ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
የመጻሕፍት ሕብረ - ቀለም ::
Forwarded from Esubalew Abera N.
ትዝታሽን_ለእኔ፣_ትዝታዬ_ለአንቺ_ኂሳዊ_ንባብ_በማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል.pdf
1.6 MB
ትዝታሽን ለእኔ፣ ትዝታዬ ለአንቺ ኂሳዊ ንባብ በማርቆስ ዘመንበረ ልዑል
ያ ዕድሜ ላይ

ሰው በተሰበሰበበት
ወይን ጭስ ጨዋታ
ዳንስ ሴት እስክስታ
ዳንኪራ ሁካታ ቡንቧታ
ግርግር ጫጫታ ነገር
ማኪያቶ የቆንጆ ሴት ከንፈር ሲቀራርብ
ተፈለኩ ብዬ
ሰው ጠራኝ ብዬ
ራሴን ገፍትሬ
ራሴን ቀጥሬ
ወደ ቤቴ ምበር
ጫማዬን ከበሬ የ ምወረውር
ከአልጋዬ ትራሴ ስር
ቀዝቃዛ ሙዚቃ ነገር
ከፍቼ ከራሴ ሃሳብ የምቀበር ።
(ያ ዕድሜ ላይ ። )
____
ሰው ሁሉ ጓጉቶ
መንገድ ጉዞ ተዘጋጅቶ
ስንቅ ተዘጋጅቶ
ጠጅ ተይዞ
ቆሎ ተይዞ
ባጋጣሚ ምክነያት
ባለቀ ሰዓት
ጉዞ ተሰርዟል !! ሲባል
ፈገግ የሚያስብለኝ

(ያ ዕድሜ ላይ )
....
ብዙ የፈረሱ ህልሞች _ ከአመድ የገቡ
ከምስጥ ጉድጓድ የጠበቡ
ሰው እየቀነስኩ
ሰው እየቀነሰኝ
አነስኩ ስል ገዝፌ የምገኝ ____( ያ ዕድሜ ላይ )

_
ሴት ቀጥሬ
ከወንበሬ ስትደርስ _ ተነስቼ ስሜ
ከወጠራት ልብስ _ዳሌ
ይልቅ ህልሟ የሚስበኝ
(ያ ዕድሜ ላይ )

ትርጉም በሌላት ዓለም _ ትርጉም የምፈልግ
የክብ ጉዞ የምስብ
ጠፍቼ _ስለመገኘት_ የማስብ
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
የሲሲፈስን ርግማን _ኑሮዬ አርጌ የተቀበልኩ
ለራሴው እርድ _ ቢላ ስዬ ያቀረብኩ
በሞቱት የምቀና መኖር የሚያስፈራኝ
_
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
ብናኝ መሆኔ የገባኝ
አዋራ መሆኔ የገባኝ
'አውራ ነኝ' የምል
__
ከመሞት ይልቅ
መኖር የሚያስፈራኝ
ሰው ያረገው የሚያስጠላኝ
ራሴው ያደረኩት የሚያስጠላኝ
በትልቁ ተጋድሜ
ትንሹ ነገር የሚያስፈራኝ
_
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
የራሴን ህይወት ማሳመር ባልችል
ለማበላሸት የማላንስ
(ካደረኩት ይልቅ
የማደርገው የሚያጓጓኝ
የማያጓጓኝ
ይቅር እንዴ ?
ላርገው እንዴ ?
ልሂድ እንዴ ?
ልምጣ እንዴ ?
ላግባ እንዴ ?
ልውለድ እንዴ ?
ልሙት እንዴ ?
የሚያስብለኝ የማያስብለኝ
(ያ ዕድሜ ላይ )

1ዱ ጌታቸው

#1ዱ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
Lyrics by: Moel and Seife Temam
#Moel #seifetemam #Gitemsitem
Forwarded from Seife Temam
''ኧረ እሰየው ተመስገን ተመስገን አዲስ ፀሐይ ወጣ
ሞት የለህም ከእንግዲህ ችግር ምናምንቴ በል ከቤቴ ውጣ
ከእንግዲህ አትችለኝም ጠንካራ ነኝ እኔ
ሰንቄያለሁና ከብረት የላቀ የብርሃን ወኔ
እስከመቼ ነፍሴ ከእውነት ቤት እርቃ
ዘልቀህ ላታዛልቅ ካንተ ጋር ተጣብቃ
ከሚወፍር በኃጥያት እንጀራ ገላዬ
መርጫለሁ መክሳት በንጹህ ህሊናዬ

ልታለማምደኝ እርኩሰት
ተጠቅመህ በቴሌቭዢን መስኮት
ባህል ሐይማኖቴን እንድረሳ
ሞክረሃል ተሞልተህ ብዙ ተስፋ
እርግጥ እልፍ አእላፎች ይዘሃል
እንደምትገዛም እቺን ምድር ተጽፏል
ግን እብሪትህ በጣም አየለና
እቺን ቁድስ አገር አዓይኑ አየና

ባምናው ቤቴ ላይ ነግሰህ ስታሸኝ ኖረሃል ያ ክንድህ በርትቶ
‘ምታለብሰኝ ያለም ካባ የሚያልፍ የሚነጥፍ የተንኮል ድሪቶ
ከእንግዲህ ግን ይብቃ ጠንካራ ነኝ እኔ
ሰንቄያለሁና ከብረት የላቀ የብርሃን ወኔ
. . . ''

በቃ በቃ - አማን ኪያሞ / Aman Kiyamo

#አማን_ኪያሞ #Aman_Kiyamo #ግጥምሲጥም #gitemsitem #ግጥማዊቅዳሜ #poeticsaturdays
አንሶሻል ዘለዓለሜ
አካል ሥጋ ጠቦሻል
ረቂቅ ነፍስ በግዘፍሽ
ከአንቺ በልጦ ምን ይዘሻል?

(ጥልመት ድ'ቅድቅ
ብርሃን ድ'ብቅ
እ'ርስት
ዝን'ግት
.
ሕዋ ዐይንሽ ላይ
ንጋቴን ልታጋፍሪበት
ያንቺን ጀንበር መሸበት....

ዝም
ዝም
ዝም
ጭልም!)

አንቺን አልፌ ሁሉን
ሁሉን ሳልፈው ተመለስሁኝ
መኖሪያሽ ነኝ የምለው
ለካስ ነዋሪሽ ነበርሁኝ

(አድማስ እኔ
ብርሃኔ እ'ጥፍ
ጥልመት አንቺ ጥ'ልፍ
ብ'ርር
ክ'ንፍ!

አልነገሩኝ አልተረዳሁ
ስበት ብርሃንን እንዲያሸንፍ!

ሳብሺኝ! ል'ጥፍ!

ቦግ...እልም
ዳግም ዝም!)

ዘለዓለሜ አንሶሽ
መሆኔ ጠቦሽ
ከእኔ ገዝፈሽ
እኔን ያዝሺኝ።
ጥልመትሽ ሁሉን ቢሞላ
አድማስ ሙሉ አበራሺኝ።

..ተንጸባረቅሁ
..ነገሥሁብሽ!

(የማይሆንን አደረግነው
በቅጽበት ሁሌን ኖርነው

...ከዕለታት ጠይም
መልከ መልካሙ ላይ
ሁሉን የሚያህልን
አንድ ነጥብ ሰማይ
አቅፈነው አደርን
ነቅተን ሕልሞች ሆንን

አንቺን አልፌ ዓለሙን
ዓለሙን ሳልፍ ተመለስሁ
አንቺን ሳልፍ - አንቺ ሁሉን
ቀኔ ሲያልፈኝ
አንቺ ሁሌ - አንቺ አሁን
ሆንሁሽና ሆንሁት ሁሉን!

ከዕለታት አንቺ ዕለት
ሰማዩን አቀፍሁት
ተሸከምሁ ሁለንታ
ደቃቃ አሁን ላይ
ዘለዓለም ተረታ...)

አንሶሻል ዘለዓለሜ
(በማን ዐይን ተመዝኖ)
ጠቦሻል ሥጋ አካሌ
(በማን አንጻር ተነጻጽሮ)

የመውደዴን ልኬት
ከመዘንሽው በእነሱ አቅም
ከአሁን ሌላ አልወድሽም

(በእነሱ ዘለዓለም
አሁን የለም!)

ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል

#ማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል #MarkOs #ግጥምሲጥም #gitemsitem #ግጥማዊቅዳሜ #poeticsaturdays
Forwarded from Free talk🤓🙃
Scar's

If I could I would sacrifices my soul, my being just to avoid falling for you

If I could I would cut my eyes out just to avoid seeing you smile

If I could I would die earlier before meeting you

I am afraid of height and falling too but some how in some ways I fall for you
Not knowing what would happen at the bottom
Whether I land on my feet or break my back,
That is how much I trusted you

I touched you infinity,
I tattooed you deep in my heart,
I wispered you to the stars, I treated you like the rarest thing in the earth,
I had butterflies in my stomach,
I was good to you

Loving you was the last thing I done
And I was good at it
Most of the times I smile
And gave you a thousand second chances, just to prove I am wrong and you right
I did Olympic worth back flip and believe you are the one

One, you left me
One, you used me
One, like you never had memories of me even the little you had , that is a big may be, you scattered them like the stars
One, sometimes when I see a couples in the streets I wish it would have been us
One, one, you smile with her like I never existed
One, I hate her

Ten, I hope she smiles with your jokes but you would remember me instead of her

Nine, I hope she would feel my infinity touch's, smell my perfume on your body and leave you

Eight, may be then you would want to know how I get my scar's

Seven, you would want to know how time heal the pain and what would you do when those days come, when you don't feel like yourself, when it is upside down

Six, you would wander, when you feel worthless, you would wander,
How I get my scar's

Five, see I ripped you out of my heart, I ripped you out of my smile,
I spoke to you in to my shadows, so you would vapor to thin air
See, I stopped my heart so i could breath again

Four, see I swallowed my pride, but it clues back to my mouth

Three, to her, to the random girl you start dating, I think I saw her in your smile but I cried and washed her too

Two, see I scratched you, from my chest, i used my finger nails

One, that is how I gat my scar's.
One , that is how I smile everyday
One , that is how l smile everyday



🦋🦋🦋🦋
@freetalkk
Forwarded from Arada Slang
ይህ ፎርም የአራዳ መዝገበ-ቃላት ለማዘጋጀት እንዲረዳ የቀረበ ነው።እባክዎ ቃል፣ ሐረግ ወይም አባባል ይፃፉ። ትርጉም ይጨምሩ።
ለትብብርዎ እናመሰግናለን::

https://forms.gle/x6GGoKoS5CKWi6kf7
ደመና ጎመራ

ከአድማስ ከሩቅ ካ'ፋፉ ላይ
የወይዛዝርት የጥጥ ፈትል መስሎ የሚታይ
ሰማይ ሊስም ከተራራው አናት ወጥቶ ሲፍገመገም
ደግሞ ሲወድቅ ÷ ደግሞ ሲተም
እንደ እሳተ ጎመራ ፅንስ ካ'ብራኩ እንደተገኘ
በነጭ ቀለም ሲጎመራ
በዝምታ ሲያስፈራራ
ዥንጉርጉሩን የእናቱን ሆድ
በአንዱ ሲያምን÷ በአንዱ ሲክድ
እንደ'ሳቱ ለዓይን ሳይከብድ
የተጠጋውን ሳያነድ
ግን.....በክህደት እሱን መስሎ
የቅርብ ሩቅ ሆኖ ሰውን አቂሎ
በአየር ተንሳፎ ÷ ተራራን ተጫምቶ
ደመና ጎመራ ጨሰ ተድበልብሎ÷ ከሰማይ ተነስቶ ÷ ከተራራው ወቶ

ህሊና ሙሉጌታ

#ህሊና_ሙሉጌታ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #gitemsitem #poeticsaturdays
የሰውነት ነገር
አለባብሶ ማረስ ከራስ ጋር ፉክክር
.
ቀኝ ረግጧል ሲባል ግራው እየሳተ
ቆሞ መሄድ ቀርቶ በድን ተጎተተ
'በ'ምነት የታነፀው' ትልቁ ደረጃ
ድንገት ተደልድሎ
ደመነፍስ ሰፈፈ ባለማወቅ ታጅሎ

ያለማወቅ ዑደት የደመነፍስ ምሪት
ዕውር ግስጋሴ ተዓምረ ቅፅበት
እገደል አፋፍ ላይ እንዳለች አንዲት ነፍስ
አንዲት ብኩን ህይወት
መርገጫዋን ሳታይ የፊቷን ስትሻ
ድ....ፍት!

(የጌታነህ ልጅ)

#የጌታነህ_ልጅ #Yegetaneh_lij #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
የመኖር ልክሽ አዙሪት

የታል አምሳያሽ
ምትክ እና ልክ የሚሆንሽ
ምንስ ብለው ሲጠሩሽ
አንቺን
እራስሽን
ነሽ?

በምን ይለካል መኖር በድህነት ከብሮ ከብዶ
በምን ይጸድቃል ካህን በሼኪው ልጅ ፍቅር አብዶ
እንዴት ይመቸው ሴጣን ብርሃንሽ ላይ ጸዳል በዝቶ
እንዴት ይዝለቀው ብርሃን ጽልመትሽ ላይ ሞት በርክቶ

ቢሸፍን ቢከልል አንቺን ችሎ የሚደብቅ
የትኛው ጋራ ነው የትኛው መቀመቅ
ደሞስ ያልታየ ሁሉ እንደሌለ ተቆጥሮ
ስለታየም ደሞ ብቻ የሌለው አለ ተብሎ
መኖርና ማኖር በተምታቱባት ኗሪ ዓለም
ከኖሩስ እንዳንቺ ነው እንዳንቺው ደሞ ካልኖሩም

ሰይፈተማም
#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
ከወደድኩኝ ቆየሁ

አብዝቶ ከመታ ልቤ ተደናግጦ ከተደናበረ
ስንቱ ልብ ተስሞ
ስንቱ ተስለምልሞ
ስንቱ ድኖ ታሞ
ስንቱ ተሰበረ

ጊዜ ጥሎኝ መጣ ወዳለሁበት ቀን ባዶ እጁን አንግቦ
ከወደድኩኝ ቆየሁ የሚለውን ልቤን ሊጎበኝ አስቦ

በመኖር ዛላ ውስጥ በቀናት ስንጥር ላይ
ከመንጋጋ መሃል የተሰነቀረች የስጋ ፍንቃይ
ጎርጉሮ እያወጣ ጨጓራዬ እንዲድን ከአንጀቴ እንዳትገባ
ለዓይኖቼ ይልካል ውበትን ዘጋግኖ ለልቤ አበባ
ያማረ በሙሉ የተንቆጠቆጠ እንዴት ይወደዳል
የተወደደ እንጂ ቢዝረከረክ ሁላ ሁል ጊዜ ያምራል

በልጅነት መንገድ ከመንጻት ነጽቼ መጓዝ ከዘነጋሁ
ድፍን ነፍፍፍ ዓመቴ እንደ ልቤ ደጃፍ እኔም ከተዘጋሁ
ከተፍለቀለኩኝ ካማረብኝ በጣም ኮርኩሬ ዘልዬ
ከተሽሞነሞንኩኝ ዓለምን ‘ረስቼ ዕቃ ዕቃ ነው ብዬ
ህጻናት አቅፌ ‘ባፋቸው አውርቼ ከተኮለታተፍኩ
‘አዋቂነት’ ንቄ እልፍ ሳቅ ካደመ’ኩ ቆየሁኝ ከወደድኩ

ብዙ ጊዜ ሆነኝ ከተንተፋተፍኩኝ ሌቱ እስከሚነጋ
መቀነት ፈትቼ ወኔ ከታጠኩኝ አልጋ እስከሚናጋ
ኮረዳ ኮርጄ ውቤ ውዴ ብዬ ለምኜ አባብዬ
ፎግሬ አፏግሬ ከደረቷ መሃል እንባ አቀባብዬ
ያላትን ሰልቤ የኔን አስረክቤ ከተሞዳሞድኩኝ
እንዲሆኑ ሆኜ አይሆኑ ሳልሆነው ቆየሁ ከወደድኩኝ

ሰይፈተማም

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
♡ Home is what you fight for ♡

I have been stuck, a little taken aback
I look around, I feel the pain
I feel the sickness, I feel the shame
What is it to be alive? What does it mean when you're not fine?

Let me explain how I feel. . .
Told how to act, how to speak perhaps how to surrender
Many define it as a form of good behavior
Sometimes I wonder, when is it ever enough? When is it ever going to end?
First observation then comes manipulation
The other well it's easy, authentication for the better of the situation
I shudder, I stutter looking at their face
I feel like screaming, I feel unsettled, I am unsettled

I went outside that day, wanted to be thrown, away,,, far away
A sound from a far tickled my earlobes
It felt right, nothing ever felt right
Want to change, mop the floors
Want to wake up, on the side of a shore
One touch, for a fear
Body warm, eyes full of tears
Felt the noises, heard all the stories

Let me adjust my memory,
Collect all the dust, understand their ways
correct all the pieces, Better will come,
Behold! and do as told
Feelings are overrated
To feel, I shallnot
To flee, I can not
To ask, I better not
Forget, oh well! I guess not

So what if I pretend?. . .please no pity
Words don't fill me
Not here to please or be pleased
Only dreamed to be free
Chose to wade in the water
How can I renege? I still want to feel the pain
Getting out sounds like a fairytale
Hhmmm,,,,,I'll treat myself and meet my saviour on the other side
Perhaps I'll leave my pain for him to find
Nothing changes either ways
I'm still stuck in this place
The only place I get to see
The only space I get to fill

I have done it before
Tried to let go
Tried to feel the light
Not expecting, to end up with such fight

Change doesn't come that easily,
it's easier to adapt than heal
You see, I'd rather share than tell
Seek, you'll get attention
Speak, you'll bring destruction
A simple sequence,,,,,, I was put
A simple rule,,,,,,, I thought
A simple order,,,,,, I never fought

In the day, I abide
In the night, I fly
The only time I touch the sky
The only space, I carry my pride
The only place, I speak my mind

I am fine,,,,, well, for now
This here is just fine,,,
I still go outside, to seek away
If not for long, a minute is okay
I won't know when,,,, I won't know how
My place is here, I shall use it somehow.
.
Written by: Deborah Dessalegn
Date: December 28th, 2019
Place: HerStories @allianceethio_francaise
Event: A night of performing arts #HERStories #AllianceEthio-Francaise

#Deborah_Dessalegn #gitemsitem #poeticsaturdays
Forwarded from Bruh Club
Less than a week before our virtual meeting!!! To book your place, simply send your full name, email address and the art form you produce to @Mahlet_mairegu!!!
ብርድ አሟሟቅ

ውርጭ ነበር
ቀዝቃዛ ዓየር
ንፋስ ነገር
ብርዳም ዘገር
ቁርፍድ ቆዳዬን ተርትሮ
ስንጥር አካሌን ገፍትሮ
እኔን ከላዬ አባርሮ

ልብ የሚያፍን ምትሃት ሰውነቴን ሲነዝራት
የሚያጀግን ፍርሃት ከንፈሬን ቃል ሲነጥቃት

መድረሻ ያጣ እጄ ጣዕም ሲለቅም ተግቶ
የኦርዮን መቀነት ንጹህ ሰማይ ላይ ጎልቶ
ያገኘኋትን ሜሮፒ ይዣት ልጠፋ ስዳረስ
ክንፌ አልታዘዝ ብሎ ጨረቃ አድርሻት ስመለስ

. . . ውርጭ ነበር
ብርድ ነገር

አገላብጦ እየገረፈ ሙቀቷ ላይ ሲያምሰኝ
ቁሩን ዓየር እየሳበች ግለት ትንፋሿን ሲያምገኝ
አንዴ ተሳምኩኝ ብሎ የእጇ ቀጭ ሲወረዛ
ካይን ገባሁኝ ብሎ ልቧ ምቱን ሲያባዛ
አይኗን በቅጡ ሳላየው ጠረኗ ውስጤ ተደፋ
እሷን ካላየሁበት አይኔም ቢጠፋ ይጥፋ
ብዬ ባቀፍኳት ሰዓት
ቀዝቃዛ ዓየር ያዘለ ውርጫም ንፋስ የበዛበት
ብርዳም ነበረ ቀኑ ጥቅምት የጠቀመበት

እያነቀኝ ሲወጣ ከልቤ ውስጥ ሾላልኮ
ቀልቤ እትት ሲላት ከአቅሏ ጋር ተንሾካሽኮ
የይለፍ ቃሉን ስነግራት ጣቶቿን ቆልፌ ይዤ
ግማሽ አካሏን አንቅቼ ግማሽ አካሌን ደንዝዤ
ስትለምነኝ ስለምናት
‘ተው እንኑር’ ‘ተይ እንሙት’
‘ተው እንኑር’ ‘ተይ እንሙት’
‘ከመኖር ብዙ አለ ካለመኖር እረፍት’
‘ከመኖር ነውር አለ ካለ መኖር እፍረት’
. . . ሁሉን ቋሚ ፍጡር
በቀስት የምቀውር
ተገኘሁኝ ዛሬ አይኔን እስክታወር
ዳስሼ ስሳከር
. . . ብርድ ነበር
ውርጭ ነገር
በራድ ንፋስ ቀዝቃዛ ዓየር . . .

‘አሁን’ ከየት ተከሰተች ይሄ ሙቀት የት ነበረ
ልቦች ተጠራሩ እንጂ የታል አንዳች የደረበ?
ከቁሩ እና ከውርጩ ከስንቱ ጉድ አውጥታኝ
የተሰጠኝን ሳልጠግበው ባልተሰጠኝ ሲከፋኝ
እጄ እንደተሸለመ ለነካበት ተባርኮ
በከንፈሬ የዳበስኩት መውደጃዋን ነበር’ኮ
ምኑ ጋር ፎረሽኩና ዘልቄ ከሷ ያልገባሁ
አንዱን ሳንጨርሰው ስለ ድጋሚው ሰጋሁ

በሆነው፣ በሚሆነው እና ሊሆን ባለው መሃል ተጥጄ
ከነበልባል ነዳድ ትኩሳት ግለቷ በርጄ
እሷን ሸኝቼ ስመለስ ወደ በረዶ ቤቷ
እኔ ቤቴን አጣሁት የት አባቴ የት አባቷ

ምን ሊቆጨኝ ምን ሊቆጫት ታሪክ ጽፈን ነፍሳችን ላይ
ብርዱን ስንሞቅ ቀንቶ ሰማይ

ሰይፈ ተማም 2013

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ