ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
4.94K subscribers
866 photos
5 videos
27 files
239 links
የዲ.ን ሄኖክ ሀይሌን ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#ሚያዝያ_9
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም
ሚያዝያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ እረፍታቸው ነው፣ የከበረ #ቀሲስ_ዘሲማስ አረፈ፣ በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #በአባ_ስንትዩ እጅ ታላቅ ምልክት ታየ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

ሚያዝያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ እረፍታቸው ነው። አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡ የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡

በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡፡

አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡

አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡ ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡

አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር፡፡ ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡

ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ፡፡

ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡ በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት ይደግማሉ፡፡ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዘሲማስ_ገዳማዊ

በዚህች ቀን የከበረ ቀሲስ ዘሲማስ አረፈ። ይህም ፃድቅ ከፍልስጥኤም ሰዎች ወገን ነው። ወላጆቹም ደጋጎች ክርስቲያኖች ናቸው ይህንን ፃድቅ በወለዱት ጊዜ አምስት አመት አሳደጉት። ከዚያም የቤተክርስቲያን ትምህርትን የሀይማኖትንም ምስጢር ህግና ስርአትንም እያስተማረ እንዲያሳድገው ለአንድ ሽማግሌ መምህር ሰጡት።

ያ ሽማግሌም ተቀበሎ ልጁ አደረገው ትምህርቱንም ሁሉ አምላካዊ ጥበብ ሀይማኖትንም አስተምሮ አመነኰሰው ዲቁናም አሾመው በበጎ ስራም አደገ ትሩፋት መስራትንም አበዛ እግዚአብሔርንም ሁልጊዜ ያመሰግነዋል በቀንና በሌሊትም መፃሕፍትን ያነባል። ስራ ሲሰራ ሲበላም ቢሆን ሁል ጊዜ ከአፉ ምስጋናዎችን አያቋርጥም። በዚያ ገዳም አርባ አምስት አመት በተፈፀመለት ጊዜ ቅስና ተሾመ ተጋድሎውንም ጨመረ።

ከዚህ በኃላም እየተጋደለና አገልግሎት በመጨመር በቅስና ሹመት አስራ ሶስት አመት ሲሆነው በዘመኑ ካሉ ተጋዳዮች ሁሉ እርሱ በገድሉ ከፍ ከፍ እንዳለ ተቃራኒ ጠላት ዲያብሎስ በልቡ ክፉ ሀሳብ አሳደረበት በልቡም ከበጎ ስራ እኔ ያልሰራሁት የቀረኝ አለን ይል ጀመር።

ነገር ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልተወውም መልአኩን ልኮ በዮርዳኖስ ወንዝ አቅራቢያ ወደ አለ ገዳም ይሄድ ዘንድ እንጂ። ያን ጊዜም ተነስቶ ሄዶ ወደዚያ ገዳም ደረሰ በገድላቸው ፍፁማን የሆኑ እውነተኞች አገራውያንን አገኘ እርሱ ከእርሳቸው እንደሚያንስ አወቀ እርሱ በአለም ውስጥ ነው የኖረውና ስለዚህ ከእርሱ ይሻላሉ።

በዚያ ገዳም ከሳቸው ጋር ኖረ ብዙ ዘመናትም አብሮአቸው ሲጋደል ኖረ። ለዚያ ገዳም መነኰሳትም ልማድ አላቸው ታላቁ ፆም በደረሰ ጊዜ የመጀመሪያውን አንድ ሱባኤ በአንድነት ይፆማሉ በቅድስት እሑድ ስጋውንና ደሙን ይቀበላሉ በማግስቱም ሰኞ ጥዋት ሀያ ስድስተኛ መዝሙር እግዚአብሄር ብርሀነ ረድኤቱን ሰጥቶ ያድነኛል የሚያስፈራኝ ምንድነው የሚለውን እሰከ መጨረሻው እየዘመሩ ይወጣሉ በሚወጡም ጊዜ ወደ በሩ ተሰብስበው በአንድነት ፀልየው እርስ በርሳቸው ሰላምታ ይሰጣጣሉ የገደሙ አበ ምኔትም ይባርካቸዋል።
ከዚህም በኃላ እየአንዳንዱ ወደ በረሀ ይበተናሉ አንዱም አንዱ ባልንጀራውን ያየ እንደሆነ እንዳያየው ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳል። ቅዱስ ዘሲማስም በየአመቱ ከሳቸው ጋራ ወጥቶ በበረሀው ውስጥ ይዘዋወራል የሚፅናናበትንም ይገልጥለት ዘንድ እግዚአብሄርን ይለምነው ነበር፡፡ ሲዘዋወርም በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያምን አገኘ ከእርሷም በልጅነቷ ወራት በእርሷ ላይ እንዴት እንደሆነና በበረሀም የሆነውን ኑሮዋን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተረዳ።

ከዚህ በኃላም በሁለተኛው አመት ስጋውንና ደሙን ያመጣላት ዘንድ ፈለገች እንዳለችውም አደረገላት። ለዚህም ፃድቅ ብሄረ ብፁአን ይገባ ዘንድ ተገባው እርሱም ገድላቸውን ፃፈ ስራቸውንና ፅድቃቸውን ገለጠ። ዘጠና ሶስት የሚሆን መላ እድሜው በተፈፀመለት ጊዜ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ስንትዩ

በዚህችም ቀን በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ስንትዩ እጅ ታላቅ ምልክት ታየ።ይኸውም የከበረች የጌታን ፆም ከመነኰሳት ጋራ ይፆም ዘንድ ወደ አስቄጥስ ወደ አባ መቃርስ ገዳም ወጣ።

ሰሙነ ህማማትም በሆነ ጊዜ ገዳማቱንና አድባራቱን ሊዘርፉና ሊማርኩ የአረብ እስላሞች ተሰበሰቡ። በቤተ ክርስቲያኒቱ በስተምስራቅ ሰዎችንም ይገድሉ ዘንድ ሰይፎቻቸውን መዝዘው በእጆቻቸውም ይዘው በአለት ላይ ቆሙ።

ኤጲስቆጶሳትና መነኰሳትም ወደ አባ ስንትዩ ተሰብስበው ከአረብ እስላሞች እንዴት እንደሆነ ነግረው ከዚያ ገለል እንዲል ለመኑት። የከበረ አባ ስንትዩም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግራቸውን አጥቦ አዲስ ስርአት የሰራበት የፋሲካ ፍስህ በአል ሳይፈፀም እኔ ከዚህ አልለይም አላቸው።

እነዚህ እስላሞችም እየደነፉ ጩኸታቸው ተጨመረ። አባ ስንትዩም የወገኖቹን ድንጋፄ በአየ ጊዜ በላዩ የመስቀል ምልክት ያለበት በትሩን ይዞ ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋራ ብሞት ይሻለኛል እያለ ወደ እነርሱ ሊወጣ ተነሣ።

ኤጲስቆጶሳቱም እንዳይወጣ ያዙት። እርሱ ግን ልባቸውን በማፅናናት አረጋጋቸውና ወደ አረብ እስላሞች ወጣ። እስላሞችም መስቀል ያለበትን በትር በእጁ ይዞ በአዩት ጊዜ ብዙ ሰራዊት እንዳሳደዳቸው ሆነው ወደ ኃላቸው ተመልሰው ሸሹ። ከዚያችም እለት ወዲህ ወደ ቅዱሳት መካናት እስላሞች አልተመለሱም።

ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
ቅዱስ ዞሲማስ በበረሀ ውስጥ ሲዘዋወር ያገኛት ቅድስት ማን ትባላለች?
Anonymous Quiz
11%
ማርያም መቅደላዊት
13%
ማርያም እንተ ዕፍረት
59%
ማርያም ግብጻዊት
16%
ማርያም ባውፍልያ
በሰሙነ ህማማትም በሆነ ጊዜ ገዳማቱንና አድባራቱን ሊዘርፉና ሊማርኩ የመጡትን የአረብ እስላሞች በእጁ በያዘው በትረ መስቀል ወደ ገዳሙ እንዳይደርሱ እንዲሸሹ ያደረገው አባት ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
20%
አባ ባውላ
38%
አባ ስንትዩ
23%
አባ አሞኒ
19%
አባ ዮሐኒ
ብሔረ ብፁዓን ሄዶ በዚያ ያሉ የቅዱሳንን አኗኗራቸውንና ገድላቸውን ተመልክቶ እነርሱንም አውርቶ በረከታቸውን ተቀብሎ ወደ ምድር ተመልሶ መጠጥቶ ገድላቸውን የጻፈው ቅዱስ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
18%
ቅዱስ ማቴዎስ
22%
ቅዱስ ዮሐንስ
46%
ቅዱስ ዞሲማስ
15%
ቅዱስ ታዴዎስ
ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ወደ ብሔረ ብፁዓን የሄደው ቅዱስ ነው?
Anonymous Quiz
54%
ቅዱስ ዮሐንስ
16%
ቅዱስ ማቴዎስ
8%
ቅዱስ ያዕቆብ
22%
ቅዱስ ስንትዩ
ጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የተወለዱት መቼ ነው?
Anonymous Quiz
20%
ታኅሳስ 10
38%
መጋቢት 9
30%
ታኅሳስ 8
12%
ሚያዝያ 8
የሐዋርያው የቅዱስ ማቴዎስ የቀድሞው ስሙ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
18%
ስምኦን
20%
ዲዲሞስ
53%
ሌዊ
9%
ሳኦል
ከአራቱ ወንጌል መካከል ቴዎፍሎስ ለተባለ የግሪክ ባለስልጣን የተፃፈው የትኛው ወንጌል ነው?
Anonymous Quiz
14%
የማቴዎስ
48%
የሉቃስ
27%
የማርቆስ
10%
የዮሐንስ
ከሚከተሉት አንዱ በዮሐንስ ራእይ ከተገለጹት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ አንዱ አይደልም?
Anonymous Quiz
13%
ኤፌሶን
30%
ጴርጋሞን
9%
ሎዶቅያ
49%
ሮም
†††  እንኳን ለአባ ይስሐቅ ጻድቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ይስሐቅ ጻድቅ †††

††† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: በጊዜው ዝነኛ ከነበሩት ከታላቁ አባ ዕብሎ (ቅዱስ ዕብሎይ) ተምረዋል:: መማር ብቻ ሳይሆንም ለ25 ዓመታት ያለ መታከት በተልዕኮ አገልግለዋል::

በእነዚህ ጊዜያትም ትሕርምትን : ተጋድሎን : ትምህርተ ቅድስናንና ሌሎች አስፈላጊ መንፈሳዊ ስንቆችን ሰንቀዋል:: በመታዘዛቸው በምድር አበውን : በሰማይ እግዚአብሔርን አስደስተዋል:: በዚህም ከእግዚአብሔር ጸጋውን : ከአበው ምርቃትን አትርፈዋል::

ጊዜው ደርሶም ታላቁ ዕብሎ ሲያርፉ አባ ይስሐቅ በዓት ለይተው ደንበኛውን ተጋድሎ ጀምረዋል:: አምላካቸውን ለማስደሰትና በቅድስና ለመዝለቅም የአርምሞ ሰው ሁነዋል:: ለሚገባው ነገር ካልሆነ በቀር አያወሩም:: ምላሽም አይሰጡም:: "ለምን?" ሲባሉ
1."ለሁሉም ጊዜና ቦታ አለው::"
2."ሰው በከንቱ በማውራቱ ከጸጋ እግዚአብሔር ይርቃል" ይሉ ነበር::

አባ ይስሐቅ የክርስቶስ መድኃኒታችንን ሕማማት ለማዘከር ሁሌ ያነቡ (ያለቅሱ) ነበር:: ቅዳሴ ሲያስቀድሱ እጃቸው የሁዋሊት ታስሮ ነበር:: ቅዱሱ ሰው ለአዝማናት እንዲህ ተመላልሰው በመልካም ዕርግና ያረፉት በዚህ ቀን ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው አይለየን::

††† ሚያዝያ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ይስሐቅ ገዳማዊ (የታላቁ ዕብሎይ ደቀ መዝሙር)
2.አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† "የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ:
ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ::
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" †††
(ይሁዳ. 1:1)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
እንኩዋን አደረሳችሁ

"' በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ "'

+*" ሰማዕታተ ኢትዮጵያ "*+

አመ ዐሡሩ ወአሚሩ ለሚያዝያ በዛቲ ዕለት አዕረፉ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ:: በረከቶሙ የሃሉ ምስሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡

ከመዝ ኮነ በውስተ ሀገረ ሊብያ በዕሥራ ምዕት ወሰብዐቱ ዐመተ ምሕረት፡፡ በአሜሃ ዘመን ተንሥኡ ተንባላት እለ ስሞሙ አይሲስ በውስተ ሀገረ ኢራቅ ወሶርያ ወሊብያ ወየመን፡፡ አሐዙ ይቅትሉ ሰብአ ዘረከቡ ወፈድፋደሰ እለ ኮኑ ክርስቲያነ በእምነቶሙ፡፡

ብዙሓን ክርስቲያን ተመትሩ አርእስቲሆሙ በአይሲስ ወተወክፉ አክሊለ ስምዕ እምእላ ሀገራት፡፡ በዝ ዘመን ውእቱ ዘረከቦሙ አይሲስ ለሰብአ ኢትዮጵያ በውስተ ሀገረ ሊብያ እንዘ የሐውሩ ኀበ ሀገረ ኢጣልያ በእንተ መፍቅደ ልቦሙ፡፡ እሉ ከሀድያን ውሉደ ሰይጣን ወአራዊተ ገዳም አሐዝዎሙ ወአዘዝዎሙ ወአፍርሕዎሙ ከመ ይክሀዱ ስሞ ለኢሱስ ክርስቶስ፡፡

ወእምዝ ዘበጥዎሙ በዘዚአሁ ዝብጠታተ በእንተ ዘኮኑ ክርስቲያነ ርእዮሙ ማዕተበ ክሣዶሙ፡፡ ውእቶሙሰ አበዩ ይእዜኒ ክሂደ ሃይማኖቶሙ እመኒ አመከርዎሙ በረሐብ ወጽምዕ ወበካልኣን ኵነኔያት፡፡ ሶበ አበዩ ክሂደ ወሰድዎሙ ኀበ ምድረ በድው ኀበ አልቦ እክል ወማይ ከመ ይእመኑ እምጽንዐ ረሐብ ወጽምዕ፡፡

ወእምዝ ጠየቅዎሙ ከመ ይብትኩ ማዕተበ ክሣዶሙ ወይክሀዱ ስሞ ለእግዚአብሔር አምላኮሙ፡፡ እሉሰ ሰማዕታት ይእዜኒ አበዩ ክሂደ ስሞ ለፈጣሪሆሙ፡፡ አዲ ይቤልዎ ለአይሲስ "ኦ አይሲስ ለእመ ክህልከ ቀቲሎታ ለሥጋነ ኢትክል ቀቲሎታ ለነፍስነ፡፡ ኢንፈርሕሂ ወኢንደነግጽ እምብልሐ ሰይፍከ እስመ አቅዲሙ ነገረነ አምላክነ እንዘ ይብል ኢትፍርሕዎሙ ለእለ ይቀትሉ ሥጋክሙ ወለነፍስክሙሰ ኢይክሉ ቀቲሎታ፡፡"

አዲ ይቤለነ በውስተ ወንጌሉ ቅዱስ እስመ ኵሉ ዘከቀተለክሙ ይመስሎ ከመ ዘመሥዋዕተ ያበውእ፡፡ ይእዜኒ አንተ ላእኩ ለዲያብሎስ ፈጽም በላዕሌነ መልእክተከ ሰይጣናዌ ወአብእ መሥዋዕተከ ርኩሰ ለእምላክከ ሰይጣናዊ፡፡ ንህነኒ ናበውእ ክሣደነ ንጹሐ ለእምላክነ ዘፈጠረነ እስመ ነአምር ዘከመ ያነሥአነ በትንሣኤሁ ቅድስት አመ ዳግም ምጽአቱ፡፡

አሲስኒ አላዊ መተሮሙ አርእስቲሆሙ በሰይፍ ወኮኑ ሰማዕተ በከመ ዛቲ ዕለት፡፡ ወእምዝ ተሀውከት ኵላ ኢትዮጵያ ወኵላ ዐለም እስመ ትርእየ ትእይንተ ጥብሐቶሙ ለሰማዕታት በመስኮተ ትእይንት፡፡ ኵሎሙ ሰብአ ኢትዮጵያ አስቆቀዉ ወበከዩ ብካየ መሪረ እንዘ ይገብሩ ሰላማዌ ትእይንተ በበአዕዋዲሁ ወበበፍኖቱ፡፡

ወይብሉ በበቃሎሙ "አይሲስ አይሲስ እንተ ትቀትሎሙ ለሰማዕታት: ወታውሕዝ ደመ ንጹሓን በበፍናዊሁ ከመ ደመ አክልብት: ይደልወከ ትቁም ውስተ ዐውደ ፍትሕ ሰማያዊ፡፡"

በዝንቱ ዘመን ቈስለ ልቡ ለህዝብ በሐዘነ ሥጋ እስከነ ይብል "ፍትሐ ጽድቅ ዘዐርገት ውስተ ሰማይ ከመ ትንበር ምስለ ዘፈጠራ እግዚአብሔር እስመ ኢረከበት ውስተ ዛቲ ምድር ኀበ ትነብር ወኀበሂ ታጸልል፡፡ ናሁ ይጸርሕ ደሞሙ ለሰማዕታት ቅድመ ገጹ ለኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይረድ ፍትሐ ርትዕ ዲበ ምድር ወይሠረው አሲስ እምውስተ ገጻ ለምድር፡፡"

በረከቶሙ: ወጽንዐ ገድሎሙ ለእሉ ሰማዕታት ይሕድር ላዕሌነ ለዐለመ ዐለም አሜን፡፡

ሰላም ለክሙ በቃለ ማሕሌት ወእንዚራ፡፡
ምስለ ሰማዕታት ዘግብጽ መከራቲክሙ ዘሐብራ፡፡
ቅዱሳን ሰማዕታት ዘኦርቶዶሳዊት ሐራ፡፡
እፎ ክህልክሙ ተዐግሦ ጽኑዕ መከራ፡፡
እስከ ክሳውዲክሙ በአሲስ ተመትራ፡፡
(ኢያዕመርኩ ከመ መኑ ጸሐፎ)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>