ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#ጥቅምት_14

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ተሰወሩ፣ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የቴዎዶስዮስ ልጅ #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ አረፈ፣ ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ አንዱ #ቅዱስ_ሐዋርያ_ፊልጶስ አረፈ፣ ከሮሜ ሀገር የሆነ የከበረ የእግዚአብሔር ሰው #ሙሽራው_ቅዱስ_ሙሴ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቁ_አቡነ_አረጋዊ

ጥቅምት ዐሥራ አራት በዚህች ቀን ታላቁና የከበረው አባታችን አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) የተሰወሩበት ነው።

እኚህ አባት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ
አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉስ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግስት እደና ይባሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድርያ ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኩሚስ በፈቃደ #እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓረገ ምንኩስና ሰጥተዋቸዋል፡፡

የንጉሳዊ የቅንጦት ኑሮ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኩስና ተወስነዋል፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ ማዕረግ አበ መነኮሳት ሆነው ተመርጠዋል።

በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችን ኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም ከአባ ፍሬምናጦስ በኋላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ተሸክሞ አክሱም አድርሷቸዋል፡፡

ተመልሰውም ሄደው ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መስክረዋል፡፡ ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱም ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡

አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀ መዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሰዋል፡፡

ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/91፥11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡

ወዲያው ሃሌ ሉያ ለ #አብ ሃሌ ሉያ ለ #ወልድ ሃሌ ሉያ ለ #መንፈስ_ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላም ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡

ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁ ብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት ሾመውላቸው በዚህች ዕለት በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ ተሰውረዋል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ

በዚህችም ቀን ዳግመኛ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የቴዎዶስዮስ ልጅ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቴዎዶስዮስ #እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው ሚስቱም በጎ የምትሠራ #እግዚአብሔርንም የምትፈራ ናት ስሟም መርኬዛ ነው። እነርሱም ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ነበር ወደ ኢየሩሳሌምም ሒደው ስእለትን ተሳሉ ቸር መሐሪ ወደሆነ #እግዚአብሔርም ለመኑ እርሱም ልመናቸውን ተቀበሎ ይህን ያማረ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም አብደልመሲህ ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም ገብረ ክርስቶስ ማለት ነው ። የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ የሥጋዊንም ትምህርት አስተማሩት ።

አድጎ በጕለመሰም ጊዜ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ አጭተው እንደ ሥርዓቱ አጋቡት ከሌሊቱ እኩሌታም በሆነ ጊዜ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ተነሥቶ ወደሙሽራዪቱ ገባ እጅዋንም ይዞ ከእርስዋ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ ። ከዚያም የሃይማኖት ጸሎት በአንድ አምላክ እናምናለን የሚለውን እስከ መጨረሻ ጸለየ የተሞሸረበትንም ልብስ ከላዩ አውልቆ የግምጃ ልብስን ለበሰ ወደ ሙሽሪቷም ሒዶ ራስዋን ሳማት እንዲህም እያለ ተሰናበታት #እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኑር ከሰይጣን ሥራ ሁሉ ያድንሽ ። እርሷም አልቅሳ ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ ለማንስ ትተወኛለህ አለችው እርሱም በ #እግዚአብሔር ዘንድ እተውሻለሁ እኔም #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ የአባቴ መንግሥት አላፊ ነውና አንቺም መሐላሽን አስቢ አላት ያን ጊዜ መሐላዋን አስባ ዝም አለች ።

ለሠርጉም የታደሙት ሁሉ እንደተኙ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ወደ ባሕርም ዳርቻ ደርሶ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞችን አገኘ የዓመት መንገድ ወደሚሆን አርማንያም እስከሚደርስ ከእነርሱ ጋር ተጓዘ ።

ነግቶ ወደ ሠርጉ አዳራሽ አባትና እናቱ በገቡ ጊዜ ሙሽራውን ልጃቸውን አላገኙትም ሙሽሪትንም ልጃችን ወዴት አለ ብለው ጠየቋት እርሷም እንዲህ አለቻቸው ። በሌሊት ወደ እኔ ገባ መሐላን አማለኝ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ ራሴንም ስሞኝ ከእኔ ዘንድ ወጣ እኔም እያለቀስኩ ብቻዬን አደርኩ ነገርዋንም ሰምተው ወድቀው በመጮህ ታላቅ ልቅሶን አለቀሱ ።

በዚያችም ጊዜ በሀገሮች ውስጥ ሁሉ ልጁን ገብረ ክርስቶስን ይፈልጉት ዘንድ ንጉሡ አምስት መቶ አገልጋዮቹን ላከ ለድኆችና ለምስኪኖችም ምጽዋት አድርገው የሚሰጥዋቸውን ብዙ ገንዘብን ሰጣቸው ።

ገብረ ክርስቶስ ግን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል #ማርያም ስም በአርማንም አገር በተሠራች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ደጅ የሚኖር ሆነ ። አባቱ የላካቸውም ሁለቱ አገልጋዮች ከዚያ ደርሰው ስለርሱ መረመሩ ግን ወሬውን ማግኘት ተሳናቸው ለድኆችም ምጽዋትን ሰጡ እርሱም ከድኆችም ጋር ምጽዋትን ተቀበለ ።

በዚያም ዐሥራ አምስት ዓመት ከኖረ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም ለአንድ ቄስ ተገለጸችለት ቦታውንም አመልክታ እንዲህ አለችው ። የ #እግዚአብሔር ሰው ገብረ ክርስቶስን ይዘህ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስገባው ከውጭ አትተወው ቄሱም #እመቤታችን እዳዘዘችው አደረገ ።

ከዚህም በኋላ የተመሰገነ ገብረ ክርስቶስ በሌሊት ተነሣ ከ #እመቤታችንም ሥዕል ፊት ቁም ጸለየ እንዲህም አላት እመቤቴ ሆይ የተሠወረ ሥራዬን አንቺ ለምን ገለጥሽ አሁንም ወደሚሻለኝ ምሪኝ ይህንንም ብሎ የ #እመቤታችንን ሥዕሏን ተሳልሞ በሌሊት ወጥቶ ወደ ባሕሩ ወደብ ደረሰ ወደሌላ ሀገርም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ተሳፈረ። ግን በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ከአባቱ አገር ደረሰ የአባቱና የእናቱም ባሮች እየናቁትና እየሰደቡት በአባቱ ደጅ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ ።
ሲገቡና ሲወጡም ሽታው እንዳያስጨንቀን ይህን ምስኪን አስወግዱልን ይላሉ ወጭትና ድስትም አጥበው በላዩ ይደፉበ፨ታል ውሾችም እንዲናከሱበትና እንዲበሉት የሥጋ ትርፍራፊ ይጥሉበታል ውሾች ግን ቁስሉን ይልሱለት ነበር እንደዚህም አብዝተው አሠቃዪት ።

ከዚህም በኋላ ወደ #እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ለመነ #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ ለአባቴና ለእናቴ ባሮች በደል እንዳይሆንባቸው ወዳንተ ውሰደኝ ። በዚያንም ጊዜ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው ። ከዚህም በኋላ ገድሉን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጻፈ በእጁም ጨብጧት አረፈ ።

በእሑድ ቀንም ሕዝቡ ሁሉና ካህናቱ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር በቅዳሴ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሳሉ የ #እግዚአብሔርን ሰው በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ቤት ፈልጉት የሚል ቃል ከሰማይ ሰሙ በዚያን ጊዜ ሔደው በአረፈበት ቦታ አገኙት። በእጁም ውስጥ የተጨበጠ ክርታስን አዩ ሊወስዷትም ሽተው መውሰድ ተሳናቸው ።

በአንድነትም በጸለዩ ጊዜ እጁ ተፈትታ ወስደው አነበቧት አባትና እናቱም ልጃቸው እንደሆነ አወቁ ታላቅ ጩኸትም ሆነ መሪር ልቅሶንም አለቀሱ አክብረውም ቀበሩት መቃብሩም በሽተኞችን ሁሉ በመፈወስ ድንቆች የሆኑ ብዙ ተአምራትን የሚያደርግ ሆነ ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ፊልጶስ_ሐዋርያ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስ አረፈ። #ጌታችንም በቂሣርያ አገር ውስጥ በአለፈ ጊዜ በውስጧ አስተማረ ትምህርቱንም ሰምቶ ክብር ይግባውና #ጌታችንን አምኖ ተከተለው ከሰባ ሁለቱ አርድእትም ጋር ተቆጠረ ።

#ጌታችንም ይሰብኩ ዘንድ ሁለት ሁለት አድርጎ በላካቸው ጊዜ ከእርሳቸው አንዱ ይህ ደቀ መዝሙር ነው ። ከ #መድኃኒታችንም ዕርገት በኋላ ሐዋርያት ከሾሟቸው ከሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የተቆጠረ ነው ። እርሱም ወደ ሰማርያ ወርዶ አስተማረ ብዙዎችንም አሳምኖ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ። ከዚህም በኋላ የተጎዳውን ሥራየኛ ሲሞንንም አጥምቆት ነበር እርሱ የ #መንፈስ_ቅዱስን ጸጋ በገንዘብ ሊገዛ አስቧልና ።

ከዚህም በኋላ ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ይሔድ ዘንድ #መንፈስ_ቅዱስ ፊልጶስን አዘዘው በሔደም ጊዜ ለኢትዮጵያ ንግሥት ለህንደኬ በጅሮንዷ የሆነ ጃንደረባውን አገኘው እርሱም እንደ በግ ሊታረድ መጣ የሚለውን የነቢይ ኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር ።

ቅዱስ ፊልጶስም ጃንደረባውን የምታነበውን ታስታውለዋለህን አለው ። ጃንደረባውም ያስተማረኝ ሳይኖር እንዴት አውቃለሁ አለ ። ቅዱስ ፊልጶስም ስለ #ጌታችን ስለ መከራው ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት ስለሆነው ሞቱ እንደተነገረ ተረጐመለት ። ጃንደረባውም #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የሕያው #እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አመነ ያን ጊዜም በ ቅዱስ ፊልጶስ እጅ ከወንዝ ውኃ ውስጥ ተጠመቀ ከውኃውም በወጡ ጊዜ #መንፈስ_ቅዱስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም ።

ቅዱስ ፊልጶስም ወደ አዛጦን ከተማ ደረሰ እያስተማረም እስከ ቂሣርያ ሔደ በከተማዎች ሁሉ በመዞር ወንጌልን ሰበከ ከአይሁድና ከሳምራውያንም ብዙዎችን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ወደ ማመን መልሶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ። ለሐዋርያ ቅዱስ ፊልጶስም ከእርሱ ጋር ወንጌልን የሚሰብኩ አራት ሴቶች ልጆች ነበሩት ። አገልግሎቱንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በቅዱስ ፊልጶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሙሴ_ሙሽራው

በዚህችም ቀን ከሮሜ ሀገር የሆነ የከበረ የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴ አረፈ ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አውፊምያኖስ የእናቱ ስም አግልያስ ነው እነርሱም #እግዚአብዘሔርን የሚፈሩ እጅግም ባለጸጎች ናቸው ። አብዝተውም ይመጸውታሉ ሁልጊዜም ይጸልያሉ እስከ ዘጠኝ ሰዓትም ይጾማሉ ድኆችንና ችግረኞችንም ሳይይዙ አይበሉም ።

ነገር ግን ልጆች የሏቸውም ነበር የ #እግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ #እግዚአብሔርን ይለምኑት ነበር #ጌታችንም ልመናቸውን ተቀብሎ ይህን መልኩ እጅግ ያማረ የከበረና የተባረከ ልጅን ሰጣቸው በወለዱትም ጊዜ በርሱ ደስ ብሏቸው ለድኆችና ለምስኪኖች ታላቅ ምሳ አደረጉ ስሙንም #ሙሴ ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም የ #እግዚአብሔር ሰው ማለት ነው ስለእርሱ #እግዚአብሔር ልመናቸውን ሰምቷልና ።

ከዚህም በኋላ ሙሴን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት መንፈሳዊና ሥጋዊ ትምህርትን ጥበብን ሁሉ አስተማሩት ። አድጎም በጎለመሰ ጊዜ አባቱ አውፊምያኖስ ሚስቱ አግልያስን እነሆ ልጃችን ሙሴ አደገ ሚስትን ልናጋባውና በጋብቻውም ደስ ሊለን ለእኛ ይገባናል አላት ። የሙሴ እናት አግልያስም ሰምታ በዚህ ነገር ደስ አላት ከሮሜ አገር ታላላቆች ሰዎች ወገንም መልኳ እጅግ ያማረ አንዲት ብላቴና አጋቡት ። ታላቅ ሠርግንም በማዘጋጀት ሸልመው አስጊጠው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጋብቻ ሥርዓት አክሊላትን አቀዳጇቸው ። ከዚህ በኋላ #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙንም ተቀብለው ወደሚሠረጉበት ቤት ገቡ ።

ከዚህም በኋላ በማግሥቱ አውፊምያኖስ ሚዜውን ጠርቶ እንዲህ አለው ሙሽራው ወደ ሙሽሪቷ ገብቶ የጋብቻውን ሕግ እንዲፈጽም ንገረው ያ ሚዜውም በነገረው ጊዜ ወደ ሙሽራዪቷ ገባ ድንቅ የሆነ ውበቷንና ደም ግባቷን ተመለከተ በልቡም አስቦ እንዲህ አለ ይህ ሁሉ ውበትና ደም ግባት አላፊ ጠፊ አይደለምን ። ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያዊት መንግሥቱ የሚደርስበትን መንገድ እንዲመራው #እግዚአብሔርን ለመነው ።

ሙሽራዪቱንም እንዲህ አላት የተባረክሽ እኅቴ ሰላም ይሁንልሽ የ #እግዚአብሔርም ፍቅር አንድነት ከአንቺ ጋር ይኑር ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ዘንድ እስከምንገናኝ ደኅና ሁኚ ። ይህንንም በሚላት ጊዜ ልብሶቹን አውልቆ ሰጥቷት ከእርሷ ዘንድ ወጣ የተሞሸረበትንም ልብስ ለውጦ ከባሕር ዳርቻ እስከሚደርስ መንገዱን ተጓዘ ።

ልብሶቹንም ሁሉ ሽጦ ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ሰጠ እርሱም ጨርቅ በመልበስ እንደ ድኃ ሁኖ ቁራሽ እንጀራ እየለመነ በየጥቂቱ እየተመገበ እስከ ሀገረ ሮሀ ድረስ ሔደ ።

ከዚያም በደረሰ ጊዜ ወደቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ለሮሀ ንጉሥ ለአቃርዮስ በስብከቱ ወራት የተላከለትን ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ሥዕልና የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል #ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ከሥዕሎቹ ተሳልሞ በረከትን ተቀበለ ወደ ልዑል #እግዚአብሔርም ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ ። ወጥቶም ኑሮውን ከድኆችና ከምስኪኖች ጋር አደረገ ።

ከዚህም በኋላ መጸለይና መጾምን ጀመረ እስከ ምሽትም ይጾማል በቀንና በሌሊትም ጸሎቱን አያቋርጥም ምጽዋትንም ከድኆች ጋር ተቀብሎ እርሱ መልሶ ለሌሎች ይሰጣል ።
በዚያቺም ዕለት በነጋ ጊዜ ወደ ሠርጉ አዳራሽ አባትና እናቱ ሲገቡ ሙሽራው ልጃቸው ሙሴ በጫጉላው ቤት እንደ ሌለ ሰሙ ደስታቸውም ወደ ኀዘን የሠርጉም ዘፈን ወደ ልቅሶ ወደ ዋይታ ተለወጠ ።

ከዚህም በኋላ አውፊምያኖስ ባሮቹን ጠርቶ ብዙ ገንዘብን ሰጣቸው እንዲህም አላቸው ልጄን እስከምታገኙት ድረስ ሁለት ሁለት እየሆናችሁ ወደ ሀገሩ ሁሉ ሒዱ ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ስጡአቸው ። እነርሱም በሀገሩ ሁሉ ተበታተኑ ። ከአባቱ አገልጋዮችም ሁለቱ አገኙት ግን አላወቁትም ምጽዋትንም ከድኆች ጋር ሰጡት ቅዱስ ሙሴም አውቋቸው እንዲህ ብሎ አመሰገነ #ጌታዬ_ፈጣሪዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ሆይ ስለ አንተ ፍቅር ከአባቴ ባሮች እጅ ምጽዋትን እቀበል ዘንድ ለዚህ ታላቅ ክብር አድለህኛልና አመሰግንሃለሁ ።

የአባቱ አገልጋዮችም ብዙ ወራት በሁሉ አገሮች ሲዞሩ ኑረው ወደ አውፊምያኖስ ጌታቸው ተመለሱ ። የ #እግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ሙሴም ከሰንበት ቀኖች በቀር እህልን የማይቀምስ እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውን በመጨመር በየሁለትና በየሦስት ቀኖች የሚጾም ሆነ ።

ከዚህም በኋላ እመቤታችን የከበረች ቅድስት ድንግል #ማርያም ከዚያች ቤተ ክርስቲያን ካህናት ውስጥ ለአንድ ደግ ጻድቅ ቄስ ተገልጻ እንዲህ አለቸው በጥዋት ወደ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ውጣ ከምሰሶ አጠገብ ብቻውን ቁሞ የሚጸልይ ሰው ታገኛለህ የ #እግዚአብሔር ሰው ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ በለው በውጭ አትተወው ጾሙ ጸሎቱ በ #እግዚአብሔር ፊት መዓዛው ጣፋጭ እንደሆነ ዕጣን ተቀባይነትን አግኝቷልና ።

ሲነጋም ያ ቄስ ወደ ቅዱስ ሙሴ ሒዶ የ #እግዚአብሔር ሰው ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ አለው ሙሴም አባቴ ሆይ በከበረ ቦታ ላይ መቆም የማይገባኝ ኃጢአተኛ ነኝና ተወኝ አለው ቄሱም ወደ ቤተ መቅደስ አስገባህ ዘንድ ከቅድስት ድንግል እመቤታችን #ማርያም ወዳንተ ተልኬአለሁ ብሎ መለሰለት ወደ ቤተ መቅደስም ያስገባው ዘንድ እንዳዘዘችው ነገረው ከዚህም በኋላ አስገባው ።

ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴ ወደ ሀገረ ጠርሴስ ይሔድ ዘንድ አስቦ እርሷም የሐዋርያው ጳውሎስ አገር ናት እንዲህም አለ እስከ ዕለተ ሞቴ በውስጥዋ እኖራለሁ ሥጋው ምንም በሮሜ አገር የሚኖር ቢሆንም የትውልድ አገሩ ናትና በረከትን እቀበላለሁ ብሎ ነው ።

በሌሊትም ወጥቶ ወደ ባሕር ዳርቻ ሔደ ወደ ጠርሴስም ይሔድ ዘንድ በመርከብ ተጫነ በባሕር መካከልም ታላቅ ነፋስ ተነሣባቸው ባሕሩም ከነፋሱ ኃይል የተነሣ ታወከ ወደየትም እንደሚሔዱ አያውቁም ነበር ቀኑ ጨልሞባቸዋልና ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት ወደ #እግዚአብሔር ለመኑ በዚያንም ጊዜ ባሕሩ ጸጥ ብሎ ታላቅ ደስታ ሆነ ብርሃንም ታየ ወደ ሮሜ ሀገር ወደብም እንደ ደረሱ አወቁ ።

ቅዱስ ሙሴም ተነሥቶ በመርከብ ውስጥ ያሉትን በሰላምታ ተሰናብቷቸው ጉዞውን ጀመረ በልቡም እንዲህ አለ ይህ ሁሉ በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ እንግዲህ እስከ ዕለተ ሞቴ ራሴን ለማንም እንዳልገልጥ ሕያው #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስን የሚያውቀኝ የለምና በአባቴ ደጅ እኖራለሁ ይህንንም ብሎ ወደ አባቱ ቤት ተጓዘ ።

በመንገድም ላይ አባቱን ተገናኘው ብዙ ሰውም ተከትሎት ነበር የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴም ቀረብ ብሎ አባቱ የተቀመጠበትን ፈረስ ልጓሙን ያዘ እንዲህም አለው #እግዚአብሔር የባረከህ ያከበረህ አንተ ደግ ሰው #እግዚአብሔርም ኃጢአትህን ይቅር ይበልህ የልብህንም ልመና ይስጥህ እኔም መጻተኛ ድኃ ሰው እንደ ሆንኩ እወቅ ለመጻተኛነቴና ለችግረኛነቴ የምትራራ ሁነህ ከማዕድህ ፍርፋሪ ልትመግበኝ ከወደድህ መኖሪያዬን በቤትህ አንጻር በደጃፍህ አድርግልኝ ዋጋህንም የሚሰጥህ #እግዚአብሔር ነውና ።

በዚያንም ጊዜ አውፊምያኖስ የልጁ የሙሴን ስደት አስታውሶ በተቃጠለ ልብ አለቀሰ መኖሪያውንም በቤቱ ደጅ እንዲሠሩለት አዘዘለት። ሁለተኛም ከአገልጋዮቹ አንዱን በሚያሻው ነገር ሁሉ እንዲአገለግለው አዘዘው ።

#እግዚአብሔር ሰው ሙሴም ያን የሚያገለግለውን ወንድሜ ሆይ ከሰንበት ቀኖች በቀር መብልና መጠጥ እንዳታመጣልኝ እለምንሃለሁ ይኸውም ከ ቅዱስ_ቁርባን በኋላ ግማሽ እንጀራና የጽዋ ውኃ ብቻ ነው አለው ። በጾምና በጸሎትም እየተጋደለ በዚያ በአባቱ ደጅ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ ።

ሰውን የሚወድ ቸር #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው ወዶ ተገለጠለት እንዲህም አለው የመረጥሁህ አንተ ብፁዕ ነህ አንተ ፈቃዴን ፈጽመሃልና በዚህ ዓለም ከደስታ ኃዘንን ከብልጽግና ድኅነትን መርጠሃልና እኔም የማይጠፋ ብልጽግናን እሰጥሃለሁ ዳግመኛም ስምህን የሚጠራ መታሰቢያህንም ለሚያደርግ የተራበውን ለሚያጠግብ የተጠማውን ለሚያጠጣ የተራቈተውን ለሚያለብስ ገድልህንም ለሚጽፍ ወይም ለሚያጽፍ ስለ ስምህ በጎ ሥራ ሁሉ ለሚሠራ ቃል ኪዳንን ሰጠሁህ ። በሰማያዊት መንግሥትም በጎ ዋጋን እሰጠዋለሁ ተጠራጣሪ ካልሆነ በዚህ ዓለምም እጠብቀዋለሁ ከበጎ ነገር ሁሉ ምንም አላሳጣውም ።

አሁንም ከአራት ቀን በኋላ እወስድሃለሁ ምርጦቼ ቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት ከአሉበትም አኖርሃለሁ ይህንንም ብሎ ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በታላቅ ክብር ዐረገ ።

ቅዱስ ሙሴም ከ #እግዚአብሔር ዘንድ ይህን ጸጋ በተሰጠ ጊዜ እጅግ ደስ አለው ያን የሚያገለግለውንም ወንድሜ ሆይ እንግዲህ ስለ እኔ ከመድከም ታርፋለህና ወረቀትና ቀለም አምጣልኝ አለው። ያ አገልጋይም ከአነጋገሩ የተነሣ አድንቆ ወረቀቱንና ቀለሙን አመጣለት የከበረ የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ገድሉን ሁሉ ጻፈ በአራተኛውም ቀን ያቺን የጻፋትን መጽሐፍ በእጁ ጨበጣት በእሑድ ቀንም በሰላም አረፈ ። ቅዱሳን መላእክት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት ለሚያገለግሉት የዘላለም ተድላ ደስታ ለሚሰጥ ለነበረና ለሚኖር ፈጣሪያችን ምስጋና ይሁን እያሉ ነፍሱን ተቀበሏት ።

ሕዝቡም ሁሉ በቅዳሴ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው እያሉ ከመሠዊያው በላይ የ #ጌታቸውን ሕጎቹንና ሥርዓቱን የሚያደርጉ ደጎች አገልጋዮች ባሮች የተመሰገኑ ናቸው እነርሱ ወደ ዘላለም ተድላ ደስታ ይገባሉና የሚል ቃልን ሲጮህ ሰሙ ።

ሊቀ ጳጳሳቱና ኤጲስቆጶሳቱ ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ሕዝብም ሁሉ በሰሙ ጊዜ በላያቸው ታላቅ ፍርሀት ወደቀባቸው ። የቅዳሴውም ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ይህን ምሥጢር ይገልጽላቸው ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር_ኢየሱስ_ክርስቶስ በመጸለይ ማለዱ በዚያንም ጊዜ የ #እግዚአብሔርን ሰው በአውፊምያኖስ ቤት ፈልጉት እነሆ እርሱ ነፍሱን በ #እግዚአብሔር እጅ ሰጥቷልና የሚል ቃልን ሰሙ ።

ሊቀ ጳጳሳቱም ይህን ነገር ሰምቶ አውፊምያኖስን ጠራውና ይህ ታላቅ ጸጋ በቤትህ ውስጥ ሲኖር በሕይወቱ ሳለ እንድንጎበኘው በረከቱንም እንድንቀበል ለምን አልነገርከንም አለው አውፊምያኖስም እንዲህ ብሎ መለሰ ክቡር አባት ሆይ ቅድስናህ ይመስክር ይህን የሚመስል በቤቴ ውስጥ እንዳለ አላወቅሁም ።

በዚያንም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ ከሁሉ ካህናትና ሕዝብ ጋር ተነሥቶ ወደ አውፊምያኖስ ቤት ሔደ የከበረ የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴንም በአረፈበት ቦታ አገኙት ክርታሱም በእጁ ውስጥ ነው ሊቀ ጳጳሳቱም ያቺን ክርታስ አንሥቶ የ #እግዚአብሔር ሰው ሙሴ የአውፊምያኖስ ልጅ እናቱም አግልያስ እስከሚለው ስሙ እስቲደርስ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አነበባት። እናትና አባቱም በሰሙ ጊዜ ደነገጡ መራር ልቅሶንም አለቀሱ ቤተሰቦቻቸውም ሁሉ ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ አጽናንቶ ጸጥ አደረጋቸው።
#ጥቅምት_17

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አስራ ሰባት በዚችም ዕለት የዲያቆናት አለቃ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ለተሾመባት ቀን መታሰቢያ ነው፣ የታላቁ ነቢይና ካህን ሳሙኤል እናት #ቅድስት_ነቢይት_ሐና የተወለደችበት ነው፣ ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ፊልያስ በሰማዕትነት ያረፈበት ነው፣ የከበረ #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ካልዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቀዳሜ_ሰማዕት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ

ጥቅምት አስራ ሰባት በዚችም ዕለት የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነ የከበረ እስጢፋኖስ ለተሾመባት ቀን መታሰቢያ ናት።

ለዚህም ለከበረ እስጢፋኖስ የ #እግዚአብሔርን ኃይልና ጸጋ የተመላ ሰው እንደነበረና በሕዝቡም መካከል ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ሥራን ይሠራ እንደነበረ የሐዋርያት ሥራ የተባለ መጽሐፍ ስለርሱ ምስክር ሆነ።

ከዚህም በኋላ አይሁድ ቀኑበት የሐሰት ምስክሮች የሚሆኑ ሰዎችንም አስነሡበት ይህን ሰው በሙሴና በ #እግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃልን ሲናገር ሰምተነዋል እንዲሉ ሐሰትን አስተማሩአቸው። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችን ጸሐፊዎችንም አነሣሡአቸው አዳርሱን ብለው ከበው እየጐተቱ ወደ ሸንጎ ወሰዱት።

የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት እነርሱም ይህ ሰው በቤተ መቅደስ ላይ በኦሪትም ላይ ስድብን ሲናገር ተው ብንለው እምቢ አለ። የናዝሬቱ #ኢየሱስ ቤተ መቅደሳችሁን ያፈርሰዋል ሙሴ የሰጣችሁን ኦሪታችሁንም ይሽራል ሲል ሰምተነዋል አሉ።

በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሁሉ ተመለከቱት ፊቱንም የ #እግዚአብሔርን መልአክ ፊት ሁኖ አዩት። ሊቀ ካህናቱም እውነት ነውን እንዲህ አልክ አለው። እርሱም እንዲህ አለ ወንድሞቻችንና አባቶቻችን ስሙ ወደ ካራን ከመምጣቱ አስቀድሞ በሶርያ ወንዞች መካከል ሳለ ለአባታችን ለአብርሃም የክብር ባለቤት #እግዚአብሔር ተገለጠለት። ካገርህ ውጣ ከዘመዶችህም ተለይ እኔ ወደማሳይህ ሀገርም ና አለው።

ከዚህም በኋላ ከከላውዴዎን ወጥቶ በካራን ተቀመጠ አባቱም ከሞተ በኋላ ዛሬ እናንተ ወደ አላችሁባት ወደዚች አገር አመጣው። ከዚህም በኋላ የግዝረትን ሥርዓት ሰጠው ይስሐቅንም በወለደው ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገዘረው እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን ገዘረው ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን ነገድ አባቶችን ገዘረ።

የቀደሙ አባቶቻችንም በዮሴፍ ላይ ቀንተው ወደ ግብጽ አገር ሸጡት #እግዚአብሔር ግን አብሮት ነበር። ከመከራው ሁሉ አዳነው በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ዕውቀትን መወደድን ሰጠው በግብጽ አገር ሁሉና በቤቱ ሁሉ ላይ ሾመው። ነገርም በማስረዘም በሰሎሞን እጅ እስከተሠራችው ቤተ መቅደስ ያለውን ተረከላቸው።

ከዚህም በኋላ ድምፁን ከፍ ከፍ አድርጎ እናንተም እንደ አባቶቻችሁ ዘወትር #መንፈስ_ቅዱስን የምታሳዝኑት ዐይነ ልቡናችሁ የታወረ ዕዝነ ልቡናችሁ የደነቈረ አንገተ ደንዳኖች አላቸው። አባቶቻችሁ ከነቢያት ያላሳደዱት ያልገደሉት ማን አለ እናንተ ክዳችሁ የገደላችሁትን የአምላክን መምጣት አስቀድመው የነገሩዋችሁን ገደላችኋቸው።

በመላእክት ሥርዓት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም። ይህንንም ሰምተው ተበሳጩ ልባቸውም ተናደደ ተነሣሣ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። በእስጢፋኖስም #መንፈስ_ቅዱስ አደረበት ሰማይም ተከፍቶ #ኢየሱስ_በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ የ #እግዚአብሔርን ክብር አየ። እነሆ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅም በ #እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ አያለሁ አለ።

ጆሮአቸውን ይዘው በታላቅ ድምፅ ጮኹ በአንድነትም ከበው ጐተቱት። እየጐተቱም ከከተማ ወደ ውጭ አውጥተው በደንጊያ ወግረው ገደሉት የገደሉትም ሰዎች ልብሳቸውን ሳውል ለሚባል ጐልማሳ ልጅ ያስጠብቁ ነበር። #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል እያለ ሲጸልይ እስጢፋኖስን በደንጊያ ወገሩት።

ዘለፍለፍ ባለ ጊዜም ድምፁን ከፍ አድርጎ አቤቱ ይህን ኃጢአታቸውን ይቅር በላቸው በደልም አታድርግባቸው ይህንንም ብሎ አረፈ። ደጋግ ሰዎችም መጥተው የእስጢፋኖስን ሥጋ ወስደው ቀበሩት ታላቅ ልቅሶም አለቀሱለት።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ነቢይት_ሐና

ዳግመኛም በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን ሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና ተወለደች።

ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት አለችው እርሷም ወላድ በመሆኗ ሐና ልጅ ስለሌላት መካንም ስለሆነች ሁልጊዜ ትገዳደራት ነበር።

ሐና ግን ፈጽማ በማዘን አትበላም አትጠጣም ባሏ ሕልቃናም ያረጋጋታል ማረጋጋቱንም አልተቀበለችውም በሊቀ ካህናቱ በኤሊ ዘመንም ወደ ቤተ #እግዚአብሔር ወጣች እያለቀሰችና እያዘነች በ #እግዚአብሔር ፊት ጸለየች እንዲህም ብላ ስለትን ተሳለች አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የሚያገለግል አደርገዋለሁ።

ካህኑ ኤሊም አያትና እርሷ የወይን ጠጅ ጠጥታ እንደ ሰከረች አሰበ እርሷ በዝምታ በልቧ ትጸልይ ነበርና በቊጣና በግሣጼ የወይን ጠጅ ጠጥተሽ ወደዚህ ወደ #እግዚአብሔር ቤት ለምን መጣሽ አሁን ሒጂ ስካርሺን በእንቅልፍ አስወግጂ አላት።

እርሷም እንዲህ አለችው የወይን ጠጅ ከቶ አልጠጣሁም ልጅ ያጣሁ በመሆኔ በልቤ አዝናለሁ እንጂ ካህን ኤሊም አጽናናት እንዲሁም ብሎ ባረካት የእስራኤል ፈጣሪ የለመንሽውን ይስጥሽ በሰላም ሒጂ በቃሉም አምና ወደ ቤቷ ገባች።

ከዚህም በኋላ ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ጡትንም በአስጣለችው ጊዜ ወደ #እግዚአብሔር ቤት ይዛው ወጣች ወደ ካህን ኤሊም አቀረበችውና እንዲህ ብላ አስረዳችው ከአሁን በፊት ልጅን ይሰጠኝ ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር ስጸልይና ስለምን ያየኸኝ ሴት ነኝ ልመናዬንም ሰምቶ ይህን ልጅ ሰጠኝ አሁንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለ #እግዚአብሔር አገልጋይ ይሆን ዘንድ አመጣሁት።

ከዚህም በኋላ ሐና #እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ልቤ በ #እግዚአብሔር አምኖ ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች። ይቺም በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ከሙሴ መኀልይ ቀጥላ ተጽፋለች።

ከዚህም በኋላ #እግዚአብሔርን አገልግላ በሰላም ጥቅምት 6 አርፋለች።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስቷ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ፊልያስ_ሰማዕት

ዳግመኛም በዚች ቀን የሀገረ ቀምስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ፊልያስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህንንም ቅዱስ በመኰንኑ ቊልቊልያኖስ ዘመን ወደ ፍርድ አደባባይ አቀረቡት ቊልቊልያኖስም ለአማልክት ሠዋ አለው። ፊልያስም እኔ ከብቻው #እግዚአብሔር በቀር ለአማልክት አልሠዋም አለ። ቊልቊልያኖስም #እግዚአብሔር ምን አይነት መሥዋዕት ይሻል አለ ቅዱስ ፊልያስም ቅን ትሑት የሆነ ንጹሕ ልቡናን ዕውነተኛ ፍርድን ቁም ነገርን እንዲህ ያለ መሥዋዕትን #እግዚአብሔር ይወዳል አለው።

ቊልቊልያኖስም የምትጋደል ስለ ነፍስ ነው ወይስ ስለ ሥጋ አለ ቅዱስ ፊልያስም ስለ ነፍስና ስለ ሥጋ ነው እነርሱ በአንድነት ይነሣሉና አለ። ቊልቊልያኖስም የምትወዳት ሚስት የምትወዳቸው ልጆች ወይም ወንድምና ዘመድ አለህን አለው ቅዱስ ፊልያስም ከሁሉም የ #እግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል አለ።
#ጥቅምት_19

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ #ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስስ እረፍቱ ነው፣ #ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ፣ ስለ #ጳውሎስ_ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ፣ የጸይለም አገር የከበረ አባት #ቅዱስ_ዮሐንስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስ

ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ፣ ፃድቅ ካህን፣ቤተ መቅደሱን በባህር ላይ ያነፀ መሀንዲስ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስስ እረፍቱ ነው።

ልክ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖትና እንደነ አቡነ ዜና ማርቆስ እርሱም ሲወለድ ወደ ምሥራቅ ዞሮ አምላኩን ያመሰገነ ሲሆን ቤቱም በብርሃን ተሞልቶ ታይቶ አዋላጆቹን ሁሉ አስገርሞ ነበር፡፡ ገና በእናቱ ማህፀን ሆኖ አጎቱ ጠንጠውድም በንግሥና ላይ ሳለ "ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል የወንድምህ ልጅ ነው" የሚል ንግርት ይሰማ ነበርና ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ›› መወለዱን ሲያውቅ ‹‹የወንድሜን ልጅ ዐየው ዘንድ አምጡልኝ›› ብሎ ላከ፡፡ ባየውም ጊዜ ደም ግባቱ እጅግ ያምር ስለነበር ‹‹ይህስ መንግሥቴን ይውረስ፣ በእውነት ልጄ ነው›› ብሎ ባረከው፡፡

ከእርሱ ጋር ስምንት ቀን ተቀምጦ በወለዳቸው ልጆቹ መካከል ሆኖ ሲጫወት በተመለከተው ጊዜ ግን በልቡ ሰይጣን አደረበትና በቅናት ሆኖ ‹‹እርሱ ነግሦ ልጆቼ ወታደሮቹ ሊሆኑ ነውን›› በማለት ይገድለው ዘንድ አሰበ፡፡ ሆኖም አማካሪዎቹ ‹‹ለጊዜው ምንም ስለማይረዳ ተወው ለወደፊቱም የንግሥና ምሥጢር እንዳያውቅ ወደ እናቱ ዘንድ መልሰውና በዚያ ከብት ሲያግድ ይደግ››ስላሉት ወደ እናቱ ላከው፡፡ እርሷ ግን በጥበብና በብልሃት አስተዋይ አድርጋ አሳደገችው። ይህንንም ሲሰማ ሊገድለው አሽከሮቹን ላከ፡፡ እናቱም የተላኩትን አሽከሮች ተቀብላ ምግብ አቅርባ አስተናገደቻቸው። ነገር ግን #እግዚአብሔር የንጉሡን ተንኮል ስለተገለጠላት ልጇን ደበቀችው፡፡ በስውርም ወስዳ ከጳጳሱ ዘንድ ዲቁና እንዲቀበል ካደረገችው በኋላ ‹‹ልጄ ሆይ! አጎትህ ሊገድልህ ይፈልግሃልና በፊቴ ከሚገድልህ ርቀህ ብትሄድ ይሻላል፣ ያዕቆብን ከኤሳው የጠበቀ አንተንም ይጠብቅህ›› ብላ ሸኘችው፡፡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስም ወደ በጌምድር ተሰደደ፡፡ (ገድሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በዚያም የሌዋውያን ወገን የምትሆን ቅድስት ሕዝባን አግብቶ ቅስናም ተቀብሏል ይላል።) ያም ሆነ ይህ ቅዱሱ በስደቱ ወቅት ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን ጥበብ ተምሮ እንዳጠናቀቀና በኋላም ወንጌልን እየሰበከ፣ በተአምራቱም ሕመምተኞችን እየፈወሰ #እግዚአብሔርንም እያገለገለ እንደኖረ ታሪኩ ያወሳል፡፡

በዚህ አይነት ሁኔታ ዓመታት ሲያልፉ #እግዚአብሔር አምላክ ንጉሥ አጎቱ ጠንጠውድም መሞቱንና በዙፋኑም እርሱ እንደሚነግሥ ነገረውና በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ወደ ሀገሩ ተመልሶ መጥቶ በላስታ ወረዳ ሳይ (ዛሬ ሸጐላ ማርያም) ከምትባል ቦታ ላይ ወንጌልን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ እንዲቀመጥ አደረገው፡፡ ትምህርቱንና ተአምራቱን ያዩት የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ነፃነትና ፍቅር የሚገኝብህ የ #እግዚአብሔር ሰው ሆይ! እኛ ሰላማዊ ብርሃናዊ ብለን ስም አወጣንልህ፣ ያንተ ግን ስምህ ማን ይባላል ንገረን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹ስሜ ይምርሃነ ክርስቶስ ነው›› አላቸው ይህኔ ሕዝቡ ሁሉ በሹክሹክታ ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሲነግሥ ሃይማኖት ይቀናል፣ ፍርድ ይስተካከላል›› እያሉ አባቶቻችን ሲናገሩ ሰምተናል አሉ፡፡

ከጠንጠውድምም ሞት በኋላ ማንም እንዳልነገሠ ሲያረጋግጡ የማን ልጅ እንደሆነ እንዲነግራቸው በ #እግዚአብሔር ስም ለመኑትና የጠንጠውድም ታናሽና የዣን ስዩም ታላቅ ወንድም የሆነው የግርማ ስዩም ልጅ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹የተነገረው ትንቢት ደርሷልና ሳንዘገይ እናንግሠው›› ብለው ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጽመው በዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡

ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በትረ መንግሥቱን ከያዘ በኋላ ሁሉም ሰው በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደ ወንጌሉ ቃል እንዲኖር በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ #እግዚአብሔርም የሚመሰገንበትን ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለትን ቦታ እንኪያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደ ሙሴ አምላኩን ማገልገል ጀመረ፡፡ በዚህም ቦታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት #መስቀል እየባረከና እርሱ ለቅዳሴ በሚገባበት ጊዜ ከአምላኩ የሚሰጠውን ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እያቆረበ ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ኖረ፡፡ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላም #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ በክብር ተገለጠለትና እንዲህ አለው፡- ‹‹ወዳጄ ይምርሃነ ክርስቶስ ይህን ሥፍራ (ዛዚያን) ልቀቅ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ አይወርድልህም፡፡ ወደማሳይህ ቦታ ተነሥተህ ሂድ፣ በዚያም እስከ ዕረፍትህ ቀን ድረስ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ይወርድልሀል፡፡ ይህን ዓለም ለማሳለፍ እስከምመጣበት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ የእኔ ጌትነት የአንተም የቅድስና ሕይወት የሚነገርበት፣ የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆንበት፣ ለምትሠራው መቅደስ ክዳን የሚሆን ሣር የማትፈልግበት ሰፊ ዋሻ እሰጥሀለው ፣ በዚያ ቤተ መቅደሴን ሥራ፣ እኔ በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለዓለም ቃልኪዳኔን አቆማለሁ፡፡ በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ‹አቤቱ የይምርሃነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ! ስለወዳጅህ ስለ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ብለህ ይቅር በለኝ› እያለ ‹አባታችን ሆይ!› የሚለውን ጸሎት የሚጸልይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ነገ ማለዳ ተነሥተህ ወግረ ስሂን ወደሚባለው የዕረፍትህ ቦታ ወደሚሆነው ዋሻ ሕዝብህን አስከትለህ ሂድ፤ በዚያም ቤተ መቅደሴን አንጽ›› ብሎ ቃልኪዳን ሰጠው።

ይምርሃነ ክርሰቶስም ሕዝቡን ይዞ ተነሳና አሁን ከቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶች 42 ኪ,ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኘውና ጥቁር አለታማ ተራራ ሥር ወዳለው የውግረ ስሂን ዋሻ አመራ። ሲደርስም ቦታው የሰዎች ይዞታ ሆኖ ስላገኘው እኔ ንጉሥ ነኝ ብሎ እነርሱን በግፍ ሳያስለቅቅ ካሳ ከፍሎ ስፍራውን ተረከባቸው። ውስጡ ግን ውሀ የቆመበት ባህርና ርኩሳት መናፍስት የሞሉት ስለነበር መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መናፍስቱን አባሮ በባሕሩ ላይ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንደሚያንጽ ገለጠለት። እርሱም በተነገረው መሠረት ለግንባታው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ከኢየሩሳሌም አስመጥቶ ማነጽ ጀመረ። የውሀውን ክፍል እንጨት ረብርቦ አፈር እየበተነ ደለደለው። ሰዎች በባህር ላይ መሠራቱን እንዳይጠራጠሩም አነስተኞ መስኮትነገር አበጀለት። (በዚህችም አሁን ድረስ በክንድ ርቀት ያህል ከሥር ያለው ውሀ ይነካል።) ከበላዩም ስስ ሆነው የተፈለጡ ድንጋዮችን በኖራ እያቦካ በማያያዝ በእኩል መጠን እየገነባ በመሀከላቸው እንደ መቀነት የተጠረቡ እንጨቶችን በማስገባት አሳምሮ አነፀው። ውስጡንም በሦስት ቤተ መቅደሶች ከፈለው በየመስኮትና በየበሮቹም ላይ እንደ ዐይነ እርግብ ሆነው የተፈለፈሉ ሐረጎችን አደረገበት ጣሪያውንም በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ ምስጢር ባላቸው የተለያዩ ቅርፆች አስዋበው። ይህን አድርጎ ሥራውን ከጨረሰ በኋላም የቅዱስ ገብርኤልን የእመቤታችንንና የቅዱስ ቂርቆስን ታቦታት አስገባበት። በድጋሚም ቤተ መንግሥቱን በዛው ዋሻ ውስጥ አነጸና በአስተዳደሩ ደሀ ሳይበድል ፍርድ ሳያጓድል ሕዝቡን በክህነቱም ንፁህ ሆኖ #እግዚአብሔርን እያገለገለ ኖረ። በስተመጨረሻም ፍጥረት ሆኖ ከመሞት ሰው ሆኖ በመቃብር ከመዋል የሚቀር አይኖርምና
#ጥቅምት_፲፱ (19)

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘውን በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ አስደናቂውን #ፃዕዳ_ዓምባ_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳምን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

አቡነ ሠይፈ ሚካኤል ከአባታቸው ከዓምደ ሚካኤልና ከእናታቸው ከኅሪተ ማርያም ተወለዱ፡፡ ወላጆቻቸው #እግዚአብሔርን የሚፈሩና በጾም ጸሎት የተወሰኑ የዋኆች ስለነበሩ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል፡፡ አባታቸው ቃለ #እግዚአብሔር እንዲማሩላቸው ልጃቸውን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ወስደው ለመምህር ሰጧዋቸው፡፡ መምህሩም በደስታ ተቀብለው ቅዱሳት መጻሕፍትንና ያሬዳዊ ዜማን አስተማሯቸው፡፡

ከዚህም በኋላ አቡነ ሠይፈ ሚካኤል "እኔን ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ #መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ" የሚለውን #ጌታችንን ቃል ለመፈጸም ዓለምን ከነምኞቷ ንቀው ትተው #መስቀሉን ተሸክመው #ጌታችን ተከተሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ዋሻዎችና ገዳማት እየሄዱ በአድያቦ ቤተ ቂርቆስ የሚባል ገዳም ደርሰው ከአቡነ ኖላዊነኄር ግብረ ምንኵስና እየተማሩ በገዳሙ ውስጥ የነበሩ መነኰሳት እስከሚደነቁ ድረስ በጽኑ ትጋትና በብዙ ትሩፋት በተጋድሎ አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ከጽኑ ተጋድሏቸው የተነሣ ሰውነታቸው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት አቡነ ዕንቆ ብርሃን ልብሰ ምንኵስናና አስኬማ መላእክት አለበሷቸው፡፡ እንዲህ ባለ ጽኑ ገድል በኣድያቦ ከመንፈስ አባታቸው ከአባ ዕንቆ ብርሃን ብዙ ዓመታትን ቆይተው በኋላ ወደ ዋልድባ ሄዱ፡፡ ዋልድባ ከገቡም በኋላ እዛ ከነበሩ ቅዱሳን ተባርከው ጽኑ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡

ከዚያም በዋልድባ ቅዱሳን ፈቃድ ወደ ወገሪቆ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሄደው አበምኔትና መምህር ሆነው አገለገሉ፡፡ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ወንጌልን እያስተማሩና ሕሙማን እየፈወሱ እስከ ጋሽ ባርካ ደብረ ሳላ የሚባል ቦታ ዞሩ፡፡ ይሄን አገልግሎታቸው ከፈጸሙ በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እየመራ ማረፍያ ቤታቸው ወደሆነችው ፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም በደብረ ከባቦ አደረሳቸው፡፡ በዚያም በጾምና በጸሎት ተጠምደው #እግዚአብሔርን አገለገሉ፡፡ሲጸልዩም እስከ ሰማይ ድረስ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ ይታያቸው ነበር፡፡

አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ አጋንንት በእባብና በንብ እየተመሰሉ ይፈታተኗቸው ነበር ነገር ግን አባታችን በጾምና በጸሎት ድል ይነሷቸው ነበር፡፡ በደብረ ከባቦ ቤተ ክርስትያን አንጸው ማኅበር አቋቁመው ለ9 ዓመት ከ6 ወር አገልግሎታቸውን እየፈጸሙና መከራ እየተቀበሉ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን በሰርክ ጸሎት እየጸለዩ ሳለ መልአክ መጥቶ "…ወደ ገዳሙ አስገባሃለሁና ተከተለኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም ከኋላው እየተከተሉ መልአኩ ወደ ዛሬይቱ ወንዶች ብቻ ወደሚገቡባት ገዳም አስገባቸው፡፡ ያቺን ለማየትም ጭምር የምታስፈራዋን መንገድ አባታችን "ጸናፌ ፅልመት"ብለው ሰየሟት፡፡ ከገቡም በኋላ በገዳሙ ውስጥ ቤተ ክርቲያን አንጸው ቤተ ማኅበር አቋቋሙ።

አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ርኲሳን መናፍስትን ከሕሙማን ያወጡ ስለነበር እነዚያ አጋንንትም "እዚህ እንድትኖር አንፈቅድልህም" እያሉ በገሃድ ለሞት እስከሚደርሱ ድረስ ዐይናቸውን አፈሰሱባቸው ሆኖም ግን መልአከ #እግዚአብሔር ዳስሶ ዐይናቸውን መልሶ አበራላቸው፡፡ እንዲሁም አጋንንቶቹ በማደርያ ቤታቸው እሳት እያቀጣጠሉ በላያቸውም ትላልቅ ድንጋዮችን እየወረወሩ ከበፊቱ በእጅጉ ይፈታተኗቸው ነበር፡፡ እነዚያ የተወረወሩባቸው ድንጋዮች ግን አቡነ ሰይፈ ሚካኤል ይጸሉዩበት በነበረ ቦታ በደቡብ አቅጣጫ ተተክለው ቀርተዋል፡፡ ድንጋዮቹ እስከ አሁን ድረስ አሉ፡፡

አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በአገልግሎታቸው ለሚያምኑ እያጽናኑና እያበረቱ፣ ለማያምኑ ደግሞ አሳምነው እያጠመቁ እስከ ማዕርገ ክህነት አድርሰው ቤተ ክርስትያን ይሠሩላቸው ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ቅዱስ አባታችን በብዙ ተጋድሎ ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውንና አገልግሎታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከ #እግዚአብሔር የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለው ጥቅምት 19 ቀን 1722 ዓ.ም በ96 ዓመታቸው ራሳቸው በመሠረቱም በገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስ ሥላሴ ዐርፈዋል፡፡

የአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤልን መንገድ የተከተሉ የዚህ ገዳም መነኰሳትም በጾምና በጸሎት ተወስነው #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ "ሑሩ ወመሐሩ" (ማቴ 28፡19) ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሐዋርያዊ ተልኮአቸውን እየፈጸሙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናን ከከረን እስከ ኦምሓጃር ከዛ አልፎም እስከ ከሰላ ሱዳን አንጸዋል፡፡ በፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም ሐምሌ 7 ቀን የ #ሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል በዓለ ዕረፍታቸው ጥቅምት 19 ቀን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በእነዚህ ክብረ በዓላት ላይ በርካታ ምእመናን ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ከበረከቱ ይሳተፋሉ፡፡ ከአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።

#ጻድቁ_አቡነ_ሠይፈ_ሚካኤል_ስለመሠረቱት_ፃዕዳ_ዓምባ_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳም

#አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል፦ እኚህ ጻድቅ በ1669 ዓ.ም የገደሙት ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ ገዳም ፃዕዳ ዓምባ #ቅድስት_ሥላሴ ከኤርትራ በዓንሰባ ዞን ከከረን 25 ኪ.ሜ እርቆ በደቡባዊ ምዕራብ ከባሕር ጠለል በላይ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ወደዚህ ድንቅ ገዳም የሚያደርሰው መንገድ ዳገትና ቁልቁለት የበዛበት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሣ ብርቱ ትዕግሥትና መንፈሳዊ ጽናት ይጠይቃል፡፡ ገዳሙ ለመድረስ ከከረን ከተማ በደቡባዊ ምዕራብ በኩል ወንዞችንና ጋራ ሸንተረሮችን ማቋረጥ ግድ ነው፡፡ ከዚያም "ድንጃ ወርቅ" በተባለ ከገዳሙ እግር ሥር በሚገኘው ረጅሞ ተራራ ከተደረሰ በኋላ ከድንጃ ወርቅ የአንድ ሰዓት ተኩል ዝግዛግ የእግር ጉዞ ያስኬዳል፡፡ ከዚያም "ማዕዶዋይ" ከተተባለው ቦታ ይደረሳል፡፡ ትርጓሜውም በርቀት የሚታይ ማለት ነው፡፡ ከማዕዶዋይ ወደ ገዳሙ ውስጥ ለመግባት ከእግር መረገጫ የማያልፍ ስፋት የሌላት በቀኝና በግራ የምታስፈራ በጭንቅ የሚሻገርዋት "ጸናፌ ጽልመት" ተብላ የምትጠራዋን አስጨናቂ ገደል ማለፍ ግድ ይላል፡፡ ይህቺን ለመሻገርም ሆነ ለማለፍ አስቸጋሪ የሆነችን መንገድ ለብዙ ጊዜ የተመላለሱባት ምእመናን ግን ከባድ እቃ በሸክም ይዘውም ቢሆን ያለ ምንም ፍርሃት ይሻገሩባታል፡፡ በጭንቅ የሚሻገርዋትን ይህችን አስጨናቂ ገደል ከታለፈ በኋላ ቀጥሎ "ደገ ሰላም" ና "መንገደ ሰማይ" የሚባል ወደ ገዳሙ የሚያስገባ ዝግዛግ መንገድ አለ፡፡

አባታችንን ወደዚህ ድንቅ ገዳም እየመራ ይዞአቸው የገባው የታዘዘ መልአክ ነው፡፡ ወደ ገዳሙ ቅጥር ውስጥ ከተገባ በኋላ ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ልዩና መንፈሳዊ ሐሴትን የሚሞሉ በርካታ ተአምራት የተፈጸመባቸውን ነገሮችን መመልከት ይቻላል፡፡ተአምራቶቹም "ድሮ እንዲህ ነበር፣ እንደዛ ተደረገ…" ተብሎ በአፈ ታሪክ ብቻ የሚወራ ሳይሆን አሁንም ድረስ በዐይን የሚታዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገዳሙ አጠገብ የሚገኙት ዛፎች ብዙ ዕድሜ ከማስቆጠራቸው የተነሣ በንፋስ ኃይል ሲወድቁ ወደ ታች መውደቅ ሲገባቸው በተቃራኒው ግን ዛፎቹ የሚወድቁት ወደ ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ገዳሙ ውስጥ በላዔ ሥጋ ሥጋን የሚበላ ንስር ሳይቀር እንኳን የሞተ እንስሳም ቢያገኝ ሥጋ የሚባል ነገር አለመብላቱ አሁንም ድረስ በዐይን
#ዳግመኛም በዚህች ዕለት ታላቁ አባት "አቡነ ሐራ ድንግል" ልደታቸው ነው፡፡
አቡነ ሐራ ድንግል፡- ጻድቁ ከአባታቸው ከሬማው ካህን ከቅዱስ ዮሐንስ ከእናታቸው ብፅዕት ወለተ ጊዮርጊስ የተወለዱት ጥቅምት 19 ቀን 1534 ዓ.ም ነው፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ጥንት በጌምድር ደብረ ታቦር አውራጃ ደራ ወረዳ ይባል በነበረው አሁን በምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ላጉና ቀበሌ ነው፡፡ ቅዱሳን የሆኑ ወላጆቻቸውም አባታችንን ከልጅነታቸው ጀምሮ በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጓቸው፡፡ አባታችንም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት በሙሉ ተምረው በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎና አገልግሎት ከኖሩ በኋላ ዓለምን ፍጹም ንቀው መንነው ወደ ሸዋ ተጉዘው ግራርያ ከሚባል አገር ደረሱ፡፡ በዚያም ዘመዶቻቸው ፈልገው ስላገኙዋቸውና ወደ ሀገራቸው ስለመለሷቸው በሌላ ጊዜ ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ አቋርጠው አሁን ገዳማቸው ካለበት ጫካ ውስጥ ገቡና ገዳመ ወንያትን መሠረቱ፡፡ በዚያም ፈተናውን ሁሉ ድምጸ አራዊቱን፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ብርዱን፣ ሐሩሩን፣ ረሃብ፣ ጥማቱን ታግሰው በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ ሰይጣንም በፈተና ሊጥላቸው አንድ ጊዜ በተዋበች ቆንጆ ሴት እየተመሰለ አንድ ጊዜ ደግሞ በሞተ ሰው እየተመሰለ እስከ ሰባት ተከታታይ ቀናት ድረስ ቢፈትናቸውም ድል አድርገውታል፡፡
አባታችን ቀን ላይ ጸሎት እያደረጉ እያለ ነብር የሚያባርራት አንዲት ሚዳቋ መጥታ ከቤት ገብታ ከአቡነ ሐራ ድንግል እግር ስር አረፈች፡፡ ነብሩም ደርሶ ከደጅ እየተቆጣ ቆመ፡፡ ይህን ጊዜ አባታችን ‹‹እርሷን ገድለህ ትበላ ዘንድ #እግዚአብሔር አልሰጠህምና ሂድ›› ባሉት ጊዜ ቃላቸውን ሰምቶ ሄደ፡፡ ሚዳቆዋም እዛው አድራ ሲነጋ በሰላም አሰናብተዋታል፡፡
አባታችን መንኩሰው በገዳማቸው ከገቡበት ፈጽመው ሳይወጡ ለ14 ዓመት በተአቅቦ ተቀምጠዋል፡፡ በአንድ ወቅት ጠላት ተነስቶ አካባቢውን በሙሉ በመውረር ሁሉን ሲማርኩ ገዳሟን አይተው ወደ እርሷም ሊገቡ ሲሉ በተአምራት ባሉበት ተይዘው ቆመው በመቅረታቸው ጉዳት ሳያደርሱባት ተመልሰዋል፡፡ ሱስንዮስ ‹‹ሁለት ባሕርይ ሁለት አካል›› የሚለውን የሮማን የረከሰ ሃይማኖት በሀገራችን ላይ እውጆ ብዙዎች ሰማዕትንትን ሲቀበሉ አቡነ ሐራ ድንግል በገዳማቸው ለብዙዎች መጠጊያ ሆነው ሃይማኖታቸውን ሲያስተምሯቸውና ሲያፀኗቸው ነበር፡፡ በንጉሡም ፊት ቀርበው በድፍረት ‹‹አንድ አካልና አንድ ባሕርይ የሆነውን መለኮትና ትስብእትን ለምን ከሁለት ወገን ትከፍለዋለህ?›› ብለው ሲገስፁት ፈርቶ አሽከሮቹን ‹‹ይህን መነኩሴ ከቤቴ አውጥታችሁ በፍጥነት ወደ ገዳሙ አድርሱልኝ›› ብሏቸዋል፡፡ እመቤታችንን ድንግል #ማርያምን እጅግ አድርገው ይወዷት ነበርና ምስጋናዋን ሲያደርሱ ሦስት ክንድ ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም የሁልጊዜ ጠባቂያቸው ነበር፡፡ በ1574 ዓ.ም አሁን በስማቸው ወደሚጠራው ገዳመ ወንያት መንነው ገቡ፡፡ በዚያም ወንጌልን እያስተማሩ፣ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረጉ፣ ሙት እያስነሱ፣ ድውያንን እየፈወሱ #እግዚአብሔርን ሲያገለገሉ ኖረዋል፡፡
አባታችን ሐራ ድንግል ‹‹የማነ ብርሃን›› የሚባል ታማኝ አገልጋይ አህያ ነበራቸው፡፡ አህያውም ጸሎታቸው ይጠብቀው ነበር እንጂ እረኛ አልነበረውም፡፡ አንገቱ ላይ ቃጭል አስረው ወደ ገበሬው አውድማ ይልኩትና አህያውም ቃጭሉን እያጮኸ ወደ አውድማው ሁሉ ሄዶ እየዞረ ‹‹ #ማርያም ባርኪ›› በረከት ሰፍረው ይጭኑታል፡፡ አህያውም ከገበሬው ሁሉ የሰበሰበውን እህል ይዞ ወደ አቡነ ሐራ ድንግል ይገባል፡፡ በፈለጉትም ሰዓት ራሱ አውቆ ይመጣላቸው ነበር፡፡ አህያውም አርጅቶ ሲሞት እንደ ሰው አልቅሰውና በአዲስ ጨርቅ ጠቅልለው ቀብረውታል፡፡ አህያቸው የማነ ብርሃን ከተቀበረበት ቦታ ላይ ጸበል ፈልቆ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ የቅዱሳኑ በረከታቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡
ታላላቆቹ ቅዱሳን እንደነ በትረ ማርያም፣ አባ ጽጌ ድንግል፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ያሉ ሌሎችም በርካታ ደጋግ ቅዱሳን ዝናቸውን እየሰሙ ከያሉበት እየሄዱ ይጎበኙዋቸውና በረከታቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግልም በክብር ካረፉ በኋላ በመካነ መቃብራቸው ላይ ለ40 ቀን ብርሃን ሲወርድ በገሃድ ታይቷል፡፡ አፅማቸውም ከዚያው ከገዳማቸው በክብር አርፎ ይገኛል፡፡ በጸሎታቸው ያፈለቁት ጸበልና የመቃብራቸው አፈር ሕመምተኞችን ከተለያዩ ደውያት ሰውንም እንስሳትንም እየፈወሰ ይገኛል፡፡ አፈራቸውና ጸበላቸው ለሥጋ ደዌ፣ ለእብጠት፣ ለቁስል፣ ለለምፅና ለመሳሰሉት ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ በዓለ ዕረፍታቸው ጥር 11 ቀን 1624 ዓ.ም ነው፡፡
የአቡነ ሐራ ድንግል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!!
#ጥቅምት_20

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ በዚህች ቀን ክቡርና ገናና የሆነ #የአባ_ዮሐንስ_ሐፂር እና የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ #የታላቁ_ነቢይ_ኤልሳዕ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዮሐንስ_ሐፂር

ጥቅምት ሃያ በዚህች ቀን ክቡርና ገናና የሆነ አባ ዮሐንስ ሐፂር አረፈ። የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ ከላይኛው ግብጽ ናቸው እነርሱም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው ግን ከእርሱ በቀር ልጅ የላቸውም የዚህ ዓለምም ብልጽግና ቢሆን የላቸውም ነገር ግን በበጎ ሥራ ባለጸጎች ናቸው ይህንንም ቅዱስ እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት ።

የዚህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ሲሆነው የ #እግዚአብሔር ቸርነት አነሣሥታው የመላእክት የሆነ አስኬማን ይለብስ ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ ይኸውም የምንኵስና ልብስ ነው።

ከዚያም በደረሰ ጊዜ አባ ባይሞይ የሚባለውን አንዱን አረጋዊ አባት ተገናኘው ዮሐንስም ሰገደለትና ወደ እርስ እንዲቀበለው ለመነው ሽማግሌውም አባት ልጄ ሆይ ያንተ በዚህ መኖር ልክ አይደለም በዚች ገዳም የሚኖሩ በእጆቻቸው ይሠራሉ በቀንና በሌሊት ይጾማሉ ይጸልያሉ በሚተኙም ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ ይተኛሉ አንተ ወጣት ጎልማሳ ስለሆንክ ይህን ሁሉ ችግር አትችልም። ነገር ግን ወደ ዓለም ተመልሰህ እንደ ሰው ሁሉ በጎ አኗኗርን ትኖር ዘንድ ይሻልሃል የዚች ገዳም ኑሮ ጭንቅ ነውና አለው።

አባ ዮሐንስም እንዲህ አለው እኔ በጥላህ ሥር ልኖር መጥቼአለሁና ስለ እግዚአብሔር ብለህ ተቀበለኝ እንጂ አትመልሰኝ ይህም አባ ባይሞይ #እግዚአብሔርን ሳይጠይቅ ምንም ሥራ አይሠራምና በዚያን ጊዜ ሥራውን ይገልጥለት ዘንድ ስለ ዮሐንስ ሐፂር #እግዚአብሔርን ለመነው የ #እግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦለት እርሱ የተመረጠ መሳሪያ ይሆናልና ተቀበለው ብሎሃል አለው።

ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ሐፂርን ወስዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገባው የምንኵስና ልብሶችንም አምጥቶ በላያቸው ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ጸለየ ከዚህም በኋላ የ #እግዚአብሔር መልአክ ተገልጾ በ #መስቀል ምልክት በልብሶቹ ላይ አማተበ ሽማግሌውም እነዚያን ልብሶች ለአባ ዮሐንስ አለበሰው ።

ከዚያቺም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ ተጋድሎንና አገልግሎትን ጀመረ አባ ባይሞይም ሊፈትነው ወደደ በአንዲትም ቀን ደብድቦ ከአንተ ጋር መኖር አልሻም ብሎ ከበዓቱ አስወጥቶ አባረረው የከበረ አባ ዮሐንስም ከሜዳ መካከል በውጭ ቆመ በየቀኑም በጥዋት እየወጣ ከእዚህ ላይህ አልሻም እያለ ይመታዋል እርሱ ግን አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ ብሎ ከእግሩ በታች ይሰግዳል ።

በሰባተኛዪቱም ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሔድ ሽማግሌው አባ ባይሞይ ወጣ አባ ዮሐንስንም ሰባት መላእክት ከበው አክሊላትን ሲያቀዳጁት አያቸው ከዚያንም ጊዜ ወዲህ መፈተኑን ተወው ወደ መኖሪያውም አስገባው።

ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን አባ ባይሞይ የደረቀ ዕንጨት አግኝቶ ወስዶ ለአባ ዮሐንስ ሰጠውና ይህን ዕንጨት ትከለው እስከሚበቅልና እስከሚአፈራ ድረስ ውኃን አጠጣው አለው ። አባ ዮሐንስም ለአባቱ ታዛዥ በመሆን ተቀብሎ ወስዶ ተከለው በየቀኑም ሁለት ሁለት ጊዜ ያጠጣዋል ውኃውም ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል የራቀ ነው።

ከሦስት ዓመትም በኋላ ያ ዕንጨት አቈጥቊጦ በቀለ ታላቅም ዛፍ ሁኖ አብቦ ጣፋጭ ፍሬን አፈራ። አባ ባይሞይም ከፍሬው ለቅዱሳን አረጋውያን ወሰደላቸውና የታዛዡንና የትሑቱን ፍሬ እነሆ ብሉ አላቸው እነርሱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው አደነቁ ለመምህሮቻቸው ለሚታዘዙ እንዲህ ያለ ጸጋ የሚሰጥ #እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

አባ ባይሞይም ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል በጽኑዕ ደዌ ውስጥ ተይዞ ኖረ አባ ዮሐንስም ያገለግለው ነበር አባ ዮሐንስን እንደፈተነው የተመረጠ መሥዋዕትን ይሆን ዘንድ በዚህ ደዌ እንዲፈተን #እግዚአብሔር ፈቅዷልና።

በሚሞትበትም ጊዜ አባ ባይሞይ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትን ሰበሰባቸውና አባ ዮሐንስንም እጁን ይዞ እርሱ ሰው ያይደለ መልአክ ነውና ተቀብላችሁ ጠብቁት ብሎ ሰጣቸው ። እርሱንም ደግሞ እንዲህ አለው ከእረፍቴ በኋላ ያን ዕንጨት ወደ ተከልክበት ቦታ በዚያ ኑር #እግዚአብሔር ላንተ ያዘጋጀልህ ነውና ብዙዎችም በአንተ እጅ ይድናሉ መታሰቢያህም በዚያ ጸንቶ ይኖራል ዜናህም በዓለም ሁሉ ይወጣል ይህንንም ተናግሮ አረፈ አክብረውም ቀበሩት።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባ ዮሐንስ አረጋዊ አባቱ አባ ባይሞይ እንደነገረው ወደዚያ ቦታ ሒዶ ኖረ ዜናውም በዓለም ሁሉ እጅግ እስከ ተሰማ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ።

በራሱ ቤተ ክርስቲያንም አበ ምኔት ሁኖ ተሾመ በሹመቱም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ እጆቹን በራሱ ላይ ሲጭን አክዮስ አክዮስ አክዮስ የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ ይህም ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል ማለት ነው ። የቊርባን ቅዳሴን በሚቀድስ ጊዜ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የማይገባቸውን ይለያቸዋል ዛሬስ ሒዳችሁ ንስሓ ግቡ ከዚያም በኋላ ተመልሳችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ ይላቸዋል።

ይህን አባ ዮሐንስንም ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ የቅዱሳን የሠለስቱ ደቂቅን ሥጋቸውን እንዲአመጣለት ወደ ባቢሎን ልኮታል ይህም በግንቦት ወር በዐሥረኛው ቀን ተጽፎአል ። በአንዲትም ዕለት አንድ መነኰስ ሊጎበኘው ወደ በዓቱ ቢመጣ አባ ዮሐንስን ተኝቶ አገኘው የ #እግዚአብሔርም መላእክት በላዩ ይጋፉ ክንፎቻቸውንም ያርገበግቡ ነበር አንዱም ሌላውን ተወኝ ክንፌን በላዩ ላኑር ይለዋል ይህንንም አይቶ #እግዚአብሔርን አመሰገነው ።

ከዚህም በኋላ የመነኩሳቱን መንደር ሊበረብሩ የበርበር አረማውያን ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጡ ጊዜ አባ ዮሐንስም ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ወደ ቁልዝም ሔደ በዚያም በአባ እንጦንስ ገዳም በጎኑ በአለ ቦታ ተቀመጠ እስከ ሚያርፍባትም ቀን ድረስ የሚያገለግለው አንድ የታመነ ሰውን #እግዚአብሔር አመጣለት ።

ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ #እግዚአብሔር ቅዱሳን ጻድቃኖቹን አባ እንጦንስን፣ አባ መቃርስን፣ አባ ጳኵሚስን ከእርሳቸውም ጋር መንፈሳዊ አባቱ አባ ባይሞይን ያረጋጉትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መለየቱን ይነግሩት ዘንድ ወደርሱ ላካቸው ። እነርሱም እንዲህ ብለው አረጋጉት ደስ ይበልህ #እግዚአብሔር የማያልቅ ተድላ ደስታን አዘጋጅቶልሃልና ክብር ይግባውና #ጌታችንም እንዳዘዘ በእሑድ ቀን ሁለተኛ ወዳንተ መጥተን ወደ ዘላለም ሕይወት እንወስድኻለን ባርከውትም ከእርሱ ዘንድ ተመለሱ ።

በዐርብ ቀንም አገልጋዩን ወደ አንድ ቦታ ላከው ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ በእሑድም ቀን ሌሊት ዶሮ ሲጮህ እሊያ ቅዱሳን ከሁሉም ቅዱሳን ማኅበር ጋር መጡ የመላእክትም ሠራዊት ሁሉ ወደርሱ መጡ በአያቸውም ጊዜ ደስ ብሎት በ #እግዚአብሔር እጅ ነፍሱን ሰጠ መላእክትም እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ነፍሱን አሳረጓት በዚያንም ጊዜ ረድኡ መጣ ነፍሱንም ከበው እያመሰገኑ ሲያሳርጓት የጻድቃንና የመላእክትን ማኅበር አይቶ እያደነቀ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ። ከመላእክትም አንዱ ወደርሱ መጥቶ የቅዱሳንን ስማቸውን በመጥራት በጣቱ እያመለከተ ይህ አባ ዕገሌ ነው ብሎ አስረዳው ረድኡም መልአኩን እንዲህ ብሎ ጠየቀው ይህ በፊታቸው ያለ ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚበራ ማን ነው መልአኩም የመነኰሳቱ ሁሉ አባት አባ እንጦንስ ነው ብሎ መለሰለት።
#ጥቅምት_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ አንድ በዚህችም ቀን #እመቤታችን_ተአምራትን_አድርጋ_ሐዋርያው_ማትያስን ከእሥራት ቤት ያወጣችበት፣ #የነቢይ_ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ፣ የማርታና የማርያም ወንድም #የቅዱስ_አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት፣ የቅዱስ አባት #አባ_ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም እረፍት ነው፣ ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#እመቤታችን_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ማትያስ_ያደረገችለት_ተአምር

በዚህችም ቀን እመቤታችን #ማርያም ተአምራትን አድርጋ ደቀ መዝሙር ማትያስን ከእሥራት ቤት አዳነችው።

የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስ ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ #ጌታችንና ወደ #እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ #መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ቅዱስ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡

እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ይዘው በአንገታቸው ገመድ አግብተው ለ3 ቀን በሀገራቸው ጎዳናዎች ላይ ሁሉ ጎተቱዋቸው፡፡ ሁለቱም ሐዋርያት በጸሎታቸው ከእሥር ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃ አፈለቁና ውኃው ሀገራቸውን ሁሉ እስኪያጥለቀልቅና ሰዎቹንም እስከ አንገታቸው ድረስ እስከሚደርስ ሞላ፡፡ ሁሉም በተጨነቁ ጊዜ ሁለቱ ሐዋርያት በፊታቸው ተገለጡና ‹‹በጌታችን እመኑ ትድናላችሁ›› በማለት ወንጌልን ሰብከውላቸው አሳመኗቸው፡፡ ምሥጢራትንም ሁሉ ገለጡላቸው፡፡ ደግሞም የአራዊት ጠባይን ከሰዎቹ ያርቅላቸው ዘንድ ወደ #ጌታችንና ወደ ተወደደች እናቱ ከጸለዩ በኋላ በ #አብ#ወልድ#መንፈስ_ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ያ የአውሬነት ጠባያቸውም ጠፍቶላቸው የዋህ፣ ቅንና ሩኅሩኆቸ ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመውላቸው ወደ ሌላ ሀገር ሄዱ፡፡

ለሐዋርያት ሞገሳቸው ጣዕመ ስብከታቸው የኾነች ክብርት #እመቤታችን ለእኛም ትለመነን!

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኢዩኤል_ነቢይ

ዳግመኛም በዚህችም ቀን የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር ስለ #ክርስቶስም በኢየሩሳሌም መኖርና ማስተማር ትንቢት ተናገረ። ደግሞም ስለ መከራው በሐዋርያትና በሰባ ሁለቱ አርድእት በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የ #መንፈስ_ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ።

ከዚህ በኋላ በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ። ሁለተኛም እንዲህ አለ ያን ጊዜ ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ #እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል።

ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት እንዲህ አለ ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ የከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል። የትንቢቱንም ወራት አድርሶ #እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነብዩ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አልዓዛር የማርታና የማርያም ወንድም

በዚችም ቀን ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው የቅዱስ አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት ሆነ።

ከክርስቲያን ነገሥታትም አንዱ ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቊስጥንጥንያ አፈለሰው። ሊአፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የደንጊያ ሣጥን ውስጥ ሁኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ ይህ በመቃብር ውስጥ አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር ይግባውና የ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ነው።

ይህንንም በአዩ ጊዜ ደስ ተሰኙበት ተሸክመውም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ወሰዱት ካህናቱም ሁሉ ወጥተው በታላቅ ክብር በመዘመርና በማመስገን ተቀበሉት በአማረ ቦታም አኖሩት በዚችም ቀን በዓልን አደረጉለት።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አልዓዛር ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘኢየሩሳሌም

በዚህችም ቀን ለከበረች አገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት የሆነ ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ #እግዚአብሔርን በሚወድ የንጉሥ ሰይፈ አርዕድ ደግሞ ቈስጠንጢኖስ ለሚባል ልጁ በሆነ በንጉሣችን በዳዊት ዘመን አረፈ።

ይህም ቅዱስ ከምስር አገር ታላላቆች #እግዚአብሔርን የሚፈሩ የክርስቲያኖች አባቶች ልጅ ነው። የዲቁና መዓረግንም ለመሾም እስከ ተገባው ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት። ከዚህም በኋላ በዲቁናው ሹመት አገልግሎቱን በአሳመረ ጊዜ የቅስና መዓረግ የሚገባው ሁኖ ቅስና ተሾመ።

በጾም በጸሎት #እግዚአብሔርንም በመፍራት የተጠመደ ሁኖ ድኆችንና ችግረኞችን የሚወዳቸው የሚረዳቸው ሆነ ያን ጊዜ የሐዋርያት የሆነች የጵጵስና ሹመት የምትገባው ሁና በከበረች አገር በኢየሩሳሌም በ #እግዚአብሔር ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ ሕዝቡንም በፈሪሀ #እግዚአብሔርና በትሕትና የሚያስተምራቸው ሆነ።

እነርሱም ስለ ቅድስናው እጅግ የሚወዱት ሆኑ መልኩና የአንደበቱ አገላለጥ እንደ #እግዚአብሔር መልአክ ያማረ ነበር። በሹመቱም ጥቂት ዘመናት ከኖረ በኋላ ከመንበረ ሢመቱ እስከ አራቀው ድረስ በላዩ ሰይጣን ምክንያትን አመጣ።

ይህም እንዲህ ነው በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ማርቆስ ዘመን በግዛቱ ውስጥ ያሉ እስላሞች ስለ ዐመፁበት የኢትዮጵያ ንጉሥ ፈጅቷቸው ነበርና ስለዚህ በግዛቱ ውስጥ በሚኖሩ እስላሞች ላይ ክፉ እንዳያደርግ ለኢትዮጵያ ንጉሥ መልእክት እንዲልክ ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን የምስር ንጉሥ አዘዘው።

አባ ማርቆስም ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ ስለሚላኩ ሰዎች ከመኳንንቱ ከኤጲስ ቆጶሳቱና ከሀገር ታላላቆች ሽማግሌዎች ጋር ተማክሮ እሊህን ብሩሀን ከዋክብት የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስን የምስር ኤጲስቆጶስ አባ ሳዊሮስን በእውቀታቸው በአስተዋይነታቸውና በቅድስናቸው መረጡአቸው ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥም ይሔዱ ዘንድ ግድ አሏቸው።
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

         🌹 #ጥቅምት ፳፩ (21) ቀን።

🌹 እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ መሰቀልህን በቅዱሳት መጻሕፍት ሰማሁ ይኽን በዐይኔ አሳየኝ በማለት #መድኃኔዓለምን_ለጠየቁት_እሱም ለገለጸላቸው፤ የንጉሡን መልዕክተኞች ከንጉሡ ቤት እንገናኝ በማለት መልዕክተኞቹ ዘጠኝ ቀን ተጉዘው ሲደርሱ እሳቸው ቀድመዋቸው ንጉሡ ቤት ለተገኙት #አቡነ_ዐሥራ_ወልድ_ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                              
🌹 #አቡነ_ዐሥራተ_ወልድ፦ በዳሞት አውራጃ ልዩ ስሟ እነሴ በምትባል ቦታ በዐፄ ሠርጸ ድንግል ዘመነ መንግሥት በ1584 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው ፃማ ክርስቶስ እናታቸው ጽጌ ማርያም ይባላሉ። ኹለቱም በሕገ #እግዚአብሔር ጽንተው የሚኖሩ በሃይማኖት በምግባር የተመሰገኑ በተጋድሎ በትሩፋት የታወቁ ክርስቲያኖች ነበሩ ነገር ግን ልጅ ስላልነበራቸው እንደ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ሁልጊዜ #እግዚአብሔርን በጸሎት ይጠይቁ ነበር አምላክን የወለደች ክብርት #እመቤታችንንም ይማጸኗት ነበር።

🌹 ኹለቱም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ በምድራዊ ሀብትም የበለጸጉ ነበሩ፤ ለድኖችና ለምስኪኖች አብዝተው ይመጸውቱ ስለነበር ከጾማቸው በኋላ ያለ ድኖችና ምስኪኖች ብቻቸውን አይመገቡም ነበር። #እግዚአብሔርም ጸሎት ልመናቸውን ተቀብሎ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወደደ። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን የ #እግዚአብሔር ሰው ለጽጌ ማርያም ታይቶ "ዝናው በአራቱ ማዕዘን ኹሉ የሚደርስ በሕይወተ ሥጋ እያለ የብዙ ሰዎችን ነፍስ በጸሎቱ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ የሚያወጣ ወደ ሰማይም ወጥቶ የ #ሥላሴን ምሥጢር የሚያይ የተባረከ ልጅን ትወልጂ ዘንድ አለሽና ደስ ይበልሽ" በማለት ካበሠራት በኋላ አቡነ ዐሥራተ ወልድ ሰኔ ሃያ ቀን ተወለዱ።

🌹 ጻድቁም በተወለዱ በስምንተኛ ቀናቸው "ለ #አብ ምስጋና ይገባል ለ #ወልድ ምስጋና ይገባል ለ #መንፈስ_ቅዱስ ምስጋና ይገባል" ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል። እስከ ዐሥራ ኹለት ዓመታቸውም ድረስ ውኃ በመቅዳት ዕንጨት በመስበር ወላጆቻቸውን ካገለገሉ በኋላ ወላጆቻቸው ወደ ታላቁ ጻድቅ ወደ አቡነ ተጠምቀ መድኅን ዘንድ ወስደው እንዲያስተምሩላቸው አደራ ብለው ሰጧቸው።

🌹 አቡነ ተጠምቀ መድኅንም ዐሥራተ ወልድን ተቀብለው የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ኹሉ አስተማሯቸው። በሚማሩበትም ጊዜ #መንፈስ_ቅዱስ በአፋቸው ያቀብላቸው ስለነበር አስቀድመው የተማሩ ይመስሉ ነበር። በሦስት ዓመትም ውስጥ መጻሕፍተ ብሉያትን መጻሕፍተ ሐዲሳትን መጻሕፍተ መነኰሳትን፣አዋልድ መጻሕፍትንም ኹሉ ከነትርጓሜያቸው ከአቡነ ተጠምቀ መድኅን ተምረው #እግዚአብሔርም ከሐሰት መጻሕፍት ከሟርት ከጥንቆላ መጻሕፍት በቀር ያልገለጠላቸው የመጻሕፍት ምሥጢር የለም። የመላእክትንና የቅዱስ ያሬድንም ዜማ ገለጠላቸው።

🌹 ከዚኽም በኋላ አቡነ ዐሥራተ ወልድ ለመመንኰስ ወላጆቻቸውን አስፈቅደው ከመምህራን ጋር ወደ ታላቁ ገዳም ወደ ደብረ ዳሞ ሔደው በዚያም መነኰሳቱን እያገለገሉ ለ25 ዓመታት ያህል በተጋድሎ ከኖሩ በኋላ በዐፄ ፋሲል ዘመን መንግሥት በ40 ዓመታቸው በ1624 ዓም መንኰሱ። ከሊቀ ጳጳሱ ከአቡነ ሚካኤልም እጅ የቅስና ማዕረግ ተቀበሉ። ከዚኽም በኋላ ከመምህራቸው ከአቡነ ተጠምተ መድኅን ጋር ወደ ጋሾላና ጉሓን ገዳማት ሔደው ተጋድሏቸውን ጨምረው መጾም መጸለይን አበዙ። ወደ ተራራ ሔደው ዳዊት ሲያነቡ ያድራሉ፣ ምሥራቅም ዙረው እምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ፤ ወደ ምዕራብም ዙረው አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ፤ ወደ ሰሜንም ዙረው አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ ወደ ደቡብም ዙረው እምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ፤ እንዲህም እያደረጉ በየዕለቱ ኹለት ሺህ ይሰግዱ ነበር። ላባቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድርን እስኪያርስ ድረስ ይሰግዳሉ፤ የቆሙበትም ምድር እንደ ጉድጓድ ይጎደጉዳል። እንደዚህ ባለ ታላቅ ተጋድሎ ጸንተው ብዙ ዘመን ኖሩ። የ #ጌታችንንም ዐርባ ጾም ምንም ሳይቀምሱ ዐርባውን ቀን ይጾሙ ነበር።

🌹 ከዚኸም በኋላ አቡነ ዐሥራት ወልድ ጃባ በሚባለው ቦታ ዐሥራ አንድ ዓመት በተጋድሎ ኖሩ። አባታችን ያከብሯት የነበረች ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የክብርት #እመቤታችን ሥዕል በዚያ ነበረችና እርሷም ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን ታደርግላቸው ነበር። ጃባ በምትባል ቦታም ዘወትር ታነጋግራቸው ነበር። በአንደኛውም ሌሊት ተኝተው ሳሉ አምላክን በድንግልና የወለደች ክብርት #እመቤታችን ተገልጣላቸው "ልጄ ወዳጅ ዐሥራተ ወልድ ሆይ! በጸሎትና በልመናህ የጃባ ሰዎች ኹሉ ይድናሉ፣ በቃልህ #ክርስቶስን አምነው በእጅህ #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ይቀበላሉ" አለቻቸው።

🌹 ከዚኽም በኋላ የታዘዘ የ #እግዚአብሔር መልአክ ለኹለቱም ቅዱሳን ተገልጦላቸው አቡነ ተጠምቀ መድኅንን ወደ ጋዝጌ እና ወደ መተከል ሔደው የከበረች ወንጌልን እንዲያስተምሩ ሲያዛቸው አቡነ ዐሥራተ ወልድን ደግሞ ወደ ጫራ ምድር ሔደው በዚያ ወንጌልን ይሰብኩ ዘንድ አዘዛቸው። ኹለቱም ቅዱሳን እርስ በርሳቸው በመንፈሳዊ ሰላምታ እጅ ተነሣሥተው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ተለያይተው ወደታዘዙባቸው ቦታዎች ሔዱ። አባታችን ዐሥራተ ወልድም እየጸለዩ ስምንት ዓመት ከስድስት ወር በርበር በምትባል በረሓ ውስጥ ሳሉ በአራቱም ማዕዝናት እየተዘዋወሩ በምሥራቅ አንድ ሽህ በምዕራብ አንድ ሺህ በሰሜን አንድ ሺህ በደቡብ አንድ ሺህ ጊዜ ይስግዱ ጀመር የክብር ባለቤት #ጌታችን_አምላካችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም በዚህ ጊዜ ተገልጦላቸው "ወዳጀ ዐሥራተ ወልድ ሆይ! ለምን ሥጋህን እንደዚህ አደከምህ" አላቸው አባታችንም " #ጌታ ሆይ! ኃይላቸውን በስግደት ቀንና ሌሊት በመትጋት የሚያደክሙ በመንግሥትህ አይደሰቱምን በዓለም የደከመ ለዘለዓለም ይድናል ጻድቃን ዳግመኛም በብዙ ድካምና መከራ ወደ #እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል" እንዳለ በማለት መለሱ። #ጌታችን_መድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ "ድካምህ በከንቱ አትቀርም በሰማያውያን መላእክት በተባረኩ ጻድቃን ድል በነሱ ሰማዕታት ንጹሐን በሚሆኑ ደናግል በፍጹማን መነኰሳት ፊት የድካምህን ዋጋ እሰጥሃለሁ። እንግዲህ ከዛሬ ጀምረህ ወደ አዘዝኩህ ቦታ ሒድ፤ "መንግሥተ ሰማያትም ቀርባለች" እያልህ የመንግሥትን ወንጌል አስተምር፣ ኃይሌ ከአንተ ጋር ይኖራልና" ብሎ አዘዛቸው።

🌹 #ጌታችን ይህን ሲነግራቸው አውሎ ነፋስ መጥቶ ጉርብ ወደ ምትባለው ዋሻ ወስዶ አደረሳቸው። በሥራ የሚኖሩ የሀገሩ ሰዎችም የአባታችን ዐሥራተ ወልድን መምጣት ሰምተው ተቆጥተው በአባታችን ላይ በጠላትነት ተነሡባቸው፣ ጋሻቸውንና ጦራቸውን ይዘው የመጡ ቢሆንም አባታችን ግን የከበረች የ #ክርስቶስን ወንጌል አስተምረው አሳምነው አጠመቋቸው። የጫራንም ሕዝብ አምስት ዓመት ካስተማሯቸው በኋላ ዳግመኛ የሻሽናን ሕዝብ ያስተምሯቸው ዘንድ የ #እግዚአብሔር መልአክ እየመራው ሻሽና አደረሳቸው። አባታችን በዚያም የሀገሩን ሕዝብ አስተምረው አጠመቁ።