#ነሐሴ_8
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ስምንት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አልዓዛር_ካህን ከሚስቱ እና ልጆቹ ጋር በሰማዕትነት ሞቱ፣ ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ #ጻድቅ_አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አልዓዛር_ካህን
ነሐሴ ስምንት በዚች ቀን አልዓዛርና ሚስቱ ሰሎሜ አንኤም አንጦኒኃስ ዖዝያ አልዓዛር አስዮና ስሙና መርካሎስ የሚባሉ ልጆቻቸውም ሰባቱ በሰማዕትነት ሞቱ።
ይህም አረጋዊ አልዓዛር ከመምህራነ ኦሪት አንዱ ነው እርሱም ለሕዝቡ አለቃና ሊቀ ካህናትም ነው በፈሪሀ #እግዚአብሔርም ሁኖ ያስተዳድራቸው ነበር። ከዚህም በኋላ ዳታንና አቤሮን በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሡባቸው ከዘመዶቹ ወገን ሦስት ካህናት በእርሱ ላይ ቀንተው ተነሡበት።
የእሊህም ስማቸው ስምዖን አልፍሞስ መባልስ ይባላል ሹመቱንም እንዲለቅላቸው ፈለጉ ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመቱ ከ #እግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሉአቸው።
ስለዚህም ነገር ወደ ግሪክ አገር ወርደው ንጉሥ አንጥያኮስን አነሳሡት መጥቶም የእስራኤልን መንግሥት እንዲወስድ ቀሰቀሱት። በመጣ ጊዜም ወደ ከተማቸው በተንኮል እንዲገባ አደረጉት።
በገባ ጊዜም ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ይዞ የእሪያ መሥዋዕትን ለሕዝቡ እንዲሠዋ አዘዘው እምቢ ባለውም ጊዜ ሰባቱን ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ሚስቱን በእሳት በአጋሉት ብረት ምጣድ ላይ አስተኙአቸው እንዲህም ምስክርነታቸውን ፈጸሙ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ኂሩተ_አምላክ_ዘጣና
ዳግመኛም በዚህች ቀን ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ኂሩተ አምላክ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክ ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው፡፡ እርሳቸውም የዐፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው፡፡ ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል፡፡ ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ #እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ፡፡ ሁለት ድንጋዮችንም በተረአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል፡፡ እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ ‹‹ዓቃቤ ሰዓት›› እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል፡፡
የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ 8 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
ዳጋ እስጢፋስ ገዳምን ከዐፄ ዳዊት ጀምሮ እስከ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የተነሡት ነገሥታት እየተሳለሙት የከበሩ ቅርሶችንና የወርቅ ዘውዳቸውን በስጦታ አበረክተውላታል፡፡ 900 ዓመት ያስቆጠሩ የብራና መጻሕፍትና ሌሎች አስደናቂ ቅርሶች የሚገኙበት ገዳም ነው፡፡ የዐፄ ዳዊት፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲልና የሌሎቹም ቅዱሳን ነገሥታት ዐፅም በዚህ ገዳም በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የዐፄ ሱስንዮስም ዐፅም በዚሁ በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር ይገኛል፡፡ ዐፄ ሱስንዮስ የፖርቱጋልን እርዳታ ለማግኘት ሲሉ የካቶሊክን የክህደት እምነት አምነው በሀገራችንም ላይ አውጀው ከ8 ሺህ በላይ ካህናት ምእመናንን ካስገደሉ በኋላ ምላሳቸው ተጎልጉሎ በክፉ አሟሟት ሊሞቱ ሲሉ ልጃቸው ፋሲል ቅዱሳን አባቶችን በመለመን በጸሎታቸው እንዲፈወሱ አድርጓቸዋል፡፡ እነ አቡነ ምእመነ ድንግል እና አቡነ ዓምደ ሥላሴ ጋር በጸሎታቸው የንጉሡን የተጎለጎለ ምላሳቸውን መልሰውላቸው ከሕመማቸውም ፈውሰዋቸዋል፡፡ ‹‹ፋሲል ይንገስ ካቶሊክ ይፍለስ…ተዋሕዶ ይመለስ…የዐፄ ሱስንዮስ ምላስ ይመለስ…እግዚአብሔር ይፍታ›› ሲል ተጎልግሉ የነበረው ምላሳቸው ተመልሰ፡፡ በዚያን ጊዜ ዐፄ ሱስንዮስ ‹‹ብቆይ ዓመት ብበላ ገአት/ገንፎ›› ብለው በመናገር ማላሳቸው እንደቀድሞው ሆነላቸው። ለንስሐ ሞት በቅተው መንግስታቸውን ለልጃቸው አውርሰው በክብር አርፈዋል፡፡ ለዚህም ነው የዐፄ ሱስንዮስ ዐፅም በታላቁ ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስ ከብዙ ቅዱሳን ነገስታት ዐፅም ጋር አብሮ መገኘቱ፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክ የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ወደ ሀገራችን ለማምጣት ብዙ የደከሙ አባት ናቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ርሀብ ስለነተሳ የዘደብረ ቢዘኑን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው ‹‹ምን ባደርግ ይሻለኛል?›› ብለው አማከሯቸው፡፡ እኚህም የዘደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን መወለድ በትንቢት የተናገሩ ናቸው፡፡ ንግሥቲቱ የዐፄ ዳዊት ሚስት የአቡነ ፊሊጶስን እግራቸውን አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ በእምነት ጠጣችው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ፊሊጶስ ንግሥቲቱን ‹‹ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል›› ብለው ትንቢት ከነገሯት በኋላ በትንቢታቸው መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልደዋል፡፡ ዐፄ ዳዊትም በዘመናቸው ስለተነሣው ርሀብ አቡነ ፊሊጶስን ሲያማክሯቸው ጻድቁ ሱባዔ ገብተው በጸሎት ከጠየቁ በኋላ ‹‹የ #ጌታችንን_መስቀል ያስመጡ›› ብለው ንጉሡን መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቁስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ካመጡት ዓሥሩ ታላላቅ ቅዱሳን ውስጥም አንዱ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ናቸው፡፡ የተቀሩት ዘጠኙ ደግሞ የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡
አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ግብፅ ሄደው ግማደ መስቀሉን ይዘው ከግብፅ ስለመጡ አንዳንድ ሰዎች ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል ነገር ግን ለሀገራቸው ለቅድስት ኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ የዋሉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ የትውልድ ሀገራቸውም ወሎ ልዩ ቦታው መርጦ እንደሆነ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_8 እና #ከገድላት_አንደበት)

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_8_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ የምሕረቱ ዕቃዎችም ከአይሁድ ብቻ አይደሉም፥ ነገር ግን ከአሕዛብ ደግሞ የጠራን እኛ ነን።
²⁵ እንዲሁ ደግሞ በሆሴዕ፦ ሕዝቤ ያልሆነውን ሕዝቤ ብዬ፥ ያልተወደደችውንም የተወደደችው ብዬ እጠራለሁ፤
²⁶ እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል።
²⁷-²⁸ ኢሳይያስም፦ የእስራኤል ልጆች ቁጥር ምንም እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይድናል፤ ጌታ ነገሩን ፈጽሞና ቆርጦ በምድር ላይ ያደርገዋልና ብሎ ስለ እስራኤል ይጮኻል።
²⁹ ኢሳይያስም እንደዚሁ፦ ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።
³⁰ እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤
³¹ እስራኤል ግን የጽድቅን ሕግ እየተከተሉ ወደ ሕግ አልደረሱም።
³²-³³ ይህስ ስለ ምንድር ነው? በሥራ እንጂ በእምነት ጽድቅን ስላልተከተሉ ነው፤ እነሆ፥ በጽዮን የእንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዓለት አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ እንደ ተጻፈ በእንቅፋት ድንጋይ ተሰናከሉ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤
¹³ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።
¹⁴ ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።
¹⁵ ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤
¹⁶ ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።
¹⁷ ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?
¹⁸ ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?
¹⁹ ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ በነጋም ጊዜ ገዢዎቹ፦ እነዚያን ሰዎች ፍታቸው ብለው ሎሌዎቻቸውን ላኩ።
³⁶ የወኅኒውም ጠባቂ፦ ትፈቱ ዘንድ ገዢዎቹ ልከዋል፤ እንግዲህ አሁን ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ ብሎ ይህን ቃል ለጳውሎስ ነገረው።
³⁷ ጳውሎስ ግን፦ እኛ የሮሜ ሰዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበው በወኅኒ ጣሉን፤ አሁንም በስውር ይጥሉናልን? አይሆንም ራሳቸው ግን መጥተው ያውጡን አላቸው።
³⁸ ሎሌዎቹም ይህን ነገር ለገዢዎች ነገሩ። የሮሜ ሰዎችም እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ፤
³⁹ መጥተውም ማለዱአቸው፥ አውጥተውም ከከተማ ይወጡ ዘንድ ለመኑአቸው።
⁴⁰ ከወኅኒውም ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፥ ወንድሞችንም ባዩ ጊዜ አጽናኑአቸውና ሄዱ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_8_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ። ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ። ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ"። መዝ 57፥8-9።
"እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤ እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላዩአትም። እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችኋል"። መዝ 57፥8-9።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ነሐሴ_8_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።
¹³ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
¹⁴ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
¹⁵ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።
¹⁶ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
¹⁷ እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።
¹⁸ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።
¹⁹ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
²⁰ ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
²¹ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
²² በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
²³ የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
²⁴ ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።
²⁵ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #እመቤታች_የማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።