ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#መስከረም_15

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን #የቀዳሜ_ሰማዕት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ ፍልሰተ አፅሙ ነው፣ #የአቡነ_ገብረ_ማርያም_ዘሐንታ እና #አቡነ_ጴጥሮስ_ዘሃገረ_ጠራው ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

ቀዳሜ_ሰማዕት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ

መስከረም ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ ለሆነ ለቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ።

ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ክርስትናን በሰማዕትነት በማሳደግ የመጀመሪያ ምሳሌ የሆነ ሊቀ መምህር ነው።

የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ ። (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ ። የወቅቱ ታላቅ መምህር ገማልያል ይባል ነበር። ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፭፥፴፫ ላይ ተጠቅሷል ። በትውፊት ትምህርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን፣ ጳውሎስን ፣ ናትናኤልን፣ ኒቆዲሞስን...) አስተምሯል ። በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር ፤ በፍጻሜውም አምኗል ። ቅዱስ እስጢፋኖስም ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ ። ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር ።

በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ ። ከ #እግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ። ለስድስት ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ ። ለስድስት ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በኋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተጠመቀ ። በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምህሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው ። "ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው ።" በሚል ላከው ። ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ እጅ ነስቶ ተማረ ። (ሉቃ. ፯፥፲፰) በዚያውም የ #ጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ ።

#ጌታም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው ፤ አጋንንትም ተገዙለት ። (ሉቃ. ፲፥፲፯) ቅዱስ እስጢፋኖስ #ጌታችን_መድኃኔ_ዓለም ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ ፤ ምሥጢር አስተረጐመ ። #ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኳል ። በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ጵጵስናን) ተሹሟል ። በበዓለ ሃምሳም #መንፈስ_ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት፣ ምሥጢርም የተገለጠለት የለም ። በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ ።

በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በ #መንፈስ_ቅዱስ ምርጫ ሰባቱ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር ። አልፎም የስድስቱ ዲያቆናት አለቃ እና የስምንት ሺው ማኅበር መሪ(አስተዳዳሪ) ሆኑዋል ። ስምንት ሺህ ሰውን ከአጋንንት መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አባቶቻችን መጠየቅ ነው ። አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለደኅንነት ማብቃት እንኳን እጅግ ፈተና ነው ። መጸሐፍ እንደሚል ግን #መንፈስ_ቅዱስ የሞላበት ማኅደር #እግዚአብሔር ነውና ለርሱ ተቻለው ። (ሐዋር፣ሥ፡፮ ቁ፡፭)

አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ሲባል እንደዘመኑ ይመስለን ይሆናል ። እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው ። ዲቁና ለእርሱ " በራት ላይ ዳርጎት" እንጂ እንዲሁ ድቁና አይደለም ።

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከ #ጌታችን ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺውን ማኅበር እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት "እጠፋ እጠፋ" አለች ። በዚህ ጊዜ "ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው " ብለው አይሁድ በማመናቸው አልቀረም ገደሉት ። እርሱ ግን ፊቱ እንደ #እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው ። በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት ። ደቀ መዝሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት ።

ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ በኃላ ይህም እንዲህ ነው ከአረፈበት ጊዜ ብዙ ዓመቶች ከአለፉ በኋላ ሦስት መቶ ዓመት ያህል ከዚያም የሚበዛ ጻድቁ ቈስጠንጢኖስ ሲነግሥ የቀናች ሃይማኖትም ተገልጣ የሕያው #እግዚአብሔር አምልኮት በሁሉ ሲዘረጋ ያን ጊዜ የቅዱስ እስጢፉኖስ ሥጋ በአለበት አቅራቢያ የገማልያል ቦታ በትምባል በኢየሩሳሌም በአንዲት ቦታ አንድ ሰው ይኖር ነበር። የዚያም ሰው ስም ሉክያኖስ ነው ተጋዳይ የሆነ እስጢፋኖስም ብዙ ጊዜ በሕልም ተገለጠለት እንዲህም ብሎ አስረዳዉ እኔ እስጢፋኖስ ነኝ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሮ አለ።

ያም ሉክያኖስ የሚባል ሰው የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነው መጥቶ በራእይ ያየውን ይህን ነገር ነገረው ኤጲስቆጶሱም ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያን ጊዜም ሁለት ኤጲስቆጶሳትን፣ ካህናትንና፣ የቤተ ክርስቲያንን ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋራ ይዞ ተነሣ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ወዳለበት ወደዚያ ቦታ ደርሰው ሊቆፍሩ ጀመሩ ታላቅ ንውጽውጽታም ሆነ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ በውስጡ ያለበት ሣጥን ተገለጠ ከእርሱ እጅግ በጎ የሆነው የሽቱ መዓዛ ሸተተ።

በሰማያት ለ #እግዚአብሔር ምስጋና ሆነ በምድርም ሰላም ለሰው ነፃነቱ ይሰጠው ዘንድ በጎ ፍቃድ እያሉ ሲያመሰግኑ የመላእክትን ቃሎች ሰሙ። እንዲህም መላልሰው ሦስት ጊዜ አመሰገኑ ኤጲስቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን ፊት ለ #ጌታ ሰገዱ ከዚያም በኋላ ወደ ጽርሐ ጽዮን እስኪያደርሱት ብዙ መብራቶችን አብርተው በመያዝ በማኀሌት ምስጋና እየዘመሩ ተሸከሙት።

ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ በኢየሩሳሌም ነዋሪ የሆነ የቊስጥንጥንያ ተወላጅ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር ለቅዱስ እስጢፋኖስም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው ወደርሷ ወስደው አኖሩት ከአምስት ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ አረፈ ሚስቱም በቅዱስ እስጢፋኖስ አስከሬን ጕን ቀበረችው። ከሌሎች አምስት ዓመቶችም በኋላ የእለእስክንድሮስ ሚስት የቧላን አስከሬን ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሔድ አሰበች ባሏንም ወደ ቀበረችው እርሱ ባሏ ወደ ሠራት ቤተ ክርስቲያን ሔደች የባሏ ሥጋ ሣጥን ግን የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በያዘ ሣጥን አምሳል ነበር በ #እግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ተሸከመችው ከዚያም ወደ ቊስጥንጥንያ ልትጓዝ በመርከብ ተሳፈረች።

በመርከብ ስትጓዝ ከሣጥኑ ጣዕም ያለው ምስጋናን የምትሰማ ሆነች እጅግም አድንቃ ያን ሣጥን ልታየው ተነሣች በውስጥ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት ሣጥን እንደሆነ ተረዳች ይህም የሆነው ክብር ይግባውና በ #እግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነም አወቀች ወደ ኢየሩሳሌም ትመለስ ዘንድ አልተቻላትም ይህንንም ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት ልዑል #እግዚአብሔርን አመሰገነች።
በአፏና በጆሮዎቿ ጸበልን ጨመሩባት፡፡ በፊቷም ‹‹እፍ›› አሉባትና ‹‹በ #ጌታዬ_በፈጣሪዬ_በኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይል ተነሺ›› አሏት፡፡ ያንጊዜም አፈፍ ብላ ከሞት ተነሣች፡፡ አባታችን ከሞት ያስነሷቸው ሰዎች እንዲሁ በጣም ብዙ ናቸው፡፡

27 ዓመት ሙሉ ሆዱን የታመመ አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አቡነ ገብረ ማርያም በመምጣት ጉዳዩን ሳይነግራቸው አንድ ቀን ቆየ፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን የመጣበትን ጉዳዩን በጠየቁት ጊዜ ‹‹አባት ሆይ ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ ታመምኩ፣ እህል አልበላም ውኃም አልጠጣም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ሆዱን ይዘው በእጃቸው አሻሹትና ምራቃቸውን ቀቡት፡፡ በዚህም ጊዜ በሆዱ ውስጥ ልዩ ልዩ ዓይነት ድምፆች ተሰሙ፡፡ በውሻ ድንፅ አምሳል፣ በድመት ድንፅ አምሳል፣ በዝንጀሮ ድንፅ አምሳልና በቁራዎቸ ድንፅ አምሳል ጮኸ፡፡ አባታችንም ልጁን ‹‹ልጄ ሆይ #እግዚብሔር አድኖሃልና ወደ ቤትህ ተመለስ›› አሉት፡፡ ልጁም ‹‹አባቴ ሆይ ተመልሼ ወደቤቴ አልገባም እስከ ዕለቴ ሞቴ ድረስ አልመለስም ከአንተም አልለይም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹በዚህ መኖር ክፍልህ አይደለምና #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለፈወሰህ ወደ ቤትህ ተመለስ›› አሉት፡፡ በደስታም ወደ ቤቱ ሄደና በሌላ ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር መጥቶ አባታችን ያደረጉለትን ተአምር ለሕዝቡ ሁሉ መሰከረ፡፡

አቡነ ገብረ ማርያም በእንዲህ ዓይነት አገልግሎት በተአምራታቸው ድውያንን እየፈወሱ ሙታንን እያስነሡ በወንጌል ቃል የነፍስን ቁስል እየፈወሱ የ #ጌታችንንም መከራውን እያሰቡ ራሳቸውን ከመከራው ተሳታፊ በመሆን ብዙ ከደከሙ በኋላ በሥጋ ሞት ከማረፋቸው በፊት ቅዱሳን መላእክት ነጥቀው ገነትንና ሲኦልን አሳይተዋቸዋል፡፡ #ጌታችንም በመጨረሻ ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ከፍጹም ድካምና መታከት ከኃዘንም ታርፍ ዘንድ ወደ ፍጹም ደስታና ወደ ዘላለማዊ ዕረፍት ወደ እኔ ና›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹ #ጌታዬ ሆይ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ?›› ቢሉት #ጌታችም ብዙ አስደናቂ ቃልኪዳኖችን ሰጣቸው፡፡ ‹‹እንደፈጠርኩህ አግኝቼሃለሁና ክብርህ እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ይሁንልህ›› አላቸውና በቅዱሳን እጆቹ ዳስሷቸው ቢስማቸው ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለይታለች።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ በአቡነ ገብረ ማርያም እና አቡነ ጽጌ ድንግል ጸሎት ይማረን በረከታቸውም በእኛ ላይ ይደርብ ለዘላለሙ አሜን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ጴጥሮስ_ዘሃገረ_ጠራው

በዚችም ቀን ደግሞ ጠራው ከሚባል አገር ለከበረ ጻድቅ አባት አባ ጴጥሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ቅዱስ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ለ #እግዚአብሔር የተሰጠ የስእለት ልጅ ነው። በአደገም ጊዜ ለታላቅ ተጋድሎ ክልቡ በቆራጥነት ተነሣ በቀንና በሌሊትም በጾም በጸሎት ተወስኖ ሁል ጊዜ #እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሆነ። ሰው የሚመገበውንም ምንም አይመገብም በዱር ያገኘውን ጥቂት ሣርን ይመገባል እንጂ።

ደገኛው ምግቡ ግን ክብር ይግባውና የ #ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ስም ማመስገን ነው። በዚህም ምግባቸው የ #እግዚአብሔር ምስጋና የሆነ ቅዱሳን መላእክትን መሰላቸው።

አሎን በሚባል የወንዝ ውኃ ላይም ይመላለስ ዘንድ ተገባው እግሮቹም አይርሱም ሥጋ እንደ ሌለው መንፈስ እስከ ሚሆን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከችግር ብዛትና ከሚለብሰው የብረት ልብስ ክብደት የተነሣ ሥጋው እጅግ ደርቆ የረቀቀም ሁኖ ነበርና በእንዲህ ያለ ተጋድሎም #እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ ወደርሱ ሔደ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም_15 እና #ከገድላት_አንደበት)