ALBA
( Ezra Pound )
As cool as the pale wet leaves
of lily-of-the-valley
She lay beside me in the dawn.
1913
የንጋት ዝማሬ
( እስራኤል )
ለዝዞ እንደረገፈ ፣ 'ርጥብ የአደይ ገላ
በጎህ ስርቀት ሳያት ፣ ከጎኔ ተንጋላ
ታሳሳ ነበረ ፣ ታበራ ነበረ
መለኮት የቀባት ፣ ጽሩይ ስዕል መስላ።
2018
~ ነፃ ትርጉም
@adamureta
@getem
@getem
@getem
( Ezra Pound )
As cool as the pale wet leaves
of lily-of-the-valley
She lay beside me in the dawn.
1913
የንጋት ዝማሬ
( እስራኤል )
ለዝዞ እንደረገፈ ፣ 'ርጥብ የአደይ ገላ
በጎህ ስርቀት ሳያት ፣ ከጎኔ ተንጋላ
ታሳሳ ነበረ ፣ ታበራ ነበረ
መለኮት የቀባት ፣ ጽሩይ ስዕል መስላ።
2018
~ ነፃ ትርጉም
@adamureta
@getem
@getem
@getem
❤39🔥8
"ግን"
.
.
በንግግር መሐል ከቁብ የማንቆጥራት፤
አብራ የታከለች "ግን" የምትል ቅንጣት፤
ጎልታ ባትሰማም እልፍ ነው ትርጉሟ፤
ብትሸፋፈንም ስዉር ነው ህመሟ።
አያሌ ነገራት በዉስጧ ደብቃ፤
ስንቱን አሰመጠች ጥላ አሳስቃ።
✍ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.
.
በንግግር መሐል ከቁብ የማንቆጥራት፤
አብራ የታከለች "ግን" የምትል ቅንጣት፤
ጎልታ ባትሰማም እልፍ ነው ትርጉሟ፤
ብትሸፋፈንም ስዉር ነው ህመሟ።
አያሌ ነገራት በዉስጧ ደብቃ፤
ስንቱን አሰመጠች ጥላ አሳስቃ።
✍ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤59👍25🔥2
ስለቴ ሰምሮ
ሕልሜ ተቃንቶ፤
ተስፋዬ አብቦ
ድካሜ አፍርቶ፤
ባዶ ሞሰቤ
በእንጀራ ሞልቶ፤
የደስታ ወጀብ ሲያርበደብደኝ
ዕንባ ብቻ ነው ከዐይኔ ሚወርደኝ፤
ደግሞ
እንደገና
ጉልበቴ ደክሞ
ኪሴ ተራቁቶ፤
ቅስሜ ተሰብሮ
ልቤ ተከፍቶ፤
የመከራ እከክ
በአካሌ ፈልቶ፤
የሐዘን ክረምት ሲያኮራምተኝ
መሳቅ ብቻ ነው የማያቅተኝ፤
እንዲህ ነኝ እኔ
ነገሬ ሁሉ ግራ ያጋባል፤
ፊቴ ከሳቀ ልቤ ያነባል፤
እንዲሁ በሩቅ አልገመትም
ተኛ ነው 'ምባል አንዴን ብሞትም።
By Tewodros kassa
@getem
@getem
@paappii
ሕልሜ ተቃንቶ፤
ተስፋዬ አብቦ
ድካሜ አፍርቶ፤
ባዶ ሞሰቤ
በእንጀራ ሞልቶ፤
የደስታ ወጀብ ሲያርበደብደኝ
ዕንባ ብቻ ነው ከዐይኔ ሚወርደኝ፤
ደግሞ
እንደገና
ጉልበቴ ደክሞ
ኪሴ ተራቁቶ፤
ቅስሜ ተሰብሮ
ልቤ ተከፍቶ፤
የመከራ እከክ
በአካሌ ፈልቶ፤
የሐዘን ክረምት ሲያኮራምተኝ
መሳቅ ብቻ ነው የማያቅተኝ፤
እንዲህ ነኝ እኔ
ነገሬ ሁሉ ግራ ያጋባል፤
ፊቴ ከሳቀ ልቤ ያነባል፤
እንዲሁ በሩቅ አልገመትም
ተኛ ነው 'ምባል አንዴን ብሞትም።
By Tewodros kassa
@getem
@getem
@paappii
❤83🔥17👍5😱2
እኔ እምፈልገው
( በእውቀቱ ስዩም)
እውነት ለመናገር እኔ ምፈልገው
ካንቺ ጋር መጋባት
ይህን ሀምሌ ፊቴን : ደጋግሞ ማራባት
ከወፎች ጋር መንቃት : በጊዜ ቤት መግባት::
"ምንም ደሃ ቢሆን: ባይኖረውም ሀብት
ከደጃፍ ሲቀመጥ: ደስ ይላል አባት"
ለሚል መናኛ ጥቅስ: ኑሮየ ማይመጥን
ሲሻኝ በየባንኩ: ስፈልግ በሳጥን
የተረፈኝ ገንዘብ
ደጃፍ ላይ ቁጭ ብየ: ድሀ የምታዘብ
ተምሳሌትነቴ የሚዳረስ ባለም
ሞዴል አባወራ ተብየ ምሸለም
አገሬን ማስከበር
ህዝቤን ማስተባበር
የልጅ ልጅ አፍርቼ
በመቶ አመት ሙቼ
ስላሴ መቀበር
ምኞቴ ይህ ነበር::
እውነት ለመናገር እኔ እምፈልገው
ወንደላጤ ኑሮ
በሴቶች መታጀብ : ልክ እንዳውራ ዶሮ
ጊዜ ጥሎኝ ቢሄድ : ቀን ቢገሰግስም
መላው ጭንቅላቴ : ገብስማ ቢለብስም
ላቅማዳም ነው እንጂ: ለትዳር አልደርስም::
ደሞ
ዘር መዝራት እርሜ ነው : ደጋግሜ ባርስም
ባለመኖር ላሉት: ስቃይ አላወርስም
ቢፈልግ ሌላው ህዝብ
ይፈልፍል እንደዝንብ
ይባዛ እንደንጉዳይ
አገር ስራው ያውጣው! ሰው የራሱ ጉዳይ!!
የራሴ ፈጣሪ- ነኝ የራሴ ገዳይ!!
እኔ እምፈልገው...
እኔ እምፈልገው..
እኔ እምፈልገው
-----------
ገንዘብ ቢመዘበር: በገንዘብ ይተካል
እድሜ ለጉልበትሽ : በላቡ ለሚያድር
በውርስ በስጦታ : ግፋ ቢል በብድር::
በቆጠብነው ቁጥር
ጊዜ ነው የሚያጥር
እድሜ ነው የሚያልቀው
የምንፈልገውን በቅጡ ሳናውቀው::
@getem
@getem
@paappii
( በእውቀቱ ስዩም)
እውነት ለመናገር እኔ ምፈልገው
ካንቺ ጋር መጋባት
ይህን ሀምሌ ፊቴን : ደጋግሞ ማራባት
ከወፎች ጋር መንቃት : በጊዜ ቤት መግባት::
"ምንም ደሃ ቢሆን: ባይኖረውም ሀብት
ከደጃፍ ሲቀመጥ: ደስ ይላል አባት"
ለሚል መናኛ ጥቅስ: ኑሮየ ማይመጥን
ሲሻኝ በየባንኩ: ስፈልግ በሳጥን
የተረፈኝ ገንዘብ
ደጃፍ ላይ ቁጭ ብየ: ድሀ የምታዘብ
ተምሳሌትነቴ የሚዳረስ ባለም
ሞዴል አባወራ ተብየ ምሸለም
አገሬን ማስከበር
ህዝቤን ማስተባበር
የልጅ ልጅ አፍርቼ
በመቶ አመት ሙቼ
ስላሴ መቀበር
ምኞቴ ይህ ነበር::
እውነት ለመናገር እኔ እምፈልገው
ወንደላጤ ኑሮ
በሴቶች መታጀብ : ልክ እንዳውራ ዶሮ
ጊዜ ጥሎኝ ቢሄድ : ቀን ቢገሰግስም
መላው ጭንቅላቴ : ገብስማ ቢለብስም
ላቅማዳም ነው እንጂ: ለትዳር አልደርስም::
ደሞ
ዘር መዝራት እርሜ ነው : ደጋግሜ ባርስም
ባለመኖር ላሉት: ስቃይ አላወርስም
ቢፈልግ ሌላው ህዝብ
ይፈልፍል እንደዝንብ
ይባዛ እንደንጉዳይ
አገር ስራው ያውጣው! ሰው የራሱ ጉዳይ!!
የራሴ ፈጣሪ- ነኝ የራሴ ገዳይ!!
እኔ እምፈልገው...
እኔ እምፈልገው..
እኔ እምፈልገው
-----------
ገንዘብ ቢመዘበር: በገንዘብ ይተካል
እድሜ ለጉልበትሽ : በላቡ ለሚያድር
በውርስ በስጦታ : ግፋ ቢል በብድር::
በቆጠብነው ቁጥር
ጊዜ ነው የሚያጥር
እድሜ ነው የሚያልቀው
የምንፈልገውን በቅጡ ሳናውቀው::
@getem
@getem
@paappii
❤73🔥11👍5🎉1
ለዚህ ነበር?
:
ሀገር ለመሲሁ . . .
ለልቡ አቡጊዳ ፥ ለአንድ ነፍሱ ሀሁ
ሲሰዋ . . .
ሲሰዋ . . .
በአዛን
በመረዋ ..
በጌታ ቃል ጥሪ ፣
እኔ የአንቺ ወዳጅ -
አተረፍኩሽ ብዬ - ተረፍኩ አለቀሪ።
፡
በአይኔ ነፋስ ዘለቀ ፤
በጫንቃዬ ጀምበር ጠለቀ
ቅዠት ሆኜ - ዳመንኩ ፤
ተስፋ ሆኜ ዘነብኩ ፤
መስኮት ሆኜ ሄጄ ..
በር ሆኜ ተመለስኩ።
˙
እሳት ሆነሽ
ደርሰሽ
ፈተንሽኝ እንደወርቅ ፤
እንዳይሆን ሆኜልሽ
እንዳልገባ ደግሞ ..
ተከዝኩልሽ ብወድቅ።
ባጣሽ ዘመን ረገምኩ ፤
ሰው መሆኔን ትቼ ..
እምባ ሆኜ ፈሰስኩ።
ከነበር ማጀቴ ተደብቄ ውዬ
ድኬ ቀን አጉድዬ
ልቅር ብትይ ምጪ¹ ብዬ
ስንት ጊዜ ከፍቶኝ ገባሁ ?
ስንት ጊዜ ባጣሽ ባባሁ ?
ስንት ጊዜ ...?
ካለመቅረት ቀዬ አንቺ ቀርተሽ ማዶ
ጭላንጭል ፋኖሴን አከሰማት መርዶ?
..
ለዚህ ነበር...?
ሞትን ያማሁ?
በሽንፈት ፊት ስሜን ያጣሁ?
:
ለዚህ ነበር...?
ደስታ ያጣኝ ?
ቀን የረሳኝ ?
ጊዜ የገፋኝ?
:
ለዚህ ነበር...?
ስም ያበጀሁ?
ልጅነቴን
እድል ቤቴን
ንቄ የዋጀሁ?
:
ለዚህ ነበር...?
እምባዬ ላይ ሳቄን ጥዬ
ጨለማዬን መጣሁ ብዬ
የሽወድኩት?
ያፌዝኩበት?
:
የእውነት ግን ለዚህ ነበር...?
ይሄ ሁሉ?
ቃል ይረሳል ዘመን ሙሉ?
ልብ ይረሳል ?
ይሄን በደል ?
የጊዜን ቀልድ?
የህይወትን ገድ ?
የእውነት ግን ልብ ይረሳል ???
?
. . .
@getem
@getem
@sirakoo
:
ሀገር ለመሲሁ . . .
ለልቡ አቡጊዳ ፥ ለአንድ ነፍሱ ሀሁ
ሲሰዋ . . .
ሲሰዋ . . .
በአዛን
በመረዋ ..
በጌታ ቃል ጥሪ ፣
እኔ የአንቺ ወዳጅ -
አተረፍኩሽ ብዬ - ተረፍኩ አለቀሪ።
፡
በአይኔ ነፋስ ዘለቀ ፤
በጫንቃዬ ጀምበር ጠለቀ
ቅዠት ሆኜ - ዳመንኩ ፤
ተስፋ ሆኜ ዘነብኩ ፤
መስኮት ሆኜ ሄጄ ..
በር ሆኜ ተመለስኩ።
˙
እሳት ሆነሽ
ደርሰሽ
ፈተንሽኝ እንደወርቅ ፤
እንዳይሆን ሆኜልሽ
እንዳልገባ ደግሞ ..
ተከዝኩልሽ ብወድቅ።
ባጣሽ ዘመን ረገምኩ ፤
ሰው መሆኔን ትቼ ..
እምባ ሆኜ ፈሰስኩ።
ከነበር ማጀቴ ተደብቄ ውዬ
ድኬ ቀን አጉድዬ
ልቅር ብትይ ምጪ¹ ብዬ
ስንት ጊዜ ከፍቶኝ ገባሁ ?
ስንት ጊዜ ባጣሽ ባባሁ ?
ስንት ጊዜ ...?
ካለመቅረት ቀዬ አንቺ ቀርተሽ ማዶ
ጭላንጭል ፋኖሴን አከሰማት መርዶ?
..
ለዚህ ነበር...?
ሞትን ያማሁ?
በሽንፈት ፊት ስሜን ያጣሁ?
:
ለዚህ ነበር...?
ደስታ ያጣኝ ?
ቀን የረሳኝ ?
ጊዜ የገፋኝ?
:
ለዚህ ነበር...?
ስም ያበጀሁ?
ልጅነቴን
እድል ቤቴን
ንቄ የዋጀሁ?
:
ለዚህ ነበር...?
እምባዬ ላይ ሳቄን ጥዬ
ጨለማዬን መጣሁ ብዬ
የሽወድኩት?
ያፌዝኩበት?
:
የእውነት ግን ለዚህ ነበር...?
ይሄ ሁሉ?
ቃል ይረሳል ዘመን ሙሉ?
ልብ ይረሳል ?
ይሄን በደል ?
የጊዜን ቀልድ?
የህይወትን ገድ ?
የእውነት ግን ልብ ይረሳል ???
?
. . .
@getem
@getem
@sirakoo
❤52🔥11👍7
እንዴት?... ይረሳኛል
.
.
ከቤተመቅደሱ ማለዳ ተገኝተን ቆመን ለቅዳሴ፣
እዉነተኛ መስዋዕት ለአምላክ ስናቀርብ ክብርና ዉዳሴ፣
በሕማማት ሰሞን እንሞት እንደሆን ፍትሐት ስንፈታ፣
ከያዙት ዘንባባ ጥቂት ዝንጣፊ ሲሰጡን የኔታ፣
በጣቴ ለክተህ ፈጥነህ ስታበጃጅ ያማረ ቀለበት፣
ኪዳን እንዲሆነን ከእጄ ልታጠልቀዉ በዚህ ቅዱስ ሰንበት።
ትክ ብዬ ሳይህ.....
አይንህ ስራህ ላይ ነው፣
ልብህ ሀሳብ ላይ ነው።
እንዴት ይረሳኛል......
#በሆሳዕና እለት ከእጄ ያገባኸዉ ዉቡ ቀለበቴ፣
ላይወልቅ ተሰፍቷል ተለይቶ አያዉቅም ከአራተኛው ጣቴ፣
ዛሬም እንደትናንት በአዝማናት ንጉደት ፈፅሞ አላረጀም፣
መዓዛው ሳይጠፋ እንደለጋነቱ ካይኔ አልተሰወረም።
✍ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.
.
ከቤተመቅደሱ ማለዳ ተገኝተን ቆመን ለቅዳሴ፣
እዉነተኛ መስዋዕት ለአምላክ ስናቀርብ ክብርና ዉዳሴ፣
በሕማማት ሰሞን እንሞት እንደሆን ፍትሐት ስንፈታ፣
ከያዙት ዘንባባ ጥቂት ዝንጣፊ ሲሰጡን የኔታ፣
በጣቴ ለክተህ ፈጥነህ ስታበጃጅ ያማረ ቀለበት፣
ኪዳን እንዲሆነን ከእጄ ልታጠልቀዉ በዚህ ቅዱስ ሰንበት።
ትክ ብዬ ሳይህ.....
አይንህ ስራህ ላይ ነው፣
ልብህ ሀሳብ ላይ ነው።
እንዴት ይረሳኛል......
#በሆሳዕና እለት ከእጄ ያገባኸዉ ዉቡ ቀለበቴ፣
ላይወልቅ ተሰፍቷል ተለይቶ አያዉቅም ከአራተኛው ጣቴ፣
ዛሬም እንደትናንት በአዝማናት ንጉደት ፈፅሞ አላረጀም፣
መዓዛው ሳይጠፋ እንደለጋነቱ ካይኔ አልተሰወረም።
✍ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤65🔥10👍5
መቃብር ምሰው አፈር አልብሰው
ደረት ደልቀው ፍም ዕንባ አፍስሰው
ደህና ሁን ብለው የመጡትን ሰው፤
ድንገት በር ላይ ጥላውን ቢያዩት - ድምፁን ቢሰሙት ፤
ምንድን ነው ሚሉት!?
ጨርቁን አጣጥፈው ስንቁን አጥቅሰው
አንገቱን አቅፈው ደረቱን ዳብሰው
ከእንግዲህስ ቻው ያሉትን ፍቅር - ከልብ ቆርጠው የሸኙትን ሰው፤
ድንገት አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ፤
እጅ እግሩን ሰቅሎ - ሀሳቡን ጥሎ ሲስቅ ቢያገኙት፤
ምንድን ነው ሚሉት!?
ይኸው እንግዲህ
ዳግም ብቅ አለ ብቸኝነቴ፤
ቻው ተባብለን ከአንዴም ሁለቴ፤
ለካስ እንደ ልጅ
አዲስ እንግዳ ከቤት ሲመጣ 'ጓዳ ሩጦ እንደሚገባው፤
እንግዳው ሂዶ እስከሚወጣ እያጮለቀ እንደሚያደባው፤
ይህ ብቸኝነት አይሄድም ጥሎ፤
ያደፍጣል እንጅ የሞተ መስሎ፤
By Tewodros kasa
@getem
@getem
@paappii
ደረት ደልቀው ፍም ዕንባ አፍስሰው
ደህና ሁን ብለው የመጡትን ሰው፤
ድንገት በር ላይ ጥላውን ቢያዩት - ድምፁን ቢሰሙት ፤
ምንድን ነው ሚሉት!?
ጨርቁን አጣጥፈው ስንቁን አጥቅሰው
አንገቱን አቅፈው ደረቱን ዳብሰው
ከእንግዲህስ ቻው ያሉትን ፍቅር - ከልብ ቆርጠው የሸኙትን ሰው፤
ድንገት አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ፤
እጅ እግሩን ሰቅሎ - ሀሳቡን ጥሎ ሲስቅ ቢያገኙት፤
ምንድን ነው ሚሉት!?
ይኸው እንግዲህ
ዳግም ብቅ አለ ብቸኝነቴ፤
ቻው ተባብለን ከአንዴም ሁለቴ፤
ለካስ እንደ ልጅ
አዲስ እንግዳ ከቤት ሲመጣ 'ጓዳ ሩጦ እንደሚገባው፤
እንግዳው ሂዶ እስከሚወጣ እያጮለቀ እንደሚያደባው፤
ይህ ብቸኝነት አይሄድም ጥሎ፤
ያደፍጣል እንጅ የሞተ መስሎ፤
By Tewodros kasa
@getem
@getem
@paappii
❤118🔥29👍12😢5😱1
📌 በሀዋሳ ከተማ አዲስ የስነ-ጥበብ ትምህርት ቤት የምዝገባ ጥሪ!
ጥበብን ለሚወዱ እና ተሰጥኦአቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ሁሉ ታላቅ እድል! በሀዋሳ ከተማ ከዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አዲስ የስነ-ጥበብ (ስዕል) ትምህርት ቤት ስራ ሊጀምር ዝግጅቱን አጠናቋል።
🎨 ለምን ይመዘገባሉ?
• በዘርፉ ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች የታገዘ ስልጠና ለማግኘት።
• ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በተቀናጀ መልኩ እውቀትን ለማዳበር።
• የፈጠራ ስራዎትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር።
🌟 የእርስዎ ድርሻ፦
ጥበብ የሀገር መገለጫ ናት! ይህ መልዕክት እንዲደርሳቸው የሚገባቸው ወጣቶች እና ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች እንዲያውቁት በማጋራት (Share በማድረግ) ማህበራዊ ሀላፊነትዎን ይወጡ።
ምዝገባው ተጀምሯል!👇👇 link ይጫኑ
https://tally.so/r/D4Jjrl.
ጥበብን ለሚወዱ እና ተሰጥኦአቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ሁሉ ታላቅ እድል! በሀዋሳ ከተማ ከዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አዲስ የስነ-ጥበብ (ስዕል) ትምህርት ቤት ስራ ሊጀምር ዝግጅቱን አጠናቋል።
🎨 ለምን ይመዘገባሉ?
• በዘርፉ ብቁ በሆኑ ባለሙያዎች የታገዘ ስልጠና ለማግኘት።
• ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በተቀናጀ መልኩ እውቀትን ለማዳበር።
• የፈጠራ ስራዎትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር።
🌟 የእርስዎ ድርሻ፦
ጥበብ የሀገር መገለጫ ናት! ይህ መልዕክት እንዲደርሳቸው የሚገባቸው ወጣቶች እና ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች እንዲያውቁት በማጋራት (Share በማድረግ) ማህበራዊ ሀላፊነትዎን ይወጡ።
ምዝገባው ተጀምሯል!👇👇 link ይጫኑ
https://tally.so/r/D4Jjrl.
Tally Forms
የ ስዕል ትምህርት ቤት በ ሀዋሳ
Made with Tally, the simplest way to create forms.
❤20
ADDIS ABABA — FOR SUDAN
Voices From Sudan
On April 21, join us for a powerful evening where film, music, and community come together to mark the 3rd anniversary of the Sudan war.
The night opens with a special live performance by The Tana Quintet by Hazim Alshafei, bringing the rhythm, soul, and resilience of Sudan to life—followed by a screening of the acclaimed film Khartoum.
✨ Free Entrance
This is more than a screening.
It’s a gathering.
It’s a shared moment.
It’s solidarity in action.
Expect a full house, a powerful atmosphere, and a night that will stay with you.
📅 Tuseday, April 21, 2026
📍 Bata Complex 22, around Golagul
🕠 5:30 PM
Bring your friends. Be present. Stand with Sudan.
#Khartoum #Sudan #AddisAbaba #InDeepCultures #FilmScreening #LiveMusic #1960Films #AddisCinemaClub
Voices From Sudan
On April 21, join us for a powerful evening where film, music, and community come together to mark the 3rd anniversary of the Sudan war.
The night opens with a special live performance by The Tana Quintet by Hazim Alshafei, bringing the rhythm, soul, and resilience of Sudan to life—followed by a screening of the acclaimed film Khartoum.
✨ Free Entrance
This is more than a screening.
It’s a gathering.
It’s a shared moment.
It’s solidarity in action.
Expect a full house, a powerful atmosphere, and a night that will stay with you.
📅 Tuseday, April 21, 2026
📍 Bata Complex 22, around Golagul
🕠 5:30 PM
Bring your friends. Be present. Stand with Sudan.
#Khartoum #Sudan #AddisAbaba #InDeepCultures #FilmScreening #LiveMusic #1960Films #AddisCinemaClub
❤13
.......
ከዛ ከማዶ ጋራ አይቼ ጭላንጭል ፀዳል፣
ለመሄድ ሳስብ ፈጥኜ ሀሳብ ሳነሳ ስጥል፣
የቅርቡን ማየት ተስኖኝ የሩቁን መንገድ ሳማትር፣
ለካ...................
የቤቴን ጽልመት ማርከሻ ኩራዝ ከቤቴ ነበር።
[ ዔደን ታደሰ ]
@topazionnn
@getem
@getem
ከዛ ከማዶ ጋራ አይቼ ጭላንጭል ፀዳል፣
ለመሄድ ሳስብ ፈጥኜ ሀሳብ ሳነሳ ስጥል፣
የቅርቡን ማየት ተስኖኝ የሩቁን መንገድ ሳማትር፣
ለካ...................
የቤቴን ጽልመት ማርከሻ ኩራዝ ከቤቴ ነበር።
[ ዔደን ታደሰ ]
@topazionnn
@getem
@getem
❤66👍18🔥5😢3😁1
የሰዉ ልጅ የሰራዉ
አብረቅራቂ መንገድ
ሳይታክት ይወስዳል
መዉሰዱ ሳይበቃዉ
አዙሮ አዙሮ....
እዛዉ ይመልሳል
እግዜር የፈጠረዉ
የሰዎች ዘመን ግን
አንድቀን ያበቃል
ሳይታሰብ
ያ ል ቃ ል...........
🖊 ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
አብረቅራቂ መንገድ
ሳይታክት ይወስዳል
መዉሰዱ ሳይበቃዉ
አዙሮ አዙሮ....
እዛዉ ይመልሳል
እግዜር የፈጠረዉ
የሰዎች ዘመን ግን
አንድቀን ያበቃል
ሳይታሰብ
ያ ል ቃ ል...........
🖊 ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤67👍16🔥2
ቁር ያቆረፈደዉ ሽብሽቡ ቆዳዬ፤
በእንባ ሞጭሙጮ የደከመው አይኔ፤
በዘመናት ንጉደት ፀጉሬ ቢሸብትም፤
መንጋጋዬ ረግፎ በድዴ ብቀርም፤
ጉልበቴ ተዳክሞ ወገቤ ቢጎብጥም፤
አንተን የሚያልመዉ ልቤ አላረጀም።
ድንገት ባጋጣሚ ልትመጣ ካሰብክ፤
ከበራፉ አለሁ ጥለኸኝ እንደሄድክ።
[ ዔደን ታደሰ ]
@topazionnn
@getem
@getem
በእንባ ሞጭሙጮ የደከመው አይኔ፤
በዘመናት ንጉደት ፀጉሬ ቢሸብትም፤
መንጋጋዬ ረግፎ በድዴ ብቀርም፤
ጉልበቴ ተዳክሞ ወገቤ ቢጎብጥም፤
አንተን የሚያልመዉ ልቤ አላረጀም።
ድንገት ባጋጣሚ ልትመጣ ካሰብክ፤
ከበራፉ አለሁ ጥለኸኝ እንደሄድክ።
[ ዔደን ታደሰ ]
@topazionnn
@getem
@getem
❤57👍7🔥5