Forwarded from LinkUp Addis
Busara Championship is starting on 19 June 2021 at Goethe Institut. The event will mainly feature three games in one srage bringing young and talented players together on one court. The games that will be featured at the event will be Joteni (Foosball), Gebeta and Busara. Training will be provided for those who do not know how to play the games. For more info about the events, go to: https://bit.ly/3v1b5Dv.
Download and enjoy the June 2021 edition of LinkUp Addis: https://bit.ly/34zMpY5. @linkupaddis
Download and enjoy the June 2021 edition of LinkUp Addis: https://bit.ly/34zMpY5. @linkupaddis
ዓለም
'የለም!'
ብትለኝም
እንደው ርዕስ ሆኜ
'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ
የት አገኘሽው በሉልኝ
የታል ዱካ ፈለጉ
ምናልባት ስፋቷ ነቅቶ
ምናልባት ንቃቷ ሰፍቶ
አሻራዬ (ash-አርዓያዬ) ተገኝቶ
መንበሬን ያመነች እንደሁ
እንደኖረ መንበር አጥቶ
'አለም የለም ለማለት ማን ነበርሽ አንቺ!' በሉልኝ
በዓለም
ላለም
በሙሉ
የሄድኩበት ላይ አብሩልኝ
እንደው እን'ዳጋጣሚ
እግሬ ያረፈበት ላይ
ይረግጥ እንደሆን ገጣሚ
እንደው እንደ ዕድል ሆኖ
(ክፉ ዕድል)
'መምህር' ይደግመው እንደሁ
የለፈፍኩትን ቃል ዘግኖ
እንዲገለጥለት በፈለገው መጠን
ለስንቱ ተገልጧል እስኪገነጣጠል
ብላችሁ ንገሯት ለዝ'ች ሟርተኛ ዓለም
መኖር ለምትሰፍር ስፍር ለምታኖር
በዘርና ቀለም!
የለም!!!
የለም!!!
እንደውም ምንም አትበሏት
ብጨልምም ብበራባት
አልነበር
'አለው' ለማለት
እንድትነቃ እንጂ ወደ 'ውነት
እንድትቀና እንጂ ከጥመት
የላ የላ ዝም በሏት እኔው ላውራት
ዓለምዬ ዓለም ብርቁ
የቱ ነው የግብርሽ ጥድቁ
እንዳንቺስ ሆኖ ሳይነቁ
መኖር ምንድነው ስንቁ?
ጽልመትሽ ብራ'ን የጠላ
ብርሃንሽ ጽልመት የከላ
'አለ'ምሽ መኖር የፈራ
'የለም'ሽ ተኑሮ ያልጠራ
'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ
ከየት ተገኘ ዓለሜ ያለመኖሬስ ፈለጉ
[የዓለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለ መኖሬስ ፈለጉ
ያ ለመኖሬስ ፈለጉ
ያ ዓለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለመ ኖሬስ ፈለጉ. . . ]
. . . ዱካዬን ብት'ደብቂም
ባለሽበት ሁሉ አለሁ
መንበሬም ካነበረሽ ነው!
የሚያኖርሽ እንደኖረው
አለም - አለሁ!
ዓለም
አለሁ!
አለማለሁ!
©️ሰይፈ ተማም
'የለም!'
ብትለኝም
እንደው ርዕስ ሆኜ
'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ
የት አገኘሽው በሉልኝ
የታል ዱካ ፈለጉ
ምናልባት ስፋቷ ነቅቶ
ምናልባት ንቃቷ ሰፍቶ
አሻራዬ (ash-አርዓያዬ) ተገኝቶ
መንበሬን ያመነች እንደሁ
እንደኖረ መንበር አጥቶ
'አለም የለም ለማለት ማን ነበርሽ አንቺ!' በሉልኝ
በዓለም
ላለም
በሙሉ
የሄድኩበት ላይ አብሩልኝ
እንደው እን'ዳጋጣሚ
እግሬ ያረፈበት ላይ
ይረግጥ እንደሆን ገጣሚ
እንደው እንደ ዕድል ሆኖ
(ክፉ ዕድል)
'መምህር' ይደግመው እንደሁ
የለፈፍኩትን ቃል ዘግኖ
እንዲገለጥለት በፈለገው መጠን
ለስንቱ ተገልጧል እስኪገነጣጠል
ብላችሁ ንገሯት ለዝ'ች ሟርተኛ ዓለም
መኖር ለምትሰፍር ስፍር ለምታኖር
በዘርና ቀለም!
የለም!!!
የለም!!!
እንደውም ምንም አትበሏት
ብጨልምም ብበራባት
አልነበር
'አለው' ለማለት
እንድትነቃ እንጂ ወደ 'ውነት
እንድትቀና እንጂ ከጥመት
የላ የላ ዝም በሏት እኔው ላውራት
ዓለምዬ ዓለም ብርቁ
የቱ ነው የግብርሽ ጥድቁ
እንዳንቺስ ሆኖ ሳይነቁ
መኖር ምንድነው ስንቁ?
ጽልመትሽ ብራ'ን የጠላ
ብርሃንሽ ጽልመት የከላ
'አለ'ምሽ መኖር የፈራ
'የለም'ሽ ተኑሮ ያልጠራ
'የለም' ለመባል እንኳ 'ነበር' በማስፈለጉ
ከየት ተገኘ ዓለሜ ያለመኖሬስ ፈለጉ
[የዓለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለ መኖሬስ ፈለጉ
ያ ለመኖሬስ ፈለጉ
ያ ዓለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለም መኖሬስ ፈለጉ
ያለመ ኖሬስ ፈለጉ. . . ]
. . . ዱካዬን ብት'ደብቂም
ባለሽበት ሁሉ አለሁ
መንበሬም ካነበረሽ ነው!
የሚያኖርሽ እንደኖረው
አለም - አለሁ!
ዓለም
አለሁ!
አለማለሁ!
©️ሰይፈ ተማም
Forwarded from Tesfahun kebede- ፍራሽ አዳሽ
#የሞት ጥቁር ወተት
የግጥም መድበል
📚📗📒📕📚
የመጽሐፍ ምርቃት
ኑ አብረን እንመርቅ . . .
🗓
ሰኔ 03/2013 ዓ.ም
ኀሙስ በ11:30 ሰዓት
📍
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት
🎙
#የዝግጅት አቅራቢዎች
ገጣሚ ነቢይ መኮንን
ገጣሚ ፍሬዘር አድማሱ
ደራሲ አዜብ ወርቁ
ተዋናይ መስከረም አበራ
ገጣሚ ረድኤት ተረፈ
ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ
ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ
ድምፃዊ ካሥማሰ
🎤
#ግጥም በውዝዋዜ
ገጣሚ ተስፋኹን ከበደ
ተወዛዋዥ ኤፍሬም መኮንን
#መድረክ መሪ
ጋዜጠኛ ክብሬ ተስፋዬ
🎼
#ሙዚቃ
በኢትዮ ጣዕም የሙዚቃ ባንድ
#አጋዥ_አካላት
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ አ.ማ
ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
አርትስ ቴሌቭዥን
ጃጃው አታሚዎች ኃ.የተ.የግ.ድርጅት
ማፊታ ዲዛይንና ዲኮር
ጃሎ ፒክቸርስ
የግጥም መድበል
📚📗📒📕📚
የመጽሐፍ ምርቃት
ኑ አብረን እንመርቅ . . .
🗓
ሰኔ 03/2013 ዓ.ም
ኀሙስ በ11:30 ሰዓት
📍
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ቤት
🎙
#የዝግጅት አቅራቢዎች
ገጣሚ ነቢይ መኮንን
ገጣሚ ፍሬዘር አድማሱ
ደራሲ አዜብ ወርቁ
ተዋናይ መስከረም አበራ
ገጣሚ ረድኤት ተረፈ
ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ
ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ
ድምፃዊ ካሥማሰ
🎤
#ግጥም በውዝዋዜ
ገጣሚ ተስፋኹን ከበደ
ተወዛዋዥ ኤፍሬም መኮንን
#መድረክ መሪ
ጋዜጠኛ ክብሬ ተስፋዬ
🎼
#ሙዚቃ
በኢትዮ ጣዕም የሙዚቃ ባንድ
#አጋዥ_አካላት
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ አ.ማ
ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
አርትስ ቴሌቭዥን
ጃጃው አታሚዎች ኃ.የተ.የግ.ድርጅት
ማፊታ ዲዛይንና ዲኮር
ጃሎ ፒክቸርስ
Forwarded from Bae🎤🎤
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
A night out with a twist on an already unique frequency - angelic musical performances, sweet poetry, and a fascinating live painter. A night like none other full of soulful/expressive/underground vibes.
We can’t wait to see you at FreeSoul ✨
When
Saturday, June 12 @ 7pm
Where
Olympia Heights (unfinished bldg)
Across from Dembel, beside the Deluxe furniture & Awash bank
@Betty_bae
A night out with a twist on an already unique frequency - angelic musical performances, sweet poetry, and a fascinating live painter. A night like none other full of soulful/expressive/underground vibes.
We can’t wait to see you at FreeSoul ✨
When
Saturday, June 12 @ 7pm
Where
Olympia Heights (unfinished bldg)
Across from Dembel, beside the Deluxe furniture & Awash bank
@Betty_bae
Forwarded from LinkUp Addis
Nu Chika Enabuka Art Center will host a toy and children's books donation day on Saturday 12 June 2021. The event will have children send toys, books and letters to children in different parts of the country. Children will also have a storytelling time with popular guests along with other activities. The entrance to the event is a toy with a children's book. Doors will open at 9:00am. @linkupaddis
እኔና መስከረም
ጉድን አስቀድሞ በጠባው መስከረም
መልሶ ሊሰለች ያልናፈቀ የለም
እንደ ዘማች ፋኖ ሜዳው አጎፍሮ
በአደይ ጥርሱ ሲስቅ በመላጣው አፍሮ
በዛ ባዶ ደብተር ስም እንኳን በሌለው
ስምሽን አየሸጎጥኩ ሜዳውን ስስለው
የእፉዬዋን ገላ ጆሮሽ ላይ ስሽጠው
የአምናው ትዝ እያኝ
መስከረም ናፈቀኝ
ሸተተኝ ጠረኑ የምሳቃው አይነት
ዶሮና አጥንቱ ተባብረው የሞሉት
ታየኝ ሌላ ክፍል ወስደው ሊለጥፉት
ታወቀኝ ከዴስኬ ስምሽን እንዳጠፉት
ምን ያረጋል ክረምት ምንያረጋል ብርዱ
ፈገግታሽ የላቸው ካርታና ገመዱ
ሽልጦና አርጩሜ
ታላቅ ፊልም ድጋሚ
ድጋሚው ድጋሚ
አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
አሁን የዝናብ ነው ጭቃ የነገሰበት
አንቺ ከቤት ስትውይ እኔ ትምርት ቤት
ከበጋው ግፋችን የምንማርበት
... የክረምት ትምህርት...
በአይኔ ለወደድኩሽ ሌላ ደርቤበት
ላንቺ የቀለድኩት ቲቲን እያሳቃት
ሳሩም አደገብን ሊደብቀን ሻተ
ጭቃው አዳለጠን ዋንጫችን ወለቀ
ይህ አሮጌ ደብተር ገጹ መጀመሪያ
ስምሽ ተስሎበት ከሜዳው ሳር ጉያ
የክረምቱን ሳልስል የክረምቱን ሳልፅፍ
ነሐሴ መጣና ጿሚ ሆኜው እርፍ
አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
አሁን የዝናብ ነው ጭቃ የነገሰበት
አንቺ ከቤት ስትውይ እኔ ትምርት ቤት
ከአዘቦት ግፋችን የምንማርበት
... የሰንበት ትምህርት...
ነጠላ አጣፍቼ ሳንቲም እያጋኘሁ
120ን ትቼ ቤተስኪያን ተገኘሁ
ይቺ ህይወት ናታ ወስዳ ያሳለመችኝ
ደጀ ሰላም ጠርታ ደሞ እያሳመችኝ
ደሞ የቆረበች ለት አፏን ነጠላ አምቆ
ያለችኝንም አልሰማሁ ከንፈሯ ካይኔ እርቆ
ደብተሬም የመዝሙር እንጂ የውዳሴያት ማህደር
በራጅ ላስቲክ ያሸኳት ቢሳልም ሰማዕት ነበር
መስከረም አትምጣ አትጥባ ግዴለም
ደብተሬ በላስቲክ ገና አልተሸፈነም
አይኔ አይኖቿን ሊያይ ድፍረት አላገኘም
ቀለም ጨርሻለሁ አበባ መሳያ
ቀለም ጨርሻለሁ ግጥም ማሳመሪያ
በቀረች ብያለሁ አበባ አየሽ ባዯ
🎤
አበባ አየሽ ወይ - የወር
አበባ አየሽ ወይ - የወር
የሷን አበባ ለወር የኔን ለዓመት አርገህ
ወዲያው ለሚያረጅ ነገር አታምጣ ቀኑን አድሰህ
... ክፍላችንን ለይተህ
አንተም ቀንህ አልፎ
ጊዜህ ተንጠፍጥፎ
እንዳልነበር ውሉ የሚለየን የለም
ዘመን ሲወነጨፍ ሌላ ሚሊኒየም
ብዙ ጉድ ሰምተናል ና ጥባ ግዴለም
ና ግባ መስከረም
አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
ለፀሀይ ቀርቤ ማውጋቱም ናፍቆኛል
ልቃጠል ልንደደው የጉድ ቀን ባይነጋም
ብርድ እያሳበቡ ሰለቸኝ መስከርም
ናፈቀኝ መስከረም
ምንቸቱን ቀይረው
መቼቱን ቀይረው
ለአዲስ ቀን አልሰጋም
ለአዲስ ቀን አልሰጋም
©️ሰይፈ ተማም 2010
https://t.me/GitemSitem
ጉድን አስቀድሞ በጠባው መስከረም
መልሶ ሊሰለች ያልናፈቀ የለም
እንደ ዘማች ፋኖ ሜዳው አጎፍሮ
በአደይ ጥርሱ ሲስቅ በመላጣው አፍሮ
በዛ ባዶ ደብተር ስም እንኳን በሌለው
ስምሽን አየሸጎጥኩ ሜዳውን ስስለው
የእፉዬዋን ገላ ጆሮሽ ላይ ስሽጠው
የአምናው ትዝ እያኝ
መስከረም ናፈቀኝ
ሸተተኝ ጠረኑ የምሳቃው አይነት
ዶሮና አጥንቱ ተባብረው የሞሉት
ታየኝ ሌላ ክፍል ወስደው ሊለጥፉት
ታወቀኝ ከዴስኬ ስምሽን እንዳጠፉት
ምን ያረጋል ክረምት ምንያረጋል ብርዱ
ፈገግታሽ የላቸው ካርታና ገመዱ
ሽልጦና አርጩሜ
ታላቅ ፊልም ድጋሚ
ድጋሚው ድጋሚ
አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
አሁን የዝናብ ነው ጭቃ የነገሰበት
አንቺ ከቤት ስትውይ እኔ ትምርት ቤት
ከበጋው ግፋችን የምንማርበት
... የክረምት ትምህርት...
በአይኔ ለወደድኩሽ ሌላ ደርቤበት
ላንቺ የቀለድኩት ቲቲን እያሳቃት
ሳሩም አደገብን ሊደብቀን ሻተ
ጭቃው አዳለጠን ዋንጫችን ወለቀ
ይህ አሮጌ ደብተር ገጹ መጀመሪያ
ስምሽ ተስሎበት ከሜዳው ሳር ጉያ
የክረምቱን ሳልስል የክረምቱን ሳልፅፍ
ነሐሴ መጣና ጿሚ ሆኜው እርፍ
አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
አሁን የዝናብ ነው ጭቃ የነገሰበት
አንቺ ከቤት ስትውይ እኔ ትምርት ቤት
ከአዘቦት ግፋችን የምንማርበት
... የሰንበት ትምህርት...
ነጠላ አጣፍቼ ሳንቲም እያጋኘሁ
120ን ትቼ ቤተስኪያን ተገኘሁ
ይቺ ህይወት ናታ ወስዳ ያሳለመችኝ
ደጀ ሰላም ጠርታ ደሞ እያሳመችኝ
ደሞ የቆረበች ለት አፏን ነጠላ አምቆ
ያለችኝንም አልሰማሁ ከንፈሯ ካይኔ እርቆ
ደብተሬም የመዝሙር እንጂ የውዳሴያት ማህደር
በራጅ ላስቲክ ያሸኳት ቢሳልም ሰማዕት ነበር
መስከረም አትምጣ አትጥባ ግዴለም
ደብተሬ በላስቲክ ገና አልተሸፈነም
አይኔ አይኖቿን ሊያይ ድፍረት አላገኘም
ቀለም ጨርሻለሁ አበባ መሳያ
ቀለም ጨርሻለሁ ግጥም ማሳመሪያ
በቀረች ብያለሁ አበባ አየሽ ባዯ
🎤
አበባ አየሽ ወይ - የወር
አበባ አየሽ ወይ - የወር
የሷን አበባ ለወር የኔን ለዓመት አርገህ
ወዲያው ለሚያረጅ ነገር አታምጣ ቀኑን አድሰህ
... ክፍላችንን ለይተህ
አንተም ቀንህ አልፎ
ጊዜህ ተንጠፍጥፎ
እንዳልነበር ውሉ የሚለየን የለም
ዘመን ሲወነጨፍ ሌላ ሚሊኒየም
ብዙ ጉድ ሰምተናል ና ጥባ ግዴለም
ና ግባ መስከረም
አንቺን ናፍቋል መሰል ሰማዩም ያለቅሳል
ቀኑ ረጃጅም ነው ለጨዋታ ያንሳል
ለፀሀይ ቀርቤ ማውጋቱም ናፍቆኛል
ልቃጠል ልንደደው የጉድ ቀን ባይነጋም
ብርድ እያሳበቡ ሰለቸኝ መስከርም
ናፈቀኝ መስከረም
ምንቸቱን ቀይረው
መቼቱን ቀይረው
ለአዲስ ቀን አልሰጋም
ለአዲስ ቀን አልሰጋም
©️ሰይፈ ተማም 2010
https://t.me/GitemSitem
Forwarded from ኩነት - Kunet (Seife Temam)
AKEBULAN
UTIO Connect and Shifta have linked up to bring you a one of a kind pop up featuring some the best brands in Addis Ababa. We’ll have some bomb food, awesome cocktails, good music and cold Heineken.
Free entrance
#June_19_21 https://t.me/Kunetz
#popupsale #shifta #Swasew #Tibeb #Enzi #Undken #Utio_Connect
UTIO Connect and Shifta have linked up to bring you a one of a kind pop up featuring some the best brands in Addis Ababa. We’ll have some bomb food, awesome cocktails, good music and cold Heineken.
Free entrance
#June_19_21 https://t.me/Kunetz
#popupsale #shifta #Swasew #Tibeb #Enzi #Undken #Utio_Connect
On days like this
I just want to rest my head
On your chest and feel your breath
On days like this
I just want to lock fingers
Take a long walk in silence
On days like this
I would lay on the grass
With you
And find shapes on the clouds
On days like this
I would look at the stars
And name you a star among the Greek gods
On days like this
I would tell you a secret
That I hid even from my own heart
On days like this
I would be your wife
Calling you mine
In this uncertain life
On days like this
I would carry your children
And smile seeing you in them
On days like this
I wish to tell the whole universe
Am in love and call you mine
While I can’t even claim my own life
©️Feben Fancho
https://t.me/GitemSitem
I just want to rest my head
On your chest and feel your breath
On days like this
I just want to lock fingers
Take a long walk in silence
On days like this
I would lay on the grass
With you
And find shapes on the clouds
On days like this
I would look at the stars
And name you a star among the Greek gods
On days like this
I would tell you a secret
That I hid even from my own heart
On days like this
I would be your wife
Calling you mine
In this uncertain life
On days like this
I would carry your children
And smile seeing you in them
On days like this
I wish to tell the whole universe
Am in love and call you mine
While I can’t even claim my own life
©️Feben Fancho
https://t.me/GitemSitem
ግራሽ ቆንጥር፡ ቀኜ አጋም
ወደን ፈቅደን ባንዋጋም
ጫፌ ሹል ነው፡ ጠርዝሽ ስለት
ብትጠጊም ብጠጋሽም...
እሾሃችን...ያንቺም የኔም ደም አለበት።
እውነት...
ደምሽ ፈስሶ ፡ ወርሶኝ ቁስል
ሹል ባትቀርጪ፡ ጠርዜን ባልስል
እኔም አንቺም እሾህ አለን፡ ቀምበጥ ለብሰን አናስመስል።
ስታለቅሺ... ራሴን ይዤ የማለቅሰው
ስትሞቺ... ለቅሶ ራሴን የምደርሰው
ስለማውቀው ሰውነቴን ሰውነትሽን
አሜኬላ ስስ አካሌን እሾኻማ ስስ ገላሽን።
ስለማውቀው ስላቃተኝ
እሾህሽ ላይ እንዳላቄም፡ ሰውነትሽ ሲጎትተኝ
ልትቆርጪብኝ ስላቃተሽ
እሾኼ ላይ እንዳትጨክኝ፡ ሰውነቴ ሲጎትትሽ
ምን ታደርጊኝ... ምን ላድርግሽ?
ሲያምረኝ ብታይ
የሆንነውን ተረት ማድረግ
ካይኖችሽ ላይ እንባ መጥረግ
የገላሽን ቁስል ማድረቅ
ወለምታሽን ጠጋኝ መረቅ
በእንባ ምትክ
ካይኖቼ ውስጥ ብችል ማፍለቅ
ባጠጣሁሽ... ብትድኚልኝ
በመዳንሽ በኩል ድኜ... መድሃኒቴ ብትሆኚልኝ
ተወጋግተን ከምናለቅስ
ተጠጋግተን ብንፈወስ
አስቀድሰን ብንቀደስ
ስለታችን ካንድ እስር ጧፍ
ሶላታችን ባንድ ምንጣፍ
ቢሆንልን...
ጽዮን ጥላ ብትሆንልን...
ቢልልን...
ፅጌነቴን እያወቅሽው፡ ቀምበጥሽን እያወቅኹት
ለእሾሄ አይደል የወጋሽኝ? ለእሾህሽ ነው ዘራፍ ያልኩት..
እንጂ ጥንቱን በለጋነት
የስልሳ መርዝ ሾ'ህ ሳንጋት
በየተራ ሳንጨልም...በፈረቃ ሳይሆን ንጋት
ሰውነቴን ስትቀርቢው... ሰውነትሽን ስጠጋጋት
ፍቅር እንጂ እልህ እንጂ መች ነበረን መወጋጋት?
እኔ ልሙት!
እንዴት ከኔ ቆንጥርሽን ?
እንዴት ካንቺ አሜኬላ ?
እንዴት ችለን ለሰውነት
ፈጠርንለት ድንበር ኬላ...?
እንዴት ... ንዴት... ?
እንዴት ... እልህ... ?
ማለት ስችል እንደቃልሽ
ማለት ስትችይ እንደቃልህ!
ማልፍ ስንችል ዝቅ ብለን
አቦሰሙን ተጣጥለን
ከሰውነት ሳንጣጣል
ወይ አንቺ እኔ ዝቅ ብንል
ብንሸነፍ ምን ይመጣል?
ምንም!
ብንችልበት ፈረቃውን
አንዱ ወጥቶ አንዱ እስኪወርድ ጥበቃውን
በጣም ብንችል ብናፈርሰው
የስልሳን መርዝ ብናፈስሰው
ብንቆጠር እንዳንድ ሰው
እንባችንን ካንድ አይን ስር ብናለቅሰው።
ምን ነበረ?
ምን ላድርግሽ... ?
እንባሽ ከላይ ቁስልሽ ከስር
ወይ ወዳንቺ
ወይ ወደኔ ጣቴን ችዬ እንዳልቀስር
ከኛ ረዝሞ፡ እሾኻችን
ከእልሃችን ማጠራችን።
ምን ላድርግሽ
እንባሽ ሲፈስ ቆሜ አያለሁ
እንዴት ብዬ
እሾህ እጄን ልጠርግልሽ እሰድዳለሁ?
እንዳላቅፍሽ ክንዴ አጋም
ሾህ እንዳልጥል አሜኬላሽ አያስጠጋም
እንዴት ልሁን?
እውነታችን ቢለያይም
ያንዳችን ውግ ላንደኛችን ባይታይም
አንቺም ቁስል እኔም ቁስል
ሰውነትን የሚመስል።
እሾህ እየረገፈ
ቀንበጡ ቀንበጡን እየተደገፈ
ቁስል አፈ ታሪክ እንባ ተረት ተረት
ገላ ያለ ኬላ ፥ ፍቅር ያለ ወረት
የሚገለጥበት
ባይገኝም እውነት
በጋራ እሚያሞኘን ቢገኝልን ውሸት...
ምን ነበረ?
እውነት... !
©️ረድኤት አሰፋ
https://t.me/GitemSitem
ወደን ፈቅደን ባንዋጋም
ጫፌ ሹል ነው፡ ጠርዝሽ ስለት
ብትጠጊም ብጠጋሽም...
እሾሃችን...ያንቺም የኔም ደም አለበት።
እውነት...
ደምሽ ፈስሶ ፡ ወርሶኝ ቁስል
ሹል ባትቀርጪ፡ ጠርዜን ባልስል
እኔም አንቺም እሾህ አለን፡ ቀምበጥ ለብሰን አናስመስል።
ስታለቅሺ... ራሴን ይዤ የማለቅሰው
ስትሞቺ... ለቅሶ ራሴን የምደርሰው
ስለማውቀው ሰውነቴን ሰውነትሽን
አሜኬላ ስስ አካሌን እሾኻማ ስስ ገላሽን።
ስለማውቀው ስላቃተኝ
እሾህሽ ላይ እንዳላቄም፡ ሰውነትሽ ሲጎትተኝ
ልትቆርጪብኝ ስላቃተሽ
እሾኼ ላይ እንዳትጨክኝ፡ ሰውነቴ ሲጎትትሽ
ምን ታደርጊኝ... ምን ላድርግሽ?
ሲያምረኝ ብታይ
የሆንነውን ተረት ማድረግ
ካይኖችሽ ላይ እንባ መጥረግ
የገላሽን ቁስል ማድረቅ
ወለምታሽን ጠጋኝ መረቅ
በእንባ ምትክ
ካይኖቼ ውስጥ ብችል ማፍለቅ
ባጠጣሁሽ... ብትድኚልኝ
በመዳንሽ በኩል ድኜ... መድሃኒቴ ብትሆኚልኝ
ተወጋግተን ከምናለቅስ
ተጠጋግተን ብንፈወስ
አስቀድሰን ብንቀደስ
ስለታችን ካንድ እስር ጧፍ
ሶላታችን ባንድ ምንጣፍ
ቢሆንልን...
ጽዮን ጥላ ብትሆንልን...
ቢልልን...
ፅጌነቴን እያወቅሽው፡ ቀምበጥሽን እያወቅኹት
ለእሾሄ አይደል የወጋሽኝ? ለእሾህሽ ነው ዘራፍ ያልኩት..
እንጂ ጥንቱን በለጋነት
የስልሳ መርዝ ሾ'ህ ሳንጋት
በየተራ ሳንጨልም...በፈረቃ ሳይሆን ንጋት
ሰውነቴን ስትቀርቢው... ሰውነትሽን ስጠጋጋት
ፍቅር እንጂ እልህ እንጂ መች ነበረን መወጋጋት?
እኔ ልሙት!
እንዴት ከኔ ቆንጥርሽን ?
እንዴት ካንቺ አሜኬላ ?
እንዴት ችለን ለሰውነት
ፈጠርንለት ድንበር ኬላ...?
እንዴት ... ንዴት... ?
እንዴት ... እልህ... ?
ማለት ስችል እንደቃልሽ
ማለት ስትችይ እንደቃልህ!
ማልፍ ስንችል ዝቅ ብለን
አቦሰሙን ተጣጥለን
ከሰውነት ሳንጣጣል
ወይ አንቺ እኔ ዝቅ ብንል
ብንሸነፍ ምን ይመጣል?
ምንም!
ብንችልበት ፈረቃውን
አንዱ ወጥቶ አንዱ እስኪወርድ ጥበቃውን
በጣም ብንችል ብናፈርሰው
የስልሳን መርዝ ብናፈስሰው
ብንቆጠር እንዳንድ ሰው
እንባችንን ካንድ አይን ስር ብናለቅሰው።
ምን ነበረ?
ምን ላድርግሽ... ?
እንባሽ ከላይ ቁስልሽ ከስር
ወይ ወዳንቺ
ወይ ወደኔ ጣቴን ችዬ እንዳልቀስር
ከኛ ረዝሞ፡ እሾኻችን
ከእልሃችን ማጠራችን።
ምን ላድርግሽ
እንባሽ ሲፈስ ቆሜ አያለሁ
እንዴት ብዬ
እሾህ እጄን ልጠርግልሽ እሰድዳለሁ?
እንዳላቅፍሽ ክንዴ አጋም
ሾህ እንዳልጥል አሜኬላሽ አያስጠጋም
እንዴት ልሁን?
እውነታችን ቢለያይም
ያንዳችን ውግ ላንደኛችን ባይታይም
አንቺም ቁስል እኔም ቁስል
ሰውነትን የሚመስል።
እሾህ እየረገፈ
ቀንበጡ ቀንበጡን እየተደገፈ
ቁስል አፈ ታሪክ እንባ ተረት ተረት
ገላ ያለ ኬላ ፥ ፍቅር ያለ ወረት
የሚገለጥበት
ባይገኝም እውነት
በጋራ እሚያሞኘን ቢገኝልን ውሸት...
ምን ነበረ?
እውነት... !
©️ረድኤት አሰፋ
https://t.me/GitemSitem
I belive in you
I believe in love
So darling
take me away from my broken spirits
Wipe away the scattred sadness
And sorrow writen all over me
Lets take awalk
Or jump
Or fly
Deep in the sea
Up on the sky
And all The ways
I wanna breath the air full of your perfume
I wanna burn by your flame
I open the gate of my heart
Till it feels with your love
So darling
Let me love you
Till I die by the joy you gave me
And I dance on my own grave
Let me love you and take all my life.
©️Mekdes Moges
https://t.me/GitemSitem
I believe in love
So darling
take me away from my broken spirits
Wipe away the scattred sadness
And sorrow writen all over me
Lets take awalk
Or jump
Or fly
Deep in the sea
Up on the sky
And all The ways
I wanna breath the air full of your perfume
I wanna burn by your flame
I open the gate of my heart
Till it feels with your love
So darling
Let me love you
Till I die by the joy you gave me
And I dance on my own grave
Let me love you and take all my life.
©️Mekdes Moges
https://t.me/GitemSitem
በይ አፈር እንጫር
ምንም ባትናገር
የዝምታዋ አድማስ ቃሏን ቢከልለኝ
መድረስ እያማራት
ሂወት መሮጥ ብቻ ሆነባት መሰለኝ
.
.
.
መሬትን ብቻ አምና....
(ነገሩን አልኩ እንጂ
እምነት አይባልም
ምርጫ ሲያጡ መውደድ በምን ይገለጣል
ሰው ከመሬት ሽሸቶ ወደምን ያመልጣል?)
ብቻ ለነገሩ...
መሬትን ብቻ አምና
መሬት ላይ ተቀምጣ እንዳቀረቀረች
በሰንጣራ ነገር አፈር እየጫረች
ተክዛ አገኘኋት
ምነው በቀረብኝ ምነው ባላየኋት
''ተይ አታቀርቅሪ
መኖር ግፈኛ ነው
ከግፈኞች ቀድሞ ለግፍ ይመረጣ
ጎንበስ ያለለትን ደጋግሞ ይረግጣል''
ልላት እየዳዳኝ
ጉልበት እያገኘሁ ጉልበት እየከዳኝ
ቀና አድርጌ ፊቷን
ድርቀት ያሻከረው ከንፈሯን አልፌ
ትኩስ እምባ
ቀመስኩ ካይኗ ስር ጨልፌ
ያኔ ቁስሏ ገባኝ
ያኔ ሆዴን ባባኝ
''ተይ'' ልላት ያልኩትን
ለራሴው ''ተው'' ብዬ ከጎኗ ተክዤ
አብሪያት ተቀመጥኩ እኔም ስንጥር ይዤ
©️አማረ ዘውዱ
https://t.me/GitemSitem
ምንም ባትናገር
የዝምታዋ አድማስ ቃሏን ቢከልለኝ
መድረስ እያማራት
ሂወት መሮጥ ብቻ ሆነባት መሰለኝ
.
.
.
መሬትን ብቻ አምና....
(ነገሩን አልኩ እንጂ
እምነት አይባልም
ምርጫ ሲያጡ መውደድ በምን ይገለጣል
ሰው ከመሬት ሽሸቶ ወደምን ያመልጣል?)
ብቻ ለነገሩ...
መሬትን ብቻ አምና
መሬት ላይ ተቀምጣ እንዳቀረቀረች
በሰንጣራ ነገር አፈር እየጫረች
ተክዛ አገኘኋት
ምነው በቀረብኝ ምነው ባላየኋት
''ተይ አታቀርቅሪ
መኖር ግፈኛ ነው
ከግፈኞች ቀድሞ ለግፍ ይመረጣ
ጎንበስ ያለለትን ደጋግሞ ይረግጣል''
ልላት እየዳዳኝ
ጉልበት እያገኘሁ ጉልበት እየከዳኝ
ቀና አድርጌ ፊቷን
ድርቀት ያሻከረው ከንፈሯን አልፌ
ትኩስ እምባ
ቀመስኩ ካይኗ ስር ጨልፌ
ያኔ ቁስሏ ገባኝ
ያኔ ሆዴን ባባኝ
''ተይ'' ልላት ያልኩትን
ለራሴው ''ተው'' ብዬ ከጎኗ ተክዤ
አብሪያት ተቀመጥኩ እኔም ስንጥር ይዤ
©️አማረ ዘውዱ
https://t.me/GitemSitem
👍1
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)