ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
4.84K subscribers
721 photos
5 videos
13 files
232 links
የዲ.ን ሄኖክ ሀይሌን ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ አባ አፍፄ ወአባ ጉባ +"+

=>አባ አፍፄና አባ ጉባ ቁጥራቸው ከተስዓቱ (ዘጠኙ)
ቅዱሳን ነው::

+"+ አባ አፍፄ +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን
ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ:: ገና
በሕጻንነታቸው
ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቀው ወደ ግብፅ ወርደዋል:: በዚያም
በአባ መቃርስ እጅ መንኩሰዋል:: አባ አፍፄ ወደ ኢትዮዽያ
የመጡት
በአልዐሜዳ ዘመን ከ8ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ነው::

+ጻድቁ ጸበል እያፈለቁ ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል::
ትግራይ ውስጥ የሐ የተባለው ቦታም ማረፊያቸው ነበር::

❖ለጻድቁ በጥቂቱ እነዚሕን እንጠቅሳለን:-

1.ከ100 ዓመት በላይ አበ ምኔት ሆነው በኖሩበት
ገዳማቸው በፍጹም ትጋት: በጾምና በጸሎት
አገልግለዋል::

2.በመጀመሪያ ያስከተሏቸውን 366 ደቀ መዛሙርት
ጨምሮ ብዙ መናንያንን አፍርተው በሃገራችን ገዳማዊ
ሕይወትን አስፋፍተዋል::

3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋ ወደ
ግዕዝ ተርጉመዋል::

4.በስብከተ ወንጌል ለሃገራችን ብርሃን አብርተዋል::
ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር "አፍፄ
(አፈ-ዐፄ)"
ብሏቸዋል:: "የዐፄ (የንጉሥ) አንደበት ያለው" ወይም
"ንግግር አዋቂ" ማለት ነው::

+ጻድቁ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን
አገልግለው በዚሕች ቀን በ684 ዓ/ም ተሠውረዋል::
እግዚአብሔርም
በስማቸው ለተማጸነ: ገዳማቸውን ለተሳለመ የምሕረት
ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::

+"+ አባ ጉባ +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት ታሕሳስ 29 ቀን በ336 ዓ/ም
በመንፈቀ ሌሊት ነው:: አባታቸው ጌርሎስ: እናታቸው
ቴዎዶክስያ ደጐች
ነበሩ::

+አባ ጉባ ("ባ" ጠብቆ ይነበብ) በተወለዱ ቀን ጌታችን
ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን
ተሞልቶ
ነበር:: ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው
አመስግነዋል::

+በልጅነታቸው መጻሕፍትን አጥንተው: ወደ ገዳመ
አስቄጥስ ገብተው መንነዋል:: ለበርካታ ዓመታት ከተጋደሉ
በኋላ ሊቀ
መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ወደ ቅድስት ሃገር ኢትዮዽያ
ሒድ" ብሏቸው ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር ወደ ሃገራችን
መጥተዋል::
በወቅቱ ዕድሜአቸው ከ140 በላይ ነበር::

+ጻድቁ አባ ጉባ እንደመሰሎቻቸው በስብከተ ወንጌል:
መጻሕፍትን በመተርጐም: ገዳማትን በማስፋፋትና አብያተ
ክርስቲያናትን
በማነጽ ቆይተዋል:: በተለይ ራማ ኪዳነ ምሕረት
የእርሳቸው ናት ይባላል::

+ጻድቁ ቅዳሴ ሲቀድሱ ከመሬት ከፍ ብለው ነበር:: ብዙ
ጸበሎችን አፍልቀው ድውያንን ፈውሰዋል:: ሙታንንም
አንስተዋል::
እመቤታችንም የብርሃን መስቀል ሰጥታቸዋለች:: ጻድቁ
ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፈው
በገዳማቸው
ተቀብረዋል::

+በዘመኑ ትኩረት ካጡ ታላላቅ ገዳማት አንዱ ይሔው
ትግራይ ውስጥ የሚገኘው የአባ ጉባ ገዳም ነው::
(በነገራችን ላይ "ጉባ" ማለት "አፈ-መዐር: ጥዑመ-
ልሳን" ማለት ነው)

❖ቸሩ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የጻድቃኑን በረከት
ያድለን::
በጸሎታቸውም በደላችንን ይቅር ይበለን::

❖ግንቦት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ አፍፄ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
2.አባ ጉባ (ከዘጠኙ ቅዱሳን)
3.አባ ስምዖን ገዳማዊ (በ7 ዓመታቸው መንነው ለ81
ዓመታት በተጋድሎ የኖሩ ሶርያዊ)
4.አባ ይስሐቅ ጻድቅ

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ በዓለ ልደቱ ለክርስቶስ
2፡ ቅድስት አርሴማ ድንግል
3፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4፡ ቅዱስ ማርቆስ ዘሮሜ
5፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ
6፡ ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
7፡ ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሐዋርያ
8፡ ጉባኤ ሰማዕታት

++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ
ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል::
ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ
በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ
ዋጋው አይጠፋበትም::
+"+ (ማቴ. 10:41)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn
Audio
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊 (ማቴ ፫:፫)

ርዕስ፦📝""መንገዱን እንዴት እናውቃለን?""  
   (ዮሐ. ፲፬:፭)

"ተግሣጽ ለኲሉ፥ ወቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ"

📅(ግንቦት 26 - 2016)

🎤 በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ዜና እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)

🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)

🔗https://t.me/zikirekdusn
▶️
https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
#አቡነ_በኵረ_ድንግል

የአቡነ ብፁዐ አምላክ ረድእ የነበሩ ሲሆን እርሳቸውም ካረፉ በኋላ ተመርጠው በደብረ ምዕዋን ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆነው ተሾመው ብዙ አገልግለዋል" ጻድቁ በምድረ ኤርትራ በምንኩስና እና በብሕትውና ጸንተው ለትልቅ ሰማያዊ ክብር የበቁ ታላቅ ጻድቅ ናቸው። በዓለ ዕረፍታቸው ሰኔ 9 ነው።

የአቡነ በኵረ ድንግል፦ አባታቸው ማርቆስ እናታቸው እግዚእ ክብራ የሚባሉ ሲሆን ጻድቁ ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ ብዙ ተኣምራት ይሠሩ ነበር" ሲወለዱም የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ከነልጇ (ምስለ ፍቁር ወልዳ) በልባቸው ላይ ተሥላ ተገኝታለች" በማሕፃን ሳሉ ተመርጠዋልና በአኵሱም ሲወለዱ እንደሌሎቹ ቅዱሳን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ብለው ስመ ሥላሴን ጠርተው አመሰገኑ። በዚያ የነበሩና ይህንን የተመለከቱ ሰዎችም ባዩትና በሰሙት ነገር እጅግ ተደነቁ።

በ40ኛው ቀናቸውም በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት እንዲቀበሉ ወላጆቻቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዷቸው በወቅቱ የነበሩት ጳጳሱ አቡነ ሰላማ ሕፃኑ ትልቅ መነኵሴና የአቡነ ብፁዐ አምላክ ደቀ መዝሙር እንደሚሆን ተገልጾላቸው ትንቢት ተናገሩ። ዳግመኛም ጳጳሱ ቅብዓ ሜሮን ሊቀቡት ሲሉ ሥዕለ ማርያም ከነልጇ በሕፃኑ ደረት ላይ ተሥላ አይተዋት ደነገጡ ወዲያውም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጸ ሳይፈሩ ሥርዓተ ጥምቀቱን እንዲፈጽሙ አዘዛቸው ዳግመኛም ..… "ስሙን በኵረ ድንግል አለው ትርጉሙም በልቡ ላይ ያየኸው ሥዕል ነው" ብሎ ነገራቸው" ሕፃኑም ከተጠመቀ በኋላ እመቤታችን ከነልጇ ጋር ተገልጻ በትእምርተ መስቀል ባረከችው ያ ትእምርተ መስቀልም ዳግመኛ በሰውነታቸው ላይ ተሳለ።

ከዚህም በኋላ አቡነ በኵረ ድንግል አድገው ቤተሰቦቻቸውን እየረዱ በእረኝነት እያገለገሉ በመልካም አስተዳደግ አደጉ" ዕድሜአቸው ለትምህርት እንደደረሰ ወላጆቻቸው ለንቡረ እድ ዮፍታሔ ሰጧቸውና አስተማሯቸው። ከቋንቋዎች ግእዝ፣ ዐረብ ዕብራይስጥ፣ ጽርዕ እና ሮማይስጥ ተማሩ፤ ብሉይንና ሐዲስን እንዲሁም ቅዱሳት መጻሕፍትን ሁሉ አጠናቀው ተማሩ። ቅኔ ድጓ ጾመ ድጓ እና የቅዱስ ያሬድን ዜማዎችም በሚገባ አጠኑ። ትምህርታቸውንም ከጨረሱ በኋላ መምህራቸው ወደ ሊቀ ጳጳስ ወሰዱአቸው በልባቸው ያለች የእመቤታችን ሥዕልም ለጳጳሱ ተገልጣ "ይህ የምወደው ልጄ ስለሆነ በልቡ ተሳልሁ ስለዚህ ዲቁና ቅስና ስጠው፣ ኤጲስ ቆጵስነትም ሹመው" አለቻቸው። ጳጳሱም ባዩትና በሰሙት ነገር ተደንቀው ተነሥተው እንደተባሉት በሦስቱ መዕረግ ሾሟቸው። ከሹመታቸውም በኋላ በአከባቢው ያሉ ሰዎች አቡነ በኩረ ድንግልን ብርሃን ለብሰው ስላዩዋቸው በጣም ተደነቁ።

ከዚህም በኋላ አቡነ በኵረ ድንግል ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ወላጆቻቸው በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ሚስት ሲያጩላቸው አቡነ በኩረ ድንግል ግን "እኔስ ፍላጎቴ በድንግልና መኖር እንጂ ማግባት አይደለም" ብለው ሌሊት ተነሥተው ከቤታቸው ጠፍተው ወደ እግዚአብሔር ቤት ሔደው "አቤቱ ጌታ ሆይ! ከዘለዓለም እሳት ከዲያብሎስ እሥራት ሰውረኝ መጥፎውን ሐሳብ ከእኔ አርቀህ ፍቃድህን እፈጽም ዘንድ እርዳኝ የእመቤታችን ሥዕል ከነልጇ በልቤ አለና ወደ ጋብቻ ዓለም ለመግባት ኅሊናዬ አልፈቀደልኝም ስለዚህ ፍቃድህ ቢሆንልኝ እንደ መላእክት ንጹሕ ሁኜ እንድኖር እለምንሃለሁ፣ አንተ ድኃና ምስኪን የማትንቅ አምላክ መሆንህን ዐውቃለሁና…" እያሉ ጸለዩ። እየጸለዩ ሳለ ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤል አስከትላ ተገለጠችላቸውና "ልጄ ሆይ! ጸሎትህ ተሰምቷልና ወደ ደብረ ዳሞ ወደ አባትህ ሒድ፣ እንዲሁም ደግሞ ወደ ደብረ ናዝሬት ወደ ብፁዐ አምላክ ዘንድ ሒድ የብዙዎች አባትም ትሆናለህ" በማላት ከባረከቻቸው በኋላ ተሰወረች።

ከዚህም በኋላ ጻድቁ መጋቢት 9 ቀን በቦታቸው ሆነው በተመስጦ እየጸለዩ ሳሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በደመና ተሸክሞ ወስዶ ደብረ ዳሞ የቅዱሳን ማረፍያ ቦታ አደረሳቸው። እመቤታችን እንደነገረቻቸው በገዳሙ አስቀድማ እንደነገረቻቸው ለረጅም ዓመታት በትሕትና ካገለገሉ በኋላ ወደ አባታቸው ወደ አቡነ ብፁዐ አምላክ ከረጅም ጉዞ በኋላ መጡ። አቡነ ብፁዐ አምላክም አስቀድመው መምጣታቸውን ያውቁ ነበርና አሁን ሲያገኗቸው እግዚአብሔርን አመስግነው በታላቅ ደስታና ትሕትና ተቀበሏቸው።

በገዳማቸውም በትሕትና እያገለገለ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን አቡነ ብፁዐ አምላክ "ዛሬ በእጅህ ቍርባን እንድንቀበል አንተ ቀድስ" አሏቸው። አቡነ በኩረ ድንግልም ቅዳሴ ገብተው አሐዱ አብ ቅዱስ… ብለው ሲጀምሩ ከመሬት ወደላይ 5 ሜትር ያህል ከፍ ብለው ታዩ፤ ይኽንንም አይተው አቡነ ብፁዐ አምላክ በጣም ተደንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። አቡነ በኵረ ድንግልም በእንዲህ ያለ ሕይወት አባታቸውን አቡነ ብፁዐ አምላክን ካገለገሉ በኋላ አቡነ ብፁዐ አምላክ ታኅሣሥ 9 ቀን የገዳማት መነኰሳትን ሰብስበው "ዛሬ ለሁላችሁ መሪ የሚሆን ትሑትና ደግ መምህር እሰጣችኋለሁ ከእኔ በታች እርሳቸውን ስሟቸው ታዘዙአቸውም" ብለው ነገሯቸው።

ዳግመኛም አባታችን አቡነ ብፁዐ አምላክ የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ የገዳሙን መነኰሳት ሰብስበው ከእርሳቸው በኋላ አባት እንዲሆኗቸው አቡነ በኵረ ድንግልን እጃቸውን ጭነው ባርከው ሾሟቸው። ከዚህም በኋላ አቡነ በኵረ ድንግል በጾም በጸሎት በስግደት ለገዳሙና በገዳሙ ለሚኖሩ መነኰሳት ሁሉ በትሕትና እያገለገሉ በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ። የገዳሙ መነኰሳትም በጣም ወደዷቸው። ተጋድሏቸውንና አገልግሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ በኵረ ድንግል እንዲህ የሚል ቃልኪዳን ገባላቸው።

"በስምህ ዝክር የሚዘክር ስምህን የሚጠራ በዕረፍትህ ቀን የታመሙትንና የታሰሩትን የጎበኘ በስምህ የተራበ ያበላ ያጠጣ የታረዘ ያለበሰ የልጁን ስም በስምህ የጠራ ይህን ሁሉ ያደረገውን እምረዋለሁ ክፉም አይነካውም፤ በደብረ ምዕዋን በአባትህ በብፁዐ አምላክ ቦታ በአንተም ቦታ የተቀበረ በቦታው ቅዱስ ቍርባን የተቀበለ ክፉ አያገኘውም፣ እምረዋለሁ፣ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምም አስገበዋለሁ ብሔረ ሕያዋንና ብሔረ ብፁዓንንም አወርሰዋለሁ…" የሚሉ ታላላቅ የምሕረት ኪዳናትን ከእግዚአብሔር ከተቀበሉ በኋላ ሰኔ 9 ቀን ትንሽ የራስ ምታት ሕመም ጀመራቸው። የገዳሙ መነኰሳትና ሌሎቹም ታላላቅ ቅዱሳን አባቶች እንደእነ አቡነ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን ያሉት እንደየ ደረጃቸው ከያሉበት ተሰበሰቡ። በዚህም ጊዜ ሥሉስ ቅዱስ ተገልጸውላቸው ድጋሚ ቃልኪዳን ገብተውላቸው አረጋጓቸውና ቅድስት ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች።

አባታችንም ካዐረፉ በኋላ በደብረ ምዕዋን ቅድስት ሥላሴ ደብረ ናዝሬት ከአባታቸው ከአቡነ ብፁዐ ኣምላክ ጋር ተቀበሩ። የአቡነ ብፁዕ አምላክ እና የአቡነ በኩረ ድንግል ገዳም ደቀ መሐሪ ጎደይቲ አካባቢ ይኛል። እነርሰም ካረፉ በኋላ እየተገለጡ በጠበላቸው አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሁለ እየፈወሱ፣ በመቃብራቸው አፈር ሙት እያስነሡ የተለያዩ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት ሲሠሩ ታይተዋል። የሠሯቸውም ተዓምራት ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደለም። ከአባታችን ከአቡነ በኩረ ድንግል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን። ምንጭ፦ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን።
††† 🌹እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ ቅዱስ ላሊበላ: ቅድስት አፎምያና ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ ይከበራሉ::

††† ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት †††

††† ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

ቅዱስ ሚካኤልን በዚሕች ዕለት ስለ እነዚህ ነገሮች እናከብረዋለን:-
1.በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ መሾሙን
2.ቅዳሴ ቤቱን (ግብፅ ውስጥ)
3.ቅድስት አፎምያን መርዳቱን
4.ቅዱስ ባሕራንን መጎብኘቱን
5.ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን
6.ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረት የሚጠይቅበት ዕለት ነውና::

††† ሊቀ መላእክት በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::

††† ቅዱስ ላል ይበላ ንጉሥ †††

††† በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በሃገራችን የነገሠው ቅዱስ ላሊበላ:-
¤በብሥራተ መልአክ ተወልዷል
¤ቅዱሳት መጻሕፍትን ገና በልጅነቱ አጥንቷል
¤የንጉሥ ዘር ቢሆንም በጾምና ጸሎት: በትሕርምት አድጓል
¤በወንድሙ ቢገረፍም ቂም አልነበረውም
¤ስለ ወዳጆቹ ፍቅር መርዝ ጠጥቷል
¤በዙፋን ላይ የኢትዮዽያ ንጉሥ ሆኖ ቢቀመጥም እርሱስ አኗኗሩ ገዳማዊ ነበር
¤ከተባረከች ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ጋር አንዲት ማዕድ ብቻ በቀን ይቀምሱ ነበር:: ለዛውም ለምለሙን ለነዳያን ሰጥተው እነርሱ የሚበሉት የእንጀራውን ቅርፍት (ጠርዝ) ብቻ ነበር::

በአካለ ሥጋ ወደ ሰማያት ተነጥቆ ብዙ ምሥጢራትን አይቷል
¤በምሳሌውም ሃገረ ሮሃን (ላስታን) ገንብቷል
¤ዛሬም ድረስ ምስጢር የሆኑት ፍልፍል አብያተ መቃድስ የእጆቹ ሥራዎች ናቸው::

ሥራውን ከፈጸመ በኋላ መንግሥቱን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አውርሶ: በመንኖ ጥሪትና በቅድስና ኑሮ በዚሕች ቀን አርፏል:: ጌታችን ስምህን ያከበረ: ዝክርህን የዘከረ: ከቤትህ ያደረውን: ከርስተ መንግስተ ሰማያት አካፍለዋለሁ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

††† በረከቱን: ክብሩን ያድለን::

††† ቅድስት አፎምያ †††
ከቅዱስ አስተራኒቆስ ጋር በተቀደሰ ትዳር የኖረች
¤ምጽዋትን ያዘወተረች
¤በፍቅረ ቅዱሳን የጸናች
¤ንጽሕናዋን ጠብቃ ሰይጣንን ያሳፈረች ደግ እናት ናት:: ዛሬ የቅዱስ ሚካኤልን ስዕል ታቅፋ: በትእምርተ መስቀልም አማትባ አርፋለች: ቅዱሱ መልአክም ወደ ገነት አሳርጓታል::

††† ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ †††

የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ:
¤በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ:
¤በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ:
¤በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ:
¤ምጽዋትን ያዘወተረ: አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤በዚህች ቀን አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

††† አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ በረከት ይክፈለን:: አሜን:: †††

††† ሰኔ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅድስት አፎምያና ባለቤቷ ቅዱስ አስተራኒቆስ
4.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
5.ቅዱስ እለ እስክንድሮስ ሊቅ
6.አባ ዮስጦስ ሊቀ ዻዻሳት (የሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ደቀ መዝሙር)
7.አባ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ድሜጥሮስ
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

††† "በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ወደ ምድር ተጣለ::" †††
(ራዕይ. 12:7)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

https://t.me/zikirekdusn
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት እና የመላእክት አዳኝነት ልዩነት-Deacon Yordanos Abebe…
የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትእና የቅዱሳንመላእክት አዳኝነት

ኅዳር 13 2011 የተሰጠ ቢሆንም ከቅዱሳን መላእክት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ይደመጥ


ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

""ከቅዱሳን ሕይወት ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!""


" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

https://t.me/zikirekdusn