ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕
215 subscribers
76 photos
298 links
ሰላም 🤚 -

📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯


በዚህ ቦት አማካኝነት https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙
➡️.  ልቦለዶችን 📖
➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕
➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚
➡️.  ግጥሞችን 📝
➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙
➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ።
አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች

▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
Download Telegram
https://t.me/hopereding

አስደንጋጭ እውነት ልንገርህ....

ማንም ሰው ነገ ጠዋት ተነስቶ ያንተን ህይወት ስለማስተካከል/መቀየር አያስብም። ማንም ሰው!  ለራስህ ህይወት ሃላፊነት ራስህ ውሰድ! ለመሻሻል ለማደግ Take full Responsibility for your life ans Start Today!

ህይወትህን  ለመለወጥ ብቸኛው መንገድ ዛሬ ያለህበት ቦታና ውጤትህ ያንተ መሆኑን መገንዘብና ለማስተካከል በመዘጋጀትና ወደ ተግባር በመግባት ነው።

ወደኋላ የሚያስቀርህና ህይወትህን የሚያበላሽ አንድ ነገር ቢኖር ከሌሎች መጠበቅ ነው። በሌሎች ላይ መተማመን ነው።

የምትነሳው በራስህ ነው ፤
የምትወድቀው በራስህ ነው ፤
የምታድገው በራስህ ነው ፤
የኋሊት የምትጓዘው በራስህ ነው።
ለውድቀትህ የሚጠየቅ ሌላ አካል የለም።   የትም ብትሆን ፣ ምንም ብትሰራ ያንተ ህይወት ሃላፊነት የራስህ ብቻ ነው ።

ላለማደግህ ፣ ላለመቀየርህ ፣ ላለማወቅህ ...ለማደግህም ለመቀየርህ ካንተ ውጪ ሌላ ተጠያቂ አካል የለም።

በራስህ ታገል ፤
በራስህ ተጣጣር በራስህ ስራ ፤ ተፋለም፣ አሸንፍ።በራስህ ተማመን!
Just Do It!

ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯
🔺!


ለአስተያየትዎ እና ጥያቄ
                👇

        በቅርብ  2 ::12 ጊዜ
      https://t.me/hopereding

#Share #Share #Share
በጫካ ውስጥ

1.ዝሆን በጣም ትልቅ
2.ቀጭኔ በጣም እረጅም
3.ቀበሮ በጣም ብልጥ
4.አቦሸማኔ በጣም ፈጣን
   
  ሆኖም  አንዱንም ከላይ ያሉትን መስፈርት ሳያሟላ #አንበሳ
የጫካው ንጉስ ነው::
               ለምን?
1.አንበሳ ደፍር ምንም የማይፈራ በራስ መተማመን የሚራመድ ::
2.አንበሳ ማንም እንደማያስቆመው  ልበ ሙሉ ነው::
3.አንበሳ  ሀላፊነትን ለመውሰድ አይፈራም::

4.አንበሳ ማንኛውም እንሰሳ ምግቡ እንደሆነ ያምናል::

5 .  አንበሳ የሚገጥሙት እድሎችን እንደሚገባው ይቆጥራል ::የሚመጡ መከራዎች እድሉን እንደ ማያስመልጡ ከእጁም እንደማያስወጡት እርግጠኛ ነው::

      እንግዲ.....
1: ፈጣን በመሆን አይደለም
2: ብልጥ መሆን አይደለም
3:ጥበኛምመ መሆን አይደለም
4:ቅልጥፍና አይደለም
    
      የሚያስፈልግህ::

1: ልበሙሉነት
2:ነገሮችን መሞከር
3:እምነት ነገሮች እንደሚሆኑ ማመን::
4:የሚያስፈልግህ በራስ መተማመና ነገሩን እንደምታደርገው  ማመን
          አንበሳ 20 ሰአት ይተኛል 4 ሰአት ይሰራል  ቢሆንም ስጋ ይበላል::ዝሆን 24 ሰአት ይሰራል ነገር ግን ሳር ይበላል::
        ሼር በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ ስላደረጋችሁ ከልብ እናመሰግናለን
🎯🎯🎯🎯🎯🎯
🔺🔻!

https://t.me/hopereding

                👇
  https://t.me/hopereding

#Share #Share #Share
➤Stay in the Lion's mood!
Please dont forget to join, like and share to all beloved ones.
#share #share #share
       #ሼር #ሼር #ሼር
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ለተጨማሪ መፅሐፍት ና ትረካ
▬ ▬   ▬▬    ▬▬     ▬▬
JOIN
@ https://t.me/hopereding
JOIN
@ https://t.me/hopereding
JOIN
@ https://t.me/hopereding
let's build big, worldwide library to all who likes to read
https://t.me/hopereding

📖 " ኣንተ ብቻ ኣይደለህም"📖

ህይወት የጨለመበት አንተ ብቻ አይደለህም፡፡
የባንክ አካውንቱ ዜሮ የሆነበት አንተ ብቻ አይደለህም፡፡ሌሎችም እንደ አንተ የጨለመ ትዳር ውሰጥ ናቸው፡፡በጓደኛ ተከድተዋል፡፡በሀለቃ ተሰድበዋል፡፡በሱስ ደቀዋል፡፡
+
ሌሎችም ራሳቸውን ይጠራጠራሉ፡፡
<ሰው ምን ይለኛል> ብለው ይጨነቃሉ፡፡
<እኔን የሚያገባኝ ባል/ሚስት ጠፍቷል ቆሜ መቅረቴ ነው> ይላሉ፡፡
+
አንተ ብቻ አይደለህም ሐጢያተኛ፡፡አንተ ብቻ አይደለህም ብቸኛ፡፡በስራቸው የተሰላቹ ብዙ ናቸው፡፡ስራ ፈልገው ያጡም ዘጭ ናቸው፡፡
+
በቁም የሞቱም አሉ፡፡አንተ ብቻ አይደለህም <አበቃልኝ> ብለህ ይምትጨነቀው፡፡ይህ የቢሊዮን ሰዎች ችግር ነው፡፡
+
የሚስቁ ሰዎችን ስታይ አትዘን፡፡ምንአልባት እነሱም ልክ እንደ አንተ በአደባባይ እየሳቁ ተደብቀው የሚያለቅሱ ሰዎች ይሆናሉ፡፡
+
ሰዎች ተዋናዮች ናቸው፡፡ከህይወታቸው በስተጀርባ ፍጹም ችግር ቢኖርም ከፊትለፊት ግን ህይወታቸውን ፍጹም አድርገው መተወን ይችላሉ፡፡ጓዳ ቢጣሉም ፊስብከክ ላይ ተቃቅፈው ፎቶ ይለቃሉ፡፡ተርበው ልብስ ይቀይራሉ፡፡የልሆኑትን ነኝ ብለው ይዋሻሉ፡፡ብራዘር አንተ ብቻ አይደለህም ጎዶሎ ህይወት የምትኖረው ሁሉም ሰው ነው፡፡
+
ለራስህ አትዘን፡፡ከፊትም ከበስተጀርባም የምትኮራበትን ህይወት ቀስበቀስ ለመፍጠር ወስን፡፡ህይወት ድራማ አይደለችም፡፡ትወናውን አቁም፡፡የእውነት መኖር ጀምር፡፡
+
#share ••●◉Join us share◉●••                                   
━━━━━━━✦🌹https://t.me/hopereding  🌹✦━━━━━━━
ገምሃልያ
                           ክፍል 14

             📖  " ማንበብ ህይወት ነው "📖

ቀናት ቀናትን እየወለዱ ሄዱ እኔም ከቀናቱ ጋር እየተሻለኝ ሄዶ መራመድ ጀመርኩ ታዲ እና ሊና ከጎኔ ተለይተው አያውቁም ከስራ እንደተመለሱ ውሎዋቸው አዳራቸው ከእኔ ጋር ነው ሁሌም ያበረታቱኛል። ጓደኛዬ ሃናንም ከስራ ወጥታ ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ እየመጣች ትጠይቀኛለች ምን እንደሚሰማኝ እምታውቀው እሷ ብቻ ናት የውስጤን አውጥቼ እምነግረው ለሷ ብቻ ነው። በመጨረሻም ከአንድ ወር በላይ በፈጀ ተከታታትይ ህክምና ሙሉ ለሙሉ አገግሜ ከሆስፒታል ወጣው አካሌ ቢድንም ግን ታላቅ የመንፈስ ስብራት ነበረብኝ አልጠግነው ነገር በምወዳት እህቴ በኩል ነው የግድ ከሁለት አንዳችን መጎዳት ነበረብን ሊኑ መቼም እንድትጎዳ አልፈልግም የሷን ጉዳት ለኔ ያድርልኝ!። ወደቤት ስመለስ ቤቱ እንደነበረው ሆኖ አልጠበቀኝም ሌላ ደሳሳ ቤት መስሎ ታየኝ አዎ ቤት ቀይራ ነበር እህቴ ለኔ ብላ ያላትን ብር ጨርሳ የቤቱን እቃ ሸጣ ከታድኤል ጋር አንድ ላይ እየኖሩ ነበር በኔ ምክንያት በኔ ምክንያት! ከዛ ከመሰለ ቤት ውስጥ ወጥታ አ..አ..ሁ..ን....
ፅናት ታሪኳን ከዚ በላይ ልትቀጥልልኝ አልቻለችም አይኖቿ በእንባ ተሞሉ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች በጣም አሳዘነችኝ በፍጥነት ኪሴ ውስጥ የነበረውን ሶፍት አውጥቼ ሰጠኃትና አይዞሽ ብዬ ለማፅናናት ሞከርኩ ብዙ ግዜ እንደዚ አይነት ሁኔታዎች ላይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም ትንሽ ከተረጋጋች በኃላ ቀለል እንዲላት ተነስተን ወክ እንድናረግ ጠየቅኳት ምንም ሳታቅማ ተነሳች የፓርኩን ባለድንጋይ ንጣፍ መንገዶች እየተከተልን ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ጀመርን ሰአቱ መሽቷል ፓርኩ ውስጥ ምንም የሰው ዘር የለም ያስፈራል ታሪኳን እንድትጨርስልኝ ፈልጊያለው ግን ደግሞ እኔ ብዙ ማምሸት አልችልም ታሪኳን ዛሬ ካልጨረሰችልኝ ነገ እንደማገኛት ምንም ማረጋገጫ የለኝ ምን እንደማደርግ እያሰላሰልኩ እያለ ዝም አልክ አለችኝ ከሄድኩበት ሃሳብ እንደመንቃት እያልኩ እእእ አይ ምንም አይደለም እየመሸ ስለሆነ ከዚ ወጥተን ሌላ ቦታ እንቀመጥ እራት በልተሻል አልኳት ሳላስበው ከት ብላ ሳቀች ምነው ብዬ ጠየቅኳትና ትዝ ሲለኝ ለካ ከከሰአቱን ሙሉ ከኔ ጋር እንደነበረች ትዝ አለኝ እኔም ፈገግ እያልኩ ኦው ይቅርታ በቃ ነይ አብረን እንብላ አልኳት እሺ ብላኝ ከፓርኩ መውጣት ጀመርን።
ወደ ቦሌ ወደሚያስወጣው አስፓልት እየሄድን ለፅናት ምን ማለት እንዳለብኝ። ቅድም ወደዚ ስመጣ ታክሲ ውስጥ ምን አነበብኩ መሰለሽ " እንደ ዳዊት ሊያነግስህ ሲፈልግ ጎልያድን የሚያክል መከራ ይልክብሃል" ምናልባት ይህንን ፅሁፍ ያነበብኩት ላንቺ እንድነግርሽ ታስቦ ይሆናል ይኀውልሽ ፅናት እኔ ስላንቺ ብዙም አላውቅም ግን እስካሁን በነገርሽኝ ታሪክ ውስጥ ፅናት እምትባል ሴት ጠንካራ እንደሆነች አይቻለው አውቃለው ህይወት ቀላል አይደለችም ሁሌም ፈተና እና መከራ የሞላባት ናት ግን እነኛ ፈተና እና መከራዎች ናቸው የህይወትን ጣእም እንድናውቅ እሚያደርጉን የሰላም ጥቅም የሚገባሽ ረብሻና ሁካታ ውስጥ ስትሆኝ ነው እንደዚሁም የህይወት ታላቅ ምስጢር የሚገባሽ ፈተና ውስጥ ስትሆኝ ነው እና እነኚን ፈተናዎችሽም አትጥያቸው በህይወትሽ ገና ብዙ እሚገጥሙሽ ነገሮች አሉ ራስሽን ለዛ ማዘጋጀት ነው ያለብሽ በእሳት ያልተነጠረ ወርቅ ለጌጥነት አይወልም በእሳት ያልተፈተነ ሸክላ ለስራ አይወልም ምክንያቱም እሳቱ ስለሚፈትናቸውና ትክክለኛ ማንነታቸውን እንዲያወጡ ስለሚያደርጋቸው ነው በፈተና ብዛት የሚመጣ ማንነት ትክክለኛ ማንነታችን ነው ብዬ አምናለው ምናልባት አጋጥሞሽ ከሆነ አላውቅም በደግ ግዜ ከጎንሽ አለው አለው የሚሉሽ ሰዎች በችግርሽ እና በፈተናሽ ግዜ ጥለውሽ ይጠፋሉ ያኔ የነሱን ትክክለኛ ማንነት ታዩበታለች እናም ፈተናዎችሽን አትጥያቸው ትክክለኛ ማንነትሽን እንድታወጪ እና ምን ያክል ጠንካራ እንደሆንሽ እንድታውቂ ይረዳሻል አልኳት። ፅናት በመገረም እያየችኝ ነበር ትንሽ ፈገግ አለችና እሺ አለችኝና ወደቦርሳዋ መለስ ብላ ዚፑን ከፍታ መጎርጎር ጀመረች ትንሽ ቆይታ አንድ ቢጫ ሃይላንድ መሰል ነገር አወጣች ጨልሞ ስለነበር ምንነቱን በደምብ መለየት አልቻልኩም ቢጫውን እቃ ወደኔ እያስጠጋችው ታውቃለህ ረምሃይ ዛሬ እዚ ፓርክ የመጣሁት አንድ የመጨረሻ ሲጋራ አጭሼ ይሄንን በረኪና ጭልጥጥጥ... አድርጌ ጠጥቼ ራሴን ላጠፋ ነበር አለችኝ በጣም ደነገጥኩ ፈፅሞ ያልጠበቅኩት ነገር ነበር ይበልጥ እየደነገጥኩ ምንንንን! ብዬ ጮህኩባት ወዲያው.አማተብኩና  በረኪናውን ከእጇ ነጠቅኳትና ያዝኩት። ፅናት ግን ማውራቷን አላቁመችም አሁንም ፈገግ እንዳለች ነው። ታውቃለህ ዛሬ ራሴን ላጠፋ እዚ ፓርክ መጣው ይህንን ፓርክ ያሳየኝ ታዲ ነበር እሱን እያስታወስኩ ሲጋራዬን ምጌ ስጨርስ በረኪናውን ለመጠጣት እያሰብኩ እያለ አንተ መጣህ እና ሲጋራውን ስጪኝ አልኩኝ ለሲጋራው ደንታ ባይኖረኝም አጋጣሚው በጣም ገረመኝ ምን አይነት ልጅ ነው እያልኩ ነበር ምናልባትም እንድታድነኝ ይሆናል አምላክ አንተን የላከህ አላውቅም!። ፅናት ይህንን ስትለኝ ከፓርኩ ወጥተን ወንዙን የሚያሻግረው ድልድይ ላይ ነበርን ወዲያው አስቆምኳትና ከድልድዩ በስተግራ በኩል ያሉ  የጎመን አትክልቶች መብራት በርቱባቸው ይታያሉ ወንዙ በመሃላቸው አቋርጦ ያልፋል ወደዛ ወሰድኳትና በረኪናውን ድልድዩ ስር አስቀመጥኩት። የውልሽ ፅናት ታሪክሽን ሙሉ ለሙሉ ስላልነገርሽኝ እኔም ለመምከር አልተመቸኝም እስካሁን የነገርሽኝ ታሪክ ራስን ለማጥፋት እንደማያደርስ በደምብ አውቃለው ከዚ የባሰ ሌላ ታሪክ እንዳለሽ ይሰማኛል ነገ ተገናኝተን ሁሉንም ከነገርሽኝ እኔ መርዳት የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ ሌላው ቢቀር እመክርሻለው ያንን ማድረግ ካልቻልኩ እኔ ይህንን በረኪና ጠጣለው ባንቺ ፈንታ አልኳት ፅናት እየሳቀች እሺ ነገ እንገናኝና ጨርስልሃለው  አለችኝ። ቃል ግቢልኝ ነገ እዚ እንደምትመጪ እና ዛሬ ራስሽን ለማጥፋት ምንም እንደማታደርጊ ቃል ግቢልኝ እመኚኝ ነገ በዚ ሰአት የሚኖርሽ ስሜት ርሌላ ይሆናል ብቻ አንቺ ቃል ግቢልኝ አልኳ እሺ አለችኝና የማርያም ጣቷን ዘረጋችልኝ እኔም ጣቴን ዘረጋሁላትና ቃል ተገባባን በረኪናውን ገፋ አድርጌ ወደ ወንዙ ጣልኩት አንተተ... ለራስህ እንዳትጠጣው ነዋ አለችኝ እየሳቅኩ ችግር የለም ነገ አዲስ እንገዛለን አልኳት ከት ብላ ሳቀች።

ከፅናት ጋር እራት አብረን በላን የተለያዩ አዝናኝ ነገሮችን እየነገርኳት አመሸን ድጋሚ ታሪኳን ጀምራልኝ እማይሆን ስሜት ውስጥ ገብታ መጥፎ ውሳኔ እንዳትወስን ብዬ በተቻለኝ መጠን ለማስረሳት ጣርኩ። እራት በልተን ከጨረስን በኃላ ነገ እሁድ ጠዋት አራት ሰአት ላይ እዚው ፓርክ እንድንገናኝ ተቀጣጥረን ተለያየን። በታክሲ ወደቦሌ እየተመለስኩ ቅድም ፓርክ ውስጥ እየገባው ፅናትን አክቻት ዝም ብያት አልፌ ተመልሼ ሄጄ ባላወራት ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቤ በጣም ተገረምኩ ፈፅሞ ሌላ ታሪክ ሊፈጠር እንደሚችል አሰብኩት ፈፅሞ ሌላ ታሪክ ይሆን ነበር ለካ ለዚ ነው ቀን ላይ እያክለፈለፈ ወደዚ ያመጣኝ አልኩ ለራሴ። ብርቅርቅታን እያነበብኩ ሲጋራ እምታጨሰውን ልጅ እንዳወራት ህሊናዬ ያስገደደኝ ለዚህ ነበር! ነገ ሳገኛት ምን እንደምትነግረኝ እያሰብኩ ለሷ እምላትን እያሰላሰልኩ ወደቤቴ ገባው

ውድ አንባቢዎቻችን ቀጣይ ክፍል ቶሎ እንዲደርሳችው #share..

https://t.me/hopereding

https://t.me/hopereding
💌💌💌💌  ገምሃልያ  💌💌💌💌
💌💌💌💌  ክፍል 17  💌💌💌💌
  📖📖🌻 "ማንበብ ህይወት ነው"🌻📖📖

እማየውን ማመን አቅቶኝ ም..ምን ምን..!!! ብዬ ተንተባተብኩበት በጣም ደንግጫለው ታዲ ከእግሬ ላይ ተነሳና ፅኑዬ ሊናን በጣም ነው እማፈቅራት ለኔ ከማንምና ከምንም በላይ ናት ያለፈው አመተ ከባድ ግዜ ቢሆንም ከእሷ ጋር ስሆን ግን ሁሉንም ነገር እረሳና ደስተኛ እሆናለው በህይወቴ እንደዚ ደስተኛ እምሆን አይመስለኝም ነበር ግን ለዚህ ሁሉ ሰላሜ እና ደስታዬ ምንጭ ነች ሊና እህትሽን ከምንም በላይ አፈቅራታለው ስለዚህም በህግ ላገባት ሚስቴ ላደርጋት አስቢያለው ከዚ በላይ ግዜ ማቃጠል አልፈልግም ይህ ሁሉ እንዲሆን ግን ያንቺን መልካም ፍቃድ እፈልጋለው እንደምታውቂው እህትሽ ካንቺ ፍቃድ ውጪ ምንም ነገር እንደማታደርግ አውቃለው ለዛም ነው ከሷ በፊት አንቺን መጠየቅና ማስፈቀድ የፈለግኩት አንቺ እሺ ያልሽውን ነገር እሷ ፈፅሞ እንቢ ልትል አትችልም ደሞ ታውቂያለሽ አሁን ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነች እእእ እና ፅኑዬ ምን ትይኛለሽ አለኝ እንደመለማመጥ እንደመቁነጥነጥ እያደረገው ታዲ እንዲ ሲጨነቅ አይቼው አላውቅም እኔም በጣም ደንግጬ እምለው ነገር ጠፋብኝ እ...እ...እ ብዬ ዝም አልኩ ሁሉም በእጄ ሆነ ሊናን ማግባት ከፈለገ የኔን ፍቃድ ማግኘት አለበት! ኣታግባት ብዬ የኔ ባደርገው ደስ ባለኝ ነበር ግን አልችልም የግድ እሷን ማግባት አለበት በሆነ ምክንያት በሆነ ተአምር ከኔ ጋር ቢሆን ምንኛ ደስ ባለኝ አውቃለው ረምሃይ እብድ ነሽ ልትለኝ ትችላለህ ግን እብድም ሆኜ ታዲን ባገኘው ምንኛ ደስ ባለኝ ግን በቃ ውስጤ ያለው ፍም እሳት ይፍለቀለቅ ጀመረ እህቴ ታዲን የነጠቀችኝ መስሎ ታየኝ በጣም ጠላኃት ሳላስበው እዛው ቁጭ እንዳልን አፌን በእጄ እንደያዝኩ በእንባ ታጠብኩ ታዲ ሲያየኝ በጣም ደነገጠ! ምነው ፅኑ ምነው... ምነው? ምን አጠፋው እሚያስቀይምሽ ነገር ተናገርኩ እንዴ እእእ ፅኑ ምን አደረኩሽ .... እሺ ይቅርታ አለኝ አንደበቱ እየተሳሰረ። በለቅሶ ብዛት እሱን መስማት አልቻልኩም መላ ህይወቴ ሲገለባበጥ ተሰማኝ ታዲ ሊናን ሲያገባት ልጅ ሲወልዱ ልጃቸውን ትምህርት ቤት ይዘው ሲሄ  አብረው በደስታ ሲኖሩ ሁሉም በህሊናዬ ተሳለ ያኔ አደጋ ባይደርስብኝ ሊና ሳትሆን እኔ ነበር እምሆነው የሚለው ክፉ ሃሳብ መጣብኝ ይበልጥ አለቀስኩ! ታዲ ምን እንደሚለኝ ግራ ገብቶት ደንግጧል። ከቆይታ በኃላ ራሴን አረጋግቼ እንባዬን ጠርጌ ተቀመጥኩ ትዝ ሲለኝ ታዲ ለምን እንዳለቀስኩ ትልቅ ማብራሪያ እንደሚያስፈልገው አወቅኩ በጣም ደነገጥኩ ለምንድነው ያለቀስሺው ሲለኝ ምን ልበለው እውነቱን አልነግረው ነገር አልችልም ትልቅ ችግር ይፈጠራል ሁሉንም በውስጤ አፍኜ ሽምጥጥ አድርጌ ልዋሸው ወሰንኩ። እንባዬን ጠራርጌ ወደታዲ ፈገግ ብዬ ዞርኩ ይቅርታ ታዲ አስደነገጥኩህ አይደል በጣም ደስ ስላለኝ ነው እሺ ያለቀስኩት ይቅርታ ስሜታዊ ሆንኩብህ ይህንን ቀን በጣም ስጠብቀው ነበር ሊና እንዳንተ አይነት ውድ ባል እንድታገባ እፈልጋለው እንድታገባት ስትጠይቀኝ ማመን አቅቶኝ በደስታ ብዛት አለቀስኩ እኔና ሊናዬ ያሳለፍነውን ህይወት ታውቀዋለ ቀላል አልነበረም እናም አሁን አጋሯ ስትሆን ስትጋቡ እሚያማምሩ ልጆች ስትወልዱ እያሰብኩ ተደሰትኩ ታዲዬ እኔ ሙሉ ፍቃዴን በደስታ ሰጥሃለው ግን እህቴን አደራ ጥላ ከለላ ሁናት ጋሻዋ ነህ በጤናም ሆነ በህመም በመልካም ሆነ በችግርህም ግዜ መቼም እንዳትታዋት ይህንን ቃል ግባልኝ አልኩት። ታዲ ይህንን ስነግረው ማመን አልቻለም ቅድም ደንግጦ የነበረው ፊቱ ተቀይሮ ፌሽታ በፌሽታ ሆኗል። እኔ አላምን....ም ፅኑዬ ቅድም እንደዛ ስታለቅሽ እምቢ እምትይ መስሎኝ በጣም ተጨንቄ ነበር እኔ.... አላ...ምን...ም!!! እና ፈቀድሽ ፅኑ አለኝ በእጆቹ ትከሻዬን እየወዘወዘ። አው ታዲ ፈቅጃለው አልኩት በዚህ አለም ላይ እማፈቅረውን ብቸኛ ሰው በገዛ ፍቃዴ እህቴን እንደያገባ ፍቃድ ሰጠሁት!
            ይቀጥላል
    
#Share  For  Ur Friends 


,,,,,,,,,,,,🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃,,,,,,,,,,,,


https://t.me/hopereding
ት እጅግ   ባዝንም ትልቅ ትምህርትን ግን አስተምሮኝ ይህቺ የተሰጠችን ህይወት አጭር ናት በሚገባ ልንጠቀምባት እንደሚገባ ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ጭምር መኖር እንዳለብኝ አስተማረኝ። ያው አሁን ከቢታ ሞት ከሁለት አመት በኃላ አሁን እንደምታዪኝ አለው እንደድሮዬ እስቃለው እጫወታለው መዝናናት ባለብኝ ሰአት ዘና እላለው በስራ ሰአት ደግሞ ስራዬን በሚገባ እሰራለው በህይወቴ ብዙ ስህተቶችን ብሰራም በነኛ ስህተቶቼ ግን ምንም ፀፀት የለብኝም አሁን ላለሁበት ማንነት ዋና መሰረት ናቸው እና ምን ልልሽ ፈልጌ ነው በእህትሽ ሞት ብታዝኚኝ  ተፅናንተሽ እንደድሮሽ የምትሆኚበት ነገር ይመጣል the only way out is through ብርሃን እምታገኚው በዋሻው መጨረሻ ላይ ነው እርግጥ ነው የሊና ሞት ቢያሳዝንም ግን በሷ ህልፈት ትልቅ ትምህርት አስተምሮሽ ሊያልፍ ይገባል የማይገድልሽ ነገር ያጠነክርሻል  እሺ... አልኩና ሳቅኩ ፅናት ተመስጣ እያዳመጠችኝ ነበር ዋይ ይገርማል እንዲ አይነት ነገር አልጠበቅኩም ነበር ሁሌ እኔ ብቻ በጣም ነበር በጣም የተጎዳው የሚመስለኝ አለችኝ። መልካም አሁን ታሪክሽን መቀጠል ትችያለች ወይስ ሌላ ግዜ ይሁን። አይ እቀጥላለው ችግር የለውም አለችኝ ፈገግ እያለች።

ይቀጥላል...

      @Manbeb2116      #Share

,,,,,,,,,,,,🍃🌹🍃🌸🍃🌹🍃,,,,,,,,,,,,


📖ይቀጥላል📖
"ማንበብ ህይወት ነው"📖 
ይቀጥላል!
  ,,,,,🌹❣️🌹❣️🌹❣️🌹,,,,,
                 ••●◉Join us share◉●••                                    
   https://t.me/hopereding    // ,,📩 https://t.me/hopereding
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ!💪

— “ገና በዘጠኝ አመቴ በግዳጅ ተደፍሬ ነበር” (ኦፕራ ዊንፍሬይ)

— ”የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን እንኳን በአግባቡ ተከታትዬ
አልጨረስኩም“ (ቢል ጌትስ)

— ”አባቴ የወሲብ፡ የስነ-ልቦና፡ የስሜት ጥቃት ያደርስብኝ
ነበር፤ ይህ ድርጊትም በ18 አመቴ ቤት ለቅቄ እስከምወጣ
ድረስ ተባብሶ ቀጥሎ ነበር“ (ከ90 በላይ የሚገመቱ
መጽሀፍት ደራሲት ጆይስ ሜየር)

— ”የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ከክፍል ክፍል ለመሸጋገር
ፍዳዬን አይ ነበር“ (ዶክተር ቤን ካርሰን)

— ”የእግር ኳስ ስልጠናዬን በአግባቡ ለመከታተል
የሚያስችለኝን ገንዘብ ለማግኘት ስል በአስተናጋጅነት
ሰርቻለሁ” (ሊዮኔል ሜሲ)

— “ቤት ስላልነበረኝ፡ በጓደኛዬ ቤት ወለል ላይ እተኛ ነበር፤
የለስላሳ ጠርሙሶችን ሰብስቤ እሸጥ ወይም በምግብ እለውጥ
ነበር፤ በአቅራቢያችን ካለ ቤተ-መቅደስ ይሰጥ ይነበረ
ሳምንታዊ ነጻ የምግብ ድርጎ ለመቀበል ዘወትር ወደዛ
አመራ ነበር“ (ስቲቭ ጆብስ)

— “አስተማሪዎቼ ‘ስንፍና’፡ ‘ውድቀት’ እያሉ ይጠሩኝ
ነበር” (ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌይር)

— ”ለ27 አመታት እስር ቤት ውስጥ
ነበርኩኝ“ (ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ)

_____
ለወዳጅዎ ያጋሩ
     📙"ማ
ንበብ 💐 ህይወት ነው"📙


https://t.me/hopereding

https://t.me/hopereding
#share
❤️❤️❤️❤️❤️ሞሮ❤️❤️❤️❤️❤️
                     ክፍል 3

ጠዋት ከእንቅልፌ ስነ ቃ ያለሁበትን ቦታ በደምብ አላውቀውም ብቻ ግማታም ቱቦ ውስጥ ተኝቼ እንዳደርኩ ገባኝ ሰውነቴ በጣም ይሸታል ለእይታም ደስ አይልም ተነስቼ ታክሲ ወደምንይዝበት ቦታ አመራው ሰዉ እያየ ሲጠየፈኝ በደምብ ይታወቀኛል ታክሲው ጋር ደርሼ ልገባ ስል ወያላው አፍንጫውን ይዞ አይቻልም ብሎ በሩን ዘጋብኝ ምንም አልመሰለኝም እንደለመድኩት በእግር መንገዴን ቀጠልኩ ግቢ አከባቢ ስደርስ ኤቤጊያ ከጓደኞቿ ጋር ከግቢ ሲወጡ ከርቀት አየኃት በጣም ደነገጥኩ እየሮጥኩ ወደኃላ ተመልሼ እየሮጥኩ ጠፋው እሷን ሳያት ለምን ፍርሃት እንደሚከበኝ አላውቅም አይደለም በቅርበት አይቻት ቀርቶ በሌለችበት ስሟ ሲነሳ እደነግጣለው ምን እንደሚሻለኝ አላውቅም። በራሴ በጣም ተናደድኩ ለአንዲት ሴት እንደዚ እሆናለው? ኤቤጊያ አይነጥላ ሆነችብኝ  ራሴን ወቀስኩት የዛሬ አመት የነበረውን ናኦድ አስታወስኩት የድሮ ማንነቴ ናፈቀኝ ደፋር፣ ከሰውጋ ተግባቢና ተጫዋች በትምህርቱ ጎበዝ ራሱን የሚጠብቅ..... ከአንድ አመት በፊት ኤቤጊያ ይህንን ግቢ ስትቀላቀል ልቤ ከሷ ጋር አብሮ ሄደ አስታውሳለው እንደሁልጊዜዋ ሰማያዊ ጅንስና ጥቁር ሸርት አድርጋ ሻንጣዋን ይዛ እዛ ረጅም አስፓልት ላይ እየጎጠተች ስትገባ እኔ ከግቢ ስወጣ ነበር ያየኋት ከዛን ግዜ ጀምሮ ልቤን የሰረቀችው ቆንጆ እንስት ሌብነቷን እንኳን ሳታውቅ ልቤን አልመለሰችልኝ እኔም ከግዜ ግዜ ፍቅሯ እየባሰብኝ ሄደ ሁሉም ነገር ቀስበቀስ እየተቀየረ ሄደ  የዛሬ አመት የነበረው ናኦድ አሁን የለም አባይ ጓደኞቼ ከኪያር ውጪ ተዘባበቱብኝ ከኔ ተለዩ ይባስ ብሎ ኤቤጊያን እንደምወዳት እያወቁ በስሟ መጫወቻቸው አደረጉኝ።  ኤቤጊያ ታክሲ ውስጥ ገብታ ከሄደች በኃላ ራሴን አረጋግቼ ወደግቢያችን በር እያመራው አስፓልት ዳር ከቆሙት መኪናዎች አንዱ በመስታወቱ ራሴን ድንገት አየሁት ደነገጥኩ ራሴን በመስታወት ካየሁት በጣም ቆየው ድሮ የማውቀው ፊት ሳይሆን ሌላ ሰው የቆመ መሰለኝ ይህንን መልክ አላውቀውም  በጣም ገርጥቶ የከሳ ጥቁር ፊት የተንጨባረረ ፀጉርና ፂም ቀጫጫ ሰውነት በዛ ቀጫጫ ሰውነት ላይ ሰፊ የቆሸሸ ልብስ ሰው ሁላ ጀዝባ ወይም ሞሮ ቢለኝ አይገርምም እውነትም ሆኛለው። ወደ ድሮ ማንነቴ መመለስ እንዳለብኝ ገባኝ ኤቤጊያ ለኔ ያላላት የፍቅር መርዝ ናት ከልቤ ቆርጬ ላስወጣት ለመጨረሻ ግዜ ለራሴ ቃል ገባው ወደ ግቢ እየሄድኩ የነበረውን ሃሳብ ቀይሬ ወደኃላ ተመለስኩ አንዱን ባጃጅ ኮንትራት አናግሬ ባያምነኝም ቅድሚያ ከፍዬው ቅር እያለው ወደ መብራት ሃይል ወሰደኝ። ኤቲኤም ብር አውጥቼ ወደ ቡቲክ አመራው ልብሶች ጫማ ሁሉንም  ገዛዛው ራሴን በአዲስ መልኩ ማየት እፈልጋለው። ልብሶቹን ይዤ አንድ ሆቴል ገብቼ አልጋ ያዝኩ ሻወር ገባው ከላዬ ላይ የተራገፈው የቆሻሻ መአት እኔና ባኞ ቤቱ ነው ምናውቅው ራሴን ታዘብኩት በጣም! ከሻወር ስወጣ ሁሉም ነገር ቅልል አለኝ ነገሮች ጥርት ብለው ይታዩኝ ጀመር አዲሱን ልብስ ለብሼ ፀጉሬን ለመስተካከል ወደፀጉር ቤት ሄድኩ ያ ጅብ የዋለበት እርሻ የሚመስለውን ጨበሬ ፀጉር በአግባቡ ተስተካከልኩት ፂሜንም እንደዛ ትንሽ መለስ ያልኩ መሰለኝ ግን አሁን ድሮ የቀይ ዳማ የመሰለው መልኬ ጠቁሮ እንዳልተመቸኝ በደምብ ያሳብቃል  ፀጉር ቆራጩን አመስኜ ወጣው። እንደሌላ ግዜ ሰው እየተጠየፈ አያየኝም ትንሽ ደስ አለኝ ወደ ቀድሞ ግብሬ መመለስ ጀመርኩ ሁሌ መብራት ሃይል ስመጣ መፅሃፍ ደርድረው ከሚሸጡት ውስጥ ራስተም ጋር ሄጄ አንድ አሪፍ መፅሃፍ ገዝቼ ወደ በቀለ ሞላ ሆቴል በአንደኛ መንገድ ላይ ወክ እያደረግኩ ሰዉን እየታዘብኩ እሄዳለ ዛሬም እንደዛ ማረግ ፈለግኩ። ራስተም ጋር ስሄድ መፅሃፎቹን እያስተካከለ ሲደረድር አገኘሁት ቀና ብሎ ሲያየኝ ደስ አለው እንዴ ናኦዴ ሰላም ነው ምነው ጠፋህ አለኝ ብዙ ግዜ ሆኖኝ ነበር ራስተም ጋር መፅሃፍ ከገዛው ሰላም ተባብለን ከጨረስን በሃላ አዲስ መፅሃፍ ገዝቼ መንገዴን ወደ በቀለ ሞላ ሆቴል በአንደኛ መንገድ ላይ አድርጌ ሄድኩ ወደ ሆቴሉ ስገባ እንድወትሮው ሰላሙን የጠበቀ ሆኖ አገኘሁት ከራስ ጋር ለማውራት ደስ እሚል ሰላማዊእና ተፈጥሮአዊ ቦታ ነው የዛሮቹ ብዛት የወፎቹ ዝማሬ ሰላም ይሰጣል እኔም ሰላሜን አገኘው አዱስ የገዛሁትን መፅሃፍ ገልጮ ትንሽ እንዳነበብኪ አስተናጋጇ  መጣች ትዝ ሲለኝ ደህና  ምግብ ከበላው በጣም ቆይቻለው የቤቱን አሪፍ ምግብና መጠጥ አዝዤ መፅሃፌን እያነበብኩ ዘመትኩበት ለዚች ቅፅበት ኤቤጊያን ረስቻት ነበረ። 12፡00 ሲል ወደ ግቢ ተመለስኩ ስደርስ እየጨላለመ ነበር ግቢ ውስጥ ስገባ መንገድ ላይ ከኪያር ጋር ተገጣጠምን ሲያየኝ ንፁህ ልብስ ለብሻለው  ፀጉሬ ተስተካክሏል በዕጄ መፅሃፍ ይዣለው ተገረመ እየሳቀ ምን ተገኘ አለኝ ምንም አልኩት እየተቻኮለ ነበር አቅፎኝ ዶርም ጠብቀኝ  እመለሳለው አሁን እያለኝ ፈገግታውን ሳይነፍገኝ እየተጣደፈ ሄደ ዶርም ስገባ ሁሉም መሳሳቅ ጀመሩ እንደ ኪያ የደስታ ሳይሆን የፌዝ እንደነበር በደምብ አውቃለው። አንደኛው በጣም እየሳቀ ሞሮሮሮ.... ምን ተገኘ ኤቢን ጠበሻት እንዴ አለኝ ተናደድኩ ሞሮ እሚለው ስድብ አናደደኝ ከተቀመጥኩበት ተነሳውና ከዚ በኃላ ሞሮ ብትለ ኝ እንጣላለን አልኩት እየሳቀ እሺ አለኝ ተናድጄ ልወጣ ስል ኪያር በሩን ከፍቶ ገባ ያለው ነገር ወዲያው ስለገባው ይዞኝ ወጣና ወደ አም ፊ አከባቢ ያሉት ደረ ጃዎች ጋር እያረጋጋኝ ሄደን ተቀመጥም። አሁን ባየው መስተካከል እንደተደሰተ ነግሮኝ እንድበረታ እያፅናናኝ ስለ ኤቤጊያ ምን ማድረግ እንዳለብኝና እሱ ለኔ እንደሚያናግራት እየነገረኝ እያለ ኤቤጊያ ከሌላ ወንድ ጋር ሆና ከኛ ፊትለፊት ደረጃዎቹ ላይ ስጥቀመጥ ድንገት አየኃት።

ይቀጥላል ....
📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖📖

     https://t.me/hopereding

       #Share   ፡፡፡

https://t.me/hopereding
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ክፍል6፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖📖
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ሞሮ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

ዳግም አይኔ ሲከፈት እዛ አስቀያሚ ሰው አልባ አስፓልት ላይ አልነበርኩም ሙሉ
ሰውነቴን ይጠዘጥዘኛል ይተፈጠረውን ነገር አንድ በ አንድ አስታውሳለው ማን
እንደበደበኝ ማን እንደወጋኝ ማነ ሊረዳኝ እንደመጣ ሰክሬ ቢሆንም አስታውሳለሁ
ናኦድ ነቃህ አለቺኝ አንድ ቀጠን ያለ ድምጽ ባለነጠለዋ ልጅ ነበረች ድምጻን
ወደሰማውብት አቅጣጫ ተገላመጥኩ ጥግ ላይ የሚገኝ የ ታማሚዎች አልጋ
ላይ 3 ሴቶች ተቀምጠው በጭንቀት እያዩኝ ነውእኔን ያዳነችኝ ባለነጠለዋ ልጅ
በአይኔ ፈለኩ መሃል ላይ ተቀምጣለች ወደ እሳ እያየው የት ነው ያለውት
አልኩዋት ድምጼ በጣም እንደተዳከመ ይታወቀኛል አፌን በጣም መረረኘኝ
አዳማ ጀነራል ሆስፒታል ነህ እንዴት ነህ አሁን ህመም ምናምን እየተሰማህ
ወይስ ብላ የጀመረችውን ሳትጨርስ ዝም አለች እኔጃ አላቅም ምን እየተሰማኝ
እንደሆነ እራሱ ማወቅ አልቻልኩም ኪያር የታለ ብዬ ጠየኩዋት ኪያር ማነው ብላ
ጠየቀችኝ ኪያር የቅርብ ጉደኛዬ ነው ስልኬ ካለ አውጪና ኪዩ ብለሽ ፈልግሽ
ደውለሸ ጥሪልኝ እባክሽ አልኩዋት እሺ አለችኝና ከ ቦርሳዋ ውስጥ የኔን ስልክ
አወጣችና መነካካት ጀመረች እሱዋ ስልኩን ጆሮዋ ላይ አድርጋ ጥሪ
ስትጠባበቅ እኔ ጎኑዋ ያሉ ልጆችን ልብ ብይ ማየት ጀመርኩኝ ከዚ በፊት
ግቢያችን ውስጥ በአይን አቃችዋለው በደንብ ባይሆንም በ አይን አቃችዋለው
ድንገት ሄሎ ኪያር አለቸው ጥያቄ በሚመስል መልክ አዎ አላት መሰለኘ ስላም
እንደምነህ ሰመሃል እባላለው አለችውና የተወሰነ ሰከንድ ልትመጣለት
ትችላለህ በተረጋጋ መንፈስ ቀለል አድርጋ ነገርችው ኤይደለም ኪያርን እኔንም
ቀልል ያለ ነገር እንደሆነ ገመትኩ ድምጹን ላውድ ላ ይ አደርችውና ኪያ
መንጫጫት ጀምረ አይ ናኦድ እንዳው ምንድነው የሚሻልህ ይሄኔ አምፑላህን
ስትጋት አድረህ ነው አሁን ጨጉዋራዬ የምትለው አንት ሞሮ ትሰማኛለህ የት ነህ
ለመሆኑ ምንህን ነው ያመመህ አንተ ጅዝባ አለ ኪያ እኔ ክፋት እንድሌለበት
ባውቅም እሱዋ ግን ድምጹ ላውድ ስለሆነ ደነገጠች የተበታተነ ሃሳብዋን
ስብስብ አድርጋ ለኔ መሸፋፈን ሞከረች ውይ እንደዛ አይደለም አይደለም ከቻልክ
መጥተህ አብረሀው ሁን አዳማ ጀነራል ሆስፒታል ቁጥር 130 አለችው ነገሩን ለ
መቁዋጨት የፈለገች ይመስል እሺ እመጣለው እስከዛ በደንብ ተንከባከቢልኝ
አላት ስልኩን ዘጋው ወደኔ እያየች ይመጣል እሺ አይዞህ አለቺኝ. ሁለቱ ሴቶች
ጉዋደኞቹዋ አሁንም እንደተለጎሙ ነው ዘምታቸው ቲንሽ ግራ ያጋባል ዝምታ በ
ክፍሉ ሞላ አእኔም ጭጭ እነሱም ጭጭ. ቲንሽ ቆይቶ አንዲት በእድሜ ግፋ
ያለች ሴት ነጭ ጋውን ለብሳ ወደ ክፍሉ ዘው ብላ ገባች. እንዴት ነህ አሁን
አለችኝ ደህና ነኝ እግዜር ይመስገን አልኩዋት ተዛማች የሆኑ ጥያቄዎች
ጠየቀችኝና ተነሳች በረንዳው ላይ መረማመድ እነደጀምር ነገረችኝና ሄደች.
ከአልጋዬ መነሳት ስጣጣር ሰመሃል አይታኝ ደግፋኝ ቀና እያደረገችኝ እያመመኝ
ተነሳው ቁስሉ ጠባሳ ሲሆን ቀጥ ብዬ መሆን አለበት በግድ እያመመኝ ቀና ቀና
አልኩ . ልቤ በፍጥነት ይመታል ድክምክም ብሎኛል ሰመሀልን ተደግፌ
መራመድ ጀመርኩ. ሰመሀል ታበረታታኛለች ቀስ እያልን እየተረማመድን ከክፍሉ
ወጥተን ኮሊደሩ ላይ መራመድ ቀጠልን. የኮሊደሩ ጥግ የአመት ያህል እራቀብኝ
ዶክተሩዋ ያለችህን ሰምተህ የል በል ቀስ አይዞሀ በርታ በል . በጣም ደከመኝ
ላብ በላብ ሆነኩ ሰመሃል ምንም ቅር ሳይላት በልብሱዋ ትጠርግልኛለች.
ሰመሃል ብዬ ጠራዋት ደንገጥ ብላ አቤት አለችኝ. ምን አይተሸብኝ ነው ግን
ይህንን ሁሉ ደግነት ለኔ ያሳሽኝ እኔ ኮ ለምንም የማልጠቅም ሞሮ እኮ ነኝ ቆጣ
እያለች የሰው ዘር በ ሙሉ አንድ ነው እርዳታዬ ለሚያስፈልገው ሰው ሁሉ እጄን
እዘረጋለው. መልካም መሆን ለራስ ነው አለችኝ እሺ ብዬ እንደኤሊ እየተጎተትኩ
መራመዴን ቀጠልኩ ግን ምን በጣም የምትገርም ልጅ ናት በውሰጤ ስለሱዋ
ማሰላሰል ጀመርኩ ምን አይነት ሰው ናት ይህን ያህል ድረስ…….. የኮሪደሩ ጥግ
ደርስን ወደሁዋላ መመለስ ጀመርን.

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ይቀጥላል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖📖
💐📖💐   

https://t.me/hopereding
              #Share
https://t.me/hopereding
💝💐🍁በጥዋትን ሰላም ይሰሙት

በይቅርታ የተጀመረ ቀን ልዩ ነው ሰላም ኣለው
>>>>>>>>>>>>>>>>> ቀን ደስታ ኣለው
>>>>>>>>>>>>>>>>>> ቀን ነጳነት ኣለው

📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖📖
  
💐#ይቅርታ /FORGIVENESS💐

*ይቅርታ የነገሮች ሁሉ ጅማሬም ፍፃሜም ነው።

*በሕይወታችሁ ደስተኛ የምትሆኑት በይቅርታ ስትመላለሱ ነው። ይቅር በሉ ያሳዘናቹትንም ይቅርታ ጠይቁ። በይቅርታ የተሞላ ማንነት ካላቹ ሕይወታችሁ የሚወደድ ይሆናል።

💗💗💗💗💗
#ይቅርታ የቆሸሸ ልብ ማጥሪያ ነው።
💞💞💞💞💞

#ስለዚህ_ተወዳጆች
    *ይቅርታ መጠየቅ እድል ነው ልባችሁ ቆሽሾ ከሆነ ዛሬውኑ አጥሩት ነገ ይቅርታ ከምትጠይቁት ሰው ጋር ተላልፋችሁ እንዳይፀፅታችሁ።

💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁
📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖📖
       #Share
💐📖💐💐🍁💐🍁💐🍁💐🍁



                   🖤SHARE🖤
በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ!💪

— “ገና በዘጠኝ አመቴ በግዳጅ ተደፍሬ ነበር” (ኦፕራ ዊንፍሬይ)

— ”የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን እንኳን በአግባቡ ተከታትዬ
አልጨረስኩም“ (ቢል ጌትስ)

— ”አባቴ የወሲብ፡ የስነ-ልቦና፡ የስሜት ጥቃት ያደርስብኝ
ነበር፤ ይህ ድርጊትም በ18 አመቴ ቤት ለቅቄ እስከምወጣ
ድረስ ተባብሶ ቀጥሎ ነበር“ (ከ90 በላይ የሚገመቱ
መጽሀፍት ደራሲት ጆይስ ሜየር)

— ”የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ከክፍል ክፍል ለመሸጋገር
ፍዳዬን አይ ነበር“ (ዶክተር ቤን ካርሰን)

— ”የእግር ኳስ ስልጠናዬን በአግባቡ ለመከታተል
የሚያስችለኝን ገንዘብ ለማግኘት ስል በአስተናጋጅነት
ሰርቻለሁ” (ሊዮኔል ሜሲ)

— “ቤት ስላልነበረኝ፡ በጓደኛዬ ቤት ወለል ላይ እተኛ ነበር፤
የለስላሳ ጠርሙሶችን ሰብስቤ እሸጥ ወይም በምግብ እለውጥ
ነበር፤ በአቅራቢያችን ካለ ቤተ-መቅደስ ይሰጥ ይነበረ
ሳምንታዊ ነጻ የምግብ ድርጎ ለመቀበል ዘወትር ወደዛ
አመራ ነበር“ (ስቲቭ ጆብስ)

— “አስተማሪዎቼ ‘ስንፍና’፡ ‘ውድቀት’ እያሉ ይጠሩኝ
ነበር” (ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌይር)

— ”ለ27 አመታት እስር ቤት ውስጥ
ነበርኩኝ“ (ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ)

_____
ለወዳጅዎ ያጋሩ
     📙"ማ
ንበብ 💐 ህይወት ነው"📙

https://t.me/hopereding
#share