አሳ ባራ ጊቴ!!!"!
ሃውሳ ዝናብ አይጥል፤
አዋሽ የሰጠውን ፤ ያበቅላል በመስኖ፤
ገምሻራየዋየ፤
ታየኝ ሰውነቷ ጃምዮ እሸት መስሎ።
ኣሳ ባራ ጊቴ፤አቶብስ የሚቴ፤
ሚሌ ወዲህ ሃራ፤ ባቲም ጎረቤቴ፤
የአፋር ልጅ ስትዘልቅ፤
ደርሶ ይታከማል፤ የሰራ አካላቴ።
አፋር በረሃ ነው ይለኛል ሞኝ ሰው፤
የአዋሽ ዳርን ሸንኮር ምነው በቀመሰው፤
በቀን በቀን ነበር፤
ሸንኮራ አምጡ እያለ የሚመላለሰው።
ገብቻለሁ ጭፍራ ከአርባዎቹ ዋርካ፤
ወትሮም የጁ ጋር ነው፤
ሃጃው የሚሰምረው፤ የዳንዮች ዱኣ የጭፍራ በረካ።
((( ጃ ኖ))💚💛❤️
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@Nagayta
ሃውሳ ዝናብ አይጥል፤
አዋሽ የሰጠውን ፤ ያበቅላል በመስኖ፤
ገምሻራየዋየ፤
ታየኝ ሰውነቷ ጃምዮ እሸት መስሎ።
ኣሳ ባራ ጊቴ፤አቶብስ የሚቴ፤
ሚሌ ወዲህ ሃራ፤ ባቲም ጎረቤቴ፤
የአፋር ልጅ ስትዘልቅ፤
ደርሶ ይታከማል፤ የሰራ አካላቴ።
አፋር በረሃ ነው ይለኛል ሞኝ ሰው፤
የአዋሽ ዳርን ሸንኮር ምነው በቀመሰው፤
በቀን በቀን ነበር፤
ሸንኮራ አምጡ እያለ የሚመላለሰው።
ገብቻለሁ ጭፍራ ከአርባዎቹ ዋርካ፤
ወትሮም የጁ ጋር ነው፤
ሃጃው የሚሰምረው፤ የዳንዮች ዱኣ የጭፍራ በረካ።
((( ጃ ኖ))💚💛❤️
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@Nagayta
ለውብ ቀን!
💚
በመማገጫው!!!
ቆለኛው ዘመዴ ከገጠር ወደ ከተማ መጥቶ ሳለ ካፍቴሪያ ይዠው ገባሁ። ባልንጀሮቼም
አብረውኝ ነበሩ። ከአጎቴ ውጭ ሁላችን ጭማቂ አዘዝን። ባልንጀሮቼ በእስትሮው /
በመምጠጫ / ጭማቂያቸውን ሲመጥጡ አያቸው።ባልንጀሮቼ በመምጠጫው እየማጉ
ሳለ አጎቴ እንዲህ ያለም የለ እያለ ተገርሞ አያቸው። እኔ ያለ እስትሮው እንዲሁ
እየጠጣሁ መሆኔን አየና አጎቴ እንዲህ አለኝ። እንደባልንጀሮችህ በመማገጫው
የማትምገው ምን ሁነህ ነው?? ብሎ አስቆኛል። እነሆ ትላንት ካፍቴሪያ ውስጥ አንዷ
ጭማቂዋን በእስትሮው ስትምግ ትርክርክ ስትል ባያት ጊዜ እውነትም የመማገጫው ወግ
ትዝ አለኝ።ይኸው ነው!!!
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@Nagayta
💚
በመማገጫው!!!
ቆለኛው ዘመዴ ከገጠር ወደ ከተማ መጥቶ ሳለ ካፍቴሪያ ይዠው ገባሁ። ባልንጀሮቼም
አብረውኝ ነበሩ። ከአጎቴ ውጭ ሁላችን ጭማቂ አዘዝን። ባልንጀሮቼ በእስትሮው /
በመምጠጫ / ጭማቂያቸውን ሲመጥጡ አያቸው።ባልንጀሮቼ በመምጠጫው እየማጉ
ሳለ አጎቴ እንዲህ ያለም የለ እያለ ተገርሞ አያቸው። እኔ ያለ እስትሮው እንዲሁ
እየጠጣሁ መሆኔን አየና አጎቴ እንዲህ አለኝ። እንደባልንጀሮችህ በመማገጫው
የማትምገው ምን ሁነህ ነው?? ብሎ አስቆኛል። እነሆ ትላንት ካፍቴሪያ ውስጥ አንዷ
ጭማቂዋን በእስትሮው ስትምግ ትርክርክ ስትል ባያት ጊዜ እውነትም የመማገጫው ወግ
ትዝ አለኝ።ይኸው ነው!!!
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@Nagayta
Forwarded from Jv
ሰላም!
😔 በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት ትምርህርት ቤት ወይም ስራ ሲሄዱ ረፍዶቦት ያውቃል
😔 በአፋጣኝ ሰነድዎ ከቢሮ &ከቤትዎ ወይንም ከሌላቦታ ወዳሉበት ቦታ እንድመጣልዎት ፈልገዉስ ያውቃሉ
😔 ወደ ምግብ ቤት ሄደው ምሳዎትን ለመብላት ግዜ አተውስ
አያስቡ፡፡ መፍትሄዉ እኛ ጋር አለ፡፡ @Tolo_Delivery_Bot የቴሌግራም ቦትን በመጠቀም የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ
👉ካሉበት ቦታ ወደሚፈልጉበት ቦታ ሞተረኛ እንዲያደርስዎት ማዘዝ
👉 ወዳሉበት ቦታ ምግብ እንዲመጣልዎት ማዘዝ
👉 ሰንዶችንና ሌሎች እቃዎችን ወዳሉበት ቦታ እንዲመጣልዎት ማዘዝ ይችላሉ፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ቶሎዴሊቨሪ ላይ ማዘዝ ይችላሉ፡፡
😔 በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት ትምርህርት ቤት ወይም ስራ ሲሄዱ ረፍዶቦት ያውቃል
😔 በአፋጣኝ ሰነድዎ ከቢሮ &ከቤትዎ ወይንም ከሌላቦታ ወዳሉበት ቦታ እንድመጣልዎት ፈልገዉስ ያውቃሉ
😔 ወደ ምግብ ቤት ሄደው ምሳዎትን ለመብላት ግዜ አተውስ
አያስቡ፡፡ መፍትሄዉ እኛ ጋር አለ፡፡ @Tolo_Delivery_Bot የቴሌግራም ቦትን በመጠቀም የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ
👉ካሉበት ቦታ ወደሚፈልጉበት ቦታ ሞተረኛ እንዲያደርስዎት ማዘዝ
👉 ወዳሉበት ቦታ ምግብ እንዲመጣልዎት ማዘዝ
👉 ሰንዶችንና ሌሎች እቃዎችን ወዳሉበት ቦታ እንዲመጣልዎት ማዘዝ ይችላሉ፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ቶሎዴሊቨሪ ላይ ማዘዝ ይችላሉ፡፡
ለጁምኣ መንደርደሪያ ጀባታ!
💚
#ውድ_እቃ_ያለቦታው_ርካሽ_ነው !!!!!
አንድ አባት ከሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ልጁን እንዲህ ሲል ተናገረው "ይህ የእጅ ሰዓት አባቴ
የሰጠኝ ነው፤ 200 ዓመታት ሆኖታል። ነገር ግን ላንተ በውርስ ከመስጠቴ በፊት ሂድ እና
ሰዓት ቤቶች ስንት ሊገዙህ እንደሚችሉ ጠይቀህ ና።" አለው።ልጁም ጠይቆ መጣ እና
"አሮጌ ስለሆነ 5 ብር እንገዛሃለን" እንዳሉት ነገረው።
አባቱም ድጋሚ ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቆች ጋር ሄዶ እንዲጠይቅ ይነግረዋል። ልጁም
ጠይቆ ይመጣ እና አሁንም ከ5 ብር በላይ እንደማይገዙት ይነግረዋል።
"ሙዚየም ሄደህ ጠይቅ" ይለዋል አባቱ። ልጁም ጠይቆ ከመጣ በኋላ "አንድ ሚሊዮን ብር
እንደሚገዙኝ ነገሩኝ" አለ።
አባቱም "እንድታውቅ የፈለኩት የአንተንም ትክክለኛ ዋጋ (ቦታ) የሚሰጥህ ትክክለኛ ቦታ
ላይ እንድትገኝ እንጂ የተሳሳተ ቦታ ላይ ሄደህ ሳይሳካልህ ሲቀር እንዳትናደድ ነው።
ምንጊዜም ያንተን ዋጋ የሚያውቁ ብቻ ናቸው ክብርም አድናቆትም የሚሰጡህ ስለዚህ
የተሳሳተ ቦታ ላይ አትገኝ!! (ምንጭ ጉዱ ካሳ ገፅ)
ታዲያ ይህንን የህይወት ሃቂቃ ወሎየ አባቶች በወዘናም ስንኞቻቸው እንደዚህ ገልጠውት
ቆየ።
ጊምባ ላይ አንበሳ፤
አላንሻ ላይ ዝሆን፤ የተገኘ እንደሆን፤
ይላሉ ይህ "አውሬ" ምን ይሆን ምን ይሆን፤
ያላቀማመጡ ያለቦታው ሲሆን።
ይኸው ነው!!!
ሸጋ ምሽት ይሁንላቹ!💚
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@Nagayta
💚
#ውድ_እቃ_ያለቦታው_ርካሽ_ነው !!!!!
አንድ አባት ከሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ልጁን እንዲህ ሲል ተናገረው "ይህ የእጅ ሰዓት አባቴ
የሰጠኝ ነው፤ 200 ዓመታት ሆኖታል። ነገር ግን ላንተ በውርስ ከመስጠቴ በፊት ሂድ እና
ሰዓት ቤቶች ስንት ሊገዙህ እንደሚችሉ ጠይቀህ ና።" አለው።ልጁም ጠይቆ መጣ እና
"አሮጌ ስለሆነ 5 ብር እንገዛሃለን" እንዳሉት ነገረው።
አባቱም ድጋሚ ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቆች ጋር ሄዶ እንዲጠይቅ ይነግረዋል። ልጁም
ጠይቆ ይመጣ እና አሁንም ከ5 ብር በላይ እንደማይገዙት ይነግረዋል።
"ሙዚየም ሄደህ ጠይቅ" ይለዋል አባቱ። ልጁም ጠይቆ ከመጣ በኋላ "አንድ ሚሊዮን ብር
እንደሚገዙኝ ነገሩኝ" አለ።
አባቱም "እንድታውቅ የፈለኩት የአንተንም ትክክለኛ ዋጋ (ቦታ) የሚሰጥህ ትክክለኛ ቦታ
ላይ እንድትገኝ እንጂ የተሳሳተ ቦታ ላይ ሄደህ ሳይሳካልህ ሲቀር እንዳትናደድ ነው።
ምንጊዜም ያንተን ዋጋ የሚያውቁ ብቻ ናቸው ክብርም አድናቆትም የሚሰጡህ ስለዚህ
የተሳሳተ ቦታ ላይ አትገኝ!! (ምንጭ ጉዱ ካሳ ገፅ)
ታዲያ ይህንን የህይወት ሃቂቃ ወሎየ አባቶች በወዘናም ስንኞቻቸው እንደዚህ ገልጠውት
ቆየ።
ጊምባ ላይ አንበሳ፤
አላንሻ ላይ ዝሆን፤ የተገኘ እንደሆን፤
ይላሉ ይህ "አውሬ" ምን ይሆን ምን ይሆን፤
ያላቀማመጡ ያለቦታው ሲሆን።
ይኸው ነው!!!
ሸጋ ምሽት ይሁንላቹ!💚
"ናካይታ"💚
@getem
@getem
@Nagayta
ኸሚስና ወሎ!!!!!
ሃሙስን ያህል ቀን፤
ዱኣን ያህል ጥይት፤
ሰማዩ ባይጀባው እሱም ባይቀበል አሚን ይሁን ብሎ።
እንደጊዜው ክፋት ፤
እንደ ቀኑ መጉደል ጅብ ይበላው ነበር ገራገሩ ወሎ።
በከሚስ ጨረቃ በወሎ ሰማይ፤
ዳና ከጀማው ስር፤
ጫሌ ወረባቦ ፤ ከዛውያው ላይ፤
በወሊዮች ከንፈር፤
ይሁንልህ ሲባል፤ ሃጃችን ሲወጣ ሲፈጠም ጉዳይ፤
ሲያፈጣጥሙልህ፤
እንካ ውሰድ ሲሉህ፤አሚን ይሁን ማለት ይገድሃል ወይ???
እኔም እንደ አመሌ፤
በከሚሱ ዱኣ ጡሃራ እጄን ይዤ ላጥብቅ መቀነቴን፤
ይሁንልህ ሲሉኝ፤
አዎን ይሁንልኝ ይሁን እያልኩ ነው፤ያጠናሁ ጉልበቴን፤
በሂስደኞች መሃል፤እንደ አላማ ሰንደቅ ፤ ያቀናሁ አንገቴን፤
እኔ የዱኣ ልጅ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
ይሁን እያልኩ ነው፤
አሚን እያልኩ ነው በየጎራው ሁሉ የዳስኩት ጠላቴን።
(( ጃ ኖ )💚💛❤
@getem
@getem
@Nagayta
ሃሙስን ያህል ቀን፤
ዱኣን ያህል ጥይት፤
ሰማዩ ባይጀባው እሱም ባይቀበል አሚን ይሁን ብሎ።
እንደጊዜው ክፋት ፤
እንደ ቀኑ መጉደል ጅብ ይበላው ነበር ገራገሩ ወሎ።
በከሚስ ጨረቃ በወሎ ሰማይ፤
ዳና ከጀማው ስር፤
ጫሌ ወረባቦ ፤ ከዛውያው ላይ፤
በወሊዮች ከንፈር፤
ይሁንልህ ሲባል፤ ሃጃችን ሲወጣ ሲፈጠም ጉዳይ፤
ሲያፈጣጥሙልህ፤
እንካ ውሰድ ሲሉህ፤አሚን ይሁን ማለት ይገድሃል ወይ???
እኔም እንደ አመሌ፤
በከሚሱ ዱኣ ጡሃራ እጄን ይዤ ላጥብቅ መቀነቴን፤
ይሁንልህ ሲሉኝ፤
አዎን ይሁንልኝ ይሁን እያልኩ ነው፤ያጠናሁ ጉልበቴን፤
በሂስደኞች መሃል፤እንደ አላማ ሰንደቅ ፤ ያቀናሁ አንገቴን፤
እኔ የዱኣ ልጅ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
ይሁን እያልኩ ነው፤
አሚን እያልኩ ነው በየጎራው ሁሉ የዳስኩት ጠላቴን።
(( ጃ ኖ )💚💛❤
@getem
@getem
@Nagayta
❤1👍1
ከሔድኩ አልመጣም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
"አትግፋኝ!"ብዬህ ነበር መዘዙን ፈርቼ፤
"አትንኪው!" ብያለሁ ቁስሌን አሳይቼ፤
"ጠግበው እንደናቁት እንደጣሉት እህል
እስከ ጥግ አይችሉም ሰዎች የኔን ያህል!"
ታግሼ. . .
አብሼ. . .
ስከፋ. .
በይሆናል ተስፋ. . .
ባልፍም በጥሞና ቃላት ባላወጣም፣
ሳይገፉኝ አልሔድም
ከሔድኩም አልመጣም!
ተንቄ. . .
ወድቄ. . .
ደቅቄ. . .
ሳልጀምር አልቄ. . .
ፈርጄ እሔዳለሁ፣ኅዘን ሳጠራቅም፤
በመሸሼ ብቻ፣ብሶቴ ባያልቅም. . .
ከጀመርኩት መንገድ፣ተመልሼ አላውቅም!
.
@huluezih
@getem
@getem
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
"አትግፋኝ!"ብዬህ ነበር መዘዙን ፈርቼ፤
"አትንኪው!" ብያለሁ ቁስሌን አሳይቼ፤
"ጠግበው እንደናቁት እንደጣሉት እህል
እስከ ጥግ አይችሉም ሰዎች የኔን ያህል!"
ታግሼ. . .
አብሼ. . .
ስከፋ. .
በይሆናል ተስፋ. . .
ባልፍም በጥሞና ቃላት ባላወጣም፣
ሳይገፉኝ አልሔድም
ከሔድኩም አልመጣም!
ተንቄ. . .
ወድቄ. . .
ደቅቄ. . .
ሳልጀምር አልቄ. . .
ፈርጄ እሔዳለሁ፣ኅዘን ሳጠራቅም፤
በመሸሼ ብቻ፣ብሶቴ ባያልቅም. . .
ከጀመርኩት መንገድ፣ተመልሼ አላውቅም!
.
@huluezih
@getem
@getem
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው!
( Bewketu Seyoum )
-
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው!
መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው!
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብስል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል!
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው...!
@getem
@getem
@paappii
( Bewketu Seyoum )
-
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትጸንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው!
መጣ መጣ መጣ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው!
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደብስል ሾላ ፍሬ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
እንኳን የእግርሽ ኮቴ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል!
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው...!
@getem
@getem
@paappii
የባሌ ሠፈር ሠዎች
የባሌ ሠፈር ሠዎች በጣምነው ሚገርሙት
እየመረጡ ነው ሠው ሠላም የሚሉት
ለስራ ስንወጣ ጠዋት ተያይዘን
ደናደርሽ ይሉኛል ገላምጠውት እሱን
እግዜርን አይፈሩ ቤተስኪያን ሲያገኙት
የፀበል ወረፋ አውቀው ሲያሥቀድሙት
ከስራ ሥንገባም በመዝናኛ ሲያዩት
ጥርቅም ያደርጉታል ግንባር እየነሱት
ወጣቶቹስ ይሁን የአዛውንቱ ለጉድ
ለንፍሮ ዘለሉት ሀዘናቸው ቢሔድ
በገባ በወጣ ምላሹ ሲያስጠላኝ
ቀድሞ ማንነቱን እያፈርኩ ጠየኩኝ
፡
ወንድም ለእህቱ ወላጅ ለልጃቸው
ሲጠብቁት ኖረው ጉድ ስላረኳቸው
ይኸው ዛሬድረስ ባሌን ጠልተውብኝ
ለእድር ብለውነው እኔንም ሚያወሩኝ።🤣
😜😜😜✍ ቅድስት
6/10/10, 2:20 a.m
@getem
@getem
የባሌ ሠፈር ሠዎች በጣምነው ሚገርሙት
እየመረጡ ነው ሠው ሠላም የሚሉት
ለስራ ስንወጣ ጠዋት ተያይዘን
ደናደርሽ ይሉኛል ገላምጠውት እሱን
እግዜርን አይፈሩ ቤተስኪያን ሲያገኙት
የፀበል ወረፋ አውቀው ሲያሥቀድሙት
ከስራ ሥንገባም በመዝናኛ ሲያዩት
ጥርቅም ያደርጉታል ግንባር እየነሱት
ወጣቶቹስ ይሁን የአዛውንቱ ለጉድ
ለንፍሮ ዘለሉት ሀዘናቸው ቢሔድ
በገባ በወጣ ምላሹ ሲያስጠላኝ
ቀድሞ ማንነቱን እያፈርኩ ጠየኩኝ
፡
ወንድም ለእህቱ ወላጅ ለልጃቸው
ሲጠብቁት ኖረው ጉድ ስላረኳቸው
ይኸው ዛሬድረስ ባሌን ጠልተውብኝ
ለእድር ብለውነው እኔንም ሚያወሩኝ።🤣
😜😜😜✍ ቅድስት
6/10/10, 2:20 a.m
@getem
@getem
(የባከነ ሌሊት ከሚለው በእውቀቱ ስዩም ግጥም የተወሰደ)
የባከነ ቀን
ወይ ፍቅረኛ አልቀጠርሁ
ወይ ላገኛት አልጠበቅሁ
ወይ ወክ አላደረግሁ
ወይ ትከሻ አልተደገፍሁ
የጉንጮቿን መሃል ቀርቤ አልተዳፈርሁ
ወይ አራት ኪሎ ቆሜ
ሲቪ ተሸክሜ
ቀጣሪ አልፈለግሁ
እግር ኳስ ለማየት የሊጉን ጨዋታ
ከኢትዮጵያ ቡና ከሰባ እንደርታ
ማን ይሆን ሚረታ?
በማለት ቋምጬ
ገንዘቤን አፍርጬ
ስታዲየም ገብቼ
ከደጋፊዎች ጋራ 'ሰልፊ' ተነስቼ
የማይረባ እግር ኳስ በማየት ሰልችቼ
ከመውጣቴ በፊት ከስታዲየሙ ሥፍራ
የሚገላመጥን ፌዴራል ሳልፈራ
ወይ 'ፑሽ አፕ' አልሰራሁ
ወንበር አልገነጠልሁ
ድንጋይ አልወረወርሁ
ወይ ዳኛ አላባረርሁ
ወይ ሞተር ላይ አርፌ
ሲበር በርሬ ሲከንፍ ከንፌ
የዕድለ-ሰበራ ቦርሳዋን መንትፌ
ያስቸገረውን ደሞ አንገቱን ቆልፌ
ወይ ፖሊስ አልያዘኝ
ተኩሶ አልጣለኝ
ጥሎ አልገደለኝ
ታሪክን አጥምሜ ፥ ፌስቡክ ላይ ሳልለጥፍ
ሰውን ሳላባላ ፥ ሕይወት ሳላስቀጥፍ
መንግሥትን ለማውገዝ ፥ መስቀል አደባባይ
ጉንዳን የሚመስል፥ ከርቀት የሚታይ
ከሕዝብ መንጋ፥ መሃል ተሰልፌ
እጃቸውን ሲያነሱ፥ አንድ እጄን አንስቼ
ደሞ ሲያሳርፉ፥ እኔም አሳርፌ
ያልገባኝንን ነገር፥ አብሬ ለፍፌ
እንዳበጀ በለው ጥያቄያቸው ስቦኝ፥
መሆኑ ይቀርና፥ በደሉ ሳይገባኝ
ጉሮሮዬን ስዬ
ባነር አንጠልጥዬ
ምራቄን መሬት ጥዬ
ኮከብ የሌለውን፥ ባንዲራ ለብሼ
መፈክር ጎርሼ
ወንጭፍ ወንጭፍ ባነር
ረገጥ ረገጥ ምድር
በማድረግ ለፍቼ
መንግሥትን ነቅፌ፥ 'ጠሚውን' ተችቼ
አስለቃሽ ጭስ ቦንቡን፥ በዓይኔ ጠጥቼ
ከፌዴራል ዱላ፥ ተርፌ አምልጬ
ኮብል ስቶን ይዤ፥ ፖሊስ ላይ ወርውሬ
መኪና አቃጥዬ፥ መስተዋት ሰብሬ
Down Down ሳልል፥ ድል ሳላስመዘግብ
ወይ ታሪክ ሳላጠም፥ ወይ ታሪክ ሳልገርብ
አለምንም ጣጣ አለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ
@getem
@getem
#jeko
የባከነ ቀን
ወይ ፍቅረኛ አልቀጠርሁ
ወይ ላገኛት አልጠበቅሁ
ወይ ወክ አላደረግሁ
ወይ ትከሻ አልተደገፍሁ
የጉንጮቿን መሃል ቀርቤ አልተዳፈርሁ
ወይ አራት ኪሎ ቆሜ
ሲቪ ተሸክሜ
ቀጣሪ አልፈለግሁ
እግር ኳስ ለማየት የሊጉን ጨዋታ
ከኢትዮጵያ ቡና ከሰባ እንደርታ
ማን ይሆን ሚረታ?
በማለት ቋምጬ
ገንዘቤን አፍርጬ
ስታዲየም ገብቼ
ከደጋፊዎች ጋራ 'ሰልፊ' ተነስቼ
የማይረባ እግር ኳስ በማየት ሰልችቼ
ከመውጣቴ በፊት ከስታዲየሙ ሥፍራ
የሚገላመጥን ፌዴራል ሳልፈራ
ወይ 'ፑሽ አፕ' አልሰራሁ
ወንበር አልገነጠልሁ
ድንጋይ አልወረወርሁ
ወይ ዳኛ አላባረርሁ
ወይ ሞተር ላይ አርፌ
ሲበር በርሬ ሲከንፍ ከንፌ
የዕድለ-ሰበራ ቦርሳዋን መንትፌ
ያስቸገረውን ደሞ አንገቱን ቆልፌ
ወይ ፖሊስ አልያዘኝ
ተኩሶ አልጣለኝ
ጥሎ አልገደለኝ
ታሪክን አጥምሜ ፥ ፌስቡክ ላይ ሳልለጥፍ
ሰውን ሳላባላ ፥ ሕይወት ሳላስቀጥፍ
መንግሥትን ለማውገዝ ፥ መስቀል አደባባይ
ጉንዳን የሚመስል፥ ከርቀት የሚታይ
ከሕዝብ መንጋ፥ መሃል ተሰልፌ
እጃቸውን ሲያነሱ፥ አንድ እጄን አንስቼ
ደሞ ሲያሳርፉ፥ እኔም አሳርፌ
ያልገባኝንን ነገር፥ አብሬ ለፍፌ
እንዳበጀ በለው ጥያቄያቸው ስቦኝ፥
መሆኑ ይቀርና፥ በደሉ ሳይገባኝ
ጉሮሮዬን ስዬ
ባነር አንጠልጥዬ
ምራቄን መሬት ጥዬ
ኮከብ የሌለውን፥ ባንዲራ ለብሼ
መፈክር ጎርሼ
ወንጭፍ ወንጭፍ ባነር
ረገጥ ረገጥ ምድር
በማድረግ ለፍቼ
መንግሥትን ነቅፌ፥ 'ጠሚውን' ተችቼ
አስለቃሽ ጭስ ቦንቡን፥ በዓይኔ ጠጥቼ
ከፌዴራል ዱላ፥ ተርፌ አምልጬ
ኮብል ስቶን ይዤ፥ ፖሊስ ላይ ወርውሬ
መኪና አቃጥዬ፥ መስተዋት ሰብሬ
Down Down ሳልል፥ ድል ሳላስመዘግብ
ወይ ታሪክ ሳላጠም፥ ወይ ታሪክ ሳልገርብ
አለምንም ጣጣ አለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ
@getem
@getem
#jeko
👍1
የልብ ቅርፅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ፍቅርን ያህል ነገር...
ተሸክሜ ስኖር ፣ በልቤ ትከሻ
"ቃል አጠረኝ" የሚል....
ቃል ካ'ፌ አይወጣም ፣ ላወድስሽ ስሻ።
........................................................
እንደውም ሳፈቅርሽ ፣ ቃል ነው የተረፈኝ
ሁሉ ያጥርብኛል.....
በልብሽ ቅርፅ ውስጥ ፣ መውደድሽ ሲያገዝፈኝ።
...............................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ሰፊ ያልሁት አለም ፣ ባንድ እርምጃ አለቀ
ሳልሄደው ሚደክመኝ...
ተራራና ጋራው ፣ ከግሬ ስር ጠለቀ።
"ሩቅ" ያልሁት ሰማይ..
ሩቅ የሚመስለኝ ፣ ነካሁት በስንዝር
ጨረቃና ፀሀይ....
ከኮከብ ያንሳሉ ፣ ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር።
.......................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ንጉስን ከዙፋን ፣ ማርከው የሚያወርዱ
የሀያላንን አቅም ፣ በጥቅሻ ሚያርዱ
ቆነጃጅት ሴቶች ...
"ቃል አጠረኝ" በሚል ቃላት የተሞሉ
ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር..
ቃል ተገኝቶላቸው ፣ "ፋንጋዎች" ተባሉ።
.........................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
"ቃል አጠረኝ "በሚል...
ባፍቃሪ አንደበት ፣ ቃል ተትረፈረፈ
ሁሉን አሳንሶ...
በልቡ ቅርፅ ውስጥ ፣ ፍቅሩን አገዘፈ
አለሙን ሰርዞ ፣ ፍቅሩን ብቻ ፃፈ!!!
..........................................
ሳፈቅርሽ ይህን አልሁ...
ፍቅርን ተሸክሞ ፣ የሚኖር ልቦና
ሁሉም ከፍቅርሽ ስር ፣ መሆኑን አውቅና
አንቺን ለማወደስ .፣..እኔም ቃል ያጥረኛል
"ቃል አጠረኝ "ማለት...
ቃል እንደሆነ ግን ፣
ፍቅርሽ ይነግረኛል!!!
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ፍቅርን ያህል ነገር...
ተሸክሜ ስኖር ፣ በልቤ ትከሻ
"ቃል አጠረኝ" የሚል....
ቃል ካ'ፌ አይወጣም ፣ ላወድስሽ ስሻ።
........................................................
እንደውም ሳፈቅርሽ ፣ ቃል ነው የተረፈኝ
ሁሉ ያጥርብኛል.....
በልብሽ ቅርፅ ውስጥ ፣ መውደድሽ ሲያገዝፈኝ።
...............................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ሰፊ ያልሁት አለም ፣ ባንድ እርምጃ አለቀ
ሳልሄደው ሚደክመኝ...
ተራራና ጋራው ፣ ከግሬ ስር ጠለቀ።
"ሩቅ" ያልሁት ሰማይ..
ሩቅ የሚመስለኝ ፣ ነካሁት በስንዝር
ጨረቃና ፀሀይ....
ከኮከብ ያንሳሉ ፣ ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር።
.......................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ንጉስን ከዙፋን ፣ ማርከው የሚያወርዱ
የሀያላንን አቅም ፣ በጥቅሻ ሚያርዱ
ቆነጃጅት ሴቶች ...
"ቃል አጠረኝ" በሚል ቃላት የተሞሉ
ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር..
ቃል ተገኝቶላቸው ፣ "ፋንጋዎች" ተባሉ።
.........................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
"ቃል አጠረኝ "በሚል...
ባፍቃሪ አንደበት ፣ ቃል ተትረፈረፈ
ሁሉን አሳንሶ...
በልቡ ቅርፅ ውስጥ ፣ ፍቅሩን አገዘፈ
አለሙን ሰርዞ ፣ ፍቅሩን ብቻ ፃፈ!!!
..........................................
ሳፈቅርሽ ይህን አልሁ...
ፍቅርን ተሸክሞ ፣ የሚኖር ልቦና
ሁሉም ከፍቅርሽ ስር ፣ መሆኑን አውቅና
አንቺን ለማወደስ .፣..እኔም ቃል ያጥረኛል
"ቃል አጠረኝ "ማለት...
ቃል እንደሆነ ግን ፣
ፍቅርሽ ይነግረኛል!!!
@getem
@getem
አውቃለሁ አታውቂም
ስላለፈው ዘመን
መርሳት የተሳነው መከረኛ ልቤን
ባንቺነትሽ ጥጋት
ሴት እየመዘነ የከሰረው ቀልቤን
፡
ያለመሆን ህመም
በመሆንሽ ላይድን ሰርክ እንደባዘነ
በአመታት ስሌት
ከስቃዩ ሳይሽር መንፈሴ እንዳዘነ
፡
አውቃለሁ አታውቂም
አለማወቅ ጠቅሞሽ ላየወጠቅመኝ ማወቄን
ሳታውቂ ባወኩት
የመታመን ብሶት እኔ መሳቀቄን፡፡
፡
ግን እንዴት ላገግም
የህመሜ ምክንያት ሆኖ መዳኒቱ
ስቃዩ በዛብኝ
ልችለው አልቻልኩም ግራ ገባኝ እቱ፡፡
፡
ለዛ ነው ሁል ጊዜ
የጀመርኩት መንገድ ደርሶ ላያደርሰኝ
በዛሬው ዓለሜ
ነገን ብናፍቅም አምና እየታወሰኝ
መኖር የታከተ
ሰቀቀናም ልቤ መሞቻውን ናፍቆ
አመታት ያለፉት
በመኖር እሳቤ ከመሞት እርቆ፡፡
(ታሮስ አለሙ)
@getem
@getem
@getem
ስላለፈው ዘመን
መርሳት የተሳነው መከረኛ ልቤን
ባንቺነትሽ ጥጋት
ሴት እየመዘነ የከሰረው ቀልቤን
፡
ያለመሆን ህመም
በመሆንሽ ላይድን ሰርክ እንደባዘነ
በአመታት ስሌት
ከስቃዩ ሳይሽር መንፈሴ እንዳዘነ
፡
አውቃለሁ አታውቂም
አለማወቅ ጠቅሞሽ ላየወጠቅመኝ ማወቄን
ሳታውቂ ባወኩት
የመታመን ብሶት እኔ መሳቀቄን፡፡
፡
ግን እንዴት ላገግም
የህመሜ ምክንያት ሆኖ መዳኒቱ
ስቃዩ በዛብኝ
ልችለው አልቻልኩም ግራ ገባኝ እቱ፡፡
፡
ለዛ ነው ሁል ጊዜ
የጀመርኩት መንገድ ደርሶ ላያደርሰኝ
በዛሬው ዓለሜ
ነገን ብናፍቅም አምና እየታወሰኝ
መኖር የታከተ
ሰቀቀናም ልቤ መሞቻውን ናፍቆ
አመታት ያለፉት
በመኖር እሳቤ ከመሞት እርቆ፡፡
(ታሮስ አለሙ)
@getem
@getem
@getem
#ተ_ረ_ት___#ተ_ረ_ት
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።
ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።
ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
© ✍ በሜሮን_ጌትነት
@getem
@getem
#jeko
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።
ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።
ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
© ✍ በሜሮን_ጌትነት
@getem
@getem
#jeko