ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
6.83K subscribers
1.22K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#አሰሮ_ለሰይጣን_ (ሰይጣንን አሰረው) #አግዐዞ_ለአዳም(አዳምን ነጻ አወጣው)፤ #ሰላም (ሰላም ፍቅርና አንድነት) እምይእዜሰ (ከዛሬ ጀምሮ) #ኮነ (ኾነ) #ፍሥሐ_ወሰላም (ሰላምና ደስታ ኾነ)፡፡ ፠ በማዕረግ ከፍ ያለው ካህንም፤ ከላይ ያለውን ዐውጆ ሲያበቃ «#ነዋ_መስቀለ_ሰላም» እያለ መስቀል ሲያሳልም ካህናትና ሕዝቡም «#ዘተሰቅለ_ቦቱ_መድኀኔ_ዓለም» እያሉ ይሳለማሉ፡፡ በማዕረግ ከፍ ያለው ካህንም፤ «#እግዚአብሔር_ይፍታ» ይላል፡፡ ግብረ ሕማማት ሲነበብበት ከሰነበተው ጠበልም ይረጫል፡፡ የተረፈውንም ጠበል ሕዝቡ ለበረከት ወደየቤቱ ይወስደዋል፡፡ ፠ ከዚያም ልኡካኑ ለቅዳሴ ይዘጋጃሉ፤ ሊቃውንት ደባትር መዘምራንም ምስማክ፥ መወድሱን ካዜሙ በኋላ በመቋሚያ ይዘምሙታል፡፡ አያይዞም በዓመት ፫ት ጊዜ የሚዘመረውን «ይትፌሣሕ ሰማይ …» የተባለውን መዝሙር ቃኝተው ከዘመሙ በኋላ «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፤ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ = ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካውን ታደርጋለች፡፡» እያሉ ይጸነጽላሉ፡፡ አያይዘውም የመዝሙሩን ሰላም (ፍጹመ ንጉሠ ኰነንዎ …)ን ይጸፋሉ፡፡ ፠ ወዲያው መንፈቀ ሌሊት ሲሆን ቅዳሴ ተቀድሶ ይቈረባል፡፡ ከዚያም ዕጣነ ሞገር = በዕጣን ፈንታ ቅኔው ተቁሞ ሠርሖተ ሕዝብ = የሕዝብ ስንብት ከሆነ በኋላ ለመፈሰክ ሕዝቡ ወደየ ቤቱ ይሔዳል፡፡ #የትንሣኤ_አከባበር_በዕለቱ ፠ ሕዝቡ በየቤቱ፣ ካህናቱም ከቤተ ክርስቲያን በየአካባቢው ባህል በተለይ አክፋዮች መጀመሪያ ቅባት አጥቶ የሰነበተ ሆድ እንዲለሰልስ የተሞቀ የተልባ ጭልቃ ይጠጣና የሹሮ ወጥ በቅቤ፣ በአይብ፣ የበረታም በዶሮ ወጥ፣ ወይም በበግና በከብት ሥጋ ወጥ ይገድፋል፡፡ ፠ በእርጎ፣ በአይብ የተደራረበ እንጀራ በግፍልፍል የሚገድፉም አሉ፡፡ በአንዳንድ የሰሜኑ ሀገራችን ደግሞ የተልባ፣ የኑግና የሱፍ ጭልቃ ከማር ጋር ታሽቶ ከተጠጣ በኋላ በእርጎ፣ በአይብ፣ በወተት፣ በቅቤና ድልህ በተቀባ እንጀራ ይገድፋሉ፡፡ ፠ በዋልድባ ገዳም ከዓመት ዓመት ምግቡ ቋርፍ ብቻ መሆኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ለትንሳኤ በዓል ከሃገራችን ካሉ ቦታዎች በተለየ ሁኔታ በዓሳ ይገድፋሉ፤ ዓሳው ሲዘጋጅም ሙሉ ለሙሉ ሆድ ዕቃው ሳይወጣ ተወቅጦ ነው፡፡ ፠ ሊነጋጋ ሲልም ከጾሙ አጋማሽ ጀምሮ ወንዱ ለእርድ የሚሆነውን ሰንጋውን፣ ሲቀልብ፣ በጉን ፍየሉን ሲሞክት ዶሮውን ሲመርጥ፣ ሲገዛ ሲለውጥ ሰንብቶ ነበርና በግልም በኅብረትም ያ ይታረዳል፡፡ ፠ ሴቶችም ቅቤውን ሲያነጥሩ፣ በርበሬውን ሲደልሁ፣ ለእንጀራና ዳቦ የሚሆነውን ዱቄት ሲያዘጋጁ ለጠላ የሚሆነውንም እኸል ሲያሰናዱ አይቡን በልዩ ልዩ ቅመም መጣጣ ሲያደርጉና ባዶ ማለትም ወገሚት የተባለውን በሽንኩርት፣ በጤና አዳም፣ ጣዕሙ እንዳይለወጥ ሲቀምሙ፤ እንደ መከለሻ፣ ጥቁር አዝሙድ የመሳሰሉትንም ሰንብተው ዝግጅቱ ተከናውኖ ነበር፡፡ ፠ ጧትም ይህ የመግደፊያ ዝግጅት በየቤታቸው ለሌላቸው ድኾች በየመንደሩ እየተዞረ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባለ ከሥጋውም፣ ከአይቡም፣ ከቅቤውም ከመጣጣሙም፣ ከእርጐውም ይታደላል፡፡ ፠ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባባለ በመጠራራት ዐብሮ ሲበላ ሲጠጣ ልዩ ልዩ ጨዋታ ሲጨዋወት ለንስሐ አባትና ለሽማግሌዎች፤ ለወላጅ አባትና እናት፤ ለወንድምና ለእኅት ለወዳጅ ዘመድም የአክፋይ ዳቦ፣ ወይም የሥጋ ወጥና የድሮ ወጥ፣ ግፍልፍል ሲወስድ ይሰነብታል፡፡ ፠ የቻለም ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ እየተገባባዘ በዓሉን በፍስሐና በሐሴት ሲያከብር ይከርማል፡፡ ‹‹ሕያው ተንሥአ እሙታን (ሕያው ከሙታን ተነሣ፡፡)›› /ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ/ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ ::
#share
Contact: https://t.me/finotehiwot1927
.Facebook...
https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
.YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w,
.Telegram...
https://t.me/medihanaelem
http://tiktok.com/@finotehiwot
www.finotehiwotsundayschool.com
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
Telegram https://t.me/medihanaelem