La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
#ጀነት_አትገኝም!

ረመዳን ወጣ፤
ሸይጧንም ተፈታ፣
ወሩን ሙሉ ሰገድኩ፤
ከእንግዲህስ ይብቃ!
ትንሽ ፈታ ልበል፤
ቀጣዩ እስኪመጣ፣
አለች ነብስያዬ፤
አሁኑኑ እንውጣ፡፡
ባንድ ወር ኢባዳ፣
ባንድ ወር ሁካታ፣
ይገኛል መስሏታል፤
የዘላለም ደስታ፡፡

ነብሴ ሆይ! ልንገርሽ፤
መሸንገልሽ ይብቃ፣
ሰው ጀነት አይገባም፣
በኼይር ስራው ብቻ፡፡
እንዲያውም ልንገርሽ፤
ስለ አንድ ደግ ሰው፣
አላህን መቶ አመት፣
ሳያርፍ ያመለከው፣
እናልሽ ይሄ ሰው፤
ሞት አይቀር ሞተልሽ፣
ስራውን ሊያስመዝን፤
አላህ ፊት ቆመልሽ፣
ከዛማ ይሄን ሰው፣
አላህ በእዝነቱ፤
ጀነት ግባ ቢለው፣
የሰራሁት ስራ፤
እጅጉን ብዙ ነው፣
ጀነትን ለመግባት፤
ስራዬ በቂ ነው፡፡
እዝነትህ ይቅርብኝ፤
አልፈልግም አለው፡፡

እናማ አምላኩ፤
እዝነቱን ሊያሳየው፣
‹‹እንደዛስ ከሆነ፤
ና ጠጋበል!›› አለው፣
‹‹ስራህን እንመዝን፤
ከበቃህ እንየው!››

መልካም ስራው ሁሉ፤
ባንድ ላይ ሆነና፣
የጌታውም ፀጋ፤
ባንድ ጎን ቆመና፣
ይነፃፀር ቢባል፤
የሰውዬው ስራ፣
እንኳንስ ለጀነት፤
ለአይኑ ምስጋና፣
ሳያደርስ አለቀች፤
አልበቃ አለችና!
እናም ውዷ ነብሴ፤
ልልሽ የፈለኩት፣
ካልታከለ በቀር፤
የአምላክሽ እዝነት፣
እንኳንስ ባንድ ወር፤
ልትገቢ ጀነት፣
ሽታዋ አይገኝም፤
ብትፆሚ ሽህ አመት፡፡
እናማ ቀጥ በይ፤
ከአመት እስከ አመት፣
ከመስጂድ አትራቂ፤
እስኪመጣብሽ ሞት፡፡
በረመዳን ብቻ፤
አላህን በማምለክ ፣
ጀነት አትገኝም፤
አንድ ወር በማሸቅ፡፡

#ሼር #share
#join
https://t.me/httpsLatahzen