ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#መስከረም_18 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓሏ ታስባ የምትውለው "ቅድስት ጸበለ ማርያም"

በጎኗ ተኝታ የማታውቅ፣ በጌታችን 40 ጾም ወራት ከሰንበት በቀር ምንም የማትቀምስ፣ ነብሮች የእግሯን ትቢያ ይልሱላት የነበረች ታላቅ ኢትዮጵያዊት ቅድስት ናት። ቅድስት ጸበለ ማርያም ጌታችን በደሃ ሰው ተመስሎ ተገልጦ ቁራሽ እንጀራ የለመናት በኃላም በጀርባዋ አዝላ የሸኘችው ታላቅ እናት ናት። እርሷም ከነቢያት፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ዕድል የተሰጣት እናት ናት፡፡ ከደናግል መነኮሳትም ዕድል ተሰጣት-መነኩሲትም ድንግልም ናትና።

ቅድስት ጸበለ ማርያም ትውልዷ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ቀሐ አካባቢ ነው፡፡ ወላጆቿ አባቷ እንድርያስና እናቷ መስቀል ክብራ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር ኮትኮተው አሳደጓት፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተከስተ ብርሃን የተባለ ደገኛ ባሕታዊ ወደ አባቷ ቤት መጥቶ ባደረበት መንፈስ ቅዱስ ኀይል የቅድስት ጸበለ ማርያምን ጸጋ አወቀ፡፡
ለወላጆቿም ‹‹ይኽቺ ልጅ ወደፊት ነፍሳት የሚድኑባት የከበረች ትሆናለች›› ብሎ በእርሷ ላይ ትንቢት ተናገረ፡፡

ቅድስት ጸበለ ማርያም ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወላጆቿ በጋብቻ ሕግ እንድትወሰን ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ቅድስት ጸበለ ማርያም ‹‹ቅዱስ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር አጭቶኛልና ፈጣሪዬን በድንግልና ለማገልገል ተስያለሁ›› በማለት ተቃወመቻቸው፡፡ ወደ አንድ ደገኛ ባሕታዊም ዘንድ ሄዳ በጸሎቱ ከዚህ ነገር እንዲያድናት ተማጸነችው፡፡ እርሱም ፈቃደ እግዚአብሔርን በጸሎት ከጠየቀላት በኋላ ማድረግ የሚገባትንና ወደፊት የሚገጥማትን ሁሉ ነገራት፡፡ እርሷም ለዕጣን እንዲሆን ጌጧን ሁሉ አውጥታ ሸጠችና ‹‹መሥዋዕቴን አሳርግልኝ›› ብላ ለባሕታዊው ሰጠችው፡፡ እርሱም ከጸለየላት በኋላ የጸሎቱን ምላሽ ነገራት፡፡

ወለጆቿም ያለፈቃዷ በሕግ ቢያጋቧትም ቅድስት ጸበለ ማርያም ግን በሌሊት ማንም ሳያያት ከጫጉላ ቤት ወጥታ ሄዳ በልዳው ፀሐይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ወደተሠራች ቤ/ክ ሄዳ እያለቀሰች ጸሎት አደረገች፡፡ እመቤታችንም ከሚካኤል ወገብርኤል እንዲሁም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተገለጠችላትና እንዲጠብቋት ነገረቻቸው፡፡ ቤተሰቦቿም እንዳያዝኑባት ፈርታ ተመልሳ ወደ ባሏ ዘንድ ብትገባም ባሏ በግብር እንዳያውቃት መላእክቱ ይጠብቋት ነበር፡፡ ባሏንም ሰውነቷ እንደእሳት ያቃጥለው ነበር፡፡ እርሱም አእምሮውን ከሳተ ከ3 ቀን በኋላ ሲነቃ የደረሰበትን ለቤተዘመዶቹ ባስዳቸው ጊዜ ‹‹ከገዳም የመጣች ከሆነች ለእኛ ልትሆን አይገባም›› አሉና አስጊጠውና ሸልመው መልሰው ወደ ቤተሰቦቿ ላኳት፡፡

አባቷም ዳግመኛ ወደባሏ እንድትመለስ በማስገደድ ብዙ አሰቃቂ ግርፋት ቢገርፋትም በተአምራት ምንም እንዳላገኛት ሆነች፡፡ ከዚኽም በኋላ ወጥታ ወደ ምድረ በዳ ሄደች፡፡ ወደ ገዳምም ሄዳ ዋሻ ውስጥ ገብታ ስትጸልይ አድራ አረፍ ስትል ነብር መጥቶ የእግሯን ትቢያ ይልሳት ነበር፡፡ ከዚያም ወጥታ ንህበት ወደሚባል ሀገር መጥታ ቶማስ ከሚባል መነኩሴ ጋር በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ ቆማ ስትጸልይ እንባዋ መሬቱን ያርስ ነበር ነገር ግን ሰው እንዳያውቅባት አፈር በላዩ ትጨምርበታለች፡፡ በአንድ ዕለትም በቤ/ክ ቆማ ስትጸልይ በሁለቱ ማዕዘን የተቀበሩ ምውታን ሲጮኹ ሰማቻቸው፣ እነርሱ ግን በሲኦል ነበሩ፡፡ ጩኸታቸውንም በሰማች ጊዜ በእንባዋ ላይ እንባን በጸሎቷም ላይ ጸሎትን ጨምራ ስለእነርሱ ለመነች፡፡ ስለእነርሱም ሱባኤ ያዘች፡፡ በባሕርይው ቸርና ይቅርባይ የሆነ ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ እነዚያን ነፍሳት ማረላት፡፡

ቅድስት ጸበለ ማርያም በምግባርና በትሩፋት በጾም በጸሎት ጸንታ ከኖረች በኋላ የምንኩስና ቀንበርን ትሸከም (በመንናኔ ትኖር) ዘንድ በብሕትውና ወደሚኖረው ታላቁ አባት ወደ አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ ዘንድ ሄደች፡፡ እርሱም ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር የደረሰው ነው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያምም ካስተማራትና በኋላ አመነኮሳትና ስሟን ‹‹ጸበለ ማርያም›› ብሎ ሰየማት፡፡ ከዚኽም በኋላ ተጋድሎዋን እጅግ በማብዛት ትሕርምትን ገንዘብ አደረገች፡፡ ከዕንጨት ፍሬዎች ውጭ የማትመገብ ሆነች፡፡ በተቀደሰችው የጌታችን 40 ጾም ወራት ግን ከሰንበት በቀር እርሱንም ፈጽሞ አትቀምስም፣ እስከ ፋሲካም ድረስ ከበዓቷ ስለማትወጣ ማንም አያያትም ነበር፡፡ ከመነኮሰችም ጊዜ ጀምሮ በጎኗ ተኝታ አታውቅም፡፡ ባመማት ጊዜም ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፡፡ በውርጭ ቅዝቃዜ መከራን እየተቀበለች በባሕር ውስጥም ቆማ እየጸለየች ታድራለች፡፡ በስግደቷም በቀን እስከ 8 እልፍ ትሰግድ ነበር፡፡ ከወንድሟ ቶማስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ተማረች፡፡ የዮሐንስን ወንጌልና የራእዩን መጽሐፍ ዘወትር በማንበብ ትጸልያለች፡፡ የእመቤታችን በዓል በሆነ ጊዜ አርጋኖን ውዳሴዋን በቀን ሦስት ጊዜ ታነባለች፣ አንቀጸ ብርሃንንም በየሰባቱ ጊዜ ትጸልያለች፡፡ የዳዊትንም መዝሙር በፈጸመች ጊዜ የጌታችንን መከራ ግርፋት እያሰበች ራሷን ሺህ ጊዜ ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም አገዛዛቸው መልካም ይሆን ዘንድ ስለ ጳጳሱና ስለ ንጉሡ አንድ አንድ ሺህ ጊዜ፣ ስለ መነኮሳትም ሺህ ጊዜ፣ ስለኃጥአንም ሺህ ጊዜ ራሷን ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም ነጭ ዕጣን በእጇ ይዛ ሰባት ቀን እስኪሆን ድረስ ዕንባዋን ታፈስበታለች፣ ያም ነጭ ዕጣን ከዕንባዋ ብዛት የተነሣ ጥቁር ይሆናል፡፡ በዓል በሚሆንበት በሰባተኛው ቀን አስቀድማ ዐውቃ በመሠዊያ ያሳርገው ዘንድ ያን ዕጣን ለቄሱ ትሰጠዋለች፡፡ እግዚአብሔርም እንደሱራፌል የጽናሕ መዐዛና እንደኪሩቤል ዕጣን ሽታ አድርጎ ከቄሱ እጅ ሲቀበል በግልጽ ታያለች፡፡
#መስከረም_18

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም አስራ ስምንት በዚህች ቀን ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር፣ የደብረ ጽጋጉ #አቡነ_አኖሬዎስ፣ ሰማዕቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ካልዕ#የአቡነ_ያዕቆብ_ግብፃዊ ዕረፍታቸው ነው። ዳግመኛም ይህች ዕለት ሐዋርያው #ቅዱስ_ቶማስ በሕንድ አገር ድንቅ ተአምር ያደረገባት ዕለት ናት፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኤዎስጣቴዎስ_ከፋሌ_ባህር

መስከረም ዐሥራ ስምንት በዚች ቀን ወንጌልን የሚሰብክ የሃይማኖት መምህር አባታችን ኤዎስጣቴዎስ አረፈ ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ክርስቶስ ሞዓ የእናቱ ስም ስነ ሕይወት ይባላል ሁለቱም ደጋጎች #እግዙአብሔርን የሚፈሩና በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ነበሩ።

ከዘህም በኋላ በከበረ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት ይህን ቅዱስ ወለዱት ስሙን የጌታ ጥብቅ ብለው ሰየሙት ። በአደገም ጊዜ የዳዊትን መዝሙርና የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍትን አስተማሩት ።

ከዚህም በኋላ የእናቱ ወንድም አባ ዘካርያስ ወደአለበት የመነኰሳት ገዳም ወሰዱት ። አባ ዘካርያስም የ #እግዚአብሔርን ጸጋ እንዳደረችበት አውቆ የምንኩስናን ሥርዓት አስተምሮ የመላእክትን አስኬማ አለበሰው ። ከገድሉ ጽናት የተነሣ በገዳም ያሉ አረጋውያን እስኪያደንቁ ድረስ በጾም በጸሎት የተጠመደ ሆነ እርሱ በጥበብና በዕውቀት የጸና ነውና ። ከጥቂት ጊዜ በኋላም ዲቁና ተሾመ የዲያቆናት አለቃ እንደሆነ እስጢፋኖስም ለቤተ ክርስቲያን አገለገለ ።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሚካኤልና ከገብርኤል ጋር ተገለጠለትና ሰላምታ ሰጠው በንፍሐትም #መንፈስ_ቅዱስን አሳደበረት እንዲህም አለው ወዳጄ ኤዎስጣቴዎስ ሆይ እኔ ከእናትህ ማሕፀን መረጥኩህ ያለ ፍርሀትና ድንጋፄ ወንጌልን ለብዙዎች ሕዝቦች ትሰብክ ዘንድ ከኢትዮጵያ እስከ አርማንያ ድረስ መምህር አደረግሁህ አንተን የሰማ እኔን ሰማ አንተን ያልሰማ እኔን አልሰማም #ጌታችንም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ በክብር ዐረገ ።

ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስም ወደ ጳጳስ ሒዶ ቅስና ተሾመ የወንጌልንም ሃይማኖት ይሰብክ ዘንድ ጀመረ ብዙ ሰዎች ወደ ርሱ እስቲሰበሰቡ ድረስ በእርሱም እጅ መንኩሰው ደቀ መዛሙርትን ሆኑት ከእርሳቸውም ታላቁ አባ አብሳዲ ነው ።

ብዙዎችንም የከፋች ሥራቸውን አስትቶ ከክህደታቸው መለሳቸው ትምህርቱም በሀገሩ ሁሉ ደረሰ በመላ ዘመኑም የሰንበታትና የበዓላት አከባበር የጸና ሁኖ ተሠራ ከሐዋርያትም ሕግና ሥርዓት ወደቀኝም ሆነ ወደ ግራ ሁሉም ፈቀቅ አላሉም ።

ወደ ኢየሩሳሌምም ሁለት ጊዜ ሔደ #እግዚአብሔርም በእጆቹ የዕውራንን ዐይኖች በማብራት አንካሶችንና ጎባጦችን በማቅናት አጋንንትን በማስወጣት ቁጥር የሌላቸው ተአምራትን አደረገ ።

ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ለመሔድ በአሰበ ጊዜ ልጆቹን ሰብስቦ የመነኰሳትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ከመናፍቃንም ጋር እንዳይቀላቀሉ አማፀናቸው ። ልጁ አብሳዲንም በእነርሱ ላይ ሾመውና ወደ ኢየሩሳሌም ሰንበትን እያከበረና የ #ክርስቶስን ሃይማኖት እያስተማረ ሔደ ። ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ብንያሚንም ደርሶ ከእርሱ ቡራኬ ተቀበለ የሃይማኖትንም ነገር ተነጋገሩ ዳግመኛም ከከበሩ ቦታዎች በመሳለም በረከትን ተቀበለ በዮርዳኖስም ተጠመቀ ።

ከዚያም ወደ አርማንያ ሔደ ወደ ኢያሪኮ ባሕርም ሲደርስ በመርከባቸው ያሳፍሩት ዘንድ መርከበኞችን ለመናቸው በከለከሉትም ጊዜ ዓጽፉን በባሕሩ ላይ ዘረጋ በ #ቅድስት_ሥላሴ ስም በላዩ ባረከ ራሱንም በ #መስቀል ምልክት አማተበ እንደ መርከብም ሁኖለት በላዩ ተጫነ ሁለት መላእክትም ቀዛፊዎች #ጌታችንም እንደ ሊቀ ሐመር ሆኑለት ። ከባሕሩም ግርማ የተነሣ እንዳይፈሩ ልጆቹን አጽናናቸው ። ግን እንዲህ አላቸው ልጆቼ በልባችሁ ቂምንና ሽንገላን እንዳታኖሩ ተጠበቁ ለኔ ግን ከእናንተ አንዱ አንደ ሚጠፋ ይመስለኛል ይህን ሲናገር ልቡ የቂም የበቀል ማከማቻ ስለሆነ ወዲያውኑ አንዱ ከእነርሱ መካከል ሠጠመ ።

#እግዚአብሔርም ፈቃድ ባሕሩን ተሻግሮ ወደ አርማንያ ከተማ ደርሶ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር ተገናኘ ሰገደለትም ከእርሱም ቡራኬን ተቀበለ ሊቀ ጳጳሱም በአየው ጊዜ ታላቅ ደስታን ደስ አለው በፍቅርም ተቀበለው ።

አባታችን ኤዎስጣቴዎስም ሁሉም በትመህርቱ አንድ እስከሆኑ ድረስ የአርማንያን ሰዎች ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው የሠሩትን ሥርዓት እያስተማራቸው ኖረ ።

ከዚህም በኋላ ዕረፍቱ ሲደርስ ክብር ይግባውና #ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳንን ሰጠው ። በአረፈም ጊዜ ጳጳሳትና ካህናት በታላቅ ክብር ገንዘው በሰማዕቱ በቅዱስ መርምህናም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቀበሩት ። ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገለጡ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አኖሬዎስ_ትልቁ

በዚችም ቀን የደብረ ጽጋግ መምህር አባ አኖሬዎስ አረፈ።

"አኖሬዎስ ትልቁ" መባላቸው "ትንሹ አኖሬዎስ" በሚል ስያሜ የተጠሩ ሌላ ጻድቅ አሉና ነው፡፡ ይኸውም ታላቁ አቡነ አኖሬዎስ አባታቸው ዘርዐ ሃይማኖት ወይም ዘርዐ አብርሃም እናታቸው ደግሞ ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ አቡነ አኖሬዎስ ታላቁ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አቡነ ዜና ማርቆስና አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር እነዚህ ሁሉም የወንድማማቾች ልጆች ናቸው፡፡

እነኚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናትም የእኅትማማቾች ልጆች ናቸው፡፡ ማለትም የአኖሬዎስ ታላቁ እናት ክርስቶስ ዘመዳ፣ የሕፃን ሞዐ እናት ትቤ ጽዮን፣ የንጉሡ የዐፄ ይኮኖ አምላክና የማርያም ዘመዳ እናት እምነ ጽዮን እኅትማማቾች ናቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ እኅትማማቾች (እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ) መድኃኒነ እግዚእ የሚባል አንድ ወንድም አላቸው፡፡ እርሱም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እናት የቅድስት እግዚእ ኀረያ አባት ነው፡፡ ማርያም ዘመዳም አቡነ ዜና ማርቆስንና ማርያም ክብራን ወልዳለች፡፡ ማርያም ክብራም ትንሹን አኖሬዎስን ወልዳለች፡፡ ታላቁ አቡነ አኖሬዎስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በኋላ ወደ ትግራይ በመሄድ ፀዓዳ ዓንባ ከተባለ ቦታ ገዳም መሥርተዋል፡፡

ግብፃዊው አቡነ ያዕቆብ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የደብረ ሊባኖሱን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን አስጠርተው ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት “ኢትዮጵያ በአንድ ጳጳስ መወሰን የለባትም፡፡ ስለዚህ ዐሥራ ሁለት አበው መርጠን ክርስትና ይስፋፋ” ብለው ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘሞረት፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋር፣ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ አኖሬዎስ ዘወረብ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘግድም፣ አቡነ መርቆሬዎስ ዘመርሐ ቤቴ፣ አቡነ አድኃኒ ዘዳሞት፣ አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል፣ አቡነ ኢዮስያስ ዘወጅ፣ አቡነ ዮሴፍ ዘእናርያን መርጠው ሀገረ ስብከት ተሰጥቷቸው ለሐዋርያዊ ተልእኮ ተሠማሩ፡፡ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱን ንቡራነ ዕድ ለስብከተ ወንጌል በመላዋ አገሪቱ ሲሠማሩ ለአቡነ አኖሬዎስ እንደ ግብጦን የተባለ ቦታ ደረሳቸው፡፡ ይህም ቦታ ከግንደ በረት እስከ ባሌ ያለውን አገር ያካትታል፡፡ እርሳቸውም ሰባት ታቦታት ይዘው በመሄድ አብያተ ክርስቲያናት ተክለው ክርስትናን አስፋፍተዋል፡፡ በአካባቢው ስብከተ ወንጌልን ካስፋፉ በኋላ ባርጋባን የተባለ የአካባቢው ሰው ተአምራታቸውንና ትምህርታቸውን ተመልክቶ በጽጋጋ
ወዲያውኑ ከሕንደኬ የጎና ነጋዴ አቤኔስ መጣ #ጌታችንም ምን ትሻለህ አለው ነጋዴውም ሐናፂ የሆነ ባሪያ እሻለሁ አለ። ጌታም ይህን ባሪያዬን ገዝተህ ውሰድ እርሱ አናፂ ነውና አለው ከዚህም በኋላ በሦስት ወቄት ወርቅ ሸጠው እንዲህም ብሎ ጻፈለት የጠራቢ ዮሴፍ ልጅ የሆነ ባሪያዬን ለጎና ነጋዴ ለአቤኔስ ሸጨዋለሁ።

ከዚህም በኋላ አቤኔስ ቅዱስ ቶማስን ተረክቦ ወደ አገሩ ወሰደው ወደ ከተማውም በቀረቡና በደረሱ ጊዜ የእንዚራና፣ የመሰንቆ፣ የዛጉፍ፣ የእምቢልታ ድምፅ ሰምተው ይህ ምንድን ነው አሉ።

ሰዎችም ንጉሥ ለሴት ልጁ ሠርግ አዘጋጅቷል ወደ ንጉሡ ሠርግ ያልሔደውን እንዲቀጡት ንጉሥ አዟል አሏቸው። ይህንን ሰምተው አቤኔስና ቅዱስ ቶማስ ወደ ሠርጉ ሔዱ ሁሉም ሲበሉና ሲጠጡ ሐዋርያ ቶማስ ምንም አልቀመሰም በዚያም ዕብራዊት የሆነች አዝማሪ አለች ። በሠርጉ ምሳ ላይ ከሚያገለግሉ ውስጥ አንድ ሰው ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስን በጥፊ ፊቱን ጸፋው ሐዋርያውም በዕብራይስጥ ቋንቋ ይቺን እጅ ውሾች ሲጎትቷት አያታለሁ አለ አዝማሪዋም ብቻዋን ሰማችው።

ይህም በጥፊ የመታው ውኃ ሊቀዳ ወደ ውኃ ጉድጓድ ወረደ አንበሳም መጥቶ ገደለውና በታትኖ ተወው አንድ ውሻም የቀኝ እጁን ይዞ ወደ ምሳ መካከል ወሰዳት ከዚያ ያሉትም ማን ነው የሞተ አሉ ሰዎችም ይህን እንግዳውን በጥፊ የመታው ያ አሳላፊ ነው አሏቸው። አዝማሪዋም በሰማች ጊዜ ወደ ሐዋርያው ሒዳ በአጠገቡ ቁማ በጥፊ የመታችኝን እጅ ውሾች ሲጎትቷት አያታለሁ ሲል እኔ ስምቼዋለሁ አለች በዚያ ያሉትም ሁሉ ይህን ሰምተው አደነቁ።

ይህም ነገር በንጉሡ ዘንድ በተሰማ ጊዜ ንጉሡ ወደ ሐዋርያው መጥቶ ዛሬ አጋብቻታለሁና ና በልጄ ላይ ጸሎት አድርግ አለው። ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስም ወደ ጫጒላ ቤት ገብቶ ስለ ሙሽሮቹ ወደ #ጌታችን ጸለየ የሃይማኖትንም ቃል አስተምሮ ባረካቸው በሐዋርያውም ቃል አመኑ ። #ጌታችንም ደግሞ በቶማስ አምሳል ተገልጦላቸው እርሱም ሃይማኖትን አስተማራቸው እነርሱም አመኑበት ጽምረታቸውንም ትተው ድንግልናቸውን ጠበቁ ንጉሥም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አመነ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

#መስከረም_18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን
2.አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ
3.ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
4.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
5.ቅድስት እሌኒ ንግሠት
6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ መርቆሬዎስ ካልዕ (ሰማዕት)
8.ቅዱስ ቶማስ ሰማዕት
9.ቅዱስ ኤፍሬም ሰማዕት
10.አባ ፊልሞስ
11.ቅዱስ ሰልሖን ሰማዕት
12.ቅዱስ አክሳኤልስ ሰማዕት
13.ቅዱስ ይስሐቅ ሰማዕት
14.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀሲስ
15.ቅዱስ ነኪጣ ሰማዕት
16.አባ ፊላታውዎስ መንክራዊ
17.አባ ኖብ ባሕታዊ
18.አባ አትናቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት
19."60" ሰማዕታት (ማሕበረ ቅዱስ አቦሊ)
20.ሊቁ አባ ዳንኤል (ኢትዮጵያዊ)

#ወርሐዊ_በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)

" እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም #ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም . . . መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: " (ማቴ. 5:13-16)

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር


(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_18)
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ መጽሐፍ፦ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና።
¹² በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤
¹³ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።
¹⁴ እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?
¹⁵ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ?
¹⁶ ነገር ግን ሁሉ ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ምስክርነታችንን ማን አመነ? ብሎአልና።
¹⁷ እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።
¹⁸ ዳሩ ግን፦ ባይሰሙ ነው ወይ? እላለሁ። በእውነት፦ ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።
¹⁹ ነገር ግን፦ እስራኤል ባያውቁ ነው ወይ? እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ፦ እኔ ሕዝብ በማይሆነው አስቀናችኋለሁ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣችኋለሁ ብሎአል።
²⁰ ኢሳይያስም ደፍሮ፦ ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፥ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ አለ።
²¹ ስለ እስራኤል ግን፦ ቀኑን ሁሉ ወደማይታዘዝና ወደሚቃወም ሕዝብ እጆቼን ዘረጋሁ ይላል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ፥
¹⁵ የጌታችንም ትዕግሥት መዳናችሁ እንደ ሆነ ቍጠሩ። እንዲህም የተወደደው ወንድማችን ጳውሎስ ደግሞ እንደ ተሰጠው ጥበብ መጠን ጻፈላችሁ፥ በመልእክቱም ሁሉ ደግሞ እንደ ነገረ ስለዚህ ነገር ተናገረ።
¹⁶ በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።
¹⁷ እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤
¹⁸ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁶ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።
²⁷ በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
²⁸ ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_18_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇

✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"አንተ ትኴንን ኃይለ ባሕር። ወአንተ ታረምሞ ለድምፀ ማዕበላ። አንተ አኅሠርኮ ለዕቡይ ከመ ቅቱል"። መዝ 88፥9-10።
"የባሕርን ኃይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ። አንተ ረዓብን እንደ ተገደለ አዋረድኸው፥ በኃይልህም ክንድ ጠላቶችህን በተንሃቸው"። መዝ 88፥9-10።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#መስከረም_18_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሉቃስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
⁹ ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ፦ የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።
¹⁰ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ዕፀ መስቀል፣ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ የአቡነ አኖሬዎስ፣ የቅዱስ መርቆሬዎስ የቅዱስ ሊቅ ያዕቆብና የቅድስት ጸበለ ማርያም የዕረፍት፣ የቅዱስ ቶማስ የተዓምር በዓልና የሁሉም ቅዱሳን በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_18 ቀን
#እናታችን_ቅድስት_ጸበለ_ማርያም በዓለ ዕረፍቷ፡- ቅድስት ጸበለ ማርያም ትውልዷ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት ቀሐ አካባቢ ነው፡፡ ወላጆቿ አባቷ እንድርያስና እናቷ መስቀል ክብራ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ በሃይማኖት በምግባር ኮትኮተው አሳደጓት፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተከስተ ብርሃን የተባለ ደገኛ ባሕታዊ ወደ አባቷ ቤት መጥቶ ባደረበት መንፈስ ቅዱስ ኀይል የቅድስት ጸበለ ማርያምን ጸጋ አወቀ፡፡
ለወላጆቿም ‹‹ይኽቺ ልጅ ወደፊት ነፍሳት የሚድኑባት የከበረች ትሆናለች›› ብሎ በእርሷ ላይ ትንቢት ተናገረ፡፡

ቅድስት ጸበለ ማርያም ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ወላጆቿ በጋብቻ ሕግ እንድትወሰን ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ቅድስት ጸበለ ማርያም ‹‹ቅዱስ ጳውሎስ ለእግዚአብሔር አጭቶኛልና ፈጣሪዬን በድንግልና ለማገልገል ተስያለሁ›› በማለት ተቃወመቻቸው፡፡ ወደ አንድ ደገኛ ባሕታዊም ዘንድ ሄዳ በጸሎቱ ከዚህ ነገር እንዲያድናት ተማጸነችው፡፡ እርሱም ፈቃደ እግዚአብሔርን በጸሎት ከጠየቀላት በኋላ ማድረግ የሚገባትንና ወደፊት የሚገጥማትን ሁሉ ነገራት፡፡ እርሷም ለዕጣን እንዲሆን ጌጧን ሁሉ አውጥታ ሸጠችና ‹‹መሥዋዕቴን አሳርግልኝ›› ብላ ለባሕታዊው ሰጠችው፡፡ እርሱም ከጸለየላት በኋላ የጸሎቱን ምላሽ ነገራት፡፡

ወለጆቿም ያለፈቃዷ በሕግ ቢያጋቧትም ቅድስት ጸበለ ማርያም ግን በሌሊት ማንም ሳያያት ከጫጉላ ቤት ወጥታ ሄዳ በልዳው ፀሐይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ወደተሠራች ቤ/ክን ሄዳ እያለቀሰች ጸሎት አደረገች፡፡ እመቤታችንም ከሚካኤል ወገብርኤል እንዲሁም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተገለጠችላትና እንዲጠብቋት ነገረቻቸው፡፡ ቤተሰቦቿም እንዳያዝኑባት ፈርታ ተመልሳ ወደ ባሏ ዘንድ ብትገባም ባሏ በግብር እንዳያውቃት መላእክቱ ይጠብቋት ነበር፡፡ ባሏንም ሰውነቷ እንደእሳት ያቃጥለው ነበር፡፡ እርሱም አእምሮውን ከሳተ ከ3 ቀን በኋላ ሲነቃ የደረሰበትን ለቤተዘመዶቹ ባስረዳቸው ጊዜ ‹‹ከገዳም የመጣች ከሆነች ለእኛ ልትሆን አይገባም›› አሉና አስጊጠውና ሸልመው መልሰው ወደ ቤተሰቦቿ ላኳት፡፡

አባቷም ዳግመኛ ወደባሏ እንድትመለስ በማስገደድ ብዙ አሰቃቂ ግርፋት ቢገርፋትም በተአምራት ምንም እንዳላገኛት ሆነች፡፡ ከዚኽም በኋላ ወጥታ ወደ ምድረ በዳ ሄደች፡፡ ወደ ገዳምም ሄዳ ዋሻ ውስጥ ገብታ ስትጸልይ አድራ አረፍ ስትል ነብር መጥቶ የእግሯን ትቢያ ይልሳት ነበር፡፡ ከዚያም ወጥታ ንህበት ወደሚባል ሀገር መጥታ ቶማስ ከሚባል መነኩሴ ጋር በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ ቆማ ስትጸልይ እንባዋ መሬቱን ያርስ ነበር ነገር ግን ሰው እንዳያውቅባት አፈር በላዩ ትጨምርበታለች፡፡ በአንድ ዕለትም በቤ/ክ ቆማ ስትጸልይ በሁለቱ ማዕዘን የተቀበሩ ምውታን ሲጮኹ ሰማቻቸው፣ እነርሱ ግን በሲኦል ነበሩ፡፡ ጩኸታቸውንም በሰማች ጊዜ በእንባዋ ላይ እንባን በጸሎቷም ላይ ጸሎትን ጨምራ ስለእነርሱ ለመነች፡፡ ስለእነርሱም ሱባኤ ያዘች፡፡ በባሕርይው ቸርና ይቅርባይ የሆነ ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ
እነዚያን ነፍሳት ማረላት፡፡

ቅድስት ጸበለ ማርያም በምግባርና በትሩፋት በጾም በጸሎት ጸንታ ከኖረች በኋላ የምንኩስና ቀንበርን ትሸከም (በመንናኔ ትኖር) ዘንድ በብሕትውና ወደሚኖረው ታላቁ አባት ወደ አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ ዘንድ ሄደች፡፡ እርሱም ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር የደረሰው ነው፡፡

አቡነ ገብረ ማርያምም ካስተማራት አመነኮሳትና በኋላ ስሟን ‹‹ጸበለ ማርያም›› ብሎ ሰየማት፡፡ ከዚኽም በኋላ ተጋድሎዋን እጅግ በማብዛት ትሕርምትን ገንዘብ አደረገች፡፡ ከዕንጨት ፍሬዎች ውጭ የማትመገብ ሆነች፡፡ በተቀደሰችው የጌታችን 40 ጾም ወራት ግን ከሰንበት በቀር እርሱንም ፈጽሞ አትቀምስም፣ እስከ ፋሲካም ድረስ ከበዓቷ ስለማትወጣ ማንም አያያትም ነበር፡፡ ከመነኮሰችም ጊዜ ጀምሮ በጎኗ ተኝታ አታውቅም፡፡ ባመማት ጊዜም ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፡፡ በውርጭ ቅዝቃዜ መከራን እየተቀበለች በባሕር ውስጥም ቆማ እየጸለየች ታድራለች፡፡ በስግደቷም በቀን እስከ 8 እልፍ ትሰግድ ነበር፡፡ ከወንድሟ ቶማስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ተማረች፡፡ የዮሐንስን ወንጌልና የራእዩን መጽሐፍ ዘወትር በማንበብ ትጸልያለች፡፡ የእመቤታችን በዓል በሆነ ጊዜ አርጋኖን ውዳሴዋን በቀን ሦስት ጊዜ ታነባለች፣ አንቀጸ ብርሃንንም በየሰባቱ ጊዜ ትጸልያለች፡፡ የዳዊትንም መዝሙር በፈጸመች ጊዜ የጌታችንን መከራ ግርፋት እያሰበች ራሷን ሺህ ጊዜ ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም አገዛዛቸው መልካም ይሆን ዘንድ ስለ ጳጳሱና ስለ ንጉሡ አንድ አንድ ሺህ ጊዜ፣ ስለ መነኮሳትም ሺህ ጊዜ፣ ስለኃጥአንም ሺህ ጊዜ ራሷን ትገርፋለች፡፡ ዳግመኛም ነጭ ዕጣን በእጇ ይዛ ሰባት ቀን እስኪሆን ድረስ ዕንባዋን ታፈስበታለች፣ ያም ነጭ ዕጣን ከዕንባዋ ብዛት የተነሣ ጥቁር ይሆናል፡፡ በዓል በሚሆንበት በሰባተኛው ቀን አስቀድማ ዐውቃ በመሠዊያ ያሳርገው ዘንድ ያን ዕጣን ለቄሱ ትሰጠዋለች፡፡ እግዚአብሔርም እንደሱራፌል የጽናሕ መዐዛና እንደኪሩቤል ዕጣን ሽታ አድርጎ ከቄሱ እጅ ሲቀበል በግልጽ ታያለች፡፡

ቅድስት እናታችን እሾህ ያለው የብረት ዛንዠር በወገቧ ትታጠቃለች፡፡ በወገቧና በጭኖቿ ያሰረችው ርጥብ የላም ቁርበት ከአጥንቶቿ ጋር ይጣበቃል፡፡ በደረቀም ጊዜ ሥጋዋ እየተቆራረጠ ይወድቃል፣ በምድርም ውስጥ ትቀብረዋለች፡፡ አምስት ጊዜም እንደዚህ እያደረገች ራሷን ጎዳች፣ ከዳነም መልሳ ታቆስለዋለች፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገለጠላትና ‹‹ወዳጄ ጸበለ ማርያም ሆይ! ሰላም ለአንቺ ይሁን›› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእንዲህ ያለ የቁስል መከራ መሠቃየት ይበቃሻል›› ካላት በኋላ ተሰወረ፡፡ እርሷ ግን ሰባት ጊዜ እስኪሆናት ድረስ ይህንን አደረገች፡፡ በዚህም ጊዜ ሥጋዋ እጅግ ታመመ፡፡ ሥጋዋ እንደ ድንጋይ ደርቆ ቢቀር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደተላለፈች ዐውቃ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ተወች፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅድስት ጸበለ ማርያም እየጸለየች ሳለ የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቆሰለ ችግረኛ ደሃ ሰው ተመስሎ ለቅድስት ጸበለ ማርያም ተገልጦ ወደ እርሷ በመምጣት ቁራሽ እንጀራ ለመናት፡፡ እርሷም ፈጥና ይዛ መጥታ ሰጠችው። እንጀራውንም ተቀብሎ ሲያበቃ ‹‹በመንገድ ብዛት ደክሜአለሁና በጀርባሽ አዝለሽ ትሸኚኝ ዘንድ እወዳለሁ›› አላት፡፡ እርሷም ለድሆች አዛኝ ናትና አዝላው የድንጋይ መወርወሪያ ያህል እንደወሰደችው ቁስሉ ይድን ጀመር፡፡ ወዲያውም ቁስሉ ድኖ ምንም እንዳላገኘው ፍጹም ደህነኛ ሰው ሆነ፡፡ ያንጊዜም ፊቱ እንደፀሐይ አበራ፣ ሁለንተናውም ተለወጠ፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ከጀርባዋ ወርዶ በፊት ለፊቷ ቆመና ‹‹የከበርሽ አገልጋዬ ጸበለ ማርያም ሆይ! ምን እንዳድርግልሽ ትወጃለሽ?›› አላት፡፡ እርሷም ከድንጋጤዋ የተነሣ እንደበድን ሆና መሬት ላይ ወደቀች፡፡ ጌታችንም አበረታትና እጇን ይዞ አነሣትና ‹‹የልብሽን መሻት ለምኚኝ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላኬ ሆይ ! በፊትህስ ሞገስ ካገኘሁ በሲኦል ያሉ ነፍሳትን ይቅር በላቸው›› አለችው፡፡ በዚኽም ምክንያት በጌታችን ቸርነትና በእርሷም አማላጅነት ብዙ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ ጌታችንም ሰላምታ ሰጥቷት በክብር ዐረገ፡፡