ግጥም
4.26K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ቃል_ብዬ_ጠራሁሽ

ስላንች ለመፃፍ ብእር እቀርፅና
ቀለሙን አቅልሜ ፈቅፍቄ ብራና

ፊደልና ቃላት እንደልጅ እያማጥኩ
ሀረግ እየመዘዝኩ ምሳሌ እየጠቀስኩ

ቃል ባጣው ልሳኔ ስፅፍ ውዬ አድሬ
ገልጨሽ ሳይበቃኝ ትደርቃለች ብእሬ

ደግሞ ተመልሼ................

ደሜን አንጠፍጥፌ ቀለሙን አቀለምኩ
አጥንቴን ፈቅፍቄ ላንች ብእር ቀረፅኩ

ብእሬን በደሜ ነክሬ ሳወጣው
አንችን እገልፅበት ቅንጣት ቃላት አጣው

ለካንስ ቃልዬ!!!

በፍቅር ነሁልሎ መንፈስ ከደከመ
ናፍቆት አገርጥቶት ልብ ከታመመ

እንኳን ቃል ተዋቅሮ ቅኔ ሊመሰጠር
ደግሞ ስንኝ ሁኖ ግጥም ሊደረደር

ደህና አደርክ ሲባል ለእግዚአብሄር ይመስገን
አንደበት ቃል ያጣል ሲመርቁት ለአሜን

ለዛ ነው ቃልዬ!!!

መግለጫ ቃል ባጣ እልፍ ዘመን ሙሉ
የብራናዬ ገፅ ግራ ገብቶት ውሉ

እየደጋገምኩኝ የፃፍኩት አንድ ቃል




ብቻ ይላል

ሌላ ቃል ተገኝቶ
ወይ ልሳንህ ፈቶ

ህቡእ በሆነ ቃል እስከምትገልፃት
ቃልህ እሷ ነችና ቃሌ ብለህ ጥራት

እናም አንች ቃሌ ነሽ ሀረግና ስንኝ
ካጠገቤ ሁነሽ ሰርክ የምትርቢኝ

እናም የኔ ንግስት

ገፅሽን አድምቄ በልቤ መዝገብ ላይ
ቃሌ ብዬ ፃፍኩሽ ቃል አጣው ቃሌ ላይ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
11👏4👍1🔥1🥰1
#ዘርን_ለማስቆጠር

እንጋባ አትበይኝ ግራ ገብቶኝ ሳለ፤
ተጋቦቶ ለመውለድ ነፃነት የት አለ?
ወልዶ  ለመከበረ ጋብቻ ቅዱስ ነው፤
የሚወለደው ልጅ መኖሪያ ከሌለው!
በይ እስኪ ንገሪኝ? አንቺ ግራ ጎኔ፤
በነፃነት አድጎ ሰው በመባል ቅኔ፤
በኢትዮጵያዊነት ካልኮራ ዓይኔ በዐይኔ፤
ለመሳቀቅማ አይበቃም ወይ የእኔ።
ሀገርን ሳልሰራ ሰው መሆን ሳይቀድም፤
ዘርን ለማስቆጠር እኔስ ልጅ አልወልድም።
         @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
    ስንታየሁ ሀብታሙ
11👏9👍1
#ፍቅር_አለቀሰ

ፍቅርን ስፈልገው ቀናቶች አለፉ
ፈለግኩት ፈለግኩት ድካም ሆነ ትርፉ
አጋጣሚ ሆኖ ተደብቆ አየሁት
አላምን ስላልኩኝ ምክንያቱን ጠየኩት
"ፍቅር አንተው ነህ ወይ?" ብዬ ብጠይቀው
ምንም መልስ ሳይመልስ እንባ ተናነቀው
ግራ ገባኝና ባግራሞት አየሁት
ቆይ ፍቅር ደስታ ነው ሲባል ሰምቻለሁ
ታድያ ያንተ ለቅሶ ከየት የመጣ ነው?
ፍቅርም መለሰልኝ አይኑን መሬት ተክሎ
መናገር ጀመረ ቃላትን ቀጣጥሎ
"ደስታማ ደስታ ነኝ ላወቀው ሚስጥሬን
ከደስታም በላይ ነኝ ከተረዱኝ እኔን
ያስለቀሰኝ ነገር ሆድ ሆዴን ያስባሰው
በኔ ስም መነገድ መቸ አቆመ ሰው
አፈቀርኩሽ ብሎ ሲዋሻት በኔ ስም
ማሬ ውዴ ብላ ከድታው ስትሄድ እሷም
በኔ ሲጫወቱ የሀሰት ጨዋታ
በኔ ሲባልጉ በኔ ስም ሲምታታ
በውሸት ዓለም ሆነው በኔ ስም ሲጠሩ
እንዴት አላነባ ካልረባ ነገሩ"
ብሎ መለሰልኝ ፍቅር በቀስታ
አንገቱን ቢያስደፉው የሀሰት ጨዋታ::
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
21👏9🥰32🔥2👍1
ጭር አለ ከተማው ጭር አለ መንገዱ
ያ ስምንተኛው ሽህ ተገለጠ ጉዱ
ሰው ሁሉ ተሳቆ ፈርቶት አንዱን አንዱ
እስከዚህ አይሎ ሰው ከሰው ሽሽቱ
ክተት ብሎ ገባ ሁሉም በየቤቱ
ጭር አለ መንገዱ ጭር አለ ከተማው
ክፉ ዘር ሲበዛ ይህን ነው የምንሰማው
እንለያይ ብለን ስንጮህ ስንፎክር
በዘር ተለያይተን አንዱ አንዱን ሲያባርር
ታሪክ እያዛባን ነገር ስንመነዝር
ኮሮና እብዱ መጣ እንደ ከብት የሚያጉር።
እንለያይ ብለን ይሄው ተለያየን
መሸሽ ጀምረናል ሰውን ሰው እያየን።
ሕሊናችን ሞቶ መለያየት ወደን
ሰው ሰውን ሸሸ በባይረስ ተገደን
ያ ስምንተኛው ሽህ ተገለጠ ጉዱ
ጭር አለ ከተማው ጭር አለ መንገዱ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
መምህር ግርማ
👍42🫡2
ነድፋኛለች ብዬ - በውበቷ ምትሃት፣
በይፋ ከስሼ- ፍርድ እንዳላቀርባት
ለካስ እሷ ራሷ - መፅሐፍ ገላጭ ናት

ከፊት እሷን መሳይ - የጠይም ወላላ፣
በድንቡሽ ብርጭቆ - ወይን እየተሞላ፣
እሱን እየጠጡ -
ለሰስ ባለ ዜማ - እየተመሰጡ
ደግሞ በመሃሉ - እየተቃበጡ
ፍቅር ፍቅር ብቻ - እየመሰጠሩ፣
ዓለምን ረስተው - ምናለ ቢኖሩ፣

ጨለምለም ባለ የብርሃን ድባብ ውስጥ፤
እልም ብሎ መጥፋት - ጭልጥ ብሎ ቅልጥ፤
በልቤ ትርታ - በነፍስ ቋንቋዬ፣
እየደባበስኳት - ምነ ባዜምኩላት - አንቺ ሆዬ ብዬ፤
10👏2🔥1
#ስጠብቅሽ_ልኑር

ቀናቶች ቢረዝሙ ቢቆጠሩ አመታት
ግዜ ቢለያየን ቢያልፉብን ዘመናት
ከልብሽ ብጠፋም ከትዉስታሽ ጓዳ
በስቃይ ታስሬ በናፍቆት ብጎዳ
ህልሜም ባይሳካ የሆዴን ባላገኝ
በደስታየ ዘመን ባይተዋር ቢያረገኝ
ግዴለም ችላለሁ ሁሉን ነገር ችዬ
እጠብቅሻለሁ ልቤን አባብዬ
የሀሳብ በረዶ ይጠለቅ በአናቴ
ይደንዝዝ አካሌ ይድከሙ ጉልበቴ
ትመጪ እንደሁ እያልኩ በተስፋ ልጠብቅ
እልፍ ግዜ ይለፍ ወዜ ሁሉ ይድቀቅ
ምን ያደርግልኛል ካንች ወድያ ኑሮ
ፍቅርሽ ይበቃኛል የስንቅሽ ቋጠሮ
በትዝታሽ ዋሻ እራሴን ደብቄ
በምናቤ ስየ ፍቅርሽን ሰንቄ
እጠብቅሻለሁ በተሰጠኝ እድሜ
ባንች ናፍቆት ፍቅር ካልሞትኩኝ ታምሜ
.....አዎ...
ስጠብቅሽ ልኑር ሳለሁ በህይዎቴ
ፍቅርም ባንች ይብቃኝ ይምከን ፍላጎቴ ::
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
      ናቲ ጥላሁን
19🥰2👍1
#ስሞት_አታልቅሱ!

ጎርፍ በላዬ ሲሄድ ዝም ካላችሁኝ፤
ምጠጣው አጥቸ ከንፍሬ እንዲህ ደርቆ ካላጠጣችሁኝ፤
ስትበሉ እያየሁ ወስፍቴ እየጮከ ካላበላችሁኝ፤
ምለብሰው አጥቸ እንዲህ ስንቀጠቀጥ፤
ልብስክን በሳጥን ቆልፈህ ካስቀመጥህ፤
ለምን ትጮሀለህ?፤
ለምን ታነባለህ?፤
ለምንስ ደረትክን ትደቁሰዋለህ?፤
"ማን ገደለው?" ቢሉህ እስኪ ማን ትላለህ?፤

እንባ ምን ሊጠቅመኝ እንባ ምን ሊፈይድ?፤
ያለቀሰ ሳይሆን በቁም ሚረዳ ነው ባምላክ የሚወደድ፤

እናልህ ወገኔ...
ደረትክን አትድቃ ሙሾው ገደል ይግባ፤
ገለከኝ አታልቅስ ይቅርብኝ ያዞ እንባ።
ከልብ ካዘናችሁ በነፍሴ ድረሱ፤
እናተ ገላችሁ ስሞት አታልቅሱ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
15👍1🔥1
#ምን_ተሰማሽ_ውዴ?

ውብነትሽም ፈክቶ ደምቀሽ በደስታ፣
መጠውለግ እንዳለ ተዘናግተሽ ለአፍታ፣
በፍካትሽ ኮርተሽ እብሪት አንቀባሮሽ፣
ነገሽን በመርሳት ዛሬን ተመክተሽ፣
መጸውለግ ሲመጣ ጊዜውን ጠብቆ፣
ወዝሽ ላይሰነብት ላይሸኝሽ አርቆ፣
ሁሉን በውበትሽ፣
ስንቱን በፈገግታሽ፣
ሴሰኛን በዳሌሽ፣
ገፍትረሽ በጡትሽ፣
ሰካራም በጠላሽ፣
ቅብጥብጥ! ሲያረግሽ፣
አስቀሽ አላግጠሽ ውበት አመፃድቆሽ
ምን ተሰማሽ? ውዴ ዛሬ ሲሸሽ ጥሎሽ!?
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍144🥰1
#የንስር_እድሜ_ይስጥሽ

ይታደስ አካልሽ - በሺ አመት ዘመንሽ፣
ከርጅና ‘ሚመለስ - የንስር እድሜ ይስጥሽ፣
እዉነተኛዋ ሰው - ካምላኬ ቀጥለሽ፣
የህይወቴ ህይወት - እማ የምወድሽ፣
የኑሮየ ድምቀት - ድንቅ ስጦታ ነሽ::

የመኖሬ ምክኒያት - ምንጯ የህይወቴ፣
የሃሴት የፍቅር - የሰላም ሙላቴ፣
ቀድመሺኝ የመጣሽ - ገፀ በረከቴ፣
ደስታሽ ደምቆ ይብራ - በ ጉሙ ህ-ይወቴ      
እማ ዉዷ እናቴ! . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .
መጠማት መራብሽ - ማጣት መራቆትሽ፣
ከሰው በታች ሆነሽ - ክብርሽን ማጣትሽ፣
እማየ ለኔ ነው - ለደካማዉ ልጂሽ፣
ከቶ በምን ቋንቋ - በምን ቃል ልግለፅሽ? እንዴት ልመልሰዉ - በዝቶብኛል ፍቅርሽ!

ይታደስ አካልሽ - በሺ አመት ዘመንሽ!
ከርጅና ሚመለስ - የንስር እድሜ ይስጥሽ!
ከዚህ በላይ እማ - ምን ቃል አለኝ ልጅሽ! . . . . . . . . . . . . . . .

እማ! . . .እማ!
ጭንቀትሽ ተጥሎ - ሸክምሽ ተንከባሎ፣
አለም ላንቺ ክብር ጎንበስ ቀና ብሎ፣
መቸገርሽ ቀርቶ - ቤትሽ ጓዳሽ ሞልቶ፣ ፊትሽ በፈገግታ - በደስታ አብርቶ፣
ጉድለትሽ ድካምሽ- እንግልትሽ ቀርቶ፣
የህይወትሽ ብርሃን - ይታይ ለአለም ፈክቶ፣
በረከት ረድኤቱን - አምልቶ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
14👍1🥰1
ማን በገላገለኝ? የእጄን ሠዓት ሠብሮ
በምናልባት አገር
በምናልባት ኑሮ
የመጣው ይምጣ እንጂ
ማን ያቅዳል ደፍሮ
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
👍141
#ወዴት_ነሽ?

የት ብዬ ልፈልግ ወዴት ነሽ ሄዋኔ፣
የአጥንቴ ክፋይ የሰራሽ ከጎኔ፣

ከበረሀው ካለሽ ንገሪኝ መጣለው፣
አሸዋ ንዳዱን ይሁን ችለዋለው፣
ውሀ ጥም ረሀቡን ባንቺ ረሳዋለው፣
ቆላም ሁኚ ደጋ ጥሪኝ እዘልቃለው፣

ቤተመንግስት ሆኚም ብቻ አለው በዪኝ፣
አልፌ ገባለው ህጉ እንኳ ቢያግደኝ፣
እንደ ወንጀለኛ በእስር ቢያስቀጣኝ፣
ይገደል ተብሎ ሞት ቢፈረድብኝ፣
አንዴ ልይሽ እንጂ ይህ አያሳስበኝ፣

ስፈልግሽ ስውል ሰርክ እያካለልኩሽ፣
ባክኜ እንዳልቀር ጥሪኝ አለው ብለሽ፣

ሄደሽም ከሆነ ወደመጣሽበት፣
መኖርሽ ካበቃ ከፍጥረታት ህይወት፣
ንገሪኝ መጣለው ውዴ ካለሽበት፣
አፈር ከጋረደው ከአካልሽ ቅሪት፣
ደራሲው እንዳለው ፍቅርን እስከ ሞት፣
እኔም ነፍሴ ትለፍ ቁጭ ብዬ ካንቺ ሀውልት፣

ጠቁሚኝ ስፍራሽን ወዴት ነሽ የት ልምጣ፣
አቀበቱን ልውረድ ሽቅቡንም ልውጣ፣
ልቤ ለብቻውን ሚያረገውን አጣ፣

አንቺንም እንደኔ ብቻነት ከጎዳሽ፣
አብሬሽ እንድኖር ንገሪኝ ወዴት ነሽ፣
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
12👍3👏3👌1
#ከትላንት_ሳንማር

ሰው ከሰው ተኳርፎ ዘመኑ ቢታደስ
አሮጌ ዓመት ወርዶ አዲስ ዘመን ቢነግሥ
እድሜ ቁጥር እንጂ ቢደመር ቢቀነስ
እኛ ሳንታረቅ እንቁጣጣሽ ቢደርስ
ፍቅር በሌለበት ውብ ድግስ ቢደገስ
የዶሮ የበጉ የበሬው ደም ቢፈስ
የከንቱ ከንቱ ነው ፍቅር ካልታደሰ
አንዱ የአንዱን ጎጆ ከፍቶ እያፈረሰ
መተሳሰብ ሳይኖር ልባችን ሳይቀና
አዲስ ዓመት መጣ ዞሮን እንደገና
ከትላንት ሳንማር በስህተት ተዘፍቀን
በእንቁጣጣሽ ዜማ እንቁ እንናፍቃለን።
       @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
11👍1🔥1
#ስላንቺ_ልንፏቀቅ

ሰወች ሳይገባቼው ሚስጥሩን ሳያቁ :
ከእሷ ምን አይቶ ነው ሲሉ ቢደነቁ:
አንቺ ግን አደራ ውዴ የኔ ፍቅር:
ጆሮሽን አትስጪ ለሚባለው ነገር:
ከጎንሽ ነኝ ዛሬም አርቅም ያንቺ አጋር:
ፍፁም አያውክሽ አሉባልታ ወሬ:
እኔ አልለውጥም ዛሬም ያውነኝ ፍቅሬ:
መከራ ሳይገርፍሽ ክፉ ቀን ሳይመጣ:
እየተሳሳምን ከሰፈር ስንወጣ:
ትዝ ይልሻል ያኔ?????????
አንድ ቁጥር ነበርን ስትቆሚ ከጎኔ:
ተቃቅፈን ስንዘምት በዚሁ ጎዳና:
እንዳላሉን ያኔ ፍቅራቼው ሲያስቀና:
እንዳ ባወሩበት በዛው ምላሳቼው:
አሁን ቢሞክሩ ሊያረጉኝ የራሳቼው:
ውዴ የኔ ፍቅር እኔን ሰሚኝ እማ:
ፈልገሽ ሳትገቢ ለዋጠሽ ጨለማ:
አልሆንህም በቃ ሂድ አትበይ አትፍሪ:
መቼም አልተውሽም አትጠራጠሪ:
እንኳን ትቼሽ ልሄድ ካጠቀብሽ ልርቅ
ቢቻል አጎንብሼ ስላንቺ ልንፏቀቅ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
6👍3🔥1
#ግመልና_መርፌ

ግመል ከሾለከ በመርፌ ቀዳዳ
ያኔ ይሰረዛል የባለጸጋ እዳ
የሚለው ጥቅስ ላይ ገብቶኝ ጥርጣሬ
እግዜሩን ጠየኩት ሽቅብ ተዳፍሬ
እርሱም መለሰልኝ ወርዶ በትህትና
ለአምላክ የሚሳነው ከቶ የለምና
ባይገባኝ ነው እንጂ ነገሩ ተጋርዶ
ኢየሱስ ያለወንድ ሰው ሆኗል ተወልዶ
ለምን ተጠራጠርኩ? በመርፌ ቀዳዳ
የትኛው ይከብዳል? ሀቁን ለሚረዳ?
መወለዱን ካመንኩ ከድንግል በድንግል
ስለምንስ አይሾልክ በመርፌ ውስጥ ግመል።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👏13🔥54🥰1
#ከዚህም_በላይ_ነሽ

ሳላገኝሽ በፊት…
መውደዴን አብዝቼ…
አንቺን እያሰብኩኝ ቆርቤ ከራሴ
‘’እንዴት ነህ?’’ ለሚሉኝ…
አንገቴን ደፍቼ ዝም ነበር መልሴ
ካገኝሁሽ በኋላ…
ማእረግ እንዳገኘ እግረኛ ወቶአደር
ደረቴን ነፍቼ ቀና ብዬ እያየሁ…
‘’ደህና ነህ?’’ ባይሉ እንኳ
‘’ደህና ነኝ!’’ እላለሁ
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ኩራት ደህንነቴ አንች ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
የሰማዩን ቀለም
የውሃውን ጣእም
ያገር ምድሩን ሽታ
ደስ ይበልም አይበል
ይጣፍጥ ወይም ይምረር
መለየት አቅቶኝ ግራ ገብቶኝ ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
ሰማይ…ሰማያዊ ውሃው ቀለም አልባ
ሀገሬ ምታምር ሽታዋ እንዳ'በባ
መሆኑን አወቅኩኝ ሰላም ከኔ አደረ
ይመስገነው ባንቺ ግራ መግባት ቀረ!
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ስሜት ሕዋሳቴ አንቺ ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
የሰኞ ማክሰኞ የመስከረም ጥቅምት
የሴኮንድ መቶኛ የሽራፊ ሰዓት
ልዩነት ሳይገባኝ ቀን በቃል ሳልቆጥር
እንዲሁ እንደዘበት እየኖርኩኝ ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
ጳጉሜ ተጨምራ…
አስራ ሁለት ወራቶች አንድ ዓመት ሞልተዋል
ሰላሳ ቀናቶች ወር ላይ ተዘርተዋል
ሰኞ ላይ ጀምረው እሁድ የሚያበቁ
ሰባት ቀናት አሉ በስም የታወቁ
ሃያ አራት ሰዓት አንድ ቀን ይባላል
ራሱ ሰዓቱ በስልሳ ተከፍሏል
ስልሳውም በስልሳ ሂደት ይቀጥላል
ይህን ታላቅ እውቀት
ይህን ታላቅ እውነት
ይመስገነውና ይሄው ባንቺ አገኘሁ
ይህ ማለት ምንድን ነው?
ቁጥሩ ብቻ ሳይሆን…
ጊዜዬም በራሱ አንቺ ነሽ ማለት ነው!
ሳላገኝሽ በፊት…
ከየትኛው አህጉር
ከየትኛው ሀገር
ከየትኛው አፈር
ከየትኛውስ ዘር
መምጣት መፈጠሬን አላውቀውም ነበር
ካገኘሁሽ በኋላ…
አህጉሩን ለየሁ
ሀገሬን አገኘሁ
አፈሩን ቀመስኩት
ራሴን አየሁት
ይመስገነውና ዘር የማይለያየኝ
ማንነቴን ያወቅኩ ውብ ኢትዮጲያዊ ነኝ!
ይህ ማለት ምንድን ነው?
እኔን ብቻ ሳይሆን
ሀገሬን ያገኘሁ ባንቺ ነው ማለት ነው!!!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ሰለሞን ሳህለ
17
#የእድሜ_ፈረስ

ጠዋት የመሰለን የእድሚያችን ነጸብራቅ
ለካስ መሽቶብናል ከአምላክ ሳንታረቅ
ከሰው ተራ ወርደን ከክብር ከፍታ
ስንባዝን በከንቱ ለምድሩ ደስታ
ለብሰን ተከናንበን የበደልን ኩታ
ጠዋት የመሰለን ድንገት ሆኗል ማታ
የእድሜ ፈረስ ፍጥነት እየገሰገሰ
ከንቱ ውበታች ሳይኖር ፈረሰ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
12🔥1
#ህገ_ሰካራም!

‹‹ነገሩ ነው እንጂ ፤ አረቄ አያሰክርም
አሳሪ ከሌለ ፣ ገመድ ሰው አያስርም
ወዳጅ ዘመድ እንጂ….
አፈር ሰው አይቀብርም ፡፡››
ይላል የሰከረ !
አረቄ ቤት ሆኖ ፣
መተዳደሪያውን ፤ ህግ እያዋቀረ፡፡
እንደሰካራም ህግ፤ እንደስካር ወሬ
አረቄ ቤት ሆኜ...
አረቄ እየጠጣሁ፤ በነገር ሰክሬ
ስለ ሰካራም ህግ ፤ ላውራሽማ ፍቅሬ፡፡

እዚህ አረቄ ቤት...
ከተሰበሰበው ፤ የሰካራም አባል
ስሙን የማላውቀው፤ ‹‹ሰካራም›› የሚባል
አንድ የሰከረ ሰው፤ እንደተናገረው
ሀገርሽ ሀገሬ….
‹‹መልሱን ጠጣንበት›› ፣
በሚለው ህግ ነው ፣ የሚተዳደረው፡፡
‹‹ለመብራት›› እያሉን ፤ ገንዘብ እያዋጣን፤
‹‹ለመንገድ›› እያሉን ፤ ገንዘብ እያዋጣን፤
‹‹ለውሀ›› እያሉን ፤ገንዘብ እያዋጣን
ለምን መብራት ጠፋ?
ለምን ውሃ የለም?
እንዴት መንገድ አጣን? ፣ ብሎ ከመጠየቅ፤
ሳይሻል አይቀርም….
መልሱን ጠጣንበት፤ የሚል ህግ ማፅደቅ፡፡

ወንጀለኛው ሁላ….
ዳኛውን ጠብቆ ገንዘብ ካቀበለ
በ ሺህ ምስክር ፊት…
የመሰረትነው ክስ፤ ‹‹ውድቅ›› ከተባለ
ለምን እዴት? የሚል…
የከሳሽ ጥያቄ ፤መልስ ካልተሰጠው፤
በሰካራም አንቀፅ…
መልሱን ጠጣንበት!
የሚለው ህግ ነው ፤የሚረጋገጠው፡፡
እንደ ህገ መንግስት…
ተፈፃሚነቱ፤ ቢሰራም ባይሰራም
መልሱን ጠጣንበት!
ብሎ ያፀደቀው፤ ህግ አለው ሰካራም፡፡
እንደሰካራም ህግ፤ እንደስካር ወሬ
አረቄ ቤት ሆኜ...
አረቄ እየጠጣሁ፤ በነገር ሰክሬ
እኔን አረቄ ቤት፤ምን እንደወሰደኝ
አረቄ መጠጣት ፤ማን እንዳስለመደኝ፤
አትጠይቂኝ ፍቅሬ፡፡
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በላይ በቀለ ወያ
8👏3👍1🥴1
"ይሄንን ገለባ፣ መሄጃህ ወዴት ነው?
   ብለህ  አትጠይቀው፣
የነገው ንፋስ ነው፣
መንገዱን  የሚያውቀው"
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
በእውቀቱ ስዩም
8👍4👏1
#እንዲህ_ያደርገኛል

እመጣለሁ ብላ የቀጠረችኝ ለት
እንዲህ ያረገኛል
ሰውነቴ ሁሉ ጆሮ ይሆንና
የብናኝ ኮሽታ ገዝፎ ይሰማኛል
ኮቴ እንደመብረቅ
እንደ አንዳች ፍንዳታ
የጆሮዬን ታንቡር ደርሶ ይጠልዘኛል
እመጣለሁ ብላ የቀጠረቺኝ ለት
እንዲህ ያደርገኛል
ጥሞናዬ ረቅቆ መንፈሴን አምጥቆ
የሷን ኮቴ ናፍቆ
የፍቅሬን አካሄድ የሰበር ስካዋን
ከእርምጃዎች ሁሉ ከዳናዎች አውቆ
በናፍቆቷ ደጋን በጉጉት ፍላጻ
ተወርዋሪው ልቤ ተወጥሮ ከረሮ
ጅስሜ እንዳሞራ እንደብርቱ ንስር
ክንፍ አውጥቶ በርሮ
ምድርና ሞላዋን ዓለምን ይቃኛል
ከፍቅሬ በስተቀር
ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ውእቱ ይለኛል
እመጣለሁ ብላ የቀጠረቺኝ ለት
እንዲህ ያረገኛል
በፍቅሯ ልዕልና በፍቅር ጽናቴ
ከመንደሬ ገዳም ከጎጆ ባዕቴ
ከመላክ .......... ረቅቄ
ከጻድቅ .......... ጸድቄ
.......እጠብቃታለሁ
እመጣለሁ ብላኝ መች ተኝቼ አውቃለሁ
ዓለም ጊዜ ፀሀይ ሁሉም ቀጥ ብለው
የኪዳኔን ታቦት ጽላቴን አክብረው
ይማፀኑልኛል ይማልዱልኛል
«ይህ ምስኪን ጻድቅ ሰው
ከአለም የመነነው
በአቱን የዘጋው
ፀሀይን አስቁሞ ጊዜን የገዘተው
እመጣለሁ ብለሽ እንዳትዘገይ ነው
እንዳትቀሪበት ነው»
ብለው ይሉልኛል
ጨረቃ ከዋክብት ይማልዱልኛል
የፍቅር ብርታቴን ሁሉም ያውቁልኛል
ከአይን ያውጣህ ከአይን ያውጣህ
ከአይን ያውጣህ ይሉኛል
አንዳንዴም ሽው ሲል እንዲህ እሆናለሁ
ከቤቴ ቁጭ ቡዬ በሀሳብ እመጥቃለሁ
እሷን እየጠበቅሁ እፈላሰማለሁ
እላለሁ..............
«ይህ ሁሉ ጥሞና ይሄ ሁሉ ብቃት
ለሌላም ለሌላም ቢሆን ምናለበት
አዬ ጊዜ ደጉ አዬ ወጣትነት»
እላለሁ............
እድሜ ለሷ ፍቅር መንፈሴን ቀጥቅጦ
ልቤን ለሚገዛው
በሌላማ ጊዜ በጥልቅ ለመመለጥ
አይምሮዬን ባዝዘው መች እሺ ይለኛል
መቼ እሺ እላለሁ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
አበባዉ መላኩ
9
#ብቸኛ_ነበሩ!

በስህተት ተባብሮ ፣ በደቦ ከሚፈርድ፤
የብቻህን ሃሳብ ፣ ዝምታህን ውደድ፤
አለምን ጠቃሚ ፣ ሆነው የተገኙ፤
በመልካም ስራቸው ፣ አንቱ የተሰኙ፤
ብቸኛ ነበሩ ፣ ሁሉም የተዋቸው፤
በደቦ ተባብሮ በግፍ የጣላቸው፤
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍182
#ምንነት

አብረን በዋልንበት - በሄድንበት ሁሉ
ካንቺ ጋራ ያዩኝ - ያልገባቸው ውሉ
ምኗ ነው እያሉ - ሰው ይጠይቃሉ።

እናምልሽ ውዴ

ምኗ ነው እያሉ - ለሚጠራጠሩ
ስለኔ ምንነት - አውቀው እንዲኖሩ
ከቻልሽ አስረጃቸው - ገልፀሽ በአጭሩ።

እሱ ማለት ለኔ - ገና ከጅምሩ
በሰም የታጠረ - ቅኔ ነው ሚስጥሩ።

ቅኔ ማለት ደግሞ - የማይታይ ጌጡ
ተዘርፎ የማያልቅ - ወርቅ አለ በውስጡ
ለሱ ግን

ከሀብቱ የሚልቅ ሌላ በዚች አለም
ደስታ የሚፈጥር ምንም ይሁን ምንም
ከኔ ሳቅ የሚበልጥ አንዳች ነገር የለም።

መሳቅ ማለት ደስታ - ደስታ ማለት ደሞ
በልቡ ማሳ ላይ - የተዘራው ቀድሞ
የመንፈሱ ችግኝ - ስጋ ያበቀለው
የሚቀጥፈው መውደድ - ጊዜ ያበሰለው
ጣፍጦት የሚበላው የነፍሱ ፍሬ ነው።
ፍሬው ባስተሳሰብ - ዳግም የሚዘራ
የዘሩ ቅርንጫፍ - ከዕምነት የተጋራ
ፍቅር ያዳበረው - ወዳጅ የሚያፈራ
ጥሩ ጓደኛነት - በሚያጠላው ጥላ
እኔ ያስጠለለ - የሆነኝ ከለላ
አፍቅሮኝ የሚኖር - የማይመኝ ሌላ
ታማኝ ወዳጄ ነው - የዕምነቴ ኬላ።
ብለሽ አስረጃቸው
ስለኔ ምንነት - ማወቅ ተስኗቸው
ምኗ ነው ለሚሉ - ፍቅር ላልገባቸው።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
7🥰4👏2🔥1