Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
6.86K subscribers
2 photos
5.86K links
ይህ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18883/

#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከምድር እስከ ህዋ ድረስ የሚገኙ መረጃዎችን በመተንተን የምርምር ሥራዎችን የሚያከናውን ተቋም መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የምርምር ሥራዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየተተነተኑ ቅድመ ትንበያና የትንበያ ሥራዎችን በመሥራት ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲጠቀሙበት ያስችላል ተብሏል፡፡

የጂኦ ስፓሻል ጥናትና ምርምር በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀረ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በዛሬው ጉብኝትም በየሥራ ክፍሎቹ የሚከናወኑ የመረጃ ትንተና እና ምርምር ሥራዎች ምልከታ ተደርጓል፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የሦስቱን አባቶችን ይቅርታ ተቀብሏል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18885/

#Ethiopia | ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካልፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚዲያ ያስተላለፏቸው ትምህርቶች ስሕተትና ነቀፋ ያለባቸው መሆናቸውን አምነው ቅዱስ ሲኖዶስንና መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታ በመጠየቅ ሊቃውንት ጉባኤ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቅስ ያቀረበውን አስተምህሮ የተማሩት የሚያምኑትና የሚያስተምሩት መሆኑን በመግለጻቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስቱን አባቶች ይቅርታ ተቀብሎ ወደፊት እንዲህ ዐይነት የስሕተት ትምህርት ውስጥ እንዳይገኙና ነቀፋ ያለበትን ትምህርታቸውን በማረምና በማስተካከል ርቱዕ የሆነውን የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን ሥርጭት ድርጅት በመቅረብ ትምህርት እንዲሰጡ በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ

ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ሕይወታችሁ በከንቱ እያለፈ እንደሆነ ለምታስቡ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18887/

#Ethiopia | አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ በአማካኝ 10 ሺ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ያመጣል ይባላል፡፡ ይህ ተጽእኖ ለክፉውም ሆነ ለደጉ የሚሰራ ሂደት ነው፡፡

በሕይወታችሁ ቢያንስ የአንድ ሰውን ሕይወት የሚለውጥ ተግባር ካከናወናችሁና ግባችሁን ከመታችሁ ሕይወታችሁ በከንቱ እንዳላለፈ ላስታውሳችሁ፡፡

አንድን ሰው ስትለውጡ፣ የአሁኑን ወይም የወደፊቱን የትዳር አጋር፣ ልጆች፣ ወዳጆችና በዚያ ሰው ተጽእኖ ስር የሚወድቁ ሰዎችን ሁሉ ሕይወት ትነካላችሁ፡፡

ከዚህ ስሌት የተነሳ ነው ቢያንስ ከ10 ሺ ያላነሰ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ የምታመጡት፡፡

ዘንግታችሁት ነው እንጂ፣ መልካም ተጽእኖ የማምጣት ብቃት ያላችሁ ሰዎች ናችሁ!

#Dreyob

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የህትመት ንግድዎን ወደ ከፍታ ለማድረስ ዝግጁ ነዎት?

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18889/

#Ethiopia | ~ NeTags በ MO ቢዝነስ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሥራዎትን ወደፊት ማራመድ የሚችሉብትን መንገድ አቅርበንሎታል!

እኛ – NeTags እንባላለን።

እ.ኤ.አ. በ2022 የተመሰረተው NeTags 🇦🇺 በሜልበርን፣ አውስትራሊያ እና 🇨🇦 በኤድመንተን፣ ካናዳ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ እየሰራን እንገኛለን።

ኢትዮጵያዊው MO ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማ. በ Open-Source SaaS solution በመጠቀም የሕትመት ኩባንያዎች ዲጂታል የንግድ ካርዶችን በራሳቸው ብራንድ እንዲይዙ፣ እንዲቀይሩ እና እንዲሸጡ ያስችላችዋል። እንዲሁም ይህን የፈጠራ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል።

ዲጂታል ቢዝነስ ካርዶች ..

የባህላዊ የወረቀት ቢዝነስ ካርዶች ጊዜ ያለፈባቸው እየሆኑ ነው። አንድ NeTags ዲጂታል ካርድ ያልተገደበ መረጃን ለምሳሌ 100,000 የወረቀት ካርዶችን ሊተካ ይችላል።

የደንበኛ ዝርዝሮች እና የኩባንያ መረጃ
ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አገናኞች
ነፃ የኢኮሜርስ ምርት ማሳያ
አብሮ የተሰራ የቀጠሮ ማስያዣ ስርዓት እና ቀላል የካርድ አስተዳደር በNeTags መተግበሪያ ያገኛሉ።

ይህ ለህትመት ንግድዎ

በNeTags በሦስተኛ ወገን ላይ ከመተማመን ይልቅ እርስዎ የቴክኖሎጂው ባለቤት ይሆናሉ።

ሶፍትዌሩን በመጠቅም የሚያገኙት ጥቅሞች፡-

ሙሉ የሶፍትዌር ባለቤትነት— virtual cards ካርዶችን እና ድረ-ገጾችን በመስራት ሙሉ በሙሉ ማስተዳደር ይችላሉ

የደንበኛ ቁጥጥርን ያውቃሉ- ሁሉንም ተጠቃሚዎች በራስዎ ሶፍትዌር ውስጥ ያስተዳድራሉ

ያልተገደበ መዳረሻ – በአጠቃቀም ላይ ምንም ገደቦች የሉትም

የራስ ብራንዲንግ – ዲጂታል የንግድ ካርዶችን በራስዎ የምርት ስም ያትማሉ እና ይሽጣሉ

የቴክኒክ ድጋፍ እና ስልጠና እንሰጣለን —ሙሉ በሙሉ ስለ አጠቃቀሙ የተረዱ መሆንዎን እናረጋግጣለን።

ልዩ እና ትርፋማ ሞዴል ነው – የተወሰኑ የማተሚያ ድርጅቶች ብቻ ያገኛሉ!

የአጭር ጊዜ ዕድል – አሁን ይቀላቀሉ!
ከጊዜ ጋር ይዘምኑ!

MO ቢዝነስ ~ ከእኛ ጋር አጋር ከሆኑ፤ አጋር ኩባንያዎች በዲጂታል ቢዝነስ ካርድ ኢንዱስትሪ ውስጥ ቁልፍ ተዋናዮች ይሆናሉ። ለአነስተኛ የህትመት ንግዶች መዳረሻ የመስጠት መብት አላቸው።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
+251-925267272
+251-925255151

https://app.netagstore.com

📍 አድራሻ
ጀሞ 1፣ Sun Moon Star Mall፣ 3ኛ ፎቅ – MO Business PLC

🌐 የበለጠ ለመረዳት፡ sales@netagstore.com
📞 ዛሬ ያግኙን!

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በስተመጨረሻም አይጦቹ ጠፉ !

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18892/

#Ethiopia | ኦልድትራፎርድ አይጦች ታዩ በማለት የክለቡ የጥራት ኮከብ ተቀንሶ ነበር አሁን ግን በምግብ ንፅህና የ2 ኮኮቦች ተሸልመዋል።

በኤፕሪል 16 ተደርጎ በነበረው የትራፎርድ ካውንስል የፍተሻ ሪፖርት “የአይጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ትልቅ ስራ መሰራቱን አምኗል” ነገር ግን የስታዲየሙ ሰባት የተለያዩ ቦታዎች – አምባሳደር ላውንጅ፣ ስዊት 7 እና የዴቪል ባርን ጨምሮ አይጥ እንደነበረባቸው ተገልጿል።

የማንቸስተር ዩናይትድ ቃል አቀባይ ክለቡ “በኦልድትራፎርድ ጠንካራ የተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴን በመተግበር ላይ ነው” እና “አፋጣኝ እና ተገቢ እርምጃ እየተወሰደ ነው” ብለዋል።
#4-3-3 sport

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት 46 ዊልቼሮችን ለአካል ጉዳተኞች አበረከተ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18894/

#Ethiopia | የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚኖሩ የአካል ጉዳት ገጥሟቸው ከቤት ወጥተው ለመንቀሳቀስም ሆነ ወደ ትምህርት ገበታ ለመቀላቀል ችግር ለገጠማቸው ልጆችና በተለያየ ምክንያት ለጉዳት ለተጋለጡ አዋቂዎች 46 ዊልቼሮችን አበርክቷል።

ድጋፉ በልጆቻቸው የአካል ጉዳት ምክንያት መስራትም ሆነ ልጆቻቸውን ማንቀሳቀስ ለተቸገሩ ወላጆች እፎይታን እንደሚሰጥ ‎ጸሕፈት ቤቱ ጠቅሷል።

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ፤ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጿል::

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“ ”አበባዩ” አዲስ ፊልም

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18896/

🎯🎯 ”አበባዩ” 🎯🎯አዲስ ፊልም

Fm pictures,B pictures የተዘጋጀው የፉአድ ሙስጠፉ አዲስ ፊልም ግንቦት 22/23/24 በድጋሜ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በታላቅ ድምቀት ይመረቃ።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ግንቦት 21 ከሐመረ ብርሀን ደብረ ምጥማቅ ማርያም አይቀርም!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18898/

በጎንደር ከተማ ቀበሌ 06 የምትገኘው ሐመረ ብርሃን ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በህዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ርብርብ ግንባታዋ 40 በመቶ ደርሷል።

ቤተ ክርስቲያኗ ከ300 ዓመታት በላይ አስቆጥራለች። አሁን በመሰራት ላይ ያለችው ቤተ ክርስቲያንም 1,700 ካሬ ላይ ያረፈች ሲሆን ስራው ከተጀመረም አንድ አመት ከ5 ወራት አልፎታል።

በዚህ ስራ ላይም እጅግ በርካታ የጎንደር ምዕመናን እየተሳተፈ ይገኛል።

በነገው እለት ማለትም ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ ሁኔታ ስለሚከበር የጎንደር ከተማ እና አካባቢው ምዕመናን መጥተው እንዲያከብሩ ተጋብዘዋል። አድራሻ፦ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 06 ነው።

ጠሪ:- ቤተ ክርስቲያኗ

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የኤም ፖክስ በሽታ በኢትዮጵያ ያለው የስጋት ደረጃ ዝቅተኛ ነው፡- የጤና ሚኒስቴር

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18900/

#Ethiopia | የኤም ፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ) በሽታ በዓለም አቀፈ ደረጃ የህብረተሰብ ጤና ስጋት ተብሎ ተየቀመጠ ቢሆንም በኢትዮጵያ ያለው የስጋት መጠን ዝቅተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኤም ፖክስ በሽታ ተጠቂ በኢትዮጵያ መመዝገቡን ተከትሎ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ለመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማብራያ ሰጥተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ አስተዳደር እስካሁን የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሦስት ሰዎች ላይ በሽታው ተገኝቷል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የቅኝት እና የምላሽ ስራዎች በጤና ሚኒስቴር እና ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሽታው በንክኪና በመተንፈሻ አካላት ቅርርብ የሚተላለፍ እንደመሆኑ መጠን፣ በሽታው በተገኘበት አካባቢ ከበሽታው ተጠቂዎች ጋር ቅርበት ያላቸው ሰዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።

የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠርም በየብስ እና በአየር በሚደረጉ ጉዞዎች ላይም ቅኝት እየተደረገ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ በሽታው በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት አምስት ወራት በ78 በመቶ አድጎል ያሉት ጤና ሚኒስትሯ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ ዝግጅት እና የምላሽ ስራዎች በቅንጅት እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

የበሽታው ምልክት ሽፍታ፣ ትኩሳት፣ ንፍፊት፣ እብጠት፣ የጡንቻ እና የጀርባ ሕመም በመሆኑ እነዚህን ምልክቶች ያየ ሰው በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም እንዲቀርብ ተጠይቋል።

አልያም 8335 እና 952 ነፃ የጥሪ አገልሎት እንዲያሳውቅ ተጠይቋል።
#fmc

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አርኤስኤፍ በፈፀማቸው ጥቃቶች ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ቆሰሉ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18902/

#Ethiopia | በምዕራብ ሱዳን ሰሜን ኮርዶፋን ግዛት በሚገኘው የትራንስፖርት ጣቢያ ላይ ያነጣጠረ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች ሲገደሉ 18 መቁሰላቸው ተሰምቷል። በሌላ ጥቃት በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በኮስቲ፣ ዋይት ናይል ግዛት የሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ መጋዘን መመታቱ ተገልፆል።

የሰሜን ኮርዶፋን ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል ኦቤይድን ጨምሮ በኮርዶፋን ክልል የሚገኙ ከተሞች በአርኤስኤፍ ከባድ መሳሪያዎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ለሳምንታት የማያቋርጥ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሲሆን በዚህም በደርዘን የሚቆጠሩ ሲቪሎች ተገድለዋል። “የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች ንብረት የሆነው ሰው አልባ አውሮፕላን የአል-ራሃድ አካባቢ አካል በሆነው አል-ሳሚሃ አካባቢ በሚገኝ የህዝብ ማመላለሻ ጣቢያ ላይ ኢላማ ያደረገ ሲሆን በጥቃቱም ቢያንስ ሶስት ሰዎችን ገድሎ 18 ሰዎችን አቁስሏል” ሲሉ የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል።

የሱዳን ጦር እና የአር ኤስ ኤፍ ታጣቂዎልኞች በሚያደርጉት የትጥቅ ግጭት በኮርዶፋን ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተባባሱ ጦርነቶች ተስተውለዋል። በኮርዶፋን ያለው የሰራዊቱ ወታደራዊ ዘመቻ ደቡብ ኮርዶፋን እና ዳርፉርን ለመቆጣጠርና በክልሉ ትልቋ ከተማ የሆነችው ኤል ፋሸር ላይ ያለውን ከበባ ለመስበር ያለመ ነው ተብሎለታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አርኤስኤፍ በሰሜን፣ ምዕራብ እና ደቡብ ኮርዶፋን ያለውን ቦታ አጥብቆ እየተከላከለ ሲሆን የሰራዊቱን ግስጋሴ ለማደናቀፍ የሰሜን ኮርዶፋን ዋና ከተማን በስትራቴጂካዊ መሳሪያዎች ደጋግሞ ኢላማ አድርጓል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኮስቲ በሚገኘው የነዳጅ ማከማቻ መጋዘን አርኤስኤፍ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ከፈፀመ በኃላ የመብት ተሟጋቾች የእሳት ነበልባል እና ጭስ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን አሰራጭተዋል።

የነጭ ናይል ግዛት ገዥ ሌተና ጄኔራል ካማር አል ዲን መሀመድ ፋድል ከጥቃቱ በኋላ የነጭ አባይ ነዳጅ ማከማቻን የጎበኙ ሲሆን በሰዓቱ የሲቪል መከላከያ ሃይሎች እሳቱን ለማጥፋት እየሰሩ ነበር ተብሏል። ገዥው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ስትራቴጂክ እና የአገልግሎት ጣቢያዎችን ኢላማ ማድረግ የፈሪ ድርጊት ነው በማለት አውግዘውታል። አክለውም የአጥቂዎችን “የሞት ጣር” በማለት በመግለፅ ሰራዊቱ የድሮን መንደርደርያ ጣብያዎችን የመቆጣጠር እና የማጥፋት ችሎታ እንዳለውም አረጋግጠዋል።
#BisratRadio

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኢትዮጵያዊቷ የእግር ኳስ ኮከብ ሎዛ አበራ የ Love In Action የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆነች

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18904/

#Ethiopia | Love In Action የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ካፒታን ሎዛ አበራን እንደ ኦፊሴላዊ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።

በዚህ ሚናዋ ሎዛ ድርጅቱ በሚያረጋቸው ህጻናትን በትምህርት እና በማህበረሰብ ልማት ፕሮግራሞች ለማሳደግ የሚያደርገውን ስራ በማስተዋወቅ እና በማስተባበር ትሰራለች።

የአምባሳደርነት ስራዋን ለመጀመር፣ ሎዛ ህዝቡን በMay 31፣ 2025 ከጠዋቱ 8:00 (Glenmont Shopping Center) ሰአት ላይ በሚካሄደው Love In Action 4Km ጎዛ/ሩጫ ላይ ሁሉም ሰው እንዲሳተፍ ጥሪ አድርጋለች።

ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ህጻናት የትምህርት sponsorship እና የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራሞች ለመደገፍ ያለመ ነው።

“Run with Purpose” በማለት ሎዛ በማህበራዊ ሚዲዋ ላይ ሰዎችን በዚህ ትልቅ አላማ ያለው ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ በማበረታታት ላይ ትገኛለች።

Love In Action ንፁህ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ እና የትምህርት መሳሪያዎችን በማመቻቸት የብዙ ህፃናትን ህይወት በመቀየር ላይ እየሰራ ይገኛል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
“ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የባህር በር የማግኘት መብት አላት”

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18906/

“ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የባህር በር የማግኘት መብት አላት”
– አምባሳደር ግሬጎር ሹስተርቺት

#Ethiopia | ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነትን መርህ የባህር በር የማግኘት መብት እንዳላት አምባሳደር ግሬጎር ሹስተርቺትስ ገለጹ።

የኢንስብሩክ ዩኒቨርሲቲ የአውሮፓ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሚኒስቴር የህግ አማካሪ እና የአውሮፓ እና ዓለም አቀፍ ህጎች የክብር ፕሮፌሰር ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የባህር በር ኮንቬንሽን መሰረት የባህር ዳርቻ ከአላቸው ጎረቤት ሀገራት ጋር በመስማማት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የባህር በር የማግኘት መብት አላት፡፡

አምባሳደር ግሬጎር ሹስተርቺትስ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ “የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የባህር ዳርቻ ማግኘት የሚችሉበት ዕድል ከዓለም አቀፍ ህግ አንጻር” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።

ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ፤ ኢትዮጵያ የጋራ ተጠቃሚነት መሰረት ባደረገ መርህ በሚካሄድ ድርድር የባህር በር የማግኘት መብት እንዳላት ዓለም አቀፍ ህጎች የሚያረጋግጡት እውነት ቢሆንም ይህ መብት ተፈጻሚነት የሚኖረው የባህር ዳርቻ ካለው ሀገር ጋር በሚደረግ ስምምነት ነው ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የባህር በር ህግ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በአካባቢው ያለውን የባህር በር የመጠቀም እና የመሸጋገር ዓለም አቀፍ መብት መደንገጉን ጠቁመዋል።

የባህር ኮንቬንሽን አንቀጽ 25 ወደብ የሌላቸው አገሮች ወደ ባህር የመግባት መብት እንዳላቸው ይግልጻል ሲሉ አስረድተዋል።

ይህ መብት የባህር በር ባለው ሀገር እና የባህር በር በሌለው ሀገር መካከል ስምምነት ላይ ከተደረሰ ሊፈጸም እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከብዙ ሀገራት ጋር ስምምነት መፍጠር የሚያስችል ልዩ አማራጮች አሏት፤ ነገር ግን ዕድሉን ለመጠቀም መንገዶችን መፈለግ እና ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድን መምረጥ ይኖርባታል ብለዋል።

የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው እንቅስቃሴ የአካባቢውን ፍላጎት ባገናዘበ እና በፍትሃዊነት መርሆች ላይ በተመሰረተ መንገድ መሆን አለበት ሲሉም አመልክተዋል።

የባህር በርን ማጋራት የንግድ ልውውጥ፣ ሰፊ የስራ ዕድል፣ የቱሪስት ፍሰት እና ሌሎች ዕድሎችን ስለሚያመጣ ለኢኮኖሚ ጠቃሚ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ዕድሉን በመመልከት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ አብሮ ለማደግ ይሰራሉ ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

#gazette_plus

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
በኢትዮጵያ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ብርቅዬ የተባለውን ሰማያዊ ላቫ አመነጨ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18908/

#Ethiopia | የኢትዮጵያ እሳተ ገሞራዎች ውስጥ እጅግ ብርቅዬ የሚባለውን ሰማያዊ ላቫ እየፈነጠቀ መሆኑ እንደ ክስተት እየታየ ይገኛል። ከኢንዶኔዢያ ጃቫ ግዛት ካዋ ኢጄን እሳተ ገሞራ ጋር ተመሳሳይነት አለው የተባለው ሰማያዊ ላቫው በመጀመሪያ እይታ ላቫው ከተራራው ላይ እየፈሰሰ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ ያልተለመደ ፍካት እንደሚታሰበው አይደለም።

“ሰማያዊ እሳት” እየተባለ የሚጠራው ይህ ክስተት በላቫ የተፈጠረ ሳይሆን ከእሳተ ገሞራው ስንጥቆች በሚወጡት የሚቃጠሉ የሰልፈር ጋዞች የሚመጣ መሆኑ ተገልጿል።

እስከ 600°C (1,100°F) የሚደርስ ሙቀት ያላቸው ትኩስ ጋዞች በአየር ውስጥ ከሚገኘው ኦክሲጅን ጋር ሲገናኙ፣ በእሳት ተያይዘው ደማቅ ሰማያዊ ነበልባል ይፈጥራሉ።

በካዋህ ኢጄን ያለው ትክክለኛው ላቫ እንደ አብዛኞቹ እሳተ ገሞራዎች የተለመደው ቀይ-ብርቱካናማ ቀለም ያለው ቢሆንም፣ የሚቃጠለው ሰልፈር ነበልባል የሚያብረቀርቅ ሰማያዊ ላቫ ምስልን የሚፈጥር ሲሆን በሌሊት ብቻ የሚታይ አስደናቂ ትዕይንት ነው ተብሏል፡፡
#menahriaFm

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ኦሮሚያ ባንክ ሚልኪ የተሰኘ ዲጂታል የብድር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መተግበርያ አስተዋወቀ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18910/

#Ethiopia | ባንኩ ያዘጋጀው ሚልኪ ዲጂታል የብድር አገልግሎት መስጫ መተግበርያ አስተዋውቀዋል።

የኦሮምያ ባንክ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተፈሪ መኮንን እንደተናገሩት ከመደበኛው የብድር አገልገሎት አሰጣጥ የተለየ ያለ ምንም ማስያዣ ዜጎች የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት መተግበርያ ነው ብለዋል።

በማስያዥ ምክንያት ከባንክ ጋር የተራራቁ ዜጎች ወደ ባንክ እንዲመጡ እና ብድር እንዲያገኙ በማሰብ ነው መተግበርያው ያስጀመርነው ብለዋል።

የሀገር ኢኮኖሚ ለማሳለጥ ኦሮምያ ባንክ ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ ቴክኖሎጂ እያስተዋወቀ ይገኛል ብለዋል።

ሚልኪ ዘመናዊ የብድር መስጫ አገልግሎት ሲሆን ዋስትናው ታማኝነት ነው ብለዋል።

ይህ የብድር ስርአት ታማኝ ለሆኑ ዜጎች የተዘጋጀ ሲሆን ዜጎች ታማኝነታቸው እንዲቀጥሉበት እና ጊዜያዊ የገንዘብ ችግራቸውን የሚያሸንፉበት እድል እንዲጠቀሙ ስራ አስፈጻሚው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሚልኪ አምስት አይነት አገልግሎት የያዘ ሲሆን ለባንኩ ሰራተኞች ለግል መስራቤት ሰራተኞች ለወጣቶች እንዲሁም ለሴቶች የብድር አገልግሎት ይዟል ነው የተባለው።

እንዲሁም ለቤት እቃዎች ለማማላት ታስቦ የተዘጋጀ የብድር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስርአትም ይዟል ብለዋል።

ሞባይላችን ለእንነዚህ አይት ቁም ነገሮች መጠቀም ይገባናል ብለዋል።

ሚልኪ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ ከ7ሺህ በላይ ደንበኞች የብድር አገልግሎት ያገኙ ሲሆን ባንኩ በ17 አመት ካበደራቸው ዜጎች በሶስት መቶ ብልጫ ማሳየቱን ነው የተነገረው።

ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትም የራሱን እርሾ እየጣለ ይገኛል ተብሏል።

ኦሮሚያ ባንክ ያስተዋወቀው ሚልኪ የብድር አገልግሎት መስጫ መተግበርያ ብሔራዊ ባንክ ተቀብሎ ወደ ስራ እንዲገባ አድርጓል።

ባሁኑ ሰአት ደንበኞቹ ከ7 ሚሊዮን በላይ መሆናቸው ተናግረዋል።

ሚሊኪ የብድር አገልግሎት ብቻ አይደለም የማህቀሠሰቡን ህይወት የሚቀይር ስርአት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ውስን የነበረው የብድር አገልግሎት ሁሉም ማህበረሰብ እንዲጠቀሙ በማሰብ ነው አገልግሎቱን ያበለጸግነው ብለዋል።

ይህ ሲስተም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያዊያን አቅም የተሰራ ነውም ብለዋል።

ሚሊኪ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን እድል ይዞ የመጣ ነው ብለዋል።

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰሎሞን ደስታ የኢትዮጵያ የዲጂታል የፋይናንስና አገልግሎት ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ወደ ሚሆን ደረጃ ተሸጋግሯል ብለዋል።

ኦሮሚያ ባንክ ያስተዋወቀው መተግበርያ ባንኮች ከውጪ ባንኮች ጋር እኩል እንዲራመዱ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ዩናይትድ ሽንፈት አጋጥሟቸዋል

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18912/

#Ethiopia | የውድድር ዘመኑ ባሳለፍነው እሁድ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ማሌዥያ በማቅናት በኳላላምፑር የድህረ የውድድር ዘመን ያደረጉት የአቋም መገምገሚያ ጨዋታን በሽንፈት አጠናቀዋል።

ከእስያ All-star ጋር ጨዋታቸውን ያደረጉት ዩናይትዶች 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት የተሸነፉ ሲሆን በጨዋታው 3 ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ብቻ ማድረጋቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

በቀጣይ የፊታችን አርብ ከሆንግ ኮንግ ብሄራዊ ቡድም ጋር ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል።

የቡድኑ ይፋዊ የቅድመ ውድድር ዝግጅቶች በቀጣዩ ሀምሌ ወር በአሜሪካ የሚጀምሩ ይሆናል።

ቀያዮቹ ሰይጣናት የ2024/25 የውድድር ዘመንን 11 የሊግ ጨዋታዎችን ብቻ በማሸነፍ 15ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው የሚታወቅ ነው።
#menahriaFm

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የዘጠኝ ዓመት ልጅ አግተው ከወላጆቹ ሶስት ሚሊየን ብር የተቀበሉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18914/

#Ethiopia | በሸገር ከተማ አስተዳደር ፉሪ ክፍለ ከተማ ውስጥ የዘጠኝ ዓመት ወንድ ልጅ አግተው ከወላጆቹ ሶስት ሚሊየን ብር የተቀበሉ ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን የሸገር ከተማ አስተዳደር ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት አስታውቋል ።

የሸገር ከተማ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የሴቶች ፣ ህፃናት እና የህገወጥ ሰዎች ዝውውር ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ዓቃቢ ህግ የሺ በንቲ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት 1ኛ ተከሳሽ ሰፍያዲን ሽፋ እና 2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ጉቱ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ቪትስ ተሽከርካሪ ይዘው ፉሪ ክፍለ ከተማ ሙዳ ፉሪ ወረዳ ሰላም መስጊድ ቀበሌ ልዩ ቦታው ዲያስፖራ የተባለ አካባቢ ድርጊቱን መፈጸማቸው ተገልጿል ።

የዘጠኝ ዓመቱን ልጅ መሐመድ ቃሲምን መስጊድ አሣየን ብለው የያዙት ተሽከርካሪ ውስጥ አስገብተው ወደ አዲስ አበባ እንደተጓዙ ገልፀዋል። ተከሳሾቹ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ አስራ ስምንት የተባለ ቦታ መኝታ ተከራይተው ልጁን በማስፈራራት ዝም እንዲል ማድረጋቸው ተጠቁሟል። ወላጆቹ ጋር ደውለው ሶስት ሚሊዮን ብር ካልተላከላቸው ልጃቸውን በሬሣ ሳጥን አድርገው እንደሚልኩላቸው በማስፈራራት ወላጆችን ሲያስጨንቁ እንደነበረ ቃላቸው ሰጥተዋል።

ወላጆችም ታህሳስ 7 ቀን 2017ዓ.ም በሁለተኛ ቀን የተባሉትን ብር አሰባስበው በመላካቸው የዘጠኝ ዓመቱን ልጅ ምሽት ላይ መስጊድ ውስጥ አስቀምጠው ሊሠወሩ ችለዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ በወቅቱ ቢያመልጡም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከአንድ ሳምንት በኋላ የካቲት 14ቀን 2017 ዓ.ም ሁለቱንም በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

ፖሊስ በሁለቱን ተከሳሾች ላይ አስፈላጊው ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለዓቃቢ ሕግ የላከ ሲሆን ዓቃቢ ሕግም በወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ አንቀፅ 1 እና በወንጀል ሕግ ቁጥር 590 ንዑ አንቀፅ 1 በመጥቀስ በሰው መጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል።

በዓቃቢ ህግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ለአካለ መጠን ያልደረሠ ልጅን፣በተንኮል በማታለል ጠልፈው መውሰዳቸው በማስረጃ ሙሉ በሙሉ በመረጋገጡ 1ኛ ተከሳሽ ሰይፍያዲን ሽፋ በ 11 ዓመት 2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል በ10 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሠኑን ዓቃቢ ሕግ የሺ በንቲ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
50 ሚሊዮን ብሩ ሊወጣ 10 ቀናት ብቻ ቀርተዋል!

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18916/

ሎተሪውን በስጦታም ለቤተሰብዎ፤ ለወዳጅዎ ይላኩ!

ስልክዎን አስጠግተው በኪው አር ኮድ ይግቡ፤
ወይንም ሊንኩን ተጭነው ሃምሳ ሚሊየን ብር ይውሰዱ

https://www.ethiolottery.et/registration?scannerId=getu-temesgen&eventId=getu-temesgen

ይቅናዎት – ይቅናን!

ዛሬ የ50 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ለሚቆርጡ 10 እድለኞች ለእያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ቦነስ ሽልማት ተዘጋጅቷል!

https://ethiolottery.et እንዲሁም በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ አሁኑኑ ይቁረጡ!

ይህን ዕድል ከወዳጅዎ ጋር ይጋሩ!

እናንተ ፤ በመላው ዓለም 🌍 የምትገኙ
ሎተሪውን በስጦታም ለቤተሰብዎ፤ ለወዳጅዎ ይላኩ!

ስልክዎን አስጠግተው በኪው አር ኮድ ይግቡ፤
ወይንም ሊንኩን ተጭነው ሃምሳ ሚሊየን ብር ይውሰዱ
https://www.ethiolottery.et/registration?scannerId=getu-temesgen&eventId=getu-temesgen

😍 ልብ በሉ
50 ሚሊየን ብር! 10 ቀናት ብቻ ቀረው!

ግንቦት 30!

የ50 ሚሊየን ብር ሎተሪ አሁኑኑ ይቁርጡ!

በ200 ብር መልቲ ሚሊየነር ይሁኑ! የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

ስልክዎን አስጠግተው በኪው አር ኮድ ይግቡ፤
ወይንም ሊንኩን ተጭነው ሃምሳ ሚሊየን ብር ይውሰዱ

https://www.ethiolottery.et/registration?scannerId=getu-temesgen&eventId=getu-temesgen

መልካም እድል!

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

ለተጨማሪ መረጃ +251977717272 ላይ ይደውሉ፡፡

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
ፈጥነን እንድርስለት

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18919/

#Ethiopia | ለወንድማችን ጋዜጠኛ ቴድሮስ ካሳሁን
እባካችሁ አግዙኝ ይላል በእዚህ ዮቱብ ላይ በለቀቀው በእራሱ ንግግር

https://youtu.be/yOWKLq7DBos?si=pmL28PqlGgIHK2jI

Tewodros Kasahun Tekle ቴዎድሮስ ካሳሁን ተክሌ የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ
ነው። በኢቢኤስ ቴሌቭዥን እና በፋና ቴሌቭዥን
የፋና ላምሮት የድምፃዊያን ውድድርን በራሱ ቀለም እና ፈጠራ በብቃት በመምራት ይታወቃል።

የፋና ላምሮት የመጀመሪያው የመድረክ አስተዋዋቂ ነበር።
#ፋና_ላምሮትን ከምዕራፍ 1 እስከ ምዕራፍ 4
የመጀመሪያውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን በብቃት አቅርቦ ነበር።

ቴዲ በአሁኑ ሰዓት
ሁለት ልጆቹን በኪራይ ቤት ጥሎ ፀበል ቦታ ነው የሚገኘው።
የገንዘብ እጥረትም አጋጥሞታል።
እባካችሁ እርዱኝ አግዙኝ እያለ ነው።

ደጋግ ኢትዮጵያውያን ቴዲን ለመርዳት

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር ፦
1000298227707

የቻላችሁትን መርዳት ትችላላችሁ።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
አልተዘረፍኩም! … የዝርፊያ ሙከራ ተደርጎብኝ አከሽፊያለሁ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18922/

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

#Ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የነበረ 7.7 ቢሊዮን ብር መዘረፉን ወይም ከባንኩ ወደ ግለሰቦች አካውንት መዞሩን ፤ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙ ፤ በዚህ ላይ የተሳተፉ አካላት እያንዳንዳቸው 50 ሚሊዮን ብር እንደደረሳቸው እና ባንኩም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ መረጃ እየተሰራጨ ነው።

ባንኩ ግን ይህ ” ፍጹም ውሸት ነው ፤ ምንም የተዘረፈ ገንዘብ ” የለም ብሏል።

” ከባንካችን ምንም የተዘረፈ ገንዘብ የለም ” ያለው ንግድ ባንክ ” ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ ነው ” ሲል ገልጿል።

ባንኩ ፤ የመዝረፍ ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች በውስጥ ቁጥጥር ስርአቱ አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ደርሶበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ሙከራውን ወዲያውኑ እንዳከሸፈው አሳውቋል።

” ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንካችንን ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አይደለም ” ብሏል።

ባንኩ፥ ” የገንዘብ ዝርፊያ ሙከራው ከከሸፈ በኃላ ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማሳወቅ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ የምርመራ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ” ሲል ገልጿል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
የዘጠኝ ዓመት ልጅ አግተው ከወላጆቹ ሶስት ሚሊየን ብር የተቀበሉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

ተጨማሪ ይመልከቱ 👉
https://amharic.getutemesgen.et/18924/

#Ethiopia | በሸገር ከተማ አስተዳደር ፉሪ ክፍለ ከተማ ውስጥ የዘጠኝ ዓመት ወንድ ልጅ አግተው ከወላጆቹ ሶስት ሚሊየን ብር የተቀበሉ ሁለት ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸውን የሸገር ከተማ አስተዳደር ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት አስታውቋል ።

የሸገር ከተማ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የሴቶች ፣ ህፃናት እና የህገወጥ ሰዎች ዝውውር ወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ ዓቃቢ ህግ የሺ በንቲ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት 1ኛ ተከሳሽ ሰፍያዲን ሽፋ እና 2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ጉቱ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ቪትስ ተሽከርካሪ ይዘው ፉሪ ክፍለ ከተማ ሙዳ ፉሪ ወረዳ ሰላም መስጊድ ቀበሌ ልዩ ቦታው ዲያስፖራ የተባለ አካባቢ ድርጊቱን መፈጸማቸው ተገልጿል ።

የዘጠኝ ዓመቱን ልጅ መሐመድ ቃሲምን መስጊድ አሣየን ብለው የያዙት ተሽከርካሪ ውስጥ አስገብተው ወደ አዲስ አበባ እንደተጓዙ ገልፀዋል። ተከሳሾቹ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ አስራ ስምንት የተባለ ቦታ መኝታ ተከራይተው ልጁን በማስፈራራት ዝም እንዲል ማድረጋቸው ተጠቁሟል። ወላጆቹ ጋር ደውለው ሶስት ሚሊዮን ብር ካልተላከላቸው ልጃቸውን በሬሣ ሳጥን አድርገው እንደሚልኩላቸው በማስፈራራት ወላጆችን ሲያስጨንቁ እንደነበረ ቃላቸው ሰጥተዋል።

ወላጆችም ታህሳስ 7 ቀን 2017ዓ.ም በሁለተኛ ቀን የተባሉትን ብር አሰባስበው በመላካቸው የዘጠኝ ዓመቱን ልጅ ምሽት ላይ መስጊድ ውስጥ አስቀምጠው ሊሠወሩ ችለዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሾቹ በወቅቱ ቢያመልጡም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከአንድ ሳምንት በኋላ የካቲት 14ቀን 2017 ዓ.ም ሁለቱንም በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

ፖሊስ በሁለቱን ተከሳሾች ላይ አስፈላጊው ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለዓቃቢ ሕግ የላከ ሲሆን ዓቃቢ ሕግም በወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ አንቀፅ 1 እና በወንጀል ሕግ ቁጥር 590 ንዑ አንቀፅ 1 በመጥቀስ በሰው መጥለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል።

በዓቃቢ ህግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ለአካለ መጠን ያልደረሠ ልጅን፣በተንኮል በማታለል ጠልፈው መውሰዳቸው በማስረጃ ሙሉ በሙሉ በመረጋገጡ 1ኛ ተከሳሽ ሰይፍያዲን ሽፋ በ 11 ዓመት 2ኛ ተከሳሽ ዳንኤል በ10 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሠኑን ዓቃቢ ሕግ የሺ በንቲ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የጌጡ ተመስገንን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet
@getutemesgenet