በዚህ ሁሉ ከዲያብሎስ ጋር ታግሎ በማሸነፍ በንስሐ እየወደቁም እየተነሱ መጋደል ነው እንጂ የኃጢአት ባርያ ሆኖ መኖር ወይም ንስሐ ሳይገቡ መጋደል ተገቢ አይደለም :: #ቅዱስ_ኢያሱ_ወልደ_ሲራክ ለልጁ የነገረው #እግዚአብሔርን ለማገልገል ከተነሣ ለሚገጥሙት ፈተናዎች ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ነው። ሰይጣን መጾማችንንና ንስሓ መግባታችንን በተመለከተ ጊዜ በመንፈሳዊ ሥራችን ይቀናል። ድካማችንን ዋጋ እንዳንቀበልም ከመንገድ ሊያስቀረን ይዋጋናል። የምንወድቅበትንም ወጥመድ ሁሉ ዘጋጃል። እጅ እስክንሰጥ አልተዋችሁም ይለናል። ነገር ግን #ቅዱስ_ጴጥሮስ እንደነገረን "ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራል በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንደተቀበሉት እየወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት (1 ጴጥ 5፥89) ሲል የመከረውን አስታውሶ መጋደል ያስፈልጋል እንጂ ተስፋ መቁረጥ ወይም ፈርቶ መሸሽ አይገባም። ይቀጥላል...