ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕
222 subscribers
65 photos
282 links
ሰላም 🤚 -

📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯


በዚህ ቦት አማካኝነት https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙
➡️.  ልቦለዶችን 📖
➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕
➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚
➡️.  ግጥሞችን 📝
➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙
➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ።
አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች

▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
Download Telegram
Let there be light

"ከየት እንጀምር?"

ወዳጄ ሆይ ለምን #ከሌለህ ነገር ትጀምራለህ? በሰው ላይ ሀዘን የሚጨምረው፤ ተስፋ መቁረጥም የሚያደርሰው፤ የበታችነትንም የሚያመጣው፤ ቅዠትንም የሚያባብሰው ከሌለ ነገር መጀመር ነው። እስኪ ራስህን አስበው? ስላላገኘኻቸውና ስላልደረስክባቸው፣ ስላመለጡህና ስላልተደረጉልህ ነገሮች ከማሰብ በእጅህ ስላለውና ስለደረስክበት ነገር ለምን አታስብም? በአንተ እጅ #ያለው ነገር በአንተ እጅ #ከሌለው ነገር ይበልጣል ወይስ ያንሳል?
.
በእጄ ያለው ትንሽ ነገር ነው፤ በእጄ የሌለው ግን አለም ሙሉ ነው። ታዲያ እንዴት በእጄ ያለው በእጄ ከሌለው ነገር ሊበልጥ ይችላል? እንደምትል አይጠረጠርም። ሲገመትም እንደዚያው ነው። አንድ እውነት ግን በእጅህ ያለው ነገር በእጅህ ከሌለው ይበልጣል። እንዴት? አልክ.....
.
በመጀመሪያ ደረጃ በእጅህ ያለው ነገር #ያንተ ነው። በእጅህ የሌለው ግን ገና ያንተ አይደለም። ያንተ የሆነው ያንተ ካልሆነው ነገር ይበልጣል። ምክንያቱም ያንተ በሆነው ነገር -መጠቀም ትችላለህ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልትጠቀም አትችልም። ያንተ በሆነው ነገር ልታዝ ትችላለህ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን -ልታዝ አትችልም። ያንተ የሆነው ነገር ማግኘትህን እርግጠኛ ሆነሀል። ያንተ ያልሆነውን ማግኘትህን ግን እርግጠኛ መሆን አትችልም፤ ያንተ በሆነው ነገር #ልትወስንበት ትችላለህ፤ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልትወስን አትችልም። ያንተ የሆነውን ነገር ለሌላው #መስጠት ትችላለህ ያንተ ያልሆነውን ግን መስጠት አትችልም። ካለህ ነገር ላይ ቆመህ የሌለህን ማየት ትችላለህ፤ ከሌለህ ነገር ላይ ቆመህ ግን ያለህን ነገር ማየት አትችልም።

እና ወዳጄ ስትቆጥር ካገኘኸውና ከሆነልህ ነገር ጀምረህ ቁጠር። ባላገኘኸው ነገር ከምትበሳጭ ባገኘኸው ነገር ተደሰት። ባልሆንከው ነገር ከምታዝን በሆንከው ነገር ሐሴት አድርግ። ባልያዝከው ነገር ከመበሳጨት በያዝከው ነገር ስራበት። ባልሆንከው ማንነት ከመቃዠት በሆንከው ማንነት መኖር ጀምር። ይህ ማለት ምን ይመስልሃል? ስትጓዝ እያረጋገጥክ ተጓዝ። መጀመሪያ ያለህን ዕወቅ ከዚያም ባለህ ነገር ምን ያህል እንደተጠቀምክበት እርግጠኛ ሁን። ላለህ ነሀር ዋጋ ስጠው። ያንተ የሆነውን ነገር አክብረው። ያን ጊዜ የሌለህን ታገኘዋለህ።
.
የሌላውን ሰው ትዳር አይተህ እርሱን ተመኝተህ እንደዚያ በሆንኩ እያልክ በሌለህ ነገር ከማዘን እስኪ በአንተ ትዳር ውስጥ ምን መልካም ነገሮች አሉ? የትኞቹን ተጠቅመህባቸዋል? የትኞቹን አድንቀሃቸዋል? ለየትኞቹስ ዋጋ ሰጥተሃቸዋል። የሌለህን ብቻ የምታይ ከሆነ ያለህን ማወቅ አትችልም። ስለ ሌለህ ነገር ብቻ የምታስብ ከሆነ ባለህ ነገር መጠቀም አትችልም።
.
አንድ ሰው አንዲት #የከሳች_በቅሎ ነበረችው። አወጣና ሸጣት። ከዓመታት በኋላ ገበያ ሲወጣ አንድ ሰው እጅግ ያማረች የኮርቻ በቅሎ ይዞ ተመለከተ። ሰውዬው ጠጋ ብሎ "ጌታው ይህችን የመሰለች በቅሎ ከየት ትገኛለች እባክዎ? እኔም ለመግዛት እፈልግ ነበር"  አላቸው። ሰውዬውም "እኔም በአጋጣሚ ከሰው ነው የገዛኋት። ስትገዛ ከስታ ልትሞት ደርሳ ነበር። የሸጠልኝ ሰው እንደነገረኝ ባለቤቷ ለበቅሎ #ግድ አልነበረውም። እኔ የበቅሎ ጠባይ ስለማውቅ ነው ከሰውዬው የገዛኋት። በአንድ አመት ውስጥ በደንብ ስይዛት ጊዜ እንዲህ ያማረች በቅሎ ሆነች" አሉት።

"መቼ ነበር የገዙት?" አላቸው
"የዛሬ አራት ዓመት ከዚሁ መንደር ገዝቷት ሲሔድ ነው ለምኜ የገዛሁት" አሉት። እራሱን እየነቀነቀ ተመለሰ። በቅሎዋ የርሱ ነበረች። የሰውዬውን ያህል ግን የበቅሎዋን ዋጋ አላወቀውም ነበር። ተፈላጊዋን ምርጥ በቅሎ ሽጦ ምርጥ በቅሎ ይፈልጋል። እኛም ያሉንን ምርጥ ነገሮች እየሸጥን የሌሉንን ምርጥ ነገሮችን እንፈልግ ይሆናል።
.
አንዳንድ ጊዜኮ የምናማርረው ችግር ስለደረሰብን ብቻ ሳይሆን ያለንን #ስለማናውቀው ጭምር ነው። ችግር በራሱ ችግር አይደለም። ችግር ችግር የሚሆነው መፍትሔ መስጠት ለማይችል ሰው ብቻ ነው። መፍትሔ መስጠት ለለመደ ችግር ትምህርት ቤት ነው። ችግርኮ የፍች፣ የመለያየት፣ የጠብ፣ የኩርፊያ፣ የክስ፣ የመለቀቂያ መንገድ የሚሆነው ለዐቅመ ቢስ ሰው ነው። ለብርቱ ሰው ግን ሞት የትንሳኤ መቅድም ነው። የሌለህን ነገር ብቻ ካሰብክ ያለህንም ታጣዋለህ። ያለህን ነገር ካሰብክ ግን የሌለህንም ታገኘዋለህ። እስኪ ወዳጄ ያለህን ዕወቀው አክብረው አሟጠህ በሚገባ ተጠቀምበት በዚያ ኑርበት አጊጥበት። ከዚያ ሌላውን ለመያዝ ፈልግ። ባለህ የማትረካ ከሆንክ ግን ሩጫህ የተሻለ ነገር ፍለጋ ሳይሆን ሌላ ነገር ፍለጋ ብቻ ይሆናል።

:#ሼር ይደረግ
https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding

​​​​◈ ━━━⸙ የታሪክ ማዕድ  ⸙━━━━ ◈


    ለምቶደው ሰው ምንም ነገር ልትሰጥ ስትፈልግ መልስ አትጠብቅ

ባንድ ወቅት ልጁ ከጎረቤታቸው ልጅ ድብን ያለ ፍቅር ይይዘዋል ታድያ የሷን ትኩረት ለመሳብ የማያደርገው ጥረት አልነበረም እሷ ያለችበት ቦታ ሁሉ ይገኛል ... ለካ ግን እሷ ነበረች ቀድማ ለልጁ ቦታ የሰጠችው እሱ የተከተላት የሚመስለው ቦታ ለካ እሷ ነበረች የምትገኘው...

ታድያ በውስጣቸው እየተፈላለጉ ሳይገላለፁ ግዜው መሮጡን ቀጠለ ይሄን የተረዳው ወንድ በድፍረት የፍቅር ጥያቄውን አቀረበ ይሄኔ ነበር ሳታንገራግር የተቀበለችው ... በዚ መልኩ የተጀመረው ፍቅር ቀጠለ...

ሁለቱም ፍቅረኛሞች ቢዋደዱም እሷ ጥርጣሬ ይገባት ጀመር ይህ የሆነው ደግሞ እሱ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ የሚሉትን የቃላት ገለፃዎች ስለማይጠቀም ነበር እሷ ደግሞ ሁሌም ከሌሎች ፍቅረኛሞች የምትሰማቸውን እሷም ትጠብቅ ነበር ሲቀጣጠሩ አምራና ተውባ ትሄዳለች ብዙዎች ሲያሞግሷት እሱ ግን ምንም ሳይላት ይቀራል በዚም ፍቅሩን የማይገልፅላትና ውብ እንደሆነች የማይነግራት ስለማይወዳት ይመስላታል... ለዛም በመሀላቸው ጭቅጭቅ ይነሳ ጀመር በሆነው ባልሆነው ስለማቶደኝ ነው... እያለች ታበሳጨዋለች ይህም እየሰፋ ሄዶ እየተዋደዱ ለመለያያት በቁ...

እህቴ

➲ አንዳንዴ እኛ ሴቶች ከሚደረግልን ይልቅ የሚወራልን ይገዛናል ይህም አግባብ አይደለምና ተጠንቀቂ...

   ➲ሁሌም እኛ ሴቶች ብልህ ነን ስለዚህም ከሱ ሳትጠብቂ ያለሽን ፍቅር ስጪ ፍቅር መስጠት ከመቀበል የበለጠ ዋጋ አለውና እወቂበት...


ወንድሜ

    ➲አንተም ብትሆን ለግንኙነትህ ሀላፊነት መውሰድን አትርሳ ሁሌም ፍቅረኛህ ከሷ በላይ ማንም እንደሌለ ንገራት ምክንያቱም ደስተኛ ታደርጋታለህ ።

           
#ሼር_ይደረግ