Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.14K subscribers
2 photos
4.67K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
እኛ ምናልባትም መሬት መንቀጥቀጥን ረስተን በሰላም ቤታችን ተኝተን ሊሆን ይችላል።

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16150/

ከሰከንድ በኃላ ምን ሊፈጠር እንደሆነ የማያውቁ ወገኖቻችንን ግን አንረሳቸውም።

አሁንም ስጋት ላይ ናቸው፤ አሁንም ሰው ይናፍቃሉ።

እኛም ጋዜጠኞች እነዚህን ወገኖች በጋራ ለመደገፍ ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ አንድ ብለን ተነስተናል።

ይህን በጎ ዓላማ ለመደገፍ እና ከጎናችን ለመቆም የተለመደ አጋርነታችሁን እንደምታሳዩን ተስፋ እናደርጋለን።

ማስታወሻ:- ለበጎ አድራጊዎች፦ የለገሳችሁበትን ደረሰኝ ብታያይዙልን እናመሰግናችኋለን።

ቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት
የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች :-

የኢት ንግድ ባንክ
1000388156728

አቢስንያ ባንክ
59997138

አዋሽ ባንክ
01308421807500

ኦሮሚያ ኀብረት ሥራ ባንክ
1011700045574

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አርቲስት ናርዶስ አዳነ የላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ብራንድ አምባሳደር ሆነች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16152/

#Ethiopia | አርቲስት ናርዶስ አዳነ ከላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት የስራ ውል ስምምነት በዛሬው እለት ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርማለች፡፡

የአርቲስቷ የአምባሳደርነት ስምምነት የሚቆየው ለሁለት አመት እንደሆነ በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል፡፡

ተዋናይት ናርዶስ አዳነ ከላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ጋር የተፈራረመችው ስምምነት፤ ለድርጅቱ በቴሌቪዥን፣ በቢል ቦርድና በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስታወቂያዎች መስራትን ያካትታል ተብሏል፡፡

ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ በዓለም አቀፍ የሪል እስቴት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን፤ በ4 ኪሎ አካባቢ አፓርታማ ሰርቶ ማስረከቡንና በአሁኑ ወቅት በቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ባለ21 ፎቅ አፓርታማ እያስገነባ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሴቶች አደባባይ ላይ የተገነባው ሐውልት ትርጉም

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16154/

#Ethiopia |በአዲስ አበባ የነበረው የሴቶች አደባባይ ስያሜውን ካገኘ ቆየት ቢልም የሴቶችን ሚና ሊያሳይ የሚችል ምንም የተለየ መገለጫ አልነበረውም፤ አካባቢውም ለዓይን ማራኪ ያልሆነ ነበር።

በካዛንቺስ መልሶ ማልማት ሥራ ይህ አደባባይ ስሙን በተግባር እንዲገልጥ ተደርጎ ሴቶችን በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እንዲሁም በፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን ወሳኝ ሚና በሚገልጽ መልኩ ተገንብቷል።

የሐውልቱ ሐሳብ ሩቅ የምትመለከት እና በእጇ ሚዛን የያዘች ሴት ምሥል ሲሆን ይህም ሀገራችን ኢትዮጵያን የምትወክል ናት።

የቆመችበት ችቦ ደግሞ ድልን ያሳያል።

ሐውልቱን የከበበው የጽጌረዳ አበባ እንደ ስሟ አዲስ አበባን ውብ አበባ ለማድረግ እየተሠራ ያለውን አዲስ አበባን እንዲወክል ተደርጎ የተሠራ ነው።

በአበባው ላይ ከዝቅተኛ ሥራ እስከ ትልቅ ኃላፊነት በተለይም በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ ዘርፎች እስከ መሪነት ድረስ ሴቶች ያላቸውን ሚና እንዲያንፀባርቅ ተደርጎ ነው የተሠራው።

በዙሪያው የሚታየው የሴቶች ምሥል፣ ሴቶች የኢትዮጵያን ብዝኃነት፣ ማኅበራዊ ትሥሥሮች እና ባህሎች በማንፀባረቅ በኩል ያላቸውን አይተኬ ሚና ያሳያል።

በአደባባዩ ግራ ቀኝ የሚታዩት ምሥሎች የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም መድረክ እያወለበለቡ ከፍ ያደረጉልንን የሴት አትሌቶቻችን ጉልህ ሚና እና የኢትዮጵያን ነፃነት በማስጠበቅ ውስጥ የኢትዮጵያውያን ሴት አርበኞች ተጋድሎን የሚዘክሩ ናቸው።

በአደባባዩ ግራ እና ቀኝ የእንዝርት እና እንጀራ ሲጋገር የሚያሳዩ ምሥሎች የተለየ ትምህርት እና ሥልጠና ሳኖራቸው እናቶቻችን ጥጥ አባዝተው፣ ፈትለው እና ወደ ልብስነት ቀይረው የሚያለብሱ እንዲሁም እንጀራ ጋግረው የሚመግቡ በተፈጥሮ የተቸራቸውን ጥበብ እና የላቀ መረዳትን የሚያመላክት ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አብራርተዋል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኮምቦልቻ : የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16158/

ከሚያዚያ 20 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

#Ethiopia | የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ዝግጅት መጠናቀቁን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ከ200 በላይ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪዎች ምርት እና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቁበታል የተባለበት ይህ ኤክስፖ የቀጠናውን እምቅ የመልማት አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሏል።

“ሰላም የኢንቨስትመንት ፓስፖርት ነው” በሚል መልእክት የሚካሄደው ኤክስፖው በርካታ የፋይናንስ ተቋማት እንደሚሳተፉም ተገልጿል።

አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ ይቀርባሉ ተብሏል።

የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ከሚያዚያ 20 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በኮምቦልቻ ይካሄዳል።

***
“የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት አካል የሆነው በኮምቦልቻ ከተማ ከሚዚያ 20 እስከ ሚያዚያ 29 2017 ዓ.ም የሚካሄደው የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው ”

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነወርቅ

ሀገር አቀፍ የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ውጤታማ እንዲሆን ልዩ ልዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን በተለያዩ አገልግሎት ዘርፎች የተሰማሩ የከተማዋ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ተሰጥተዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊና ወሎ ኮምቦልቻ ሀገር አቀፍ የኢንዱስትሪ እና የፋይናንስ ኤክስፖ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሁሴን ሙሔ የተቋቋሙት ንዑሳን ኮሚቴዎች ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን ገልፀው ለእንግዶች ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነወርቅ የኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት አካል የሆነው በኮምቦልቻ ከተማ ከሚዚያ 20 እስከ ሚያዚያ 29 2017 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢንዱስትሪ እና ፋይናንስ ኤክስፖ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው ብለዋል።

በርካታ የፋይናንስ ተቋማት በኤክስፖው ይሳተፋሉ ያሉት ምክትል ከንቲባው አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለእይታ እንደሚቀርቡና ተቋማቱ ተኪ ምርት እንዲያመርቱ የሚበረታቱበት ሁነት እንደሆነም አስረድተዋል ።

ዩኒቨርሲቲዎች እና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የምርምር ስራዎቻቸው እና የቴክኖሎጂ ውጤቶቻቸውን ያቀርባሉ ያሉት ምክትል ከንቲባው፤ የከተማዋን የወደፊት የመልማት ዕድል የሚወሰኑ ውይይቶች ይካሄዳሉ ሲሉም አብራርተዋል።

የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችም በሁሉም ዘርፍ እየተጠናቀቁ መሆኑን ገልፀው ማኅበረሰቡም የተለመደውን የእንግዳ ተቀባይነት እሴቱን በተግባር እንዲያሳይ አሳስበዋል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ጎፋ ዞን : የመሬት መንሸራተት አደጋ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16160/

👉በአደጋው የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል

#Ethiopia | በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ የጣለ ከባድ ዝናብ በወረዳው ጃዉላ ጎሬ እና ጃዉላ ባላላ አርከታ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ለአሐዱ አስታውቋል።

በወረዳው ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት መሬት መንሸራተት የተከሰተ ሲሆን፤ አደጋውም በንብረትና እንሰሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው።

“ይህ ያልተቋረጠ ዝናብ የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ መጥለቅለቅን አስነስቷል፣ ይህም ለአደጋው ዋና መንስኤ ነው” ሲሉ የጎፋ ዞን በጊዜ ጎፋ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የአለም መሪነህ ለአሐዱ ተናግረዋል።

በጃዉላ ጎሬ ቀበሌ የመሬት መደርመስ በመከሰቱ የአርሶ አደሮችን መኖሪያ ቤትና ሰብል መውደሙንና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ “በጃውላ ባላላ አርከታ ቀበሌም በአካባቢው የጎርፍ አደጋ የአንድን ነዋሪ ሕይወት በአሳዛኝ ሁኔታ አልፏል” ያሉ ሲሆን፤ በሁለቱም ወረዳዎች በርካታ ወገኖች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም፤ አካባቢው አስቸጋሪው የመሬት አቀማመጥ ችግሩን እንደሚያባብሰው ገልጸዋል።

“ዛሬ የጎርፍ መከላከያ ገነባን ነገር ግን በዝናብ ጊዜ ሁሉ ይሰበራል” ያሉት ኃላፊው፤ “እዚህ ያለው አፈር በጣም ለም ነው ነገር ግን ይህ በከባድ ዝናብ ወቅት ለአደጋ ተጋላጭ ያደርገዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአከባቢው ተዳፋት የመሬት ገጽታ በተለይም ለመሬት መንሸራተት እና ለጎርፍ ተጋላጭ እንደሚያደርገው የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ለአካባቢው ነዋሪዎች አደጋን እንደሚጨምር ተመላክቷል።

በምላሹም ባለስልጣናት እና የህብረተሰብ ክፍሎች የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ የሚያስችል የግጦሽ ሳር መትከል መጀመራቸው ነው የተገለጸው፡፡

በአሁኑ ወቅት የሚፈጠሩትን አደጋዎች ለመቅረፍ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ የመከላከል እና የማገገሚያ ሥራ እየተሰራ ስለመሆኑም ኃላፊው አስረድተዋል።

በተመሳሳይ በወረዳው በአንኮ ታዳጊ ማዘጋጃ ቀበሌ ትናንት ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ ወደ 4:00 ሰዓት አከባቢ ጀምሮ አዉሎ ንፋስ ጋር ተቀላቅሎ የዘነበው ዝናብ የብዙ ሰዎች ቤትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዚሁ ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ229 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
#ahaduRadio

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6.2 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መደረሱ ተሰምቷል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16162/

#Ethiopia | በዛሬው እለት በቱርክ 6.2 በሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የሀገሪቱ የአደጋ እና የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ባለስልጣን (AFAD) አስታወቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በኢስታንቡል እና በአጎራባች አካባቢዎች በጠንካራ ሁኔታ የተሰማ ሲሆን ይህም ነዋሪዎች በፍርሃት ህንጻዎችን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

የኢስታንቡል ገዥ ፅህፈት ቤት “እስካሁን ምንም አይነት የጉዳት ሪፖርት አልደረሰም ፡፡ የሚመለከታቸው ክፍሎቻችን የመስክ ቅኝት ጥረታቸውን ቀጥለዋል” ብሏል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን “መልካም ምኞቴን ለዜጎቻችን አቀርባለሁ፣ ጉዳዩን በቅርብት እየተከታተልን ነው” ብለዋል።
#ethioFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በህንድ ካሽሚር በቱሪስቶች ላይ በተከፈተ ጥቃት ቢያንስ 26 ሰዎች ተገደሉ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16164/

#Ethiopia | በህንድ ጃሙ እና ካሽሚር ግዛት ውስጥ ታጣቂዎች በቱሪስቶች ላይ በከፈቱት ጥቃት 26 ሰዎች ሲገደሉ ሎሎች 17 ሰዎች መቁሰላቸውን እሮብ እለት ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ በመግለጫው ኡክሎ እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ከተፈፀመ አስከፊ ጥቃት መካከል አንዱ ሲሆን በህንድ እንዲህ ዓይነት ክስተት ሲያጋጥም ከሁለት አስርት ዓመታት በኃላ ነው ተብሏል።

ጥቃቱ በፓሃልጋም በተሰኘው አካባቢ በሚገኝ ሜዳማ ስፍራ ሲሆን ከሞቱት ሰዎች መካከል 25 ህንዳውያን እና አንድ የኔፓል ዜጋ መሆናቸውን ፖሊስ ገልጿል።

እ.ኤ.አ. ከ2008 የሙምባይ ግድያ በኋላ በህንድ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የከፋው ጥቃት ተብሏል። ጥቃቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሳዑዲ አረቢያ የሁለት ቀናት ጉብኝታቸውን አቋርጠው ረቡዕ ጠዋት ወደ ኒው ዴሊ ተመልሰዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሯ ኒርማላ ሲታራማን የዩናይትድ ስቴትስ እና የፔሩ ጉብኝታቸውን “በዚህ አስቸጋሪ እና አሳዛኝ ጊዜ ከሕዝባችን ጋር ለመሆን” በሚል ማሳጠራቸውን ተናግረዋል።

ሞዲ በአውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከብሄራዊ ደህንነት አማካሪያቸው፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የመከሩ ሲሆን ልዩ የደህንነት ካቢኔ ስብሰባ መጠራታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ጥቃቱ ሞዲ እና የሂንዱ ብሄረተኛ የባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ የጃምሙ እና ካሽሚርን ከፊል የራስ ገዝ አስተዳደር በመሻር እና ለረጅም ጊዜ ችግር ውስጥ ለነበረው ክልል ሰላም እና ልማት ለማምጣት ትልቅ ስኬት ነው ብለው ለገመቱት በሙሉ እንደ ውድቀት ተቆጥሯል።

ብዙም እውቅና የሌለው ታጣቂ ቡድን የሆነው “የካሽሚር ተቃዋሚ” ለጥቃቱ ሃላፊነቱን መውሰዱን በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፈው መልእክት ገልጿል።

በክልሉ ከ85,000 በላይ ሰዎች እንዲሰፍሩ መደረጉ ቅሬታውን ገልጿል፣ ይህም “የሕዝብ ለውጥ” እንዲፈጠር አድርጓል ብሏል። ቡድኑ በሰጠው መግለጫ “የተጠቁት ግለሰቦች ተራ ቱሪስቶች አልነበሩም፣ ይልቁንም ከህንድ የፀጥታ ኤጀንሲዎች ጋር የተገናኙ እና የተቆራኙ ናቸው” ብሏል።
#ዳጉ_ጆርናል

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“የቆንስላ ኦፊሰሮች ያለፈውን የጉዞ ታሪክ እና ጥፋቶች ማየት ስለሚችሉ ማምለጥ የሚችሉበት መንገድ የለም” – በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16166/

#Ethiopia | በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሰጠው ማስጠንቀቂያ ከተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ በአሜሪካ የሚቆዩ ሰዎች ድጋሚ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ መደረግን ጨምሮ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ይወቁ ብሏል።

የቆንስላ ኦፊሰሮች ያለፈውን የጉዞ ታሪክ እና ጥፋቶች ማየት ስለሚችሉ ማምለጥ የሚችሉበት መንገድ የለም ነው ያለው።

ከዚህ ቀደም በአምባሳደሩ ኤርቪን ማሲንጋ አማካኝነት በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ መግባት፣ ቪዛ ለማግኘት መዋሸት፣ ያለ ህጋዊ የስራ ፍቃድ ስራ መስራትና የቪዛ ጊዜ ካበቃ በኋላ በአሜሪካ መቆየት ከባድ ቅጣት ያስከትላል ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል።

ይህን መሰል ማስጠንቀቂያ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ኢምባሲዎችም በተመሳሳይ ይህንን ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ “ከቀናት በፊት አሜሪካን መጎብኘት በነጻ የተሰጠ አይደለም። ይሄ ሕጎቻችንን እና እሴቶቻችንን ለሚያከብሩ ሰዎች የተሰጠ ልዩ መብት ነው” ሲሉ ገልጸው ነበር።
#tikvah

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ለዩኒቨርስቲ መምህራን የቀረበ የምርምር ስኮላር ጥቆማ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16168/

#Ethiopia | የFulbright 2026-2027 የአፍሪካ ምርምር ስኮላር ፕሮግራም ይፋ ሆኗል።

ፕሮግራሙ ሁለት አይነት አሰጣጦች ሲኖሩት በመጀመሪያው ፕሮግራም ዶክትሬት የሚጠይቅ (Post-doctoral) ሲሆን ሁለተኛው ፕሮግራም የማስተርስ ድግሪን የሚጠይቅ ነው።

በሁለቱም ፕሮግራሞች ማመልከት የሚችሉት የዩኒቨርስቲ መምህራን (ሌክቸሮች) ናቸው።

የቆይታ ጊዜው እንደ ፕሮግራሙ አይነት ሲለያይ አመልካቾች ከነሐሴ 2026 በኋላ እና ከመጋቢት 2027 በፊት #በአሜሪካ ተገኝተው ምርምራቸውን መጀመር መቻል አለባቸው።

የዕድሜ እና የፆታ ገደብ እንደሌለው የተገለጸ ሲሆን አመልካቾች ከJuly 31, 2025 በፊት ማመልከት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ ዕድል ሚመለከታችሁ ዝርዝሩን ከኢንባሲው ድረ-ገጽ 👉https://surl.li/qudtze ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አርሰናል ከክሪስታል ፓላስ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16170/

#Ethiopia | በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀግብር የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በሜዳው ኤምሬትስ ስታድየም ክሪስታል ፓላስን የሚገጥም ይሆናል፡፡

ሊጠናቀቅ የ4 ሳምንታት እድሜ ብቻ የቀረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በትናንትናው እለት የ34ኛ ሳምንት መርሀግብሩን ማከናወን ጀምሯል፡፡

ዛሬ ሊጉ ቀጥሎ ሲደረግ ምሽት 4፡00 ላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከመሪው ሊቨርፑል በ13 ነጥቦች የራቀው እና የዋንጫ ተስፋው ሙሉ በሙሉ ያበቃ የመሰለው አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በኤምሬትስ የሚጋብዝ ይሆናል፡፡

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ፖርትማን ሮድ ስታድየም አቅንተው በደረጃው ግርጌ ላይ የሚገኘው ኢፕስዊች ታውንን 4ለ0 በሆነ ሰፊ ዉጤት ማሸነፋቸው አይዘነጋም፡፡

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ከፈረንሳዩ ክለብ ፓሪሴንት ዤርሜይን ጋር ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቀው አርሰናል ለቋሚ ተጨዋቾቹ እረፍት ሊሰጥ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ክሪስታል ፓላስ ባለፉት 3 ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች ማሸፍ ባይችልም በኦስትርያዊው አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር እየተመራ መልካም የሚባል የውድድር አመትን እያሳለፈ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ፓላስ በደረጃው 44 ነጥቦችን ሰብስቦ 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ሁለቱም ክለቦች በሰልሀርስት ፓርክ ባደረጉት የመጀመርያ ዙር የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ በአርሰናል 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
#hagerieTv

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“አሁን ላይ ዋናዉ አላማችን 70 እንደርታን እንዴት እናቆየዉ የሚለዉ ነዉ” አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀይዬ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16172/

#Ethiopia | መቀሌ 70 እንደርታ ዘንድሮ ከአራት አመታት ቆይታ በኅላ ዳግም ፕሪሚርሊጉን ከተቀላቀለ በኋላ በሜዳም ላይም ሆነ ከሜዳ ዉጭ ባሉ ጉዳዮች በእጅጉ እየተፈተነ ይገኛል። አሁን ላይ ላለመዉረድ እየታገለም ነው።

ቡድኑ አሁን ላይ በሚገኝበት ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከብስራት ቴሌቪዥን ስፖርት ዝግጅት ክፍል ጋር የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀዬ ቆይታ አድርገዋል።

ክለቡ አሁን ያለበት ወቅታዊ አቋም ጥሩ እንዳልሆነ ይገባናል አሁን ላይ እቅዳችን መቀሌ 70 እንደርታን እንዴት በፕሪሚርሊጉ እናቆየዉ የሚለዉ ነዉ ብለዋል።

ዘንድሮ ከሶስቱ የትግራይ ክልል ተወካይ ክለቦች መካከል ሁለቱ ወራጅ ቀጠናዉ ላይ ይገኛኑ። በዚህ ሳቢያም በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያሉ ስፖርት አፍቃሪያን ክልሉ በፕሪሚየር ሊጉ ተወካይ ሊያጣ ነው የሚል ስጋት ውስጥ ገብተዋል።

ይህ ሀላፊነትም አሁን ላይ በዋናነት መቀሌ 70 እንደርታ ላይ የወደቀ ይመስላል። ምንም እንኳን በሂሳባዊ ስሌት ሶስቱም ክለቦቹ መዉረዳቸዉ ገና ባይረጋገጥም መቀሌ 70 እንደርታ የተሻለ የመትረፍ እድል ያለው በመሆኑ ተፅእኖው በእነሱ ላይ እንዳረፈ አሰልጣኙ ተናግረዋል

አሰልጣኝ ዳንኤል አያይዘዉም ክልሉ አሁን ላይ ባለበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ሳቢያ አሁን ላይ የፋይናንስ ችግሮች አሉብን ብሏል። ይህ የተጫዋቾቹ ስነ ልቦና ላይ ጫና ቢያሳድረም ከተጫዋቾች ጋር በመነጋገገር ቅድሚያ ለክለቡ ትኩረት በመስጠት ክለቡን ለማቆየት እየታገሉ ይገኛሉ በዚህም ሊመሰገኑ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ባለፉት ጨዋታዎች ላይ በተከታታይ ሽንፈት ለማስተናገዳችን ዋነኛ ምክንያት ያገኘናቸዉን የግብ ዕድሎች አለመጠቀም ነዉ ለቀጣይ ጨዋታዎች ስህተቶቻችን አርመን ወደ አሸናፊነት እንመለሳለን ሲሉም ነግረዉናል።

መቀሌ 70 እንደርታ ባለፉት 7 ጨዋታዎች በ5ቱ ሲሸነፍ ማሸነፍ የቻለዉ ሁለቱን ብቻ በመሆኑ ማግኘት ከሚገባዉ 21 ነጥብ ማሳካት የቻለዉ 6 ነጥብ ብቻ ነዉ። ይሄን ተከትሎ ቡድኑ በ28 ነጥብ ወራጅ ቀጠናዉ አፋፍ ላይ ተቀምጧል።
#BisratFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ታላቅ የክብር ቀን ሚያዚያ 17/18/19

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16174/

🚩

ማን ይቀራል በወንጌል ያልዳኑትን አዳዲስ ነፍሳት -ህሙማን -በአጋንት እስራት የተያዙትን -በተለያዩ ስቃይ ውስጥ ያሉትን ጌታ ቢፈቅድ በህይወት ብንኖር …ይዘን እንገናኝ

ከማለዳው 12:00 እስከ ከሰአት 9:30 ድረስ

መጽሐፈ ምሳሌ 15:3፤ የእግዚአብሔር ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፤
ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።
🕊️ 🕊️ ታላቅ የክብር ቀን 🕊️ 🕊️
ምሳሌ 15:3 “የእግዚአብሔር ዓይኖች በየስፍራው ናቸው ክፉዎችንና ደጉን ያዩ” ይላል።

እግዚአብሔር በሁሉም ቦታ እንዳለ እና ሁሉንም ነገር እንደሚመለከት የኃጥአን እና የጻድቃንን ድርጊት እንደሚያይ ይህ ቃል ያጎላል

ከእግዚአብሔር እይታ የተሰወረ የሚያቅተው የማያየው ምንም ነገር እንደሌለ ይናገራል

ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እግዚአብሔር ጣልቃ ሊገባ ልናመሰግነው ከፊታችን ይህንን አዘጋጀልን

ከእግዚአብሔር እይታ የተሰወረ የሚያቅተው የማያየው ምንም ነገር እንደሌለ እነሆ
እንዲህ አለን
ኑ እፈርዳለው ኑ እዳኛለው አሜን!!

እግዚአብሔር ይህንን ቀን አዘጋጀልን
ወንጌል ይሰበካል ብዙዎች ይፈወሳሉ ነፃ ይወጣሉ
እስራቶችን ይበጠሳል የልጁ የኢየሱስ ስም ይከብራል
ብዙዎች ወደ መንግስቱ ይጨመራሉ

🚩ማንም ሰው እንዳይቀር ከማለዳው 12:00 ጀምሮ
የሚያበቃበት ሰአት ከሰአት 9:30 ይሆናል

የመንግስቱ ወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አድራሻ፡-ታክሲ ወይም አውቶቡስ ለምትይዙ

ከአራት ኪሎ ታክሲ ተራ ቤላ ታክሲ በመሳፈር ቤላ አስራ አስራ ስምንት ማዞሪያ ወደ አቦ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ዳገቱን እንደወጡ በስተግራ በኩል ያገኙናል !
Our church Address Gps
Taxi 🚖 ride|| taxi 🚕

https://maps.app.goo.gl/26Gu8Y9VFS8eCi96A?g_st=it

ለበለጠ -መረጃ
+251944723090
+251944723091
+251944723092
+251944723093

www.thegospelofkingdom.org

🚩ኑ በ4 ኪሎ ቤላ 18 ማዞሪያ ሲደርሱ ይውረዱ የመንግሥቱ ወንጌል አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን

Gps location just click
https://maps.app.goo.gl/ks7RCA2krKzB9kjZ8?g_st=ic

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16177/

#Ethiopia | በምዕራብ አርሲ ዞን ኔጌሌ አርሲ ወረዳ ራፉ ሃርጊሳ ቀበሌ በደረሳ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት ሲያልፍ በ22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ደረሰ፡፡

አደጋው የደረሰው፤ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በማጋጨቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከሟቾች በተጫመሪ በ16 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኔጌሌ አርሲ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡#FBC

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አንድ ማይልን ከ4 ደቂቃ በታች የመግባት አዲሱ ፕሮጀክት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16179/

#Ethiopia | ናይክ አንድ ማይልን ከ4 ደቂቃ በታች የመግባት ፕሮጀክቱን ይፋ አድርጓል።

ይህንን አዲስ ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠችው አትሌት ደግሞ ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕየጎን ሆናለች።

በሴቶች ከአሁን በፊት አንድ ማይልን ከ4 ደቂቃ በታች መግባት የቻለ አትሌት የለም።

የርቀቱ የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት ፌዝ ኪፕየጎን ናይክ ያዘጋጀውን አዲስ ፕሮጀክት በድል ለመወጣት በብዙ መመዘኛዎች የተሻለችዋ አትሌት ሆና ተገኝታለች።

በቅርቡ በሮያል ሶሳይቲ ኦፕን ሳይንስ በታተመ ጥናት ኪፕየጎን ያላት ሀይል እና ጽናት በበርካታ የፍጥነት ስልቶች ተመዝኖ አንድ ማይልን ከአራት ደቂቃ በታች የመግባት አቅም እንዳላት ተቀምጧል።

“BREAKING 4” የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲሱ ፕሮጀክት በሰኔ ወር አጋማሽ በፓሪስ እንዲደረግ ቀጠሮ ተይዞለታል::

አዘጋጆቹ ለእቅዱ ተግባራዊነት ተስማሚ የአየር ሁኔታ የሚኖርበትን ዕለት እንደሚከታተሉም ይፋ ተደርጓል።

የአትሌት ፌዝ ኪፕየጎን የአንድ ማይል የአለም ክብረ ወሰን ሞናኮ ላይ ያስመዘገበችው 4 ደቂቃ 07.64 ሰከንድ ነው።

ፌዝ ኪፕየጎን አዲሱን ፕሮጀክት በድል ለመወጣት አሁን ካላት ምርጥ ሰአት እስከ 8 ሰከንድ ማሻሻል ይጠበቅባታል።

ያለፉት ሶስት ኦሎምፒኮች የ1500 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ባለቤቷ ፌዝ ኪፕየገን በርቀቱ በአለም ሻምፒዮና 4 የወርቅ ሜዳልያ በመውሰድ የሚስተካከላት የለም።

ናይክ ከአሁን በፊት ማራቶንን ከ 2 ሰአት በታች በመግባት ፕሮጀክቱ ኬንያዊው ኢልዩድ ኪፕቾጌ 1 ሰአት 59 ደቂቃ 40 ሰከንድ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ምንም እንኳን አትሌቱ ያስመዘገበው ሰአት በበርካታ አሯሯጮች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች እንዲሁም ለብቻው ለአንድ አላማ ያደረገው በመሆኑ በአለም አትሌቲክስ እውቅና የተሰጠው ባይሆንም።

በአንተነህ ሲሳይ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
Tsehaye & Neway ELEGANCE CONCERT

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16181/

መግቢያ ትኬትዎን በቴሌብር

ቅዳሜ ሚያዝያ 18

ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ

በማሪዮት ሆቴል

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የቀድሞው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ደመላሽ ካሳዬ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16183/

#Ethiopia | የቀድሞው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ዓለም ባንክ በሚገኘው ጀሞ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዛሬ ተፈፅሟል።

ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ስራ ከሰሩና በትጋታቸው ጉልህ ሚና ካበረከቱ ባለሙያዎችና አመራሮች መከካል ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ በፕሮጀክት ተጫዋችነት እንዲሁም በኦሜድላ ክለብ ተጫዋችነትና አሰልጣኝነት አገልግለዋል።

በስፖርቱ ኢንተርናሽናል አሰልጣኝነት ደረጃ በመድረስ ሀገራቸውን ከማስጠራትና በፌደሬሽኑ ለበርካታ ዓመታት በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴነት ከመሥራታቸው በተጨማሪ፤ ከ2005 – 2009 ዓ.ም የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት በመሆን አገልግለዋል።

ከእጅ ኳስ ፌደሬሽን በተጨማሪ ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በጥናትና ምርምር፣ በኢንስፔክሽንና በመምህርነት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት አገልግለዋል።

ተቋማቱም በቀድሞ ባልደረባቸው ኮማንደር ደመላሽ ካሳዬ (ዶ/ር) ህልፈተ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

በላሉ ኢታላ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ፖሊስ ከአዲስ_ስታንዳርድ የወሰዳቸውን የኤሌክትሮኒክስ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16185/

መሳሪያዎች በአፋጣኝ እንዲመልስ ሲፒጄ ጠየቀ

#Ethiopia | በፖሊስ በተወሰዱት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል ስጋቱንም ገልጿል

ፖሊስ በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ባደረገው ብርበራ በወሰዳቸው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ተቋም (ሲፒጄ) ትላንት ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ስጋቱን አስታወቀ።

በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን ምርመራ እንዲያቋርጥ የጠየቀው ሲፒጄ፤ የተወሰዱት የተቋሙ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችንም በአፋጣኝ እንዲመልስ አሳስቧል።

“አዲስ ስታንዳርድ ላይ የተፈጸመው ብርበራ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት ነፃ ሚዲያዎችን ዝም ለማሰኘት እያካሄደው ያለው ዘመቻ አካል ነው፤ የተቋሙን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች መውሰዱ በውስጣቸው የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችልበት እድል ከፍተኛ ነው” ሲሉ የሲፒጄ አፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ ስጋታቸውን መግለጻቸውን አስታውቋል።

ስድስት የደንብ ልብስ ያልለበሱ የፖሊስ አባላት መሆናቸውን የገለጹ ሰዎች ሚያዝያ 9 ቀን2017 ዓ.ም የአዲስ ስታንዳርድን ቢሮ መበርበራቸውን፣ የዜና ክፍል ኃላፊውንና የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊውን ለምርመራ ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መውሰዳቸውን የድርጅቱ መስራች ፀዳለ ለማ ለጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ተቋሙ (CPJ) ተናግረዋል።

ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳላቸው ቢናገሩም፣ ግልባጭ ሳያሳዩ ወደ ተቋሙ ቢሮ ዘው ብለው መግባታቸውን፤ የተቋሙ ጋዜጠኞች ሁከት ሊያስከትል የሚችል ዘጋቢ ፊልም በማዘጋጀት ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እንደነገሯቸው ፀዳለ ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ ክሱ ሀሰት መሆኑንና ድርጅቱ ዘጋቢ ፊልሞችን የማዘጋጀት አቅም እንደሌለው መግለጻቸውን ሲፒጄ በመግለጫው አካቷል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
#Update

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16187/

በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ከ150 በላይ ሰዎች መጎታቸው ተገለጸ፡፡

#Ethiopia | በቱርክ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለማምለጥ የሞከሩ ሰዎች ተጎድተው ለህክምና ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል፡፡

በሬክተር ስኬል 6.2 በተመዘገበው በዚሁ አደጋ በድምሩ 16 ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባቸውን ሦስት ከተሞች ማካለሉ ተዘግቧል፡፡ #timescolonist

#Thiqah

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
SHIRGOOD Concert

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/16189/

በ ሽርጉድ ኮንሰርት እየተዝናኑ ዕድለኛ ይሁኑ!

Ethiolottery.et

የኢትዮጵያ ጥሪ አገልግሎት

TICKETS AVAILABLE ON

ETHIOPIAN LOTTERY SET

SHIRGOOD ENTERTAINMENT

nont 50ሺ ብር ለማሽነፍ፤

ETHIOLOTTERY.ET

AL P50 ሚሊየን ብር ሎተሪ ይቀረጡ!

SCAN and REGISTER

TAMCON

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet