ግጥም ብቻ 📘
67.1K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
175 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
የምድር ስንክሳር
ሰረክ እያቃተተኝ ኑሮዬ ባይወዛም
ባ'መዳም ህይወቴ
እስቃለሁ እንጂ ማልቀስ አላበዛም፡፡

ስለዚህ አንዳንዴ
ጥላኝ ሄደች ብዬ ብዘበራርቅም
ይኸው ፈገግታዬ
ድሮም በራሴ እንጂ ባንቺ ጥርስ አልስቅም፡፡
😁

(ታሮስ አለሙ)

@getem
@getem
@getem
🤩1
#ያልተግባቡ~ልቦች

ወደ ቤታችን በሙሉ አቋማችን ስንመለስ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ዓለም ሰበዞች
በኑሮ ጣቶችሽ ህይወትን ሲገምዱ
ያ'መክንዮሽ ሚዛን
ባሰፈረው ልኬት የህሊናሽ ፍርዱ
ለባለቀን እንጂ
ለግዜ ምርኮኛ ውሳኔሽ አይራራም
ከምክንያት በቀር
እውነት ይሉት ፈሊጥ በፍርድሽ አይሰራም፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
ግዜ ጥሎኝ ሳለ በይሆናል ተስፋ ያልሽኝን ረስቼ
ከባለቀን ጋራ
ሰርክ እሟገታለሁ
እውነትን ፍለጋ ምክንያትን ትቼ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ክታብ ገፆች
የኑሮን ሆ-ህ-ያት ገልጠው ሊያስነብቡ
በማራኪ ቀለም
የልብሽ ድርሳን ላይ ሀሳብ ሲከትቡ
በገድላት ቋንቋ
ያ'ለም ጀብደኞችን ፅፈው ሲያስቀምጡ
ነግረሺኝ ነበረ
ለኔ አይነት ምናቦች ቃል እንደማይሰጡ፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
ቀን መሽቶ ሲነጋ ያልሽን ረሳለሁ
መፃ'ፍሽ ገፆች ላይ
እኔን መሳይ ምናብ ይኸው ፈልጋለሁ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ሰማይ ዳምኖ
ዶፍ እያወረደ በመብረቅ ሲታጀብ
ልብን ሊያበሰብስ
መንፈስ እያራደ ከሚፈጥረው ወጀብ
የሞቀውን ገላ
የቤትሽ ወጋግራ ታዛሽ ቢያስጠልልም
ካጥሩ ይዘጋል
የኔ አይነቱን እርቃን ከዶፍ አያስጥልም፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
ሰማዩ ሲያነባ ህግጋቱን ሽሬ ወዳ'ንቺ ሮጣለሁ
እራቁት ገላዬን
ከተዘጋው ቤትሽ ላስጠልል መጣለሁ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ጓዳ ማጀት
ከተ'ትረፈረፈው ከሞላው መዐዱ
በመለገስ ጥበብ
መሶብሽ ተከፍቶ የመስጠት ልማዱ
በበረከት ሰቀል
የገበታሽ እምነት ሰው እየመዘነ
ነግረሺኝ ነበረ
ለጠገበው እንጂ
ለተራበ አንጀት ንፉግ እንደሆነ፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
በራብተኛ ክብሬ ተመፅዋቹን ሳለሁ
ከጠገቡት እኩል
በታጠፈ አንጀቴ ከ'ማድሽ ቀርባለሁ፡፡

እንዳይገርምሽ ውዴ
በቃ እኔ እንዲህ ነኝ
ያልሽኝን ምረሳ የሰሚ ደንቆሮ
አንቺ ደግሞ እንደዛ
አፍሽ የማይደክመው ህግሽን ተናግሮ

ግና ምንም እንኳን
ምክንያትሽ ከ'ምነቴ በግብር ተጣርሶ
ያልሽውን የረሳ
በካኝ እኔነቴ
ባንቺ ዓለም ምናቦች ቢኖርም እረክሶ
:
ከክርስቶስ ገደል
ከመስቀሉ ማዶ በቋጠርኩት ተስፋ
ስለፍቅር ብዬ
በ'ውነቴ ል'ሸነፍ በምክንያት ልገፋ
ድሮም እንደዚህ ናት
ባንቺ አይነት ምክንያቶች ዓለም፡፡

(ልብ አልባው)

@getem
@getem
#የልቤ....#እምነት_ክደት_ቃል
፨፨፨፨
፨፨፨
፨፨
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)

የልክ ሚዛኔ ፥ ላንቺ ተሰበረ
ሰው ሲመዝን ኖሮ
በገለባ አለም ፥ ወርቅ አንቺን ሰፈረ
እቱ ለግላጋዋ !!
እንዶድ ፍቅርሽ ደርሶት
ቅምሻን የታደለ ፥ ካዘኔታሽ ጥዋ
እንኳን እኔ ቀርቶ
መውደድ ያልሸተተው
ለበቀል መሀላ ፥ እራሱን የሰዋ
ሳጥናኤል ይገራል
ሰውነት ሰው ሲሆን
ካንቺ መዲያ ላሳር ፥ ሰው ማለም ይከብዳል ።
#አየሽ
ልኬት ለሰበረ ፥ የፍቅር ናሙና
ቃል እየቀረፁ ፥ መቀኞ ቢወርዱ
ምላስ ያነክሳል
አልማዝ ባየ ግዜ
ኮምቼ ሲቆልል ፥ ለከረመ ልምዱ
ጨለማ ተዘግቶ ፥ አዘቅት የከረመ
ብርሀን ቢግቱት ፥ አይኑ እንደታመመ
#ያ' ሰውዬሽ....................... ነኝ እኔ
በወገግታው ዳፍንት ፥ ያጣሁሽ ከጎኔ ።
ቀሽም ቃላቶቼ ፥ ቃልኪዳን አድሰው
ለሰበርኩት ልብሽ ፥ ካሳ ባይሆንሽም
በመምጣትሽ ስካር ፥ ደስታን ባላሟሽም
ያዘገየሽ ግዜ ፥ ቀድሞ ቢወስድሽም
ከኔ ለፈቀቀ ፥ ያንቺ ልዕልና
ጎረበጠኝ ብዬ ፥ አንቺን አልወቅስሽም
አንዳንዴ ባይገርምሽ
ፅጌሬዳ አበባ ፥ ውበቷ ሳያንሳት
ሳይነኳት የሚደርስ
ያንን ሁሉ እሾህ ፥ ለጉድ ያሸከምካት
በለስ....ሺ ምንተሺ
እሾህ ቆዳ ስፌት ፥ ጣሟን ያለበስካት
ም'ነው .... አልክ እግዜሩ ?
እላለው
ለሰውነት ህመም
መድህኒት የምትሆን ፥ እንዲት እግሯ ልጅህ
ሰርክ ጠዋት ማታ ፥ ሳትለይ ከደጅህ
በቁም ከሞቱ ጎን ፥ በመስክ አውለሀት
እንዳረጀ ቀብር ፥ በሙታን ወረዳ ፥ ሳማ የከበባት
ምንኛ....ብትወዳት ?
ምንኛ...ብታምናት ?
#እላለው !!
ይሄም ውጣ ውረድ ፥ እያብሰከሰከ ሆዴን ቢበላኝም
ንስር ማንነትሽ
መውጫ ቢያጣ ፥ ብዬ አያሳስበኝም
#ይልቅ
ኩፍኩፍ ይመስል
ትዝታሽ በግዜ ፥ በዋዛ ባይለቅም
መጣሽ ከማለቴ
ለመለመ ያልኩት ፥ በቅፅበት ቢደርቅም
ሞገስሽን ያዬ ልቤ
ምን እንደሚልሽ አያውቅም።

@Abr_sh

@getem
@getem
@getem
በገና ሰሞን ባህላችን ከምዕራባውያኑ መደበላለቅ ከጀመረ ቆይቷል። ያንን አስመልክቶ ኣንድ-ሀገር/ቢያ-ቶኮ ከተሰኘው አዝናኝ ወጎችና ግጥሞችን ካካተተው መጽሐፌ ውስጥ በገጽ 77 ያለውን ሜሪ X-mas የተሰኘ ግጥም ተጋበዙልኝ።
እድል
"""""""
ችለው አይጋፉት
እንዴት ያደርጉታል የእድልን ጠማማ
እንዲያው ዘመም ያለ
አሮጌ ቤት አይደል በባላ አይቃና!

@getem
@getem
@getem

#አብርሃም
እግረ-መንገድ!(ልዑል ኃይሌ)
አውርደው ያን ፍሬ ቅጠፈው ያን ቅጠል፤
ምናገባህና ለሕልወተ-ፍጥረት እንዲህ ምትቃጠል፤
ካገኘኸው ብላ ካገኘኸው ጠጣ፤
ለተበዪ እያዘንህ ራስህን አትቅጣ፤
ብላ ብላ ብላ
ጠጣ ቤት ያፈራው፤
ምስጋና ቢስ መሐል
ፍፁም እንዳታዝን ሐጢያትህን አትፍራው፤
ካጋጠመህ እደር
ካጋጠመህ ይንጋ ይገፈፍ ጨለማ፤
በማማረጥህ ነው
ምርጫ ቢስ ሚያደርግህ በሞላ ከተማ፤
ሳታማርጥ!....
ታኅሳስ 15, 2012ዓ.ም.

@getem
@getem
@getem
ካለፈ በኃሏ

ከጊዜው በኃሏ
ከረፈደ ወዲህ… እንባ ከደረቀ
በዚያው ላይመለስ ፀሀይ ከጠለቀ
ካከሸፍኩት ትላንተ በበቀለ ዛሬ
አመፃ ነው ማሰብ የሚጣፍጥ ወሬ
.
.
.
Dashu2

@getem
@getem
ነበረ!

እንደነገርኩህ ነው የለም የምነግርህ
ብቻ ግን ይኸውልህ ፥
ፊቱ እህል ቀርቦ መብላት ያላወቀ
በርሀብ የራደ በችግር ያለቀ ፥
ለእንቆቅልሽ መፍቻ የመሰረት ያለ
ሰንደቃ'ላማ ፊት ሀገሩን 'ሚረሳት አንድ ወጣት ነበረ!
'
ውሉ የጠፋበት ዳቦ መግዣ ያጣ
ለእርዳታ ስንዴ ገንዘብ የሚያዋጣ፤
ፅድቅ ይሉት ኩነኔ አጣምሮ ሚሰፋ
ቀኑ እንዳይገፋው፥ ቀኑን የሚገፋ!
ካልሲ ለጠየቀው ጫማ እየጨመረ
አፀድ ስር ቁጭ ብሎ እርቃኑን የቀረ
አንድ ወጣት ነበረ!
'
እንጀራ አቅርቦ መብላት የሚያስጠፋው
እየቀለድክለት ቀልድክ የሚያስከፋው ፣
መርዶ እየነገርከው ጮቤ ሚያሰረግጠው
ተስፋ'ለህ ስትለው ተስፋ ሚያሰቆርጠው፣
መድሃኒት ፍለጋ እንዳቀረቀረ፥ አጎንብሶ የቀረ
አንድ ወጣት ነበረ!
'
ብርቱ! ሆነ ስንል፤ ደ'ሞ እየደከመ
መዳኑ ነው ሲባል፤ ብሶ እየታመመ፥
መውደቁ ነው ስንል፤ ድሆ እየተነሳ
ሊታወስ ነው ሲባል፤ ሰርክ እየተረሳ፥
ብቻውን የቀረ፣
አንድ ወጣት ነበረ!
'
ከእንቅልፉ ሲነቃ፤ እንቅልፍ የሚጥለው
ድነሀል ስትለው፣ ድህነት! የገደለው፤
ከመሔዱ ብዛት መንገድ ያከሰረው
ከመንገዱ ይልቅ መድማት ያስተማረው፣
በመንገድ በመድማት በመሔድ የቀረ፣
የማርያም ንግስ እለት ደጃፏ ቁጭ ብሎ ማርያምን ሚረሳት አንድ ወጣት ነበረ!
'
"በምድር ዘላለም" አቀርቅሮ የቀረ፣
ነበረ የሚለኝ አንድ ወጣት ነበረ!
በጠራራ ፀሀይ ይነጋል እያለ ጨረቃን በመስደብ ብዙ አመት የኖረ፣
አንድ ወጣት ነበረ!
በየ እግረ መንገዱ "በተስፋ" የኖረ፣
እስታውሰኝ የሚለኝ አንድ ወጣት ነበረ!
በአዳም ፊርማ ላይ አሻራ ፍለጋ አቀርቅሮ የቀረ፣
ቀና በል የሚለኝ አንድ ወጣት ነበረ!
'
እንጀራ ለመብላት፤ እንጀራ የሸጠ
ከሚዲያ ጀርባ ሊቀበል የሰጠ፣
ዝንት አለም ሲጠላ ሲገፋ የኖረ
ሰርአተ ቀብሩ ላይ ምስኪን ነበር እኮ አፈር በልቶት ቀረ፤
ብለው ማያወሩለት አንድ ወጣት ነበረ!
'
በአንድ ወጣት ታሪክ ተመስጦ የቀረ፣
አንድ ወጣት ነበረ እያለ የሚፅፍም አንድ ወጣት ነበረ!
ነበረ!
ነበረ!!
ነበረ!!!

(ዩህንስ ስለሺ)

@getem
@getem
@getem
አለሁኝ_በደህና
(በዕውቀቱ ሥዩም)
.
አንቺ እንደምን አለሽ
… እኔ አለሁ በደህና
ይመስገን ዳመና
በገበሬው አጥንት – መሬቴን እያረስኩ
በገበሬው እንባ – ማሳ እያረሰረስኩ
እንጀራ ቢጠፋ – ገበሬ እየጎረስኩ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
.
ሰው ሲያፈርስ እያየሁ
ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭጋ ነገር ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
…ያለምንም ፀፀት
…ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
ኣለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና።
በምቾት መዲና
የነዳያን ትዝብት እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳ ጎዳና ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አንዳቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ
ልክ እንደ ደባሎች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብ ላይ እጀን እየሰደድሁ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
.
ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
መዓበል ሲቃረብ ያመልጣል ሽመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ዳመና
የኔ ሃዘን ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ ይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል።
.
ይህንን እያየሁ ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና ይመስገን ዳመና
አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
ኣለሁ ግርምት ኖሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
............የማስበው ኖሮኝ
.................የምለው ቸግሮኝ
@getem
@getem
#jeko
"የምፃተኛው_ኑዛዜ
በእውቀቱ ስዩም

ካ’ገር ጫፍ እስከጫፍ በጥላህ ከልለህ
ተራራው የኔ ነው ለምን ትለኛለህ?
ወንዙ ድርሻዬ ነው ለምን ትለኛለህ?
እንኳንስ መሬቱ አንተም ያ’ንተ አይደለህ።
እኔ መጻተኛ አንተ ኗሪ ነኝ ባይ
እኔ እግሬን ስከተል ርስትህን ስታይ
ስቀርብህ ገፋኸኝ ስትገፋኝ ቦታ አጣሁ
ድንኳን ብትተክል፣ ነፋስ ሆኜ መጣሁ።
ያ’ባትህ ያ’ባቴ
ጠበኛ ስማቸው
ጠበኛ ሕልማቸው
በሕይወት ተጣሉ፣ ታረቁ ባፅማቸው
ባፈር ተቃቃሩ፣ አፈር አስማማቸው
በዙሪያቸው በቅሎ ከቧቸው ሞት ደኑ
መተቃቃፍ መርጠው ማማና ወይን ሆኑ።
ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት
ያ’ባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት
አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወድቀኽ
አካሌ ደረቴ መኾንኽን መች አወቅኽ ??? !!!

@getem
@getem
@getem
👍1
ኑረት-ሂደት-ሂደት
(ልዑል ሀይሌ)

ከገላ ተቆርጦ ዕትብቴ ሲቀበር፤
ለአፈር ማንነቴ
ለሞት ቀብድ ነበር።
.
ታዲያ...
ምነው ተዘነጋኝ?!
.
ዳግም የሚቀበር
ቀሪ ገላ እንዳለኝ፤
ትምክህተኛ ሆኜ
በኑረቴ ዘመን
የራቅኩኝ ቢመስለኝ፤
ያው...
አሁንም
ቀብድ የተያዘብኝ ቁራጭ እትብት ነኝ!።


@getem
@getem
👍1
#ያልተግባቡ~ልቦች

ወደ ቤታችን በሙሉ አቋማችን ስንመለስ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ዓለም ሰበዞች
በኑሮ ጣቶችሽ ህይወትን ሲገምዱ
ያ'መክንዮሽ ሚዛን
ባሰፈረው ልኬት የህሊናሽ ፍርዱ
ለባለቀን እንጂ
ለግዜ ምርኮኛ ውሳኔሽ አይራራም
ከምክንያት በቀር
እውነት ይሉት ፈሊጥ በፍርድሽ አይሰራም፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
ግዜ ጥሎኝ ሳለ በይሆናል ተስፋ ያልሽኝን ረስቼ
ከባለቀን ጋራ
ሰርክ እሟገታለሁ
እውነትን ፍለጋ ምክንያትን ትቼ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ክታብ ገፆች
የኑሮን ሆ-ህ-ያት ገልጠው ሊያስነብቡ
በማራኪ ቀለም
የልብሽ ድርሳን ላይ ሀሳብ ሲከትቡ
በገድላት ቋንቋ
ያ'ለም ጀብደኞችን ፅፈው ሲያስቀምጡ
ነግረሺኝ ነበረ
ለኔ አይነት ምናቦች ቃል እንደማይሰጡ፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
ቀን መሽቶ ሲነጋ ያልሽን ረሳለሁ
መፃ'ፍሽ ገፆች ላይ
እኔን መሳይ ምናብ ይኸው ፈልጋለሁ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ሰማይ ዳምኖ
ዶፍ እያወረደ በመብረቅ ሲታጀብ
ልብን ሊያበሰብስ
መንፈስ እያራደ ከሚፈጥረው ወጀብ
የሞቀውን ገላ
የቤትሽ ወጋግራ ታዛሽ ቢያስጠልልም
ካጥሩ ይዘጋል
የኔ አይነቱን እርቃን ከዶፍ አያስጥልም፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
ሰማዩ ሲያነባ ህግጋቱን ሽሬ ወዳ'ንቺ ሮጣለሁ
እራቁት ገላዬን
ከተዘጋው ቤትሽ ላስጠልል መጣለሁ፡፡

አዎ ነግረሺኛል!!

ያ'ንቺ ጓዳ ማጀት
ከተ'ትረፈረፈው ከሞላው መዐዱ
በመለገስ ጥበብ
መሶብሽ ተከፍቶ የመስጠት ልማዱ
በበረከት ሰቀል
የገበታሽ እምነት ሰው እየመዘነ
ነግረሺኝ ነበረ
ለጠገበው እንጂ
ለተራበ አንጀት ንፉግ እንደሆነ፡፡

እኔ ግን የዋህ ነኝ
በራብተኛ ክብሬ ተመፅዋቹን ሳለሁ
ከጠገቡት እኩል
በታጠፈ አንጀቴ ከ'ማድሽ ቀርባለሁ፡፡

እንዳይገርምሽ ውዴ
በቃ እኔ እንዲህ ነኝ
ያልሽኝን ምረሳ የሰሚ ደንቆሮ
አንቺ ደግሞ እንደዛ
አፍሽ የማይደክመው ህግሽን ተናግሮ

ግና ምንም እንኳን
ምክንያትሽ ከ'ምነቴ በግብር ተጣርሶ
ያልሽውን የረሳ
በካኝ እኔነቴ
ባንቺ ዓለም ምናቦች ቢኖርም እረክሶ
:
ከክርስቶስ ገደል
ከመስቀሉ ማዶ በቋጠርኩት ተስፋ
ስለፍቅር ብዬ
በ'ውነቴ ል'ሸነፍ በምክንያት ልገፋ
ድሮም እንደዚህ ናት
ባንቺ አይነት ምክንያቶች ዓለም፡፡
(ልብ አልባው)

@getem
@getem
#ፌዝ ያዘለ ዋይታ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።
ቅዱስ ቃሉ ሲገልጥ ፥ በቅዱሱ መጣፍ
ለእስራኤል አፅድቆት ፥ የግብፁ ዱላ ሊያርፍ
ሀዘንን አርቆ ፥ መከራን ሊያጎላ
እነሆኝ ራሄል ...
ልጇን ወለደችው ፥ በምጥማጡ ስፍራ
ከዛም ገደለችው ፥ ስቃይ በልቧ አዝላ።
ደግሞም ለንጉሱ....ለክፋቱ ተረክ
ለግብሩ ውንጀላ ፥ ለታሪኩ ንረት
ራሄል እንባዋን ፥ በአየር አንሳፋ ለእግዜር ላከችለት።
ብሎ ይተርታል!
ወዲህ ያለ ጠያቂ ...
የእናትነት ዋጋ ፥ በንጉስ ትዕዛዝ ፥ ዋጋው የማይነጥፍ
መሆኑን ያወቀ የቅኔ አዋቂ በቃላቱ ሲጥፍ...
"ራሄል ለልጇ ፍቅሯ ባይወሰን መገደብ ባይኖረው
የእናትነት ልቧ የእናትነት ሆኖ ራሮት ቢዋጀው
በእኩይ ንጉስ ቁጣ ትዕዛዝን ፈርታ ልጇን ባትገለው !"
ብሎ ይቧልታል እግዜሩን ሲተቸው።

@getem
@getem
@getem
ሙግት ወይስ እውነት?
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
በፍላጎት መንገድ...
በምኞት ጎዳና ፣ ስመጣ ተጉዤ
ገንዘብ እየፈለግሁ...
"ፍቅር ይበልጣል" የሚል ፣ ከንቱ ሙግት ይዤ
እኔም ልክ እንዳንቺ...
ከገንዘብ ወዳጅ ጋር ፣ ተከራክሪያለሁ
ገንዘብ የማይገዛው...
ብዙ ደስታ አለ ፣ ስል አስረድቻለሁ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ግን ደሞ ግን ደሞ...
በማስረዳቴ ውስጥ ፣ አለ የሚያስረዳኝ
ከፍቅር ከገንዘብ...
ከምንም የሚበልጥ ፣ "እውነት " ይሉት አዳኝ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እናም እውነት ማለት...
በጭራሽ አይደለም!
አንድድ እውነት ለማቆም ፣ አንዱን እውነት መጣል
አትጠራጠሪ!!!
አንዱ ገንዘብ ሲመርጥ ፣ አንዱ ፍቅር ይመርጣል
ሒጅ ወደ ፈለግሽው!!!
ከፍቅር ከገንዘብ ፣ ፍላጎት ይበልጣል፡፡

@getem
@getem
@getem
👍2
ታሮስ አለሙ
#ሞታለች~ማለቴ

ያኔ ጥንት ድሮ
በልቦና ሰበዝ በእምነት ድር ታስረን
ስለ እውነት ላንዝል
በፍቅር ለፍቅር ባደርንበት ዘመን
ከሀረጋት መሀል
እኛን ለማወደስ ለአፍ ቀሎት ቃሉ
ስለ መልካም ምኞት
ካ'ይን ያውጣችሁ ብሎ የመረቀን ሁሉ፡፡

በዘመን ሀዲድ ላይ
ዛሬ ግን "ያ" ጊዜ ዓመታት ተሻግሮ
የማይሆነው ሊሆን
የተገላቢጦሽ ነገር ተቀይሮ
በቀዬው ጎዳና
አንቺ የሌለሽበት ብቻዬን ስባዝን
ባልተጨበጠ ውል
በትዝታሽ ዜማ ቆዝሜ ሳላዝን

ሁኔታዬን አይተው
ደረቅ ከንፈር መጠው
ድንገት ሲጠይቁኝ የት ሄዳ ነው ብለው
አንገቴን ደፍቼ
በተሰበረ ቅስም ሞታለች የምለው
ስለሞትሽ አይደለም
ከልቤ አውጥቼ ስለቀበርኩሽ ነው፡፡

@getem
@getem
@getem
(እጅግ ለምወድሽ - ለማስብልሽ ሴት
ለጫማዎቼና - ለቪትዜ እመቤት፤
የአዲስ ዓመት - መልካም ምኞት!)
ደፂን ባንቺ ጉዳይ ባላምነውም
እሷ አክሱም ጽዮን ትጠብቅሽ፤
እንደ ታዬዎቹ ከላይ ከአፍና
ከታች የሆድ አተት ትሰውርሽ!
የፍቅር ኖቤል አሸንፊ
የራስሽ ክልል ይኑርሽ፤
ይኾኖ ይባል ይደንግጥ
በሜቴክ አይን የሚያይሽ።
ቻናል ቀይሪ አይበሉሽ
ያስወራሽ የፍቅር ቋንቋ፤
ግንባርሽ ብልፅግና ይጥራ
ያውጣሽ ከችግር አረንቋ!
ሀብትሽ በፎርብስ ገፆች
አንደኛ ተብሎ ይዘገብ፤
ዲፋክቶ ዳሌሽ በዩኔስኮ
በሚዳሰስ ቅርስነት ይመዝገብ።
ይምጠቅ በሕዋው ይናኝ
ሳተላይት ይሁን ስኬትሽ፤
ጠሚ እንዳጠጣው ችግኝ
ይመር - ይለምልም ሕይወትሽ።
ጠላትሽ አንጀቱ ይቃጠል
አርሰናል ይሁን የሱ ዕጣ፤
የቫይበር ወሬው ተለቅሞ
በፌስቡክ ገፆች ላይ ይውጣ።
ለመንፈስሽ ዕረፍት ያድለው
እንደቤተመንግሥት ይታደስ፤
ምቀኛሽ እረፍት አያግኝ
እንደሀገራችን ሰላሙ ይደፍርስ።
እኔንም. . . .
የፍቅርሽን ሰንሰለት የምሰብር
አፍራሽ መሆኔን የምረሳ፤
ማነህ ተብዬ ስጠየቅ
የምል ያድርገኝ ቶሎሳ!!
ቶሎሳ!
ቶሎሳ!
ቶሎሳ!

@getem
@getem
@paappii

#gemechu merara fana
1
"ነፍስሽን አፈቀርኩ"
(መልአኩ ስብሐት ባይህ)

**************
ቅሩብ ውስጠ ወይራ
ከውዳዴሽ ጌራ።
በአክናፋት ብትከንፊ
ሕዋሴን ብትቀዝፊ
ልቤን አለምልመሽ ምናቤን ብታርፊ።
እርሰትሽ ሰረፀኝ
ልግስናሽ ሰመጠኝ
የአንቺነትሽ ፈለግ እኔነቴን ዋጠኝ ።
እናም ደም-ሥርዓቴ
ሀሴት ተንሳፎፍቴ
እቅፍ አኮቴቴ ።
ስል አፈቅራሻለሁ
ከዕውንሽ የዛቅኩት ዕውንሽን ይዤ ነው
ከመንገድ የላቀ መንገድ ተጉዤ ነው።
እናም ደም-ሥርዓቴ
ከእስትንፋስሽ ስነፍስ
ነፍሴ ከነፍስሽ አውድ ሳትኮንን ትቀደስ
መወድስ ዓለሜ በእሺታሽ ይወደስ።
ጎነ ግራነትሽ ቁራሸ መክሊትሽ
በኔ ተመስጥሮ
አድምታ ይሁነኝ አድምነት ድሮ።
አንድምነት አንቺ
እኔ ያንቺ ፍቺ።
በአቅራቦትሽ ጥጋት
ነፍስሽን ምጠጋት።
.
.
.
ተጻፈ:-፲፯/፲፩/፳፻፲፩ ዓ.ም
@getem
@getem
@poem_with_mela
ብቸኝነት !
/ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም/
ቀኑ ተሰናብቷል
ጨለማው በርትቷል
ጨረቃ የት ጠፋች?
ምን ሆኑ ኮከቦች?
ጅቦች አይፈነጩ
ውሾች አይንጫጩ፡፡
ጨለማው ፍጹም ነው
ነፋስ ጭራሽ አይነፍስ
ዛፍ አይወዛወዝ አንድ ወፍ አይላወስ
ሁሉም ፀጥ
በያለበት ለጥ፡፡
ሰው ሁሉ ምን ነካው?
ድምፁ እንዲህ የጠፋው?
እኔንስ ምን ነካኝ?
እንቅልፍ የማይወስደኝ?
እኔ ብቻዬን ነኝ በዚህ ደረቅ ውድቅት፤
ልቤ እየቃተተ ጠልቶ ብቸኝነት፡፡
ሰው አለወይ ባገር?
ማረፊያ ለፍቅር?
ፈላጊና፤ ተፈላጊ ሁሉ
ቀናው ወይ በሙሉ?
የቀረ የለም ወይ በዓለም አለኔ
በምኞት ኩነኔ?
እኔ እንደዚህ ስዋኝ ባሳብ በትካዜ
የት ይሆን ያለሽው አንቺ ይህን ግዜ
ምን ታደርጊ ይሆን?
እንገናኝ ይሆን?
መች ይሆን ዕለቱ?
መች ይሆን ሰዓቱ?
የትስ ይሆን ቦታው?
እንዴት ይሆን እውቂያው?
እጠብቅሻለሁ ልቤን እየታዘዝሁ፤
አትቅሪ፤ ፈልጊኝ፤ እፈልግሻለሁ፡፡

@getem
@getem
@paappii
1👍1
#ጭብጨባ
(በተመስገን መሰረት)
.
ጭብጨባ አትውደድ፣ አይምሰልህ የብርታት
ከመውደቋ በፊት......
ቢንቢም መስሏት ነበር፣ አድናቆት የሰጧት፡፡

@getem
@getem