ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
ኅዳር 21 ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ )

ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/
share እና like ያድርጉ
#ኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የምናከብርበት_ምክንያት_

፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6)

፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23)

፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት ፥ በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/

፬ኛ. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/

፭ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....)

፮ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮንጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡

፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላ በአንበሳ ውድምና፤ ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡

፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡

፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን (ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ቢሆንም) ቅዳሴ ቤት የተከበረበት በመሆኑ፡፡
————
#ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ድንግል_ማርያም_

፠ ታቦተ ጽዮንን፤ ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤
✤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች ፥ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/ ፥ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/ ፥ ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት የቈራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/ ፥ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/ ፥ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/ ፥ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/ ፥ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/ ፥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡
ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት)
በንጽሕናና (በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር) በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7/
፠ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች
✤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች ናት፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነች፤
ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/
——-
**** በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ምሥጢሩን ከምሥጢር አመሳጥሮ፤ እንደ ሸማ አንከባሎ፥ እንደ ወርቅ ከብልሎ እንዲህ አስቀምጥታል፤
«ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤
ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤
ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡
ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
#share
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
#Share #like