ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕
219 subscribers
65 photos
282 links
ሰላም 🤚 -

📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯


በዚህ ቦት አማካኝነት https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙
➡️.  ልቦለዶችን 📖
➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕
➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚
➡️.  ግጥሞችን 📝
➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙
➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ።
አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች

▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
Download Telegram
'ሕልሚ ናይ ዝኾነ ይኹን ሰብ ኣይትቕተሉ'
           🙏በጃኹም


ንሓደ ፉጡር ንምጥፋእ ማለት ንምቕታል ቅድሚ ምሕሳብኩም፡
ኩሉ ግዜ ነቶም ኣብኡ ዝምርኮሱ ወይ ድማ ብዛዕባ እቶም ብእኡ ዝጥወሩ ሕሰቡ።

ናይ ሓደ ሰብ ሕልምን ራኢን ኣብ ትቐትልሉ ግዜ እቲ ዝሳቐ ንሱ ዘይኮነ እቶም ኣብቲ ሕልሚ ብምምርኳስ ሕልሞምን ራእዮምን ክጭብጡ ተስፋ ዝነበሮም ሰባት ኢዮም።

ማዕረ ክንደይ ንእሽቶ መሲሉ ይረአ ብዘየገድስ፡ በጃኹም ኣብኡ ዝምርኮሱ ብዙሓት ስለዝኾኑ፡ ሕልሚ ናይ ዝኾነ ይኹን ሰብ ኣይትቕተሉ፡፡

https://t.me/hopereding
📙 ትጋ~

ስላንተ ቢያወሩ ሰዎች ተደራጅተው፣
ካየህ እለፋቸው ከሠማህም ተወው፤

የሠነፍ ስራው ነው በሌላው የቀና፣
አንተ ንፁህ ከሆንክ ባለህበት ፅና፤

አንተን ለማቀጨጭ ሺ ቃል ቢወረወር፣
አስብ ተረጋግተህ እራስህን መርምር፤

የተባለው ነገር እውነትነት ካለው፣
እራስህን ለውጥ አ'ጣል ተጠቀመው፤

እንጅ ያ ሠው
ጠላቴ ነው አትበል ለበቀል አትቁም፣
ከስራህ ፊት ሁሌ ፈጣሪን አስቀድም፤

ነገሩ ጠንቅ ቢሆን አንተን የሚጎዳ፣
በአለም የጭንቅ ቀን መኖሩን ተረዳ፤

በውሸት ማዕበል አለም ብትናጋ፣
ማንንም አትስማ
ማደሪያህ ነውና ለስራህ ግን ትጋ፤

https://t.me/hopereding
📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖📖
                    "በደስታ እንተኛ"
        

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው
ተኝተዋል! ... ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል።
አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል
ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል ...
ከመስኮት አጠገብ ነው።
ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት
በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል።
እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ
ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣
በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት
እንደሚያሳልፉ... ወዘተ
አውርተዋል።
⚂ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ
ውጭ እየተመለከተ
ሁሉን ነገር #በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል።
".....በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁ
ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን
መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ...
ፍቅረኛሞች በአንድ
እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ ..
ከሀይቁ ባሻገር ውብ
የሆነ ከተማ ይታየኛል .... ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ "
በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ
ይተርክለታል! ... በዚህ
አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።
አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች።
ከመስኮት አጠገብ ያለው የተቀመጠው
በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች።
ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ።
ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን
ጠርታ አዘዘቻቸቸው! ...
ያ ብቻውን የቀረው በጀርባው የተኛው በሽተኛ አልጋውን
ከመስኮቱ አጠገብ እንዲወስዱለት ጠየቀ።
ወሰዱለት።
ሟች የነገርውን በሙሉ  በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ
ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ
ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!
"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ። "ሰዉዬው ብዙ አስደሳች
ነገሮችን በዚህ መስኮት
አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት። "ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል
#አይነስውር ነበር
አለችው።"
ልብ የሚነካ ነገር.... ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን
ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ
ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።
አንዱን ለማጠንከር ወይም ለማበርታት የኛ ጥንካሬና ብርታት
አስፈላጊ ነው።
  ለሰወች ደግ ነገር በማድርግ
የተጨነቀ አምሮአቸውን ፈታ ዘና
እናድርግ
ስለዚህ ይሄንን ታሪክ ሼር በማድርግ
ደስታን እናስተምር፣
እንማር
❤️ በደስታ እንተኛ
📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖

    https://t.me/hopereding
የብራዚል እስረኞች አንድ መፅሐፍ አንብበው ሲጨርሱ ሪፖርት ያቀርባሉ 4ቀንም ከእስር
ዘመናቸው ይቀነስላቸዋል። ይህ አሰራር ወደ እኛ ሀገር ቢመጣስ ብዬ ተመኘሁ ለምን
አትሉኝም ? ብዙ እስርቤቶች እና ብዙ እስረኞች ስላሉን :: ባይሆን ይቺን እንኮርጅ ! ! እስቲ
ምን ትላላችሁ ?

📖📖💐"ማንበብ ህይወት ነው"💐📖

https://t.me/hopereding
 
https://t.me/hopereding
•••••••••••••••••••ሞሮ••••••••••••••••
.            •••••••ክፍል_33••••••

ኪያር ሰአቱን እያየ አረ ብቃ እንሂድ እዚው ልናድር ነው እንዴ አለን ሳይታወቀን ብዙ ሰአት ቆይተን ነበር። ከአዩ ሆቴል ወጥተን ወደ አዳማ ዩኒቨርስቲ ሄድን ልክ በሩ አከባቢ ስንደርስ መኪናዋን አቆምኳት ልቤ በፍጥነት እየመታ ነበር ጭንቀቴ ለማንም ሰው ያስታውቃል መሪውን ጭምቅ አድርጌ ያዝኩት ሰሙ እጄን እያሻሸች ናዲ ቅድም ያልኩህን አስታውስ አለችኝ እሺ አልኳትና ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ቀና ብዬ አከባቢውን አየሁ ምድረ ተማሪ ሻንጣውን እንደያዘ ወደ ግቢ ይተምማል ይወጣል ይገባል በሩ ጋር ጥበቃዎቹ ሻንጣ እየፈተሹ ነው ወከባ በወከባ ነው ቨከን ብዬ መኪናዋን ወደ በሩ አስጠጋውና ሻንጣዎቻችንን ለማስፈተሽ ወጣን። ከ30 ደቂቃ በላይ ከቆምን በኃላ አስፈትሸን ወደ ውስጥ ገባን። መጀመሪያ ሰሙን ወደ ሴቶች ዶርም አደረስናት መንገዱ ላይ ያሉት ሰዎች እንዳለ አይናቸውን ወደኛ ጣሉ ሰዉ ይበልጥ ሲያፈጥብን ልቤ በፍጥነት ይመታ ጀመር ሁሉም ሰው እየሳቅ እንደድሮው ሞሮው ጀዝባው እያለ የሚሳለቅብኝ መሰለኝ ቶሎ ብዬ ሰሙን በቃ ማታ እራት አብረን እንበላለን ቻው ብያት ውስጥ ገባው። እሷም ስለገባት ሳታጨናንቀኝ ቻው ብላኝ ሄደች። ቶሎ ብዬ መኪናዋን አስነስቼ እኔና ኪያር ወደተመደብንበት ዶርም ሄድን።
እኔና ኪያር የዶርማችን ብሎክ ስር መኪናዋን አቁመን ሻንጣዎቻችንን አውርደን ከታች የተመደብንነትን ዶርም ለማየት የተለጠፉት የስም ዝርዝር ላይ ስማችንን ፍለጋ ገባን እንዳጋጣሚ አምና በነበርንበት ነው የተመደብነው ከኪያር ጋር መሆኔ ደስ ቢለኝም ከሱ ውጩ ከአዲስ ስዎች ጋር እንዲደርሰኝ ፈልጌ ነበር። ሻንጣችንን ይዘን ወደ ሁለተኛ ፎቅ አዲሱ ዶርማችን ወጣን። ዶርሙን ከፍተን ስንገባ የዶርማችን ልጄች እየተንጫጩ ነበር እኔን ሱያዩኝ ሁሉም ናዲ.... እያሉ ሞቅ አድርገው ሰላም አሉኝ ኪያርን ረሱት እንዴት ነው? ሰላም ነው? ተጠፋፋን አይደል? በጣም አምሮብሃል ምን አጊንተሽ ነው? እንዴት ነህ ውጪ ያለችው መኪና ያንተ ናት አይደል?.... የጥያቄ መአት አዘነቡ ገረመኝ አምና አንድም ቀን ዞር ብለው ያላዩኝ ልጆች አሁን .... በጣም ተገረምኩና ኪያርን ዞር ብዬ እያየሁት ፈገግ አልኩ አይን ለአይን ተግባብተናል። ኮስተር ብዬ ደህና ነኝ አልኳቸውና ሻንጣዬን ይዤ ገባው አንደኛው ቆይ ላግዝህ ብሎ ሻንጣዬን ሊቀበለኝ ሲል አይ አያስፈልግም ራሴው ማስገባት እችላለው አመሰግናለው አልኩት። እኔና ኪያር ያልተያዘውን ድርብ አልጋ እንደድሮዋችን እኔ ከታች እሱ ከላይ ያዝን። ሻንጣዎቻችንን ከፍተን ለኛ ቅርብ የሆኑት ሎከር ላይ እቃዎቻችንን በስነስረአቱ እያወጣን ደረደርን አልጋችንን አነጠፍን በድሮ ነገር መመለስ ስላልፈለግኩ ሁሉም ያመጣሁት ነገር አዲስ ነው። እኔና ኪያር ይህንን ስናደርግ ሁሉም ዝም ብለው ያዩናል። ደክሞኝ ስለነበር አዲስ ባነጠፍኩት አልጋ ላይ ጋደም አልኩ የልጆቹ ሁኔታ በጣም እያስገረመኝ ነው አምና እንደዛ አይንህን ለአፈር ብለው እንዳልተጠየፉኝ አሁን አለውልህ አለውልህ አሉኝ አወይ ሰው ገራሚ ፍጥረት እንዲህ እንደ እስስት ይቀያየራል።
የተወሰነ ሰአት አሸልቦኝ ከተኛው በኃላ ስነሳ 11፡30 ሆኗል ኪያርን ቀስቅሼው ተነሳ ሰሙ ጋር ደውዬላት እንድንወጣ ነገርኳት ወዲያው ተነስቼ ልብሴን መለባበስ ጀመርኩ ለውጥ የጀመርኩት ከአለባበሴም ጀምሮ ነበር። ነጭ ሸሚዝ በበርገንዲ ክራባት እና በእርሳስ ከለር ሱሪ አደረግኩ ኪያርም እየዘነጠ ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ዶርሙ በር ላይ የተለጠፈ መስታወት ስለነበር ራሴን ላይ ሄድኩ መነፅሬን አድርጌ ፍሩዝ ፀጉሬን ሳስተካክል የዶርሜ ልጆዥ እያዩኝ በለው ናዲ... የምር አምሮብሻል ወዴት ልትወጪ ነው እንዲ ሽክ ብለሽ እኛም እንምጣ.. አሉኝ ድሮም እንዲ ናቸው አውቃቸዋለው በከንቱ ውዳሴ ይሸነግላሉ የሆነ ነገር ሲፈልጉ። አይ ይቻልም ፕሮግራም አለብን አልኳቸው ኪያር ና ቶሎ በል አልኩት ከእንደነኚ አይነት አስመሳይ እስስቶች ጋር ደቂቃ መቆየት አልፈለኩም ኪያርን አቻኩዬ አስወጣቼው ሄድን።
ይቀጥላል.......

34 👇👇
••••••••••••••••••ሞሮ •••••••••••••••••••
.           ••••••••ክፍል_34•••••••

እኔና ኪያር ሰምሃልን የቀጠርንበት ቦታ ቆመን እየጠበቅናት ከርቀት አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ስትመጣ ታየን መልኳ በውል አይታይም ብቻ በጣም የሚያምር ቀይ የእራት ልብስ አድርጋለች ንፋሱ ነጣ ያለ ቡኒ ፀጉሯን ያዘናፍለዋል ፍዝዝ ብዬ ቀረው የሆነ የህንድ ፊልም ላይ ያለች ሞዴል መስላ ታየችኝ ኪያር ጎኔን ጎሸም አደረገኝና አረ... እዛጋ እምትመጣውን ቀይ ለባሽ ቺክ እያት አለኝ ሳይታወቀኝ ወይኔ.... አልኩ ድምፅ አውጥቼ ምነው አለኝ ኪያር እንደ ኤቤጊያ እቺንም ልጅ ልወዳት ነው እንዴ አልኩት ኪያር ከት ብሎ ሳቀና አንተ በል ስነስርአት አንተ ደሞ ግቢ ስንገባ የመጀመሪያው ቀን ብቻ ነው እንዴ እማታቃትን ሴት እምታፈቅረው አለኝ። ፍዝዝ ብዬ እእእእ. .. አልኩት ኪያር ቆጣ ብሎ በል በል አሁንማ እንደባለፈው ስትሆን አላይህም በል እንሂድ ብሎ ልጅቷን እንዳላያት ይጎትተኝ ጀመር እየሳቅኩ አረ ልቀቀኝ አንዴ ልያትና እንሄዳለን አልኩ ተይሆንም ጀዝቢቲ እንሂሂ...ድ እያለ ፊቴን አዞረኝና መመለስ ጀመርን ትንሽ እንደሄድን ወደኃላ ስዞር ልጅቷ እጇን ወደኛ አቅጣጫ አውለበለበች ኪዩ አረ እየጠራችን ነው እኛን አልኩት ዞር ብሎ አያት እጇን ወደኛ አቅጣጫ እያውለበለበች ነው ሁለታችንም አከባቢያችንን ገልመጥ ገልመጥ እያለን አየን ከኛ ሌላ ማንም የለም ኪያር እኛን ነው እምትጣራው ብሎ ጠየቀኝ ምንም ሳልለው እስክትመጣ መጠበቅ ጀመርኩ። እየቀረበች ስትመጣ ማንነቷን መለየት ጀርን ኪያር ከት ብሎ ሳቀ ሃ..ሃ..ሃ..ሃ.... ወይኔ ውርደት ናዲ ፎንቃ ሊጠልፍሽ የነበረው ከሰሙ ነበር? ሃ..ሃ... አንተ ደሞ እንዴት አባቷ ናው ያማረባት ፀጉሯ እንዲ አልነበረም አይደል ቅድም ልብ አላልኩትም አለኝ። ሰምሃል መሆኗን ሳቅ ይበልጥ ተሸማቀቅኩ ወይኔ... አልኩ ኪያር እያየኝ ዝም ብሎ ይስቃል ሰሙ ስትደርስ የኪያር ሳቅ እየተጋባባት ምንድነው እሚያስቃችው አለችን እኔም እየሳቅኩ ባክሽ የሆነ ቀልድ ትዝ ብሎን ነው እምንስቀው አልኳት። ምንድነው ከኔም ንገሩኝና ልሳቅ ብላ ጠየቀች ወደኔ እያየች በ ፍጥነት አእምሮዬ ውስጥ ከሰማኃቸው ቀልዶች ማሰላሰል ጀመርኩ ደንግጬ ስለነበር ምንም ሊመጣልኝ አልቻለም ፈጠን ብዬ ባክሽ ይህንን ያክል ከሳቅሽ ይበቃሻል በኃላ ነግርሻለው አልኳት እሺ አለችና ክንዴን ያዘችኝና እንሂድ በቃ አለችን ክንዴን ስትይዘኝ ውጤን የሆነ ነገር ነዘረኝ ይህንን ስሜት ከዚ በፊት አውቀዋለው ውስጤ ተደበላለቀ። ሰሙ እኔና ኪያር መሃል ገብታ የሁለታችንንም ክንድ እንደያዘች ከግቢ መውጣት ጀመርን ልቤ ዝም ብሌ ይደነግጣል ራሴን ምን ሆኜ ነው ብዬ ጠየቅኩ። እየሄድን እያለ ሰሙ ሁለታችንንም ልብ ብላ ከላይ እስከታች አየችንና በጣም ዘንጣቹኃል ናዲ ነጭ ሸሚዝ በበርገንዲ ከረባት ይሄድብሃል ኪዩ ደሞ ሙሉ ጥቁር አሪፍ ምርጫ ነውበጣም አምሮባችኃል የሆነ ትልቅ ፕሮግራም ተጠርታችው ነው የሚመስለው አለችን። ኪያር እየሳቀ ያንቺንስ ማን አየልሽ የሌለ ሽክ ብለሽ የለ እንዴ ደሞ መቼ ነው ፀጉርሽን ቡኒ ያደረግሽው ቅድም እንደዚ ነበር አላት። ቅድም ነው ባክህ እንደዚ ያደረኩት እንዴት ነው ይሄድብኛል? አለችው ፀጉሯን እየነሰነሰች ኪያር እያያት በጣም!! አላት ወዴኔ ዞራ እእእ ናዲ አለችኝ ሰመመን ውስጥ ገብቼ ሰሙና ኪያ ያወሩትን ስላልሰማው ደንግጬ እእእ ምን? አልኳት ይሄድብኛል ወይ እንደዚ ፀጉሬ ወይስ ደስ አላለህም በቃ እንደነበረው አደርገዋለው አለችኝ አረ ያምርብሻል አልኳት።
በሚያምሩት ጥርሶቿ እየተፍለቀለቀች እሺ አለችኝ። ሁሉም ሰው አይኑን እኛ ላይ ጥሏል ሲያልፉ እንደ ድመት አይናቸው ተጋጉሎ እስኪወጣ እያፈጠጡብን ያልፋሉ። እንደለመድነው ከግቢያችን ፊትለፊት ወደ የኃና ሆቴል ገባን እዛ ቁጭ ብለን እራት እየበላን እየተጨዋወትን አመሸን። ኪያር በዚው ኦቨር ካልወጣን ብሎ ጭቅጭቅ እያደረገን ነው። አረ... በናታችው እንደዚ ዘንጠን ከግቢ የወጣነው እዚችው እራት በልተን ልንመለስ ነው እንዴ በዚው get down ከበርቻቻ እንበልበት ይለናል እኔና ሰሙ እየሳቅን አረ.... አይሆንም እንለዋለን እንዲ እየተጨቃጨቅን እያለ ኤቤጊያ ከራስታው ልጅ ጋር ሆና ወደ ሆቴሉ ገባች እሷም በጣም ዘንጣለች።

35 ይቀጥላል.......

https://t.me/hopereding
══════◄••❀••►══════
🌹🌿🌙✿...

❝በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።....

በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው።..መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።..አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል።..ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል።..ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።...

ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም።.. ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!..

አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጧችኋል፤ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኗችኋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኗችኋል።❞

ስብሃት ገብረእግዚአብሄር

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
       💐ማንበብ ህይወት ነው
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
https://t.me/hopereding
❥❥__⚘_❥❥
በፍጹም ተስፋ እንዳትቆርጡ!💪

— “ገና በዘጠኝ አመቴ በግዳጅ ተደፍሬ ነበር” (ኦፕራ ዊንፍሬይ)

— ”የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን እንኳን በአግባቡ ተከታትዬ
አልጨረስኩም“ (ቢል ጌትስ)

— ”አባቴ የወሲብ፡ የስነ-ልቦና፡ የስሜት ጥቃት ያደርስብኝ
ነበር፤ ይህ ድርጊትም በ18 አመቴ ቤት ለቅቄ እስከምወጣ
ድረስ ተባብሶ ቀጥሎ ነበር“ (ከ90 በላይ የሚገመቱ
መጽሀፍት ደራሲት ጆይስ ሜየር)

— ”የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ከክፍል ክፍል ለመሸጋገር
ፍዳዬን አይ ነበር“ (ዶክተር ቤን ካርሰን)

— ”የእግር ኳስ ስልጠናዬን በአግባቡ ለመከታተል
የሚያስችለኝን ገንዘብ ለማግኘት ስል በአስተናጋጅነት
ሰርቻለሁ” (ሊዮኔል ሜሲ)

— “ቤት ስላልነበረኝ፡ በጓደኛዬ ቤት ወለል ላይ እተኛ ነበር፤
የለስላሳ ጠርሙሶችን ሰብስቤ እሸጥ ወይም በምግብ እለውጥ
ነበር፤ በአቅራቢያችን ካለ ቤተ-መቅደስ ይሰጥ ይነበረ
ሳምንታዊ ነጻ የምግብ ድርጎ ለመቀበል ዘወትር ወደዛ
አመራ ነበር“ (ስቲቭ ጆብስ)

— “አስተማሪዎቼ ‘ስንፍና’፡ ‘ውድቀት’ እያሉ ይጠሩኝ
ነበር” (ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌይር)

— ”ለ27 አመታት እስር ቤት ውስጥ
ነበርኩኝ“ (ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ)

_____
ለወዳጅዎ ያጋሩ
     📙"ማ
ንበብ 💐 ህይወት ነው"📙

https://t.me/hopereding
#share
​​ደግመህ🛢

የፈሰሰን ውሀ መልሰህ ባታፍሰው
ጎትተህ ያለፈን ጊዜ ባትመልሰው

ደግመህ እንደገና ብትሞክር ምናለ
ውሀው ፈሰሰ እንጂ እቃው እኮ አለ።

             ይ🀄️🀄️ሉን        
        "ማንበብ ህይወት ነው"
         መልካም ለሊት   🙏🙏🙏
 
    https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding
​​••••••••••••••••••ሞሮ••••••••••••••••••••
            •••••••ክፍል 35••••••••••


መቀመጫ ቦታ ፍለጋ ወደያ ወዲህ ስትዞር ከኛ ጋር ተገጣጠምን  ልክ ስታየኝ ናዲ....! ብላ እየጮኀች እኛ ወደተቀመጥንበት ቦታ ሮጣ መጥታ ተጠመጠመችብኝ ሰሙንና ኪዩንም ሞቅ አድርጋ ሰላም አለቻቸውና ወዲያው ወደኔ ዞራ አንተ.... እንዴት ነው ያማረብህ በናትህ በጣም ወፍረሃል ቀልተሃል ደግሞ አረ... የምር ናዲዬ ደስ ይላል በጣም ሸበላ ቆንጅ...ዬ ሆነሃል አለችኝ እኔም እየሳቅኩ አመሰግናለው አቢ ሰላም ነዋ ተጠፋፋን አልኳት። ምን ተጠፋፋን ትላለህ አንተ ነህ የኮራኀው እንጂ እኔማ ስንት ግዜ ላግኝህ ብዬህ ነበር አለችኝ። እየሳቅኩ አ..ይ ... ምነው ብቻሽን እንዲ ዘንጠሽ አልኳት ውይ ረስቼው አለችኛ ወደኃላ ዞራ ናታን ብላ ራስታውን ልጅ ጠራችው ቀስ እያለ እኛ ወደተቀመጥንበት ቦታ መጣና ሰላም አለን። ኤቤጊያ እየተፍለቀለቀች ከናንተጋ ብንቀመጥ አይደብራችሁም አይደል ያው ቦታም የለም ደሞ አለችኝ ወደ ሰሙና ኪያር እየዞርኩ አየኃቸው ኪያር ምንም አልመሰለውም ሰሙ ግን እንዲው የደበራት መሰለኝ። እንቢ ማለቱ ስለከበደኝ አረ ተቀመጡ ችግር የለውም አልኳት እየተፍለቀለቀች ወንበር ስባ አጠገቤ ተቀመጠች ናታንም ወንበር ስቦ ተቀመጠ እሱም የደበረው ይመስላል።
እኛ ምግብ በልተን ጨርሰን ስለነበር እኔ ሰሙን እንነሳና እጃችንን ታጥበን እንምጣ አልኳት ኤቤጊያ ፈጠን ብላ ና ከኔ ጋር እንሂድ እኛም አሁን ስለምንበላ ልታጠብ አለችኝ ሰምሃልን ዞር ብዬ አየኃት በእጇ እንድሄድ ነገረችኝ እሺ ብያት ተነሳው ኤቤጊያ እጄን ይዛኝ ሄድን። በኔ እቅድ ሰሙን ይዣት ሄጄ ምን እንደደበራት ልጠይቃት ነበር ያሰብኩት ግን አልተሳካም። እጃችንን እየታጠብን እያለ ወደ መስታወቱ እያየች ናዲ ግን ምን አጊንተህ ነው እንዲ ያማረብህ ቆይ የእውነት በጣም ነው ያማረብህ አለችኝ እየተገረምኩ አመሰግናለው አልኳት ራሴን በመስታወቱ  አየሁት አምና የነበረው ለመሞት አንድ ሃሙስ የቀረው ናኦድ አልነበረም። በመስታወቱ ራሴን ትክ ብዬ እያየሁት እያለ ኤቤጊያ ወደታች ስባኝ ጉንጬን ግጥም አድርጋ ሳመችኝ እየሳቅኩ ምን ተገኘ ስላት እንዲው... ናፍቀኀኝ ስለነበር ነው የዛኔ ከግቢ ስመጣ የተገናኘን እኮ ነው አልናፈቅኩህም ኣለችኝ። አረ እንሂድ እየጠበቁን ነው አልኳት ስንቆይ ሌላ ነገር እንዳያስቡ ብዬ ፈጠን ብዬ ከመታጠቢያው ቀድሚያት ወጣው። ከኃላ ሮጥ ብላ ተከተለችኝ ሄደን ቦታችን ላይ ስንቀመጥ ኪያር እና ናታንን  እያወሩ ነበር ተነስ ታጥበን እንምጣ አለውና ተነሳ በእጁ ሰሙ እንድትነሳ ነገራት ታጥባቹ ኑ እኔ ቀጥሎ እሄዳለው አለችው እሺ ብሏት ሄዱ። ቤቱ በሙዚቃ ይናጣል ወደ ሰምሃል ጆሮ ጠጋ ብዬ ምናው ሰሙ ደና አይደለሽም እንዴ የደበረሽ ነገር አለ ኣልኳት። አይ ምንም የለም አለችኝ አነጋገሯ እንደደበራት ይበልጥ ያሳብቅባታል እነኪያር ሲመለሱ እሷ ልትታጠብ ሄደች እሷ እንደሄደች ትንሽ ቆይቼ እኔም ተነሳው ኤቤጊያ እጄን ያዝ አድርጋኝ የት ልትሄድ ነው ናዲ አለችኝ ኣንዴ ሽንትቤት ደርሼ መጣው አልኳትና ሄድኩ። መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ስገባ ሱሙ እያለቀሰች ነው ደንግጬ ምነው ሰሙዬ ምን ሆንሽብኝ አልኳት ድምፃን ሳግ እያነቀው ም..ምንም አልሆንኩም አለችኝ አቦ ሰሙ አትደብሪኛ እንዲ እያለቀስሽ አይቼሽ እንዴት ምንም አልሆንኩም ትይኛለሽ አልኳት። መጠጣት እፈልጋለው አለችኝ ምን? አልኳት ያልጠበቅኩት መልስ ስለነበር መ..ጠ..ጣ..ት እፈልጋለውውው አለችኝ  ይበልጥ ጮክ ብላ ለምንድነው ምትጠጪው አልኳት በቃ ዝምብለህ ውሰደኝ ናዲ መጠጣት ነው ያማረኝ አለችኝ። እሺ ወስድሻለው ግን ቅድም ኪያርም ኦቫር መውጣት እፈልጋለው ስላለኝ እሱንም እንጠብቀውና አብረን እንሂድ አልኳት እሺ... እልላችኝና እንባዋን በሶፍት ጠራርጋ የተበላሸው ፊቷን አስተካክላ ወጣን። ቦታችን ላይ ስንቀ መጥ ኪያር እያጣደፈ እሺ አኖቭርም አለ ወደኔ አፍጦ እያየ ኤቤጊያ ቀበል አድርጋው ዉዉዉ.... ልቶቭሩ ነው ደስ ሲል እኔም የሌለ መጨበስ  አምሮኛል አለችን ሁላችንንም እየሳቀች እያየች። እነኤቤጊያ እራት በልተው ከጨረሱ በኃላ ሁላችንም ተነሳን ወደ ኪያር ጠጋ ብዬ ሰሙ የሆነ ነገር ደብሯቷል እና እኔም አንተም በደምብ እንጠብቃት እሺ አልኩት እሺ ብሎኝ ኣምስታችንም ኮንትራት ባጃጅ ውስጥ ጥብቅብቅ ብለን ገብተን ወደ መብራት ሃይል ሄድን። ቬጋስ ክለብ ገባን ወዲያው ኪያርና ኤቤጊያ ተነስተው መጨፈር ጀመሩ እኔ ሰሙ እና ናታን መጠጥ አዘን ቀስ እያልን ስንጠጣ ሰሙ በፍጥነት የመጣውን ሶስት ደብል ጂን ሻት በአንዴ ዥው አድርጋ ላፈችው አረ ስሙ ተረጋጊ ገና እኮ ነው አልኳት ዝም ብላ አየችኝና ሌላ ጂን አዘዘች። ኪያር እና አቢጊ እየጠጡ ይጨፍራሉ ሶስታችን እነሱን እያየን እንሳሳቃለን በመሃል አቢጊ እኔን እየጎተተች ወደ ውስጥ አስገብታኝ መደነስ ጀመርን አንድ ሶስት ዘፈን ከጨፈርን በኃላ ስለደከመኝ ልቀመጥ ወደቦታዬ ስመለስ አቢጊ እእጄን ያዝ አደረገችኝና አንዴ ውጪ ደርሰን እንምጣ ንፋስ እንቀበል ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም አለችኝ እሺ አልኳትና ለሰሙ በእጄ ምልክት ሰጥቻት ይዣት ወጣው። ልክ በሩ ጋር ደርሰን  ትንሽ ንፋስ ከተቀበለች በኃላ ከአንገቷ ቀና አድርጊያት እንዴት ነሽ አሁን ትንሽ አልተሻለሽም አልኳት። ኤቢጊያ በፍጥነት ናዲ የዛኔ ቤርጎ አብረኀኝ ካደርክ ቀን ጀምሮ ስላንተ ማሰብ አላቆምኩም ወድጄሃልው ብላ ከንፈሬን ግጥም አድርጋ ሳመችኝ ሞቅታውም ስለነበት ትንሽ እንደተሳሳምን ራሴን ተቆጣጥሬ ገፋኃትና ምን እየሆንሽ ነው ብዬ ጮኬባት ስዞር ሰምሃል በእጃ ቢራ እንደያዘች ደረጃው ላይ ሆና ሁሉንም ነገር እያየች ነበር።

   ይቀጥላል

🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹🌹🌹
​​•••••••••••••••••••ሞሮ••••••••••••••••
          ••••••• ክፍል 36 •••••••••


ልቤ በፍጥነት ይመታል ኤቤጊያ እየተቅለሰለሰች ወደኔ ተጠግታ እስክትይዘኝ ድረስ  አጠገቤ እንደነበረች ሁላ ረስቻት ነበር ከሰምሃል ጋር አይን ለአይን ፍጥጥ ብለን እየተያየን ነው ሃሳቤ ሁሉ እሷ ጋር ሄደ ምን እንዳስደነገጠኝ አላውቅም እኔና ሰሙ ጓደኛሞች ነን እንጂ ሌላ ነገር የለንም ወደራሴ መለስ ብዬ ራሴን ጠየቅኩት ለምን ደነገጥኩ ምን አስደነገጠኝ? ሰምሃልን እንደምኔ ነው እንዴ እማያት? ቀና ስል ሰምሃል የነበረችበት ቦታ ላይ የለችም በንዴት ወደ ኤቤጊያ እየዞርኩ ሰሙ የት ሄደች አልኳት ምነው እኔ አልበልጥብህም ከእሷ አለችኝ  ኡፍፍፍፍፍ ብዬ ራሴን ያዝኩና ኤቤጊያ!? የተጠየቅሺውን ብቻ መልሺ ብዬ ጮህኩባት ደንግጣ ወድውስጥ ነው የተመለሰችው ብላኝ አውርታ ሳትጨርስ እየሮጥኩ ወደክለቡ ደረጃውን ወጣው ምን ልላት እንደምችል አላውቅም ብቻ ላገኛት ፈለግኩ ሳላውቅ ስሜቷን የጎዳሁት መስሎ ተሰማኝ። ውስጥ ስገባ ሰሙ ከኪያር ጋር እየጠጣች ነው ሄጄ አብሪያቸው ተቀመጥኩ ሰሙ ፊት ላይ ምንም አይነት አሉታዊ ነገር አይነበብም።  ሰላም ነው አይደል ሰሙ አልኳት እየሳቀች ሰላም ነው አለችኝ አሳሳቋ ከወትሮው የተለየ ሆነብኝ እንደተናደደች ገብቶኛል ግን ምንም አይነት ነገር ላገኝባት አልቻልኩም እያወራን እያለ ኤቤጊያ መጥታ አጠገባችን ተቀመጠች። ኪያር የተፈጠረውን ነገር ስላላወቀ ተሻለሽ አቢ አላት አው ደህና ነኝ አለችው። የተወሰነ ግዜ አብረን እያወራን ቆየን ግን ከዚ በላይ ክለብ ውስጥ መቆየት አልፈለግኩም ወደ ግቢ ተመልሼ አልጋዬ ላይ መተኛት ፈለግኩ ስልኬን አውጥቼ ሳይ እኩለለሊት ሆኗል ውይ.... ወደ ግቢ መመለስ አንችልም እዚው ማደራችን ነው ብቃ አልኳቸው። እናድራለና ደሞ ለማደር አለች ኤቤጊያ የጀመረችውን ቢራ ችርስ እንድናጋጭ ወደላይ እያነሳች ኪያርም አነሳ ሰሙ የጀመረችውን ጂን በአንዴ ጭልጥ አድርጋ ጠጣችውና አስተናጋጁን ሌላ እንዲያመጣ ስታዘው ለአስተናጋጁ ያነሳችውን እጃን ወደታች እያደረግኩት ሰሙ ይበቃሻል ከዚ በላይ ጥሩ አይደለም አልኮሆል አልኳት። ኮስተር ብላ እየተኮላተፈች እ..እን..ጠጣ ብለ..ክ አ...አይደለ ያመጣ...ሀኝ...እ...እጠጣለው አለችኝ። እኔም እየተቆጣሁ ሰሙ ይበቃሻልልል አልኳት ኪያርም ተደምሮ ይበቃል አላት

እሺ መተኛት እፈልጋለው አሁን አለችን ሁለታችንንም እያየች እኔም ከዚ በላይ መቆየት ስላልፈለግኩ እጄን ወደኪሴ እየሰደድኩ ሲያስተናግደን የነበረውን አስተናጋጅ በምልክት ጠራሁት እኔና ኪያር ሂሳብ ከፍለን ተነሳን ኤቤጊያም ተነሳች ሰሙ በጣም ስለሰከረች ኪያር ደግፏት ተነሳች። ልንንቀሳቀስ ስንል ናታን አትቆዩም በቃ እኔ እቆያለው እናንተ ሂዱ አለን ድብሮት ነበር መሰለኝ በጣም ሲጠጣ ነበር ያመሸው እንደነበር ራሱ ረስቼዋለው።
በእኩለሊሊት ማደሪያ ቤርጎ ፍለጋ እዛው አከባቢ መንቀሳቀስ ጀመርን። በስተመጨረሻአንድ ሆቴን ለአራታችን አልጋ አገኘንና በየክፍላችን ገብተን ተኛን። ቢደክመኝም እንቅልፍ አልወሰደኝም እየተገላበጥኩ ቅድም ስለተፈጠረው ነገር ማሰላሰል ጀመርኩ ሰአታት አለፉ..... በመሃል የክፍሉ በር ተንኳኳ ደንገጥ ብዬ ማን በዚ ለሊት.እንደሚያንኳኳ እያሰብኩ ማነው? አልኩ ኮስተር ብዬ። የሚንሾካሾክ ድምፅ እእኔ... ነኝ... አለኝ የኤቤጊያ ይሁን የሰምሃል ድምፅ መለየት አልቻልኩም.ከሁለቱ አንዷ እንደሆነች እርግጠኛ ነበርኩ። ወደበሩ ተጠግቼ በሩን ከፈትኩት። ኤቤጊያ ነበረች የክፍሏን አንሶላ እንደለበሰች ዘው ብላ ገብታ በሩን ከውስጥ ቆለፈችው በሁኔታዋ ተደናገጥኩ ወደኔ ዞራ በእልህ እያየችኝ ማንም ወንድ እንዳንተ ኮርቶብኝ አያውቅም አለችና የለበሰችውን አንሶላ ወደመሬት ጣለችው ከውስጥ ምንም ነገር አልለበሰችም ሙሉ ኣቁቷን ከፊቴ ቆመች።

      ይቀጥላል
https://t.me/hopereding
🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹🌹🌹
                https://t.me/hopereding
                 ተሰፋ ⭐️

ጓል 17ዓመት ከላ ካብ ኮለጅ ተሶጊጋ

✍️  ጓል25 ዓመት ምስ ኾነት ኣዴኣ ሞይታታ
✍️  ጓል 26ዓመት ምስ ኾነት  ጠኒሳ
✍️  ጓል 27ዓመት ምስ ኮነት ሓዳር መስሪታ
✍️  ብዓል ቤታ ልዑል ጭኮና ይገብረላ ነይሩ እንተኮነ  ግን  ኣብዚ ሓዳር ኸላ ጓል ወሊዳ።
✍️  ጓል 28 ዓመት ምስ ኾነት ዝመስረተቶ ሓዳር ፍሪሱ  ። ቡዙሕ ሕማምን  ጭንቀትን  ውን ገይራ
✍️ ኣብ 29ዓመታ  ብሓገዝ ትነባበር ነይራ
✍️ ኣብ 30 ዓመታ ሞት ተመንያ ነይራ ገዛእ ርእሳ ንምጥፋእ  ውን ሓሰበት     ይኩን ምበር ህይወታ ንምቅያር  ምስ ካልእ ሰብ ዝሓሸ ነገር ንምስራሕ ወሰነት ።
✍️ ኣብ 31 ዕድሜኣ ናይ መጀመርታ መጽሓፋ ኣሕተመት
✍️  ኣብ 35 ዓመታ 4መጻሕፍቲ ብምሕታም ናይቲ ዓመት ብልጽቲ ደረሲት ተባሂላ፡
✍️ ኣብ 42 ዓመታ ኣብ ውሽጢ ሓደ መዓልቲ 11 ሚልዮን  ቅዳሕ መጻሕፍቲ  ሸይጣ
✍️ እዛ ጓል ኣንስተይቲ J.K. Rowling  ትብሃል  ኣብ መበል 30  ዓመታ ገዛእ ርእሳ  ንምጥፋእ ሓሲባ ዝነበረት እያ ።ደራሲት  መጽሓፍ  Harry potter  ካብዚ መጽሓፍ ጥራይ15ቢልዮን ዶላር  ረኺባ  ብደረጃ ዓለም ኣብ ተርታ ሃብታማት ተሰሪዓ ።

ተስፋ ብዘይ ምቁራጽ ተጊህካ ስራሕ  ጽኑዕ ዕላማ ይሃልኻ  ኣብ እግዚኣብሄር እመን።
  
https://t.me/hopereding

             ➲ ፍቅር ዕውር ነው      
                 
   

አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ፡፡እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን የቆዳ በሽታ ያዛት፡፡ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች፡፡በቀን በአንደኛው ባልዋ ለጉብኝት ራቅ ወደላ ስፍራ ሄደ፡፡በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጠመውና እና ዓይኑን አጣ፡፡ሆኖም የጋብቻ ህይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ፡፡ግን ቀናት እያለፉ ውበቷን ደረጃ በደረጃ አጣች፡፡

   ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳራቸው ሕይወት ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡አንድ ቀን በድንገት ሞተች፡፡ ድንገት መሞቷ ታላቅ ሀዘን አምጥቶለታል፡፡ሀዘን ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ፡፡በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች 
አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? በእነዚህ ሁሉ ቀናት ሚስቱ ነበር የምትረዳው፡፡ ብለው ይወያዩ ነበር፡፡ሰውየውም

     አይነስውር አይደለሁም ብሎ መለሰ፡፡ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነው፡፡ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እነዳልሆነ እንዲሰማት ነበር፡፡ስለዚህ እንደማላይ ነገርከት፡፡እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች፡፡እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው ፡፡

አንዳንድ ጊዜ አውቀን አየተን ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዬች ስናልፋቸው ፣ በዙሪያችን ካሉ ሰዎችን ጋር ያለን መልካም ግንኙነት እንዲጠነክር ይረዳል፡፡


━━━━━━━✦🙏✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን🙏
https://t.me/hopereding

#ቻርሊ_ቻፕሊን_ከቀልዱ_ባሻገር_ይህንን_ብሎ_ነበረ

አንድ ቀን ህዝብ ተሰብስቦ ወደሚጠብቀው አዳራሽ አመራና በጭብጨባ ከተቀበሉት በኃላ ወደ መድረክ እንዲወጣ ተጋበዘ
በመጀመርያ የሚያምር ቀልድ ነገራቸው አዳራሹ በፉጨት ተቀወጠ በሳቅ ደመቀ። ከዚያም ያንኑ ቀልድ ደገመላቸው ግማሾቹ ሳቁ ግማሾቹ ደግሞ ግራ ተጋቡ..

#ለሶስተኛ ጊዜ አሁንም ቀልዱን ደገመው።በዚህ ሰዓት ግን አንድም የሚስቅ ሰው አልነበረም። ያኔ ቻርሊ በጣም ደስ አለው ከዛም ኢሄን ተናገረ..
(በአንድ ቀልድ ደጋግማችሁ እንደማትስቁ ሁላ ስለምን በአንድ ነገር ደጋግማችሁ ታለቅሳላችሁ?

"ህይወትኮ እጅግ ውብ ናት" ዛሬ በህይወት ካላችሁ ነጋችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ። በትናንት ውስጥ ስላጣችሁት ነገር አታስቡ ዛሬን ብቻ በህይወት በመኖራችሁ ፈጣሪን አመስግኑ።

ዛሬ ውስጥ ጠንካራ ከሆናችሁ ነጋችሁ የተዋበ ይሆናል። ነጋችሁ የሚጥም ይሆናል አሁንም አሁንም አሁንም በሂወት መኖራችሁን ብቻ እያያችሁ  ፈጣሪን  አመስግኑ!

#ወዳጄ ከተሰጣን ስጦታዎች ሁሉ ህይወታችን ይበልጣልና፤ በህይወት ካላችሁ ደሞ በነጋችሁ ላይ ለውጥ መፍጠር ትችላላችሁ።

አንብባችሁ ሼር ኮሜንት ማድረጉን አትርሱ 🙏
​​---፨•••••••••••••ሞሮ••••••••••••••••፨---
        --፨•••••• ክፍል 37 •••••••፨--

https://t.me/hopereding

ኤቤጊያ ራቁቷን አጠገቤ ቆመች! ምንም አይነት ስሜት ውስጤ የለም ኤቤጊያ ይበልጡኑ ርካሽ ሆና ታየችኝ ወደኔ ስትጠጋ ገፈተርኳት ወደ አልጋው ወደቀች ደንግጣ ምነው? አለችኝ ምን እየሆንሽ ነው ያምሻል ደህና የተሻሻልሽ መስሎኝ ነበር አንቺ ግን ያው ነሽ i cant believe that i wasted all those times wishing you were mine እንደዚ አይነት ቀላል ሴት አትመስይኝም ነበር  ለካ እንቺን ሳፈቅርሽ የነበርኩት ለዚ ነው ለተራ ርካሽ ስሜት ከዚ በላይ ነበር እምፈልግሽ ከዚ ግዜያዊ ስሜት በላይ ነበር ያፈቀርኩሽ  አልኳት።  እንባዋ እየመጣ የጣለችውን አንሶላ አንስታ ድጋሚ ለበሰችውና ወደኔ እየተጠጋች ናዲ እኔኮ አፈቅርሃለ... ብላ ሳትጨርስ በንዴት ገነፈልኩባት ዝም በይ! እንዳንቺ አይነት ሴት ፍቅር ሊገባት አይችልም  አፈቅርሃለው ስትይ አታፍሪም አንቺ ፍቅር ሳይሆን እልህ ነው የያዘሽ። ፍቅርና እልህ ተቀራራቢ ስሜት ቢኖራቸውም የሰማይና ምድር ልዩነት ነው ያላቸው አንቺ ከእኔ ፍቅር ሳይሆን እልህ ነው የያዘሽ እንጂ  ፍቅር አይደለም... ፍ..ፍቅር ማለት እኮ... ተቁነጠነጥኩ  እሷን በማፍቀር ያሳለፍኳቸው ሁለት አመታት እየቆጩኝ ፍቅርን እንዴት ማስረዳት እንዳለብኝ ለሷ ስል እንዴት እየተሰቃይየው እንዳሳለፍኩ በቃላት ማስረዳት አቃተኝ ... ፍቅር ማለት እኮ.. ፍቅር ማለት ዛሬ አንስተሽ ነገ እምትጥይው ነገር ሟለት አይደለም ፍቅር ከስሜታዊነት በላይ ነው እኛ ውሾች አይደለንም በየቦታው እምንልከሰከሰው ስሜታችንን መቆጣጠር እምንችል ሰዎች! ነን ሰዎ....ች! ፍቅር በስሜት እሚለካ ነገር አይደለም እሺ ፍቅር ማለት.. ከዚ በላይ ማስረዳት አቃተኝ ኤቤጊያ እንዲህ ስጮህባት በሃፍረት ተሸማቃ እያለቀሰች ነበር።
አልጋው ላይ እሷ በተቀመጠችበት ተቃራኒ ሄጄ ተቀመጥኩ።  ከደቂቃዎች በፊር ራቁቷን ሆና እንደቆመች በአይነህሊናዬ ተሳለች በለሆሳስ ይህንን ርካሽ ገላ ነበር ያፈቀርኩት አልኩ ለራሴ። በራሴ.በጣም አፈርኩ ሃፍረቴ ቀስበቀስ መልሶ ወደንዴት ተቀየረ እኔም ሳይታወቀኝ ራቁቴን በፓንት ብቻ ተኝቼ.እንደነበር ታወሰኝ ደነገጥኩ በዚ ቅፅበት ሰምሃል ብትመጣ ምን ልታስብ እንደምትችል መገመት አልከበደኝም የኤቤጊያ ለቅሶ ከኃላዬ ይሰማኛል ላያት አይደለም ድምፃን ራሱ መስማት አስጠላኝ። ኤቤጊያ አታልቅሺ ወደ ክፍልሽ ግቢና ተኚ እኔም ልተኛበት አልኳት እያለቀሰች በፍጥነት ከአልጋው ተነሳችና ቆማ ራሴን አሳልፌ ለሰጥህ ስለነበር ነው አይደል ርካሽ ያልከኝ ብላኝ መልስ ሳትጠብቅ ወጣችና ሄድች አካሄዷ ስላላማረኝ ተከትያት ወጣውና ወደክፍሏ መግባቷን ካረጋገጥኩ በኃላ ታመልሼ ገብቼ በሩን ዘጋሁት። እኔም ራቁቴን ስለነበርኩ ብርዱ ሲፀናብኝ አልጋውጥ ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛው።
ምን እንዳነቃኝ ሳላውቅ ጠዋት 12፡00 አከባቢ ተነሳው ልብሴን ለባበስኩና ፊቴን ለመታጠብ ከቤርጎው ወጥቼ ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ሳልፍ ሰምሃል የተኛችበት ክፍል ክፍት ሆኖ አየሁት ግራ እየገባኝ ቀስ ብዬ ገባው ማንም የለም አልጋው ተነጥፏል የት ሄደች በዚ በለሊት? ብዬ ራሴን ጠየቅኩ ክፍሉ ውስጥ እየትንጎራደድኩ ማንም እንደሌለ ካየው ብኃላ ስልኬን አውጥቼ ወደ ሰምሃል ጋር ደወልኩ አይነሳም ደግሜ ደጋግሜ ብሞክርም ይጠራል ግን አይነሳም። የሆነ መጥፎ ነገር የደረሰባት መሰለኝና በፍጥነት ወደ ኪያር ክፍል ሄጄ ቀሰቀስኩት ኪያር እየተነጫነጨ ተነስቶ በሩን ከፈተውና.ምንድነው? አለኝ እየተበሰጫጨ ሰምሃል ክፍሏ የለች ም ስደውልላት ደግሞ አታነሳም ስልክህን ስጠኝ ባንተ ልሞክርላት አልልኩትና ወደክፍሉ ዘው ብዬ ገባው ፍቃደኝነቱን ሳልጠይቅ ስልኩን ኮመዲኖው ላይ በአይኔ ፈልኩ አገኘኁት ወዲያው ሰምሃል ጋር ደወልኩ ወዲያው ተነሳና ወ..ወዬ ኪዩ አለችኝ ድምፃ እያለቀሰች እንደሆነ በደምብ ያስታውቃል ከበስተጀርባ የቤተክርስቲያን ቅዳሴ ድምፅ ይሰማኛል ትንሽ ዝም ካልኩ በኃላ ኪያ አይደለሁም ሰሙ ናዲ ነኝ ስል ስልኩ ተቋረጠ።

       ክፍል 38     ይቀጥላል
​​-፨•••••••••••••••ሞሮ ••••••••••••፨-
         ••••••••ክፍል 38 ••••••••
https://t.me/hopereding

ልክ ስልኩ እንደተቋረጠ መልሼ ደወልኩላት ይጠራል ግን አይነሳም ደግሜ ደጋግሜ ብሞክርም አይነሳም እንደተቀየመችኝ ገባኝ። ትንሽ ለማሰብ ሞከርኩ ቅድም አንስታ ሄሎኪያር ስትል ከጀርባዋ የቤተክርስቲያን የስርአተ ቅዳሴ ድምፅ ሰምቼ ነበር ቤተክርስቲያን ገብታ እንደሆነች ለማወቅ አልከበደኝም ግን የት ቤተክርስቲያን ልትሆን እንደምትችል ማሰብ ጀመርኩ ከመብራት ሃይል ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በቅርብ ርቀት ይገኛል ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ባልሆንም ለመሄድ ወሰንኪ። ኪያርን ነግሬው ከቤርጎ ወጥቼ መንገዴን ወደ ቅድስት ማርያም አደረግኩ። ለሊቱ ገና እየነጋ ስለነበር የመብራት ሃይል አስፓልት ፀጥ ረጭ እንዳለ ነው አልፎ አልፎ ቆሌ የሚገፉ ባጃጆች ሽውውው... እያሉ ባጠገቤ እንደፌንጣ እየዘለሉ ያልፋሉ። የአስፓልቱን ብርትኳናማ መብራት እየታከኩ ጥጌን ይዤ እየሄድኩ ቀስ በቀስ ከቅድስት ማርያም የሚሰማው የካህናት የሚስረቀረቅ የቅዳሴ ዜማ እየቀረበ መጣ ፍጥነቴን ጨምሬ ወደቤተክርስቲያኑ ገሰገስኩ።
ቅድስት ማርያም አከባቢ ስደርስ በዛ ፅልመት ነጫጭ የለበሱ ምእመናን ፈጠን ፈጠን እያሉ ተሳልመው ወደ ውስጥ ይገባሉ እኔም እነሱን ተከትዬ ገባው። በዛፍ የተከበበው ቤተክርስቲያኑ ውስጥ በየዛፎቹ ስር እና በየድንጋይ ወንበሮቹ ልክ ሰዉ ቆሞ እያስቀደሰ ነው። በአይኔ ቀይ ቀሚስ የለበሰች ሴት መፈለግ ጀመርኩ በጉል በኩል  ያለው በር ስለገባው ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ያለው ሰው በከፊል ነበር የሚታየኝ። ትንሽ ለማሰብ ሞከርኩ ባለፈው እዚህ የመጣን ግዜ የተቀመጥነው ፀበል ቤቱ አከባቢ እንደሆነ ትዝ አለኝና ሰዉን ሳልረብሽ ቀስ ብዬ በቤተክርስቲያኑ ጀርባ በኩል ወደ ፀበል ቤቱ ጋር ሄድኩ። ሁሉም በቆመበት ሲያስቀድስ እኔ ስንቀሳቀስ በጣም ተሳቀቅኩ በቅዳሴ ሰአት መንቀሳቀስ እንደማይፈቀድ ሰሙ እንደነገረችኝ አስታወስኩ ይበልጥ ተሳቀቅኩ። ፈጠን ብዬ ወደ ፀበል ቤቱ አከባቢ ጋር ሄድኩ
በአይኔ ከሚያስቀድሱት ሰዎች ሰምሃልን እየፈለኳት ነበር። የለችም አንዲት ቀይ የለበሰች ሴት አይቼ ወደሷ መሄድ ስጀምር ቀና ስትል አየኃት ሰምሃል አይደለችም ደንገጥ ብዬ ወደኃላ ተመለስኩ። ሙሉ ፀበልቤቱ አከባቢ ቀይ የለበሰች ሴት ካለች አይኔን እስኪደክመኝ እያንከራተትኩ ፈለግኩ ግን አልነበረችም ተስፋ ቆርጬ ልመለስ ዞር ስል ከኃላ ጥግ ላይ አንድ ቀይ ቀሚስ ብቻ የለበሰች ሴት አንገቷን ደፍታ ኩርምትምት ብላ ተቀምጣ  አየው በልቤ ሰምሃል እንድትሆን ፀሎት እያደረግኩ ወደሷ ሄጄ ብዙም ሳልቀርባት  ፊቴን ወደቤተክርስቲያኑ አዙሬ ቆምኩ።
ልጅቷ ሰምሃል እንደሆነች ለማወቅ አልከበደኝም ቡኒ ፀጉሯ እና የለበሰችው ቀይ ቀሚስ በቀላሉ እንድለያት አድርጎኛል። በጥዋቱ ቅዝቃዜ እየተንቀጠቀጠች እያለቀሰች ነበር አንጀቴ ተላወሰ። እንዳጋጣሚ ለማታ ብዬ ይዤው የወጣሁትን ጃኬት አስተካከልኩና እዛው አንገቷን ደፍታ በተቀመጠችበት ሳለብሳት ድንግጥ ብላ ተነስተነሳ ቆመች እኔ መሆኔን ስታውቅ ትንሽ ውጥረቱ ቀለል አለላት ደግሞ መልሳ እየተኮሳተረች ምን ልታደርግ መጣህ አለችኝ አንቺን ፈልጌ ነዋ ምን ሆነሽ ነው ሰሙ ቆይ ምንድነው ያስቀየምኩሽ ነገር በማርያም ንገሪኝ ትናንተ ከተገናኘን ግዜ ጀምሮ ደብሮሽ ነበር ምንድነው የበደልኩሽ አልኳት። አይኗ ለሊቱን ሙሉ ስታለቅስ አድራ በጣም ቀይ ሆኖ ያስታውቅባታል ዘለላ እንባዋን እየጠረገች አንተ ምንም አላደረግከኝም ናዲ ምንም ያጠፋኀው ነገር የለም ችግሩ እራሴው ጋር ነው ያለው እሱን ደግሞ ራሴው እፈታዋለው አለችኝ። እኮ ምንድነው የተፈጠረው ነገር ምን እኔ እማላውቀው የቤተሰብ ችግር ተፈጥሮ.... ሳጨርስ አቋረጠችኝ ናኦድ! አለችኝ ቆጣ እያለች አሁን የፀሎት ሰአት ነው የምናወራበት ግዜ አይደለም አለችኝ ይበልጥ ቆጣ እያለች ትእዛዟን አክብሬ ዝም አልኩ።

            
         

        ክፍል 39  ይቀጥላል
  https://t.me/hopereding
  "እዚህ ማቆም፡ክልክል፡ነው"

ትላልቅ፡ህንጻዎች፡ድርጅቶችና፡መስሪያ፡ቤቶች፡ዙሪያ መኪና፡እንዳይቆም፡ከተፈለገ፡ማቆም፡ክልክል፡ነው
(No Parking) የሚል፡ምልክት፡ይቀመጥና፡መኪና እንዳይቆም፡ይሆናል፡፡ አንተም፡በሕይወትህ፡አስፈላጊ
አይደሉም፡ብለህ፡ለምታስባቸው፡አሉታዊ፡ነገሮች፡ሁሉ
ፊት፡ንሳቸው፡፡ ማቆም፡ክልክል፡ነው፡በላቸው
ለእናንተ፡የሚሆን፡ቦታ፡የለኝም፡በላቸው
ለድክመት፡ማቆሚያ፡ቦታ፡የለኝም
ለሽንፈት፡ማቆሚያ፡ቦታ፡የለኝም
ለመሀይምነት፡ማቆሚያ፡ቦታ፡የለኝም
ለውድቀት፡ማቆሚያ፡ቦታ፡የለኝም
ለአለመቻል፡ማቆሚያ፡ቦታ፡የለኝም
ለተስፋ፡መቁረጥ፡ማቆሚያ፡ቦታ፡የለኝም
ልብህ፡ውስጥ፡ያሉህን፡ክፍት፡የማቆሚያ፡ቦታዎች፡ሁሉ
ለመልካም፡ሀሳቦች፡ብቻ ተይዟል” ብለህ አስቀምጣቸው
- ሌሎች የውስጤን ሳያውቁ በቃህ ሲሉኝ የማልቆም - ሌሎች አቅም የለህም፡ሲሉኝ፡የማልሸሽ
ሌሎች፡ድሮ፡ በሰራሁት፡ሲገምቱኝ፡እኔ፡ግን፡የዛሬዬን፡የአሁኔን፡የማውቅ
ለውሰጤ የምነግር፡አሸናፊ፡ፈረስ፡ነኝ።
#"አይ_እቴ"



እሷ፡-
"መልኩ ደምግባቱ ቁመናው ምን ቢያምርም 
በቁንጅናው ብቻ ሰው አይፈቀርም።
እንዴት ይፈቀራል?
እንዴት ይወደዳል?
በል እስኪ ተናገር እርግጥ ቆይ ያስኬዳል?
አይ አይመስለኝም ...
ያን ዳር የለሽ ስሜት ልብ እስካልወለደው
ስለሚያምር ብቻ አልችልም ልወደው።"


እኔ፡-
" እንዲ እንዲ እያልሺኝ አትከራከሪ
እረ እንደው አንቺ ሴት ምናለ ብታፍሪ።
አይ እቴ ...
እኔ አንቺን ማፍቀሬ እያለ ምስክር
ባይገባሽ ነው እንጂ አያሻም ነበረ በዚ ርዕስ ክርክር።"


━━━━━━━━✦
✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

Join us 
🙏
https://t.me/hopereding