ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
4.84K subscribers
721 photos
5 videos
13 files
232 links
የዲ.ን ሄኖክ ሀይሌን ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
ናቸው እንጂ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ለአባታችን አዳምና ለእናታችን ለሔዋን ‹‹መልካምና ክፉውን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብሉ (ዘፍ 2፡18›› ሲል መቼም ቢሆን አትብሉ ማለቱ እንደሆነ ያለ ነው፡፡

በጾም ወቅት በፈቃዳችን ሥጋችንን ስለምናደክም ‹‹መቼም የማይጾሙትን›› የበለጠ ልናደርግ፣ ‹‹መቼም ከማይበሉት›› ደግሞ የበለጠ ልንከለከል እንችል ይሆናል፡፡ ይህ ማለት ግን የጾም ወቅት ሲያልፍ ወደ ነበርንበት እንመለስ ማለት አይደለም፡፡ በጾም ወቅት የነበሩንን መልካም ነገሮች ከጾሙም በኋላ ይዘናቸው ልንቀጥል ይገባል እንጂ፡፡ በጾም ወቅት የተውናቸውን የሚጎዱን ነገሮች ደግሞ ከጾም በኋላ መልሰን ልንይዛቸው አይገባም፡፡ እንደተውናቸው ልንቀጥል ይገባል እንጂ፡፡ ሰለዚህ በጾም ወቅት ያለንን ተሞክሮ በማጽናት ‹‹ መቼም የማይጾሙትን›› መቼም አለመጾም፣ ‹‹መቼም የማይበሉትን›› ደግሞ መቼም አለመብላት ይገባናል፡፡ ይህንን ስናደርግ ‹‹የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል። የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፡- እነሆኝ ይላል። ኢሳ 58፡8-9›› እንደተባለው ይሆንልናል፡፡

የ‹‹ #ቀሳውስት_ጾም›› ወይስ የ #ክርስቲያኖች_ሁሉ_ጾም?

የሐዋርያትን ጾም አንዳንዶች ‹‹የቀሳውስት ጾም›› ሲሉት ይሰማል፡፡ ይህም ከአሰያየሙ ጋር የተያያዘ ብዥታን በመጠቀም ላለመጾም የሚፈልጉ ወገኖች ያመጡት አስተሳሰብ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች ‹‹የሐዋርያት›› የሚለውን ቃል ብቻ በመውሰድ ጥንት ይህንን ጾም ሐዋርያት ብቻ እንጂ ሕዝቡ አልጾመውም፤ ዛሬ ደግሞ በሐዋርያት እግር የተተኩ ካህናት (ቄሶች) ናቸውና ጾሙም የእነርሱ ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ብዙውን ጊዜም ቀሳውስት አበክረው ስለሚጾሙትና በሕዝቡም ዘንድ ይህ ስለሚታወቅም ጭምር ነው ይህ አስተሳሰብ የመጣው፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ይህን የአዋጅ ጾም ጳጳስ፣ ቄስ/መነኩሴ፣ ዲያቆን፣ ሰንበት ተማሪ ምዕመን ሳይል በ40 እና በ80 ቀን የተጠመቀና ዕድሜው ከሰባት ዓመት በላይ የሆነው ሁሉ እንዲጾም አውጃለች፡፡ እኛም እነርሱን ተከትለን፣ በእነርሱ ሥርዓት በመመራት፣ በሐዋርያት ላይ ያደረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብት በእኛም ላይ እንዲያድርብን በየዓመቱ ጾመ ሐዋርያትን ሌሎችንም አጽዋማት አክብረን መጾም እንደሚገባን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስኗል (ፍት.ነገ. 15፡ 586)፡፡

#የሐዋርያት_ጾም_የእኛም_ጾም_ነው

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›› እንዳለ (ኤፌ 2፡20) በሐዋርያት መሠረትነት ላይ ለታነጽን ለእኛ ለክርስቲያኖች የሐዋርያት ጾም የእኛም ጾም ነው፡፡ የሐዋርያት ጾም  ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ስብከተ ወንጌልን ለመፈጸም በየሀገሩ ከመሰማራታቸው በፊት በሁሉም ነገር እግዚአብሔር እንዲረዳቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ እኛም የሐዋርያትን ጾም ስንጾም ሁል ጊዜ በንስሐ ታጥበን እና ነጽተን ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን ቀሪ ዘመናችንን እግዚአብሔር አምላክ እንዲባርክልንና ሰላምን ፍቅርን እና ጤናን እንዲሰጠን መጾም ይኖርብናል:: ይህ የሐዋርያት ጾም በሐዋርያት እግር የተተኩ የቤተክርስቲያንን አገልጋዮችም አገልግሎታቸውን እንዲባርክላቸውና ምዕመኑን ወደ መልካም ጎዳና እንዲመሩ የሚጸልዩበት ጾም ነው፡፡

በአጠቃላይ በሐዋርያት ጾም የሐዋርያት ክብራቸውና አገልግሎታቸው ይታሰባል፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው የሐዋርያትን በረከት ለመላበስ፣ እነርሱ ድል ያደረጉትን ዓለም እንድናሸንፈው አምላካችንን ለመማጸን ነው፡፡ በዚህ ጾም ሐዋርያት ሁሉን ትተው ጌታን መከተላቸው፣ ዓለምን ዞረው ማስተማራቸውና ስለ ቅዱስ ስሙ በጽናትና በጥብዐት መከራ መቀበላቸው ይዘከራል፡፡ ምዕመናን እና ካህናትም የቅዱሳን ሐዋርያትን መንፈሳዊ ተጋድሎ እያሰብን በዘመኑ ሁሉ በፍቅር በተዋበ የመታዘዝ ፍርሃት የየራሳችንን መዳን እንፈጽም ዘንድ (ፊልጵ. 2፡12) ጾምን በመጾም፣ ጸሎትን በመጸለይ ከእግዚአብሔርና በንፁህ ደሙ ከዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጋር ያለንን ፍጹም አንድነት ልናጸና፣ ራሳችንን ከኃጢአት ከበደል አርቀን በመታዘዝ ጸጋ የጾምን በረከት ልንቀበልበት ይገባል፡፡

ለዚህም የ #እግዚአብሔር ቸርነት፣ የ #እመቤታችን አማላጅነት የ #ቅዱሳን_ሐዋርያት ጸሎት ይርዳን፡፡ አሜን፡፡