ግጥም
4.26K subscribers
26 photos
1 video
10 links
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል

መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን

Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post

ADMIN 👉 @Big_jor
Download Telegram
#ከክፋት_ሰውረኝ?!

የእባብ ልብን ይዘው እርግብ ነን ከሚሉ፣
በቀበሮ ተግባር በበግ ስም ከሚምሉ፣
ቃል እየጠቀሱ በክፋት ከራሱ ፣
በተኩላ ስጋ የብግ ለምድ ከለብሱ፣
የአምላክን ስም ጠርተው በቃሉ ከማይኖሩ፣
በእግዚአብሔር ዝማሬ ሰይጣን ከሚያከብሩ፣
እግራቸው ከመቅደስ ልባቸው ከክፋት፣
ቃላቸው የንብ ማር ተግባራቸው እሬት ፣
ከሆነ ሰዎች ዘንድ እግዚአብሔር ነጥለኝ፣
ጻድቅ ባልሆን እንኳን ከክፋት ሰውረኝ?!
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍5🥰3👏2🔥1
#ሶሊያና

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ

እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰወች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
(ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም )
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ኤፍሬም ስዩም
👍75
#ተሻለህ_አትበሉኝ!

ያሽለኛል ብዬ የጠጣሁት ኮሶ
ይቆርጠኝ ጀመረ ከበሽታው ብሶ
መድሀኒት ይሆነናል ነበረ ምኞቴ
ሃኪሙን አምኜ በእምነት መጠጣቴ
ለካስ ተመረዟል መድሀኒቱ ዛሬ
ለዚህ ነበር ለካስ ብሶብኝ ማደሬ
ተሻለህ አትበሉኝ እያያችሁ ብሶ
መርዝ ሆኖ አሰቃዬኝ ይሄ የዘር ኮሶ።
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
   ስንታየሁ ሀብታሙ
👍83👏3
ልብስህን ያስቀርበዋል? ወይም ልብስህ በሞት እንደተቀጣ ነው?
በBroken hearts ላይ እንደአንተ የቀጠቀሱ ነፍሶች እዚህ ተሰባበሩ!
አዲሱን መጀመር? ሆኖም ከባለፉት ቤጥሎች አትቀርፉ።
ግባ አንዴ የልብስ ቀለም ከተጠፋበት ቦታ – ከአንደኛው እቻው ወዲያ ልብስህ ይበራል!

#ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች
#እንደገና

እንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡
ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡
ሌላም ብዙ ነበር
ሌላም… ደግሞ ሌላ
አለብኝ ትዝታ!
ዘመዶቼ ሳሙኝ
ጓደኞቼም ጋብዙኝ
ሊስትሮ ጨብጠኝ
ባለጋሪ ንዳ መንገዴን አሳየኝ
ያገሬ ልጅ ቆንጆ ‹‹ቤት ለእንግዳ›› በይኝ
አለብኝ ትዝታ…
        @gitm_post
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
ገ/ክርስቶስ ደስታ

💓 ራስዬ አላሳዉሪ።: የስኬት ተራራን እንዴት መውጣት እንደሚቻል? በስኬት የራስን አብዛኛውን ዘዴ፣ አስተዳደርና እንቅስቃሴ አግኝ፤ የግል ልምድ አግኝ! | InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች
3
“1 ቀን ያህል ፈቃድ ያለው ነገር አለ?
እኔ የገና አውቅልኝ፣ 00 ብር እንዴት ነው?
መረዳት የምትፈልጉት አሁን አልቅሱ

#ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች.
አዲስ የ4K ጥራት ፎቶ በፍላጎት ትጠብቃለህ?
በቀላሉ ቦታ እና ለsamrt-profile–wallpaper የምታጠቀም ፎቶዎች, የተመረጡ motivational ገጽታዎችና quotes ይፈልጋሉ?
ኢትዮጵያን የመጀመሪያውን እና ብቸኛ የመሆኑን ቻናል አትተዉ፤ አሁኑኑ join በሉ!

#ad InsideAds ነፃ ተመዝጋቢዎች