ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
6.83K subscribers
1.22K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የተጸነሰችው መቼ ነው?
Anonymous Quiz
6%
ሐምሌ 30
19%
መስከረም 21
58%
ነሐሴ 7
18%
ግንቦት 1
“የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታቶላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ የሰጠ" ንጉሥ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
2%
ሐና
17%
ሄሮድስ
74%
ጲላጦስ
7%
ቀያፋ
እንኩዋን ለቅዱሳት ደናግል ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" ቅዱሳት ደናግል "*+

=>ቅዱሳት ደናግሉ አጋሊዝ (አጋሊስ): ኢራኒና ሱስንያ ይባላሉ:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ተሰሎንቄ የምትባል ሃገር ውስጥ ይኖሩ ነበር:: ሦስቱም እጅግ ቆንጆዎችና ከብዙ ወንዶች ዐይን የሚገባ መልክ ቢኖራቸውም የእነርሱ ምርጫ ግን ሰማያዊ ሙሽርነት ነበርና በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::

+ለብዙ ዓመታትም ደናግሉ በሚኖሩበት ደብር ውስጥ በቅድስና ኑረዋል:: ከቆይታ በሁዋላ ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ሲመጣ ለጊዜውም ቢሆን ወደ በርሃ ሸሽተው ተቀመጡ::

+ያሉበትን ቦታ የምታውቅ አንዲት ደግ ባልቴት እየሔደች ትጎበኛቸው : በእጃቸው የሚሠሩዋቸውን የተለያዩ እቃወችንም እየሸጠች እኩሉን በስማቸው መጽውታ በተረፈው ለራት የሚሆን ደረቅ ቂጣ ትገዛላቸው ነበር::

+አንድ ቀን ግን አንድ አረማዊ ሰው ተከትሏት መጥቶ በማየቱ 3ቱንም ደናግል ወደ ከሐዲው ንጉሥ አቀረባቸው:: ንጉሡ ሃይማኖታቸውን ቢክዱ የሐብትና የስልጣን ተስፋ እንዳላቸው ነገራቸው:: ደናግሉ ግን በፍቅረ ክርስቶስ በመጽናታቸው ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በዚሕች ቀን አስገድሏቸዋል::

=>የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን:: ከደናግሉ በረከትን ያሳትፈን::

=>ሚያዝያ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳት ደናግል አጋሊዝ: ኢራኒና ሱስንያ
2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (ፋርስ (ኢራን) ውስጥ የተሰየፉ)
3.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn
ቅዱሳት አጋሊስ ኤራኒና ሱስንያ የየት ሀገር ሴቶች ናቸው?
Anonymous Quiz
29%
የሮም
15%
የፍልስጤም
41%
የተሰሎንቄ
15%
የግብፅ
ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
እግሩን አጥቦ እጣቢውን ይጠጣው የነበር አባት ማን ይባላሉ?
Anonymous Quiz
26%
አባ በርሱማ
19%
አባ ባውማ
41%
አባ ብሶይ
13%
አባ ገብርኤል
ጻድቁ አቡነ ኪሮስ ያረፉበት ቀን መቼ ነው?
Anonymous Quiz
30%
መስከረም 8
33%
ሚያዝያ 8
12%
ነሐሴ 8
25%
ሐምሌ 8
የጌታችን ዐበይት በዓላት ስንት ናቸው?
Anonymous Quiz
46%
7
7%
8
44%
9
2%
10
በያስቆርቱ ይሁዳ የተተካው ሐዋርያ ማን ይባላል?
Anonymous Quiz
9%
ፊልጶስ
14%
ፊልሞና
60%
ማትያስ
17%
ቶማስ
የሚያስፈሩ የሕይወት ፈረሶች አርባዕቱ እንስሳ የሥላሴን መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው የሚባሉት እነማን ናቸው?
Anonymous Quiz
17%
ሱራፌል
48%
ኪሩቤል
17%
አጋዕዝት
17%
አርባብ
የእመቤታችን ድንግል ማርያም የወላጆቿ መቃብር።