"#ሰላም_ለያዕቆብ_ምንዙህ_ዘኮነ_በረከቱ_ብዙኀ እምጠሉ ለሰማይ ወእምስፍሓ ለምድር፤ ዘአስተርአዮ እግዚአብሔር ገጸ በገጽ ወተናገሮ በምድረ ሎዛ፤ ወሰመየ ስሞ እስራኤል"። ትርጉም፦ ከሰማይ ጠልና ከምድርም ስፋት ይልቅ በረከቱ የበዛ የኾነ እግዚአብሔር ፊት ለፊት የተገለጸለት (የታየው) በሎዛ ምድርም የተናገረው፤ ስሙንም እስራኤል ብሎ ለሰየመለት ቅምጥል ድልድል ለኾነ #ለቅዱስ_ያዕቆብ ሰላምታ ይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።