ጋበዘው።

ከአልማዝ ከሉል የተሰሩት ጌጣጌጦች አፍዝዘውት ለረዥም ግዜ ሲያማርጥ ቆየ። ፈገግ አለና እፁብ ድንቅ የሆነ ከአልማዝ የተሰራ የአንገት ጌጥ በቀይና በአረንጓዴ ክፋይና ሀር የተጌጠ የፀጉር ሪቫን እንዲሁም ውብ የሆኑ ሸዋሊያና ቀለበቶችን መርጦ መያዝ ወደ ሁረል ዓይኗ ሚስቱ ሄደ።

እሷ ጋርም እንደደረሰ በስስት እየተመለከታት በፍፁም የደስታ ስሜት ተውጦ ዓይኗን እንድትጨፍን ካደረገ በኋላ ጌጣጌጦቹን አውጥቶ በአንገቷ ላይ ሐብሉን በጣቷ ላይ ቀለበቱን አጠለቀ።

ዐይኗን ልትገልጽ ስትል በእጁ ካስጨፈናት በኋላ ሸዋሊያውን አደረገላት። ምንም እንኳ ጌጣጌጦቹ በጣም ድንቅ ቢሆኑም የእርሷ ቁንጅና በቃላት ስለማይገለጽ በውበቷ የተዋጡ መሰሉ። በዕርግጥም ተውጠዋል።

አንገቷ ስር ከሳማት ቡሃላ ወደ ጆሮዋ ተጠግቶ እንዲህ አላት…
«አንቺን የመሰለች ቆንጆ ሚስት ጌታዮ ስለጠኝ ምስጋና ይገባዋል።

«ምስጋና ለአላህ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን፡፡ የገነትን ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንኾን ላወረሰን ይገባው»…
አል ዙመር =74

ይቀጥላል በአላህ መልካም ፍቃድ!

#share #ሼር

https://t.me/httpsLatahzen
በርሶ መንገድ

በርሶ የቀን ውሎ ቀኑን ቢወጥነው
በፈገግታዎ ልክ ሳቁን ቢመጥነው
ባንቱ ውብ ባህሪ ክፋቱን ቢፍቀው
በእዝነቶ ብርሃን ነፍሱን ቢያደምቀው።
የአማኝ ባህሪ ባንቱ ግብር ቢኳል
ሀሉም በታደለ የጀነትን አስኳል።

#Share #Share

https://t.me/httpsLatahzen
🌹ሃጅ ለመድርግ ላቃተን ሰዎች #ጁመዓ ለኛ ሃጃቺን ነውና አላህ ከመጣው በላዕ ከሚመጣው በላዕ ሁሉ ነጃህ ብሎን ሃጃቺንሁሉ የሚይወጣበት በሰላት በሰለዋት በኢባዳ ፍክት ፍክትክት ብለን ምናሸበርቅበት ምርጥዬ😍
🤲🤲ጁመዓ ይሁንልን🤲🤲
#Share_Share ለወዳጆህ
Join 👉
https://t.me/httpsLatahzen👈 Join
#ጀነት_አትገኝም!

ረመዳን ወጣ፤
ሸይጧንም ተፈታ፣
ወሩን ሙሉ ሰገድኩ፤
ከእንግዲህስ ይብቃ!
ትንሽ ፈታ ልበል፤
ቀጣዩ እስኪመጣ፣
አለች ነብስያዬ፤
አሁኑኑ እንውጣ፡፡
ባንድ ወር ኢባዳ፣
ባንድ ወር ሁካታ፣
ይገኛል መስሏታል፤
የዘላለም ደስታ፡፡

ነብሴ ሆይ! ልንገርሽ፤
መሸንገልሽ ይብቃ፣
ሰው ጀነት አይገባም፣
በኼይር ስራው ብቻ፡፡
እንዲያውም ልንገርሽ፤
ስለ አንድ ደግ ሰው፣
አላህን መቶ አመት፣
ሳያርፍ ያመለከው፣
እናልሽ ይሄ ሰው፤
ሞት አይቀር ሞተልሽ፣
ስራውን ሊያስመዝን፤
አላህ ፊት ቆመልሽ፣
ከዛማ ይሄን ሰው፣
አላህ በእዝነቱ፤
ጀነት ግባ ቢለው፣
የሰራሁት ስራ፤
እጅጉን ብዙ ነው፣
ጀነትን ለመግባት፤
ስራዬ በቂ ነው፡፡
እዝነትህ ይቅርብኝ፤
አልፈልግም አለው፡፡

እናማ አምላኩ፤
እዝነቱን ሊያሳየው፣
‹‹እንደዛስ ከሆነ፤
ና ጠጋበል!›› አለው፣
‹‹ስራህን እንመዝን፤
ከበቃህ እንየው!››

መልካም ስራው ሁሉ፤
ባንድ ላይ ሆነና፣
የጌታውም ፀጋ፤
ባንድ ጎን ቆመና፣
ይነፃፀር ቢባል፤
የሰውዬው ስራ፣
እንኳንስ ለጀነት፤
ለአይኑ ምስጋና፣
ሳያደርስ አለቀች፤
አልበቃ አለችና!
እናም ውዷ ነብሴ፤
ልልሽ የፈለኩት፣
ካልታከለ በቀር፤
የአምላክሽ እዝነት፣
እንኳንስ ባንድ ወር፤
ልትገቢ ጀነት፣
ሽታዋ አይገኝም፤
ብትፆሚ ሽህ አመት፡፡
እናማ ቀጥ በይ፤
ከአመት እስከ አመት፣
ከመስጂድ አትራቂ፤
እስኪመጣብሽ ሞት፡፡
በረመዳን ብቻ፤
አላህን በማምለክ ፣
ጀነት አትገኝም፤
አንድ ወር በማሸቅ፡፡

#ሼር #share
#join
https://t.me/httpsLatahzen
አዲስ ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቹ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ:
-- @kjumj_official_bot--
Barattota haaraa UNIVERSITY JIMMA isin gahee hunda:-
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

እንደሚታወቀው ዩኒቨርሲቲያችን ግንቦት 04 እና 05 መጥራቱ ይታወቃል ስለዚህ ወደ ግቢ ስትመጡ ያለምንም መንገላታት ለመቀበል ሙስሊም ተማሪዎች ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቀው እናንተ በጉጉት እየጠበቁ ነው።
በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ወንድሞች ማግኝት ትችላላቹ።
Akkuma beekamu Yuunivarsitiin Jimmaa Barattoota haaraa bara 2014 MoE irra gara JU tti ramadamtaniif waamicha kan taasisee Caamsaa 04 fi 05 tahu isaa kan beekamudha kanaaf JAMA'AN BARATTOTA UNIVERSITY JIMMA isiin simachuf qophii isaa xumuratee haawwiin isiin egaa jira .
®Main campus®
~ማዕሩፍ ሰዒድ-MARUF SAID - 0945020813
~አወል ኸድር ~AWOL KADIR-0910502916
~አብዱልአዚዝ ኢድሪስ~ABDULAZIZ IDRIS - 0949916760
ሙሀመድ ጀማል ~MOHAMMED JEMAL- 0910857885
®JIT CAMPUS ®
~አንዋር መሀመድ ~ANWAR MOHAMMED - 0920886879
~ሲቶሌ አባስ ~SITOLE ABAS- 0972180276
~አብደላህ ሸምሰዲን ~ ABDALLAH SHAMSUDIN- 0948780414
®AGRI CAMPUS ®
-ሚፈታህ ጀማል ~MIFTAH JAMAL- 0930474983
-ጁድ አህመድ ~JUD AHMAD - 0960238991
ስለየትኛውም መረጃ ትብብር ለምትፈልጉ
ወንድም እህቶች በነዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉ።
*ለበለጠ መረጃ ይህን ቦት ተጠቀሙ
*fresh ተማሪዎች በዚህ bot መመዝገብ ትችላላችሁ
*Barattonni #Fresh taatan Bot ii jama'a kanaan #galmaa'u ni dandessan.
--------------
@kjumj_official_bot
--------------
*Main campus ለምትመጡ ተማሪዎች جماعة طلاب المسلمين بجامعة جما JUMJ ተብሎ የተፃፈበት ነጭ ቲሸርት አርገን እንቀበላችሁዋለን።
*Main campus barattota galtaniif T-shirt جماعة طلاب المسلمين بجامعة جما JUMJ kan jedhu, uffannaa kanaan kan isiin simannu ta'u isiin beksifna.
*Yeroo dhuuftan odeffannoo barbaaddan argachuufi akka hin rakkaneef bilbila Amiroota Jama'a kana fayyadamaa.

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ
JAMA'A BARATTOOTA YUNIVERSITII JIMMA

#Share #Share waliif godhaa!
@jumjofficialpage
https://t.me/JUMJk_Da3wa
https://t.me/KjumjVoice