ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕
215 subscribers
76 photos
298 links
ሰላም 🤚 -

📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯


በዚህ ቦት አማካኝነት https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙
➡️.  ልቦለዶችን 📖
➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕
➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚
➡️.  ግጥሞችን 📝
➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙
➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ።
አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች

▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
Download Telegram
​​➛➛ከመናገር ማሰብ ይቅደም➛➛

➲ በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል። ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት፡፡

አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፤

አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፤

አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡

ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ "ሽንኩርቱን እበላለሁ" አላቸው፡፡
:
አንድ ኪሎ ሽንኩርት ቀረበለት፡፡ ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ታድያ ዓይኑ ማልቀስ ፣ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ፤ አልቻለም። ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡

ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም፡፡ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡

«እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡

«አልቻልኩም» አላቸው፡፡

«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡

«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡

«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት።

ብዙዎቻችን ከመናገራችን በፊት ማሰብ ሳንቸል ቀርተን በዘፈቀደ በተናገርነው ቃል እራሳችንን ፣ ቤተሰቦቻችንን ፣ ጎረቤታችንን አልፎም ሀገርን እረብሸናል፤ ጎድተናል፡፡ ሁሌም ከማውራታችን ከመፃፋችን በፊት የምናገረው ፣ የምፅፈው ነገር ሰዎችን ያስከፋል? እውነት ነው ብለን እንጠይቅ፡፡ እውነት እራሱ የብዙሀንን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ካለቦታውና ካለወቅቱ አይገለፅም፡፡
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/hopereding
ጠብቄሽ ነበር
እስክትመጣ
አለ አይደል
እንደናፈኩሽ እንደምትወጂኝ እስክትነገሪኝ
ካለእኔ ከባባድ ጊዜያትን እንዳሳለፈሽ
በመለያየታችን የሆንኩትን ሁሉ እንደሆንሽ
እስክትነግሪኝ ጠብቄት ነበር....😥
አልመጣቺም!

እሷ ዘግይታ ይሁን እኔ ፈጥኚ
እንጃ ብቻ ቀስ በቀስ
መሔዱን ተለማመድኩት:
አለ አይደል
እሷን ባጣው ብዬ ሳስብ ይሰማኝ የነበረው ስሜት እና ከተለያየንነ
የተሰማኝ ስሜት ለራሴም አስገረመኝ...🤔
ምናልባትም መጠበቅ አድክሞኝ ይሆናል::😥
እዚጋ የገባኝ
ነገሮች ሲታስቡ ..ሲሆኑ እና ከሆኑ በኋላ ጭራሽ የተለያየ ስሜት
እንዲሰማን ማድረጋቸው ነው ::

ብቻ ግን ጠብቄያት ነበር.....
የምናዘወትርበት ቦታነ መንገድ ላይ
ድንገት ብንገናኝ እንኳ
የማወራውን ተለማምጄ ድንገት ወደቀደመው ነገራችን ብንመለስ
ለልደቱ የሚሆን ስጦታን ገዝቼ ...💐🎂

አበድኩልህ የሚሉኝን ሴቶች ፍቅረኛ አለኝ እያልኩኝ ሸኝቼ ...
ለጓደኞቼ በእኔ እንዴት አስችሏት ይጨክናለች
ተውት በቅርቡ እንመለሳለን እያልኩኝ...😥

ያላእሷ ያላፍኳቸውን ቀናት እየረገምኩኝ...🤔

እየሁ እከራረም እየሁ ጊዜያት እያለፍኩ መምጫዋን ስጠብቀ
ነበር...

ዘገየች መስል ወይም ፈጠንኩኝ መሰል
ኑረቱ ድብዝዝ ካለብኝ በኋላ..

አንድ ቀን ከእንቅልፌ ባንኚ ስነሳ

እንዴት እረሳኋት ብዬ ማሰብ ስጀምር

ናፍቆት እይነት ስሜት ሲሰማኝ

ሳላስበው ድንገት ደወለች

ስልኩን ለማንሳት እመነታሁ

በስነስርዓቱ ከእንቅልፌ መንቃቴንም ተጠራጠርኩ
ደውላ ነው ደውዬ የሚለውን ሳስብ ስልኩ መጥራት እቆመ
ተነሳሁነ ሻወር ወስድኩ

የተጫጫነኝ ነገር ከራሴ ላይ ተንሸራቶ ሲወርድ
የሆነ ሸክሜ ሲቀል እይነት ስሜት ተስማኝ

የምወደውን ፍርፍር እና ቡናዬን ጠጣሁ
መኝታዬ ላይ ተመቻችቼ ተቀምጩ ማስብ ጀመርኩ
ወደኋላ የመጎተት እይነት ሀሳብ

ስልኬን ስከፍት የፅሁፍ መልዕክት እገኘው

"ሲመችህ መልስህ ደውል ላወራህ እፈልጋለሁ "

ደስ አለኝ ምን እንደሆነ እስካሁን የማልለየው አይነት ስሜት ተስማኝ
ደወልኩ በመጀመሪያው ጥሪ ተነሳ

አወራን ት ለቀናት ደግ መን ተደዋወልን ት ተገናኘን


ያለፍኩትን ህመም ሲታመም አየሁት ትዝ ኣለኝ

አብሮኝ መሆን እንደምትፈልግ ደጋግማ ነገረችኝ

አሺም አምቢም ሳልል ወደ ቤቴ ሄደኩ

ቤት ስገባ ከዚህ በኋላ አንዳትደውየልኝ መልዕክት ልኬ

ስልኳን Blacklist ውስጥ ከትቼ ተኛሁ

በጊዜው ፈልገን ያጣነው ነገር ካለፈ በኋላ ሲመጣ ለምንድነው ደስ
የማይለው?
👭ሀለት እህትማማቾች አባታቸው በጠና ለአመታት ይታመማል ሁለቱ እህትማማችች አባታቸውን እያስታመሙ ሳለ አንደኛዋ ጥቂት ወራተ ካስታመመች በሀላ መሰልቸት ጀመረች ሰበብ እየፈለገች ከአባቷ አካባቢ ትርቃለች በመጨረሻም የማስታመ ሙ ሀላፊነት በመሉ አንደኛዋ ላይ ይወድቃል
         ታዲያ ይሄን ያስተዋሉ ታማሚ አባት ዘወትር እህትሽ ወዴት አለች እያሉ ይጠይቃሉ ታጋሽ እህት ግን አላውቅም አባዬ ትላለች ከብዙ አድካሚ እና አሰልቺ አመታት በሀላ አባት ተዳከሙ እናም ሁለቱ ልጆቻቸው የአባታቸውን የመጨረሻ ቃል ለመስማት አባታቸው አጠገብ ቆሙ አባትም ትዕግስተኛዋንና እስከመጨረሻ ያስታመመቻቸውን ልጃቸውን ወደራሳቸው ጠርተው ይናገሩ ጀመር """ልጄ ቤትሽ ይቆሽሽ ሁሌም ቆሻሻ አይጣው ""
ሁለተኛዋንና ስልቹዋን ልጃቸውን ጠርተው ""ልጄ ሁሌም እንደፀዳሽ ኑሪ ያስቀመጥሽውን ማንም ሳያበላሽብሽ እንደተቀመጠ ቤትሽ እንደተፀዳ ይቆይሽ""
       ብለው መረቋቸው  ሰው ሁሉ ተገረመ እሳቸውም አረፉ ከአመታት በሀላ ትዕግስተኛዋና ቤትሽ ይቆሽሽ የተባለችው እህት ብዙ ልጆች ወለደች ቤቷ በልጆች መጫወቻና በልጆች ምግብ ፍርፋሪ  ሞላ በደስታ ሳትሰለች እያፀዳች ልጆቿን በፍቅር አሳደገች በመጨረሻም ልጆቿ ጥሩ ቦታ ደርሰው ከብቸኝነት ከድህነት ኑሮ አሳረፏት አያትም ሆነች
  በተቀቃራኒው ስልቹዋ እና ፀድተሽ ኑሪ የተባለችው እህት አንድም ፍሬ ሳይኖራት በልጅ አምሮት እንደተሰቃየች ቤቷ አፅድታ እንደተወችው የሚጠብቃት ያስቀመጠችውን የሚደፋ ያጠበችውን የሚያቆሽሽ ያኖረችውን ከቦታው የሚያንቀሳቅስ ልጅ ባይኗ እንደዞረ በስራ ደክማ ታማም ስትተኛ ቀና እርጎ የሚያስታምማት ልጅ ሳይኖራት ኖረች
  እንግዲ ልጆች ሲኖሩን ኡፍ አበላሹት ኤጭ ደፉት እያልን የምንማረር ሰዎች ይህ ጥሩ አይደለም እኛ ያገኘነውን በረከት ያጡ ብዙ አሉና ተመስገን እንበል በበረከቶቻችን ዘወትር እንደሰት እናመስግን
https://t.me/hopereding
ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም"
ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም"
50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው

ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝ
"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"
በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት😍
     ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው ❤️🙌🏼
https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding
እንኳን ከኔ ጠፍተሽ...እንኳን ከኔ እርቀሽ
አጠገቤም ሆነሽ ትናፍቂኛለሽ...
የመዋደድ ኬላ መድረሻ ድንበሩ
መናፈቅ እኮ ነው የፍቅር ደም ሥሩ

አለሽ ጨረቃ ላይ
አለሽ ፀሐይዋ ላይ
አለሽ ሰማዩ ላይ
የትም አይሻለሁ የኔ ሙሉ ክፋይ

ተራራው አንቺ ነሽ
ባሕር ወንዙ አንቺ ነሽ
አገር ምድሩ አንቺ ነሽ
የትም ቦታ ሆኜ የትም ቦታ ሆነሽ


        የፍቅር_ደብዳቤ ቁጥር 98


  ┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹ለ13✿🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
         https://t.me/hopereding
   https://t.me/hopereding     
        🌹🌺 የደሃ ፍቅር❤️

በቴሌግራም  እንደ ተከታታይ ፊልም በጉጉት የሚጠበቅ እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️የደሀ ፍቅር
🌺የተሰኘው ልብ አንጠልጣይ አጓጊና ተወደጅ የፍቅር ታሪክ ይዤላችሁ መጥቻለው በማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕 ቴሌግራም ገፅ ብቻ እንደምትወዱት ምንም ጥርጥር የለውም። በ ቅርብ ቀን💛 የደሀ ፍቅር ይጀምራል...

https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding
     👭ሀለት እህትማማቾች
https://t.me/hopereding
     👭ሀለት እህትማማቾች

አባታቸው በጠና ለአመታት ይታመማል ሁለቱ እህትማማችች አባታቸውን እያስታመሙ ሳለ አንደኛዋ ጥቂት ወራተ ካስታመመች በሀላ መሰልቸት ጀመረች ሰበብ እየፈለገች ከአባቷ አካባቢ ትርቃለች በመጨረሻም የማስታመ ሙ ሀላፊነት በመሉ አንደኛዋ ላይ ይወድቃል
         ታዲያ ይሄን ያስተዋሉ ታማሚ አባት ዘወትር እህትሽ ወዴት አለች እያሉ ይጠይቃሉ ታጋሽ እህት ግን አላውቅም አባዬ ትላለች ከብዙ አድካሚ እና አሰልቺ አመታት በሀላ አባት ተዳከሙ እናም ሁለቱ ልጆቻቸው የአባታቸውን የመጨረሻ ቃል ለመስማት አባታቸው አጠገብ ቆሙ አባትም ትዕግስተኛዋንና እስከመጨረሻ ያስታመመቻቸውን ልጃቸውን ወደራሳቸው ጠርተው ይናገሩ ጀመር """ልጄ ቤትሽ ይቆሽሽ ሁሌም ቆሻሻ አይጣው ""
ሁለተኛዋንና ስልቹዋን ልጃቸውን ጠርተው ""ልጄ ሁሌም እንደፀዳሽ ኑሪ ያስቀመጥሽውን ማንም ሳያበላሽብሽ እንደተቀመጠ ቤትሽ እንደተፀዳ ይቆይሽ""
       ብለው መረቋቸው  ሰው ሁሉ ተገረመ እሳቸውም አረፉ ከአመታት በሀላ ትዕግስተኛዋና ቤትሽ ይቆሽሽ የተባለችው እህት ብዙ ልጆች ወለደች ቤቷ በልጆች መጫወቻና በልጆች ምግብ ፍርፋሪ  ሞላ በደስታ ሳትሰለች እያፀዳች ልጆቿን በፍቅር አሳደገች በመጨረሻም ልጆቿ ጥሩ ቦታ ደርሰው ከብቸኝነት ከድህነት ኑሮ አሳረፏት አያትም ሆነች
  በተቀቃራኒው ስልቹዋ እና ፀድተሽ ኑሪ የተባለችው እህት አንድም ፍሬ ሳይኖራት በልጅ አምሮት እንደተሰቃየች ቤቷ አፅድታ እንደተወችው የሚጠብቃት ያስቀመጠችውን የሚደፋ ያጠበችውን የሚያቆሽሽ ያኖረችውን ከቦታው የሚያንቀሳቅስ ልጅ ባይኗ እንደዞረ በስራ ደክማ ታማም ስትተኛ ቀና እርጎ የሚያስታምማት ልጅ ሳይኖራት ኖረች
  እንግዲ ልጆች ሲኖሩን ኡፍ አበላሹት ኤጭ ደፉት እያልን የምንማረር ሰዎች ይህ ጥሩ አይደለም እኛ ያገኘነውን በረከት ያጡ ብዙ አሉና ተመስገን እንበል በበረከቶቻችን ዘወትር እንደሰት እናመስግን
🌺🌺🌺🌺🙏🙏🙏🙏
https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding

"ምን ኣነበብኩ ከሞት የምታተርፈው ትዝታ ብቻ ነው"
የሚል ነገር...
ኣሁን ላይ ቡዙዎቻችን ኣኗኗሪችን ትዝታ ብቻ ነው

ኣድርገን ሳይሆን ኣስታውሰን ፈገግ የምንልባቸው ነገሮች በዝተዋል...

ምስጋና ለእነርሱ ትላንታችን ውሰጥ ለነበሩ.....
🌺🌺🌺🌺🙏🙏🙏🌺🌺🌺
https://t.me/hopereding
ከአመዷ ጀርባ

..እናም እራሴን መዋሸት ደከመኝ። የውሸት መጀመሪያ እራስን
መዋሸት ነዋ፤ ውሸት ስለደከመኝ ለማመፅ ወሰንኩ። ይሄ ውሳኔ ከእኔ
የመጣ አለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የተሰማኝን፣ ያሻኝን ስናገር፣ እራሴን
መሆን ስጀምር እና ብዙሃኑን መከተል ሳቆም፣ 'አመፀኛ ናት፣ ወፈፍ
ያደርጋታል፣ በሽ ናት'፣ የሚል የመጀመሪያ ደረጃ “የእውነት" ማዕረግ
ተሰጠኝ። ይሄ ታሪካዊ ማዕረግ፣ የትኛውም እራሱን ለሚያዳምጥ
የሰው ልጅ፣ ብዙሀኑ ለዘመናት ሲጠቀሙበት የነበረ በመሆኑ፣
ማንንም እንደማያስከፋ መረዳት ያስፈልጋል። እውነትሽን በነፃነት
መናገር የምትችይው በስካር እና በእብደት ጥላ ስር ከሆንሽ ብቻ
ነው፡፡ ለዚያም ነው፣ የሰው ልጅ ዘመኑን በሙሉ እራሱን አልኮል ጥላ
ስር መወሽቅ የሚፈልገው፡፡ ይህ፣ እየተካሄደ ያለውን እወነታ ለመካድ፣
ላለማየትና ላለመስማት፣ ወይም ኅላፊነት ላለመውሰድ ያግዘዋል።

https://t.me/hopereding
🔣🔣🔣🔣🔣🔣❣️🔣🔣🔣🔣🔣🔣


       አንድ ጊዜ ጸጥታ 👌


ደስታና ሠላም፡ የውስጥ መረጋጋት ፣
ትልቅ ሀብት ናቸው፡ ኑሮን ላወቀበት ። 

የጸጥታ ዛፍ ስር  ቁጭ፡  ብሎ መጠለል፣
መንፈስን ማናፈስ ፡ ጭንቀትንም ማቅለል ።

አንድ ጊዜ ጸጥታ !
ዝግ ብሎ ማድመጥ የልብን ትርታ ።

ለደቂቃዎች ያህል ፡ ራስን ማዳመጥ፣
በዝምታ ባህር ፡ ወደ ጥልቁ መስመጥ።

ጩኸት መጯጯኹን ፡መግታት ለአንድ አፍታ ፣
ትርምስ ትርምስምሱን፡ ሁካታ ዋይ ዋይታ ፣
አንድ ጊዜ ጸጥታ !

በጽሞና ሀሳብ ፥ በተመስጦ መዋጥ ፣
ሠላምን መፈለግ ፡ራስን መሰብሰብ ።

አንድ ጊዜ ጸጥታ!
ለአንድ አፍታ ዝምታ ።

✍️
ማንበብ ሕይወት ነው
https://t.me/hopereding
❝Bittersweet or Fragile❞
---
Everything that is born will fade away,
Leaving behind shadows of yesterday.
It's a truth that brings some tears,
Yet it’s a reality I hold dear.

The thought of love can be quite wild,
But the fear of loss leaves me reviled.
I hesitate to bring a child to this place,
For the pain of loss is a heavy embrace.

I'm afraid to love, for I dread the pain,
Not wanting to hurt or feel the same.
Oh, the universe, why are we so blind,
To our fragile hearts and troubled minds?

2..21
https://t.me/hoperedingኣይነስወር ኣይኑ በርቶ
ማየት የጀመረ ቀን ላይ...
መጀመሪያ የሚወረውረው ነገር
በህይወት ሁሉ የረዳው በትሩን ነው የሚወረወረው?

✍️የማወራው ሰለ በትሩ ግን ኣይደለም?
https://t.me/hopereding
" ከንቱ መሆን አልፈልግም ፡ ለማላቃቸው ሰዎች
እንኳን ሳይቀር ደስታን መፍጠር እፈልጋለሁ።
ከሞት በኋላም ቢሆን መኖር እሻለሁ።።

✍️ አና ፍራንክ
​​መካድ ያመነጨው እርግማን

ወደድኩህ ስትይኝ
ሰጥቼሽ አልነበር ክቡር ድንግል ልቤን፣
በፍቅር አስክረሽ እስክነጠቅ ቀልቤን?

አፈቀርኩህ ስትይ
በገላሽ ልገድፍ ሁዳዴን ጾም ጥሼ፣
አልተጋደምኩም ወይ እምነት ተንተርሼ?

ግን ምን ዋጋ አለው
አንፍሰሽ ጥለሽው መውደዴን በወንፊት፣
ተጀቡነሽ አየው የማስመሰል ቅርፊት።
ደሞ አለማፈርሽ
በማጣት ገደል ስር ገፍተሽኝ ለመሄድ፣
ሾርበሽ ቆየሽኝ
አትወደኝም የሚል ሀሰት ለበስ ገመድ።
ጠንቅቀሽ እወቂ
የማፍቀርን ሚዛን ተፈቃሪ አይለካም፣
መቀበልን ሚሻ በመስጠት አይረካም።

ተቀበይ!!
:
አንጥፌልሽ ሳለ የገላዬን ምንጣፍ፣
ንቀሽ ስለተኛሽ በክህደት መዳፍ፤
ሕመም እንድትዘግኚ!
ስቃይ እንድትቀምሺ!
በንዴት ካረረው ጥቀርሻ ልቤ ላይ፣
ነድዬ አዘንባለሁ የ'ርግማኔን ቀላይ።

እነሆ በስብሺ!!
:
እምነቴን ተርትረሽ ለእጦት የዳርሽኝ፣
ዐይንሽ ብርሃን ይመኝ አይማርሽ ወረርሽኝ!!
ተስፋዬን ቦጫጭቀሽ የጣድሽኝ ለጽልመት፣
መርጋት አምሮሽ ይቅር ያንከልክልሽ ክህደት!!
ፍቅሬን አመናጭቀሽ ምሬት የጋበዝሽው፣
ኑሮ ኮሶ ያጥባሽ ይጥላሽ የወደድሽው!!
የኔን ሕመም ሁሉ በተራሽ ቅመሽው!!



       *💔*
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢


   
https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding
ተጀመረ ተጀመረ ተጀመረ

​​"የድሀ ፍቅር"

በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ,::

ክፍል 1⃣
      ቢኒያም እባላለው ተወልጄ ያደግሁት ስም የለውም ማለቴ አዲስ አበባ ሆኖ አስፓልት ዳር ትንሽዬ የሸራ ዳስ ውስጥ  ነው አባቴን አላውቀውም እናቴ ነች ያሳደገችኝ ሌላም እንድ ወንድም አለኝ ናቲ ይባላል,ብቻ እናታችን እኛ እንዳንራብ የምትችለውን ሁሉ ታደርግልናለች ከሰው እኩል እንጂ ከሰው በታች ስትሆኑ ማየት አልፈልግም ትላለች ,
   
        እናቴ ያገኝችውን ትሰራለች የፓላስቲክ ቤት ብትኖረንም እናቴ ተመላላሽ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማንጠፍ ከዛ  መልስ ደግሞ ተመላላሽ የሰው ቤት እንጅራ መጋገር ልብስ ማጠብ ትሰራለች ብቻ እረፍት የላትም እኔም ትንሽ ጠንከር ሰላልኩ ጫማ መጥረግ ማስቲካ ከረሚላ የሞባይል ካርድ እሽጣለው ብቻ ትንሽም ቢሆን አግዛታለው እናቴ ትምህርቴን በደንብ እንድማር ትፈልጋለች ,
  
         በቃ ከሀብታም ልጅ እኩል አድርጋ ትልቅ ትምህርት ቤት አስገባችኝ እሷ እየለፋች ለኔ ለወር ለትምህርት ቤት ትከፍላለች የ 10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነኝ ጎበዝ ስለሆንኩ ተማሪዎቹም አሰተማሪዎቹም ይወዱኛል ድህነቴ ትዝ አይላቸውም እኔም የእናቴን ምኞት ለማሳካት በርትቼ አጠናለው እማራለው በትርፍ ጊዜዬ እናቴን አግዛታለው  ከትምህርት ቤት እምደተመለስክ የተቀዳደደ ሱሪዬን ለብሼ ወደ ስራ እሄዳለው እናቴን ማገዝ ግዴታዬ ስለሆነ,.
  
     በትምህርት ቤታችን ውስጥ በጣም የዋህና ምስኪን ሜላት ናት አንዳንዴ ምሳ ስለማልቋጥር የሷን ምሳ አብረን እንበላለን ብቻ ጥሩ ልጅ ነች በጣም ተቀራርበናል የኔ ማንነትና እሷ ግን በፍፀም አይገናኝም ሰማይና ምድር ነበር ነገር ግን በሁለታችን ልብ ውስጥ ፍቅር ተፈጠረ,
   
       እኔና ሜላት የፍቅር ግንኝነት ጀመርን እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እሷ ግን የሀብታም ልጅ ነች በፍቅር ግን ሁለታችንም እኩል ነን ሀብታሞች,የሚገርመው ድህነቴን እያወቀች ለደቂቃ ተከፍታብኝ አታውቅም ሁሌም አብራኝ ነች የምንኖርበት የሸራ ቤት እንኳን ደብሯት አያውቅም ብቻ ሁለታችንም በፍቅር  ክንፍ ብለናል,
       
       የትምህርት ክፍላችን አንድ ስለሆነ በትምህርት  በደረጃና በእውቀት ትንሽ በለጥ ስለምላት እረዳታለው እኔም የእናቴን አላማና ፍላጎት ለማሳካት በደንብ እየተማርኩ ነው አስረኛ ክፍልን ማትሪክ ተፈተንን,ሁለት ወር ክረምትን ሜላት ከቤት ብዙም መውጣት ስለማይፈቀድላት በሳምንት አንዴ እየተገናኝን ቀጠልን ተነፋፍቀን ስንገናኝ ደስ ይለኛል ሁለት ወር ክረምትን እኔ የቀን ስራ እየሰራሁ እናቴን ያንኑ ስራዋን እየሰራች ቤት ተከራየን ከዝናብ ብቻ የምታድን ትንሽዬ ቤት በ100 ብር አገኝንና እዛች ውስጥ መኖር ጀመርን አሁን ጎርፍ መጣ አልመጣ ሀሳብ የለም ብቻ ተመስገን ነው .
 
        ሜላት ቤተሰቦቿ ሳያዬ ልብስም እቃም ታመጣለች የማይፈልጉትንም ታመጣልናለች ደስተኛ ባልሆንም እምቢ ማለት ግን አልፈልግም  እምቢ ስል አንዳንዴ ሲከፋት ሰለማይ ነበር  ዝም የምላት መድረስ አይቀር መስከረም ደረሰ የማትሪክ ውጤት መጣ,.......


    ይቀጥላል✍🏻 
https://t.me/hopereding
"ከምንም በላይ "መጠበቅ" ሰውን ይጎዳል።
ሰውን አለማግኘቱን ኣለመምጣቱ ሳይሆን መጠበቁ ይበልጥ ይጎዳል