፡፡፡፡፡፡50 ፍቅር እና እንቅፋት፡፡፡፡፡፡
ይኼ ክሩ ልቤ ክርነቱን ሸሽቶ
በመውደድሽ ዳብሮ በፍቅርሽ ጎልብቶ
ክር አልሆን ብሎኛል ክርነቱን ረስቶ
እንዲያ ነው ክርነት……
ለወደዱት መርፌ ራስን አሹልኮ
ለተነጠለ ነብስ አንድነትን ሰብኮ
ዘምዝሞ መስፋት ነው
የሚል ስብከት ሰማው
መርፌ ሆነሽ ባይሽ ክሩን ሆኜ መጣው
ግን ደግሞ አለሜ…
ክር እና መርፌውን የሚነጣጥሉ
ዘምዛሚዎች በዝተው
ሴራ ቢበዛብን
ወስፌ ልሁን ስትይ ጅማት ሆኜ መጣው
ይኸው ሌላ ሴራ….
ጫማቸው ሲቀደድ ማሰፋቱን ትተው
መጣል የመረጡ ተራማጆች በዝተው
መተያየት ጠማን
ላይደርሱ ሲጓዙ ጫማቸውን ቀደው
እናም እልሻለው……
ግንድ እንኳ ብትሆኚ ሲባጎውን ሆኜ
እኚህ ነፍሶቻችን አንለያይ ቢሉ
አትጠራጠሪ
ባልጠፋ መሞቻ ራስን ለመስቅል እኛን ይመርጣሉ፡፡
2008 አ.አ
#Beruk_korsawi
@getem
@getem
ይኼ ክሩ ልቤ ክርነቱን ሸሽቶ
በመውደድሽ ዳብሮ በፍቅርሽ ጎልብቶ
ክር አልሆን ብሎኛል ክርነቱን ረስቶ
እንዲያ ነው ክርነት……
ለወደዱት መርፌ ራስን አሹልኮ
ለተነጠለ ነብስ አንድነትን ሰብኮ
ዘምዝሞ መስፋት ነው
የሚል ስብከት ሰማው
መርፌ ሆነሽ ባይሽ ክሩን ሆኜ መጣው
ግን ደግሞ አለሜ…
ክር እና መርፌውን የሚነጣጥሉ
ዘምዛሚዎች በዝተው
ሴራ ቢበዛብን
ወስፌ ልሁን ስትይ ጅማት ሆኜ መጣው
ይኸው ሌላ ሴራ….
ጫማቸው ሲቀደድ ማሰፋቱን ትተው
መጣል የመረጡ ተራማጆች በዝተው
መተያየት ጠማን
ላይደርሱ ሲጓዙ ጫማቸውን ቀደው
እናም እልሻለው……
ግንድ እንኳ ብትሆኚ ሲባጎውን ሆኜ
እኚህ ነፍሶቻችን አንለያይ ቢሉ
አትጠራጠሪ
ባልጠፋ መሞቻ ራስን ለመስቅል እኛን ይመርጣሉ፡፡
2008 አ.አ
#Beruk_korsawi
@getem
@getem
።።።።። ዋ! ።።።።።
አይኔ ወደደሽ ስልሽ፣
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት
ምኞትሽ ሰመረ
አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው አንደዘበት።
ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ አይን ዛሬም አይሻለው።
ደሞ አንደዚ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሽና።
በረከት በላይነህ
@getem
@getem
@gebriel_19
አይኔ ወደደሽ ስልሽ፣
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት
ምኞትሽ ሰመረ
አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው አንደዘበት።
ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ አይን ዛሬም አይሻለው።
ደሞ አንደዚ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሽና።
በረከት በላይነህ
@getem
@getem
@gebriel_19
❤1
#ስንት_አለ!
ስንት አለ መሠለህ,,,,,
በዓለምህ የግራ ጎን
የግራ እቅፍ ተወሽቆ~ የነገር ጭራ 'ሚሰነጥቅ
ለውድቀቱ ልል መሠላል
ቋሚ አግዳሚ ደርድሮ~ የምፅዓት ቀን 'ሚጠብቅ
ሆዱን ት'ቢት ያሳበጠው
የነገር ዕቃ 'ጭንቄ' አልቦ~ የአ'ምሮ ብል የበላው
የቀና አስተሳሰብ ፀር
የጥላቻ ግንብ አናፂ~ ትህትና የራቀው
ስንት አለ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
የፊደል ልምሻ ተጠቂ
ወፍ ዘራሽ ወሬ ሰባቂ~ የፌስቡክ ላይ አለቃ
በኔነት ውጋት ተወግቶ
እኛነት የሚናፈቀው~ ውሃ 'ማይቋጥር ጭቃ
ከሻገተው ፖለቲካ ስር
እግር እግር እያለ~ ከስር ከስር የማይጠፋ
በጠፋ ማንነቱ ውስጥ
ራሱ ራሱን ደብቆ~ ራሱን ሊያገኝ 'ሚለፋ።
ደግሞ በሌላ ጎን,,,,,,,,,,,,,,,,
በጥቂቶች የጭካኔ ስም
በሆድ አደር ታላቅ ወንድሙ~ ስሙ የተሰበረ
በጥጋባቸው የጫማ ሶል
በግፍ እየተረገጠ~ አጥንቶቹን የቆጠረ
ከወንድሞቹ እንዳይውል
እገዳ የተጣለበት~ ከሁለት ያጣ ጎመን
ከወዲህ ጡጫ አደካክሞት
ከወዲያ የምላስ ጦር~ ያሻከረበት ልቡን
ያንዲት ኢትዮጵያ ናፋቂ
የሀገር ትንሳዔ ወዳጅ~ የውደቀቷ ታማሚ
ልበ ሙሉ ልብ አልባ
በረሃቧ ተጎድቶ~ በልማቷ ታካሚ
የቁርጥ ቀን አለኝታዋ
የቁም እስር ታስሮላት~ አንበጣ ልቡ ከሞላ
ህይወቴ ውሉ ጠፋባት
የኔነት ስሜቱ ገንኖ~ ያ'ብሮነት ክሩ ከላላ።
@SemenehamareTops
@getem
@getem
@getem
ስንት አለ መሠለህ,,,,,
በዓለምህ የግራ ጎን
የግራ እቅፍ ተወሽቆ~ የነገር ጭራ 'ሚሰነጥቅ
ለውድቀቱ ልል መሠላል
ቋሚ አግዳሚ ደርድሮ~ የምፅዓት ቀን 'ሚጠብቅ
ሆዱን ት'ቢት ያሳበጠው
የነገር ዕቃ 'ጭንቄ' አልቦ~ የአ'ምሮ ብል የበላው
የቀና አስተሳሰብ ፀር
የጥላቻ ግንብ አናፂ~ ትህትና የራቀው
ስንት አለ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
የፊደል ልምሻ ተጠቂ
ወፍ ዘራሽ ወሬ ሰባቂ~ የፌስቡክ ላይ አለቃ
በኔነት ውጋት ተወግቶ
እኛነት የሚናፈቀው~ ውሃ 'ማይቋጥር ጭቃ
ከሻገተው ፖለቲካ ስር
እግር እግር እያለ~ ከስር ከስር የማይጠፋ
በጠፋ ማንነቱ ውስጥ
ራሱ ራሱን ደብቆ~ ራሱን ሊያገኝ 'ሚለፋ።
ደግሞ በሌላ ጎን,,,,,,,,,,,,,,,,
በጥቂቶች የጭካኔ ስም
በሆድ አደር ታላቅ ወንድሙ~ ስሙ የተሰበረ
በጥጋባቸው የጫማ ሶል
በግፍ እየተረገጠ~ አጥንቶቹን የቆጠረ
ከወንድሞቹ እንዳይውል
እገዳ የተጣለበት~ ከሁለት ያጣ ጎመን
ከወዲህ ጡጫ አደካክሞት
ከወዲያ የምላስ ጦር~ ያሻከረበት ልቡን
ያንዲት ኢትዮጵያ ናፋቂ
የሀገር ትንሳዔ ወዳጅ~ የውደቀቷ ታማሚ
ልበ ሙሉ ልብ አልባ
በረሃቧ ተጎድቶ~ በልማቷ ታካሚ
የቁርጥ ቀን አለኝታዋ
የቁም እስር ታስሮላት~ አንበጣ ልቡ ከሞላ
ህይወቴ ውሉ ጠፋባት
የኔነት ስሜቱ ገንኖ~ ያ'ብሮነት ክሩ ከላላ።
@SemenehamareTops
@getem
@getem
@getem
#ሀገርሽ....#ሀገሬ
፨፨፨፨
፨፨፨
፨፨
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
ትርጉም የሰጠሽው ፥ ለብኩን መኖሬ
ሀገሬ ነሽ !! አንቺ ፥ ያድማስ መነፅሬ
ከማይሰማ ግዑዝ ፥ በዘመድ ፍለጋ ፥ እራሴን አጥሬ
ጋራ ሸንተረሩን...
ከምንጅላቴ እኩል ፥ አላውቅም ቆጥሬ ።
#አየሽ !!
በልኬ ተፈጥሮ ፥ በደም የታሰረ
ወግ ፣ ልማድ ፣ አብሮነት
ችግር ፣ ከደስታ ፥ አብሮኝ የቆጠረ
#ሀገር_ለኔ_ሰው_ነው_!!
በውስን ቦታ ላይ ፥ በጋራ ማንነት ፥ ለዝንት የሰፈረ ።
እንጂማ....
ሀገርሽ .....ሀገሬ
ጫካው እና ዱሩ
የሚፈሰው ጅረት ፥ ሳር የሞላ ምድሩ
እያለ ሚዘፍን ፥ ማማለል አስቦ
እንስሳ ነው ውዴ
ሳር እንጋጥ ብሎ ፥ የሚወጣው ደቦ።
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
@getem
፨፨፨፨
፨፨፨
፨፨
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
ትርጉም የሰጠሽው ፥ ለብኩን መኖሬ
ሀገሬ ነሽ !! አንቺ ፥ ያድማስ መነፅሬ
ከማይሰማ ግዑዝ ፥ በዘመድ ፍለጋ ፥ እራሴን አጥሬ
ጋራ ሸንተረሩን...
ከምንጅላቴ እኩል ፥ አላውቅም ቆጥሬ ።
#አየሽ !!
በልኬ ተፈጥሮ ፥ በደም የታሰረ
ወግ ፣ ልማድ ፣ አብሮነት
ችግር ፣ ከደስታ ፥ አብሮኝ የቆጠረ
#ሀገር_ለኔ_ሰው_ነው_!!
በውስን ቦታ ላይ ፥ በጋራ ማንነት ፥ ለዝንት የሰፈረ ።
እንጂማ....
ሀገርሽ .....ሀገሬ
ጫካው እና ዱሩ
የሚፈሰው ጅረት ፥ ሳር የሞላ ምድሩ
እያለ ሚዘፍን ፥ ማማለል አስቦ
እንስሳ ነው ውዴ
ሳር እንጋጥ ብሎ ፥ የሚወጣው ደቦ።
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
@getem
ዜና የገለፀው ህልፈት!?
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።
ህልሜ ላይ ተኝቼ ፥ አንድ ቀስቃሽ ሳጣ
ውል ፍቺው ተስቶኝ ፥ ከቀረሁ በሌጣ
ህላዌዬ ላንዱ...
እርኩስ መንፈስ ሆኖ ፥ አበሳን ካመጣ
ሞት ማለት ይሄ ነው ፥ የህይወት ቆረጣ።
ስሚኝ እታለሜ!
አለሁ ለማለቱ ፥ ቆሞ ለመሄዱ
ዘርን ለመተካት ፥ ልጅን ለመውለዱ
ለአንድ ራስ ለመኖር ፥ እህል ለመቅመሱ
ዝግ ብሎ ለመጓዝ ፥ ለመለሳለሱ
ለጥሉ ለውጊያው ፥ ፍቅር ለመንሳቱ
ለአንዲት ጭብጥ መና ፥ ለመቀራመቱ
ለግፊያ ለጡጫው ፥ ለመሙላት በመንገድ
ለስሪያ ለሴሱ ፥ ከእንስት ለመላመድ
ለዚህ ለዚህ ላለው የተፈጥሮ እውነት
ሰው መሆን ባላሻ ከእንስሳ መለየት !
አዎን!
ለቅኔዋ ህይወት ...
ህብረ ቃል መስጥሬ ወርቁን ሳላወጣ
በትንፋሼ ወበቅ ...
ዉርጩ ላየለበት ...ለተገፋ ነዳይ ሙቀት ሳላመጣ
በጉብዝና ወሬ ፥ እየተናነስኩኝ ፥ ሳልቆም ለምስጋና
ጥላቻ አዝሞት ...
ላዘነበለ ዳስ ፍቅር ማገር ሆኖኝ ጎጆ ሳላቀና
ሚስማር እያቀበልሁ ፥ ለመሲህ ስቅላት
መልካሙን ሳልዘራ በፀሎት በሶላት
ህልሜን ሳልፈታ ፥ በቀናቴ ንጋት
በስንፍና ገበር ፥ ስጋዬን ለብጬ
ለምስር ወጥ አምሮት ፥ ብኩርና ሽጬ
ቀልቤን እየነሳሁ ለሰላሳ ዲናር
አቅሌን እየሳትሁኝ በእስክስታ በስካር
ንግስናዬን ሽሬ ፥ ከአዳም ተናንሼ
ኖሬያለሁ አልልም ፥
የዝምታው ዳኛን፥ መልኩን በመውረሴ።
አዎን !
ይኸው ባንቺ ዘመን ...
ሰው መሆን ተስኖን ፥ የሰው ስጋ ወርሰን ፥ ሳንኖር እንደሰው
ሞተዋል ሲሉን ነው ፥ አልሞትንም እያልን ፥ መግለጫ ምንሰጠው ።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።
ህልሜ ላይ ተኝቼ ፥ አንድ ቀስቃሽ ሳጣ
ውል ፍቺው ተስቶኝ ፥ ከቀረሁ በሌጣ
ህላዌዬ ላንዱ...
እርኩስ መንፈስ ሆኖ ፥ አበሳን ካመጣ
ሞት ማለት ይሄ ነው ፥ የህይወት ቆረጣ።
ስሚኝ እታለሜ!
አለሁ ለማለቱ ፥ ቆሞ ለመሄዱ
ዘርን ለመተካት ፥ ልጅን ለመውለዱ
ለአንድ ራስ ለመኖር ፥ እህል ለመቅመሱ
ዝግ ብሎ ለመጓዝ ፥ ለመለሳለሱ
ለጥሉ ለውጊያው ፥ ፍቅር ለመንሳቱ
ለአንዲት ጭብጥ መና ፥ ለመቀራመቱ
ለግፊያ ለጡጫው ፥ ለመሙላት በመንገድ
ለስሪያ ለሴሱ ፥ ከእንስት ለመላመድ
ለዚህ ለዚህ ላለው የተፈጥሮ እውነት
ሰው መሆን ባላሻ ከእንስሳ መለየት !
አዎን!
ለቅኔዋ ህይወት ...
ህብረ ቃል መስጥሬ ወርቁን ሳላወጣ
በትንፋሼ ወበቅ ...
ዉርጩ ላየለበት ...ለተገፋ ነዳይ ሙቀት ሳላመጣ
በጉብዝና ወሬ ፥ እየተናነስኩኝ ፥ ሳልቆም ለምስጋና
ጥላቻ አዝሞት ...
ላዘነበለ ዳስ ፍቅር ማገር ሆኖኝ ጎጆ ሳላቀና
ሚስማር እያቀበልሁ ፥ ለመሲህ ስቅላት
መልካሙን ሳልዘራ በፀሎት በሶላት
ህልሜን ሳልፈታ ፥ በቀናቴ ንጋት
በስንፍና ገበር ፥ ስጋዬን ለብጬ
ለምስር ወጥ አምሮት ፥ ብኩርና ሽጬ
ቀልቤን እየነሳሁ ለሰላሳ ዲናር
አቅሌን እየሳትሁኝ በእስክስታ በስካር
ንግስናዬን ሽሬ ፥ ከአዳም ተናንሼ
ኖሬያለሁ አልልም ፥
የዝምታው ዳኛን፥ መልኩን በመውረሴ።
አዎን !
ይኸው ባንቺ ዘመን ...
ሰው መሆን ተስኖን ፥ የሰው ስጋ ወርሰን ፥ ሳንኖር እንደሰው
ሞተዋል ሲሉን ነው ፥ አልሞትንም እያልን ፥ መግለጫ ምንሰጠው ።
@getem
@getem
@getem
ለሰንበታችን!
💚
የሁለቱን ገናኖች እና ግዙፋን ሰዎቻችንን "ትዝታዎች" በጠዋቱ ተጋበዙልኝ።
- የሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን "ትዝታ" ሥዕል እና
- የሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህንን "ትዝታ" የተሰኘውን ውብ ግጥሙን ከ"እሳት ወይ አበባ"
መድብሉ ገፅ 99 ላይ ያገኘሁትን እነሆ !
* * *
ትዝታ
-------
ዓይንህን በዓይኔ ፀንሼ፣ የቀስቱን ጮራ እንደ ቋጠርኩ
ሌሊት በህልሜ አማምጨህ፣ ሕመምህን እየፈጠርኩ
ቀን ጥላህን እንደለበስኩ
የፍቅራችንን ነበልባል፣ በቁም ሰመመን እንዳቀፍኩ
ልብ ውስጥ እንዳዜሙት ሙሾ፣ የሲቃ ስልት እንዳቃጨልኩ
የነፍሴን የእሳት ዘለላ፣ ጎዳናህ ላይ እንዳነጠብኩ
እንደ ገደል ዳር ቄጤማ፣ የስጋት እንባ እንደ ቃተትኩ
ሕይወቴን ላንተ እንዳሸለብኩ
ሕልምህን በጄ እንደ ዳሰስኩ
ያን የመጀመሪያ ሞቴን፣ በመሸ ቁጥር እንደ ሞትኩ
አለሁ፣ እንደ ብኩን መረብ፣ ትዝታህን እንዳጠመድኩ።
----------------------------
፲፱፻፶፱ - ገርበ ጉራቻ
መልካም ሰንበት!💚
@getem
@getem
@Nagayta
💚
የሁለቱን ገናኖች እና ግዙፋን ሰዎቻችንን "ትዝታዎች" በጠዋቱ ተጋበዙልኝ።
- የሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን "ትዝታ" ሥዕል እና
- የሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህንን "ትዝታ" የተሰኘውን ውብ ግጥሙን ከ"እሳት ወይ አበባ"
መድብሉ ገፅ 99 ላይ ያገኘሁትን እነሆ !
* * *
ትዝታ
-------
ዓይንህን በዓይኔ ፀንሼ፣ የቀስቱን ጮራ እንደ ቋጠርኩ
ሌሊት በህልሜ አማምጨህ፣ ሕመምህን እየፈጠርኩ
ቀን ጥላህን እንደለበስኩ
የፍቅራችንን ነበልባል፣ በቁም ሰመመን እንዳቀፍኩ
ልብ ውስጥ እንዳዜሙት ሙሾ፣ የሲቃ ስልት እንዳቃጨልኩ
የነፍሴን የእሳት ዘለላ፣ ጎዳናህ ላይ እንዳነጠብኩ
እንደ ገደል ዳር ቄጤማ፣ የስጋት እንባ እንደ ቃተትኩ
ሕይወቴን ላንተ እንዳሸለብኩ
ሕልምህን በጄ እንደ ዳሰስኩ
ያን የመጀመሪያ ሞቴን፣ በመሸ ቁጥር እንደ ሞትኩ
አለሁ፣ እንደ ብኩን መረብ፣ ትዝታህን እንዳጠመድኩ።
----------------------------
፲፱፻፶፱ - ገርበ ጉራቻ
መልካም ሰንበት!💚
@getem
@getem
@Nagayta
የፃፍኩልሽን ደብዳቤ አታንብቢው!
(ልዑል ኃይሌ)
ሞኝ ነው ወረቀት
የፃፉለትን ቃል ያምናል ተቀብሎ፤
አልወዳትም የሚል
ፅሁፍ ሰፈረበት የኔን እውነት ጥሎ፤
ከንዴት ስነቃ
ወረቀት የያዘው ረገምኩት ያንን ቃል፤
መውደዴ እንዴት ጠፋው
በብጣሽ ወረቀት እንዴት ፍቅር ያልቃል?፤
.
ይህን የውሸት ቃል
የውሸት ደብዳቤ ጨምድጄ እንዳልቀደው፤
እንዲሠጥሽ ብዬ
አዘጋጅቼለት ፖስተኛ ወሠደው፤
ግን ደግሞ ፈራሁኝ
በዚህ ቅፅበት ምክንያት አንቺን እንዳላጣ፤
የፍርዴን ደብዳቤ
የሚሽርልኝን ቅፅበት ከየት ላምጣ?፤
.
ሌላ ደብዳቤ ፃፍኩ!..
ይድረስ ለማልወድሽ
ለማትናፍቂኝ ሴት ለማልፈልግሽ ሠው፤
ከሃዲ ነች ብልም
ሰሚ ስለማጣ ዓለሙ ይቅመሠው፤
ሂጂለት ሕዝበ-አዳም
ምን ተዳዬ 'ኔ ብቻ ለምን 'ታመማለሁ፤
ማመን የፈለገ ይምጣና ይጎብኘኝ
ስታርጂኝ የቀረ ጠባሳ ይዣለሁ፤
ካመንሺም እመኚ
ካላመንሺም ይቅር፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
የዕቃቃ ጨዋታ የማስመሠል ፍቅር፤
.
ደገምኩት!ያንን ቃል
የላዩን መልዕክቴን የፊቱን ደብዳቤ፤
ሞኝ ነው ወረቀት
ምንም አልገባውም
ባሠፈርኩበት ቃል እንዲያ መንገብገቤ፤
.
ደግሜ መከርኩት
'አትመልከትብኝ የልቤን ስብራት'፤
ይልቅ እንዳልታመምኩ አስመስለህ ጥራት፤
ብዬ ብገስፀው
እያስተሳሰረ ከልቤ ሕመም ጋራ፤
እውነቴን መሸፈን
ክህደቴን መሸፈን ወረቀቴ ፈራ፤
.
እውነት ነው!
.
ሞኝ ነው ሞኝ ነው
ሞኝ ነው ወረቀት፤
እንዴት ብሎ አመነኝ
ባሰፈርኩበት ልክ በፃፍኩበት ርቀት፤
.
(ቲሽ!...ቀደድኩት!..)
.
(በቃ ትቼዋለሁ)
ለማስፈር ከበደኝ
ለዛኛው ደብዳቤ ማስተባበያ ቃል፤
ባስተባብለውም
የብዕሬ ቀለም ከልቤ እውነት ርቋል፤
.
ደጋግመሽ ብትጥይኝ
ያላንቺ ማትወጣ ጀምበር ታቅፌያለሁ፤
ይሄንን እያወቅኩ
አልወድሽም ብዬ እንዴት እፅፋለሁ?፤
ስለዚህ ሲደርስሽ
"ወረቀት ሞኝ ነው" የሚል ቃል አስታውሺ፤
ሞኝ አያጣላንም
ቀዳድደሽ ጣዪና ደግመሽ ተመለሺ፤
ታኅሳስ 5,2012 ዓ.ም.
@getem
@getem
@getem
(ልዑል ኃይሌ)
ሞኝ ነው ወረቀት
የፃፉለትን ቃል ያምናል ተቀብሎ፤
አልወዳትም የሚል
ፅሁፍ ሰፈረበት የኔን እውነት ጥሎ፤
ከንዴት ስነቃ
ወረቀት የያዘው ረገምኩት ያንን ቃል፤
መውደዴ እንዴት ጠፋው
በብጣሽ ወረቀት እንዴት ፍቅር ያልቃል?፤
.
ይህን የውሸት ቃል
የውሸት ደብዳቤ ጨምድጄ እንዳልቀደው፤
እንዲሠጥሽ ብዬ
አዘጋጅቼለት ፖስተኛ ወሠደው፤
ግን ደግሞ ፈራሁኝ
በዚህ ቅፅበት ምክንያት አንቺን እንዳላጣ፤
የፍርዴን ደብዳቤ
የሚሽርልኝን ቅፅበት ከየት ላምጣ?፤
.
ሌላ ደብዳቤ ፃፍኩ!..
ይድረስ ለማልወድሽ
ለማትናፍቂኝ ሴት ለማልፈልግሽ ሠው፤
ከሃዲ ነች ብልም
ሰሚ ስለማጣ ዓለሙ ይቅመሠው፤
ሂጂለት ሕዝበ-አዳም
ምን ተዳዬ 'ኔ ብቻ ለምን 'ታመማለሁ፤
ማመን የፈለገ ይምጣና ይጎብኘኝ
ስታርጂኝ የቀረ ጠባሳ ይዣለሁ፤
ካመንሺም እመኚ
ካላመንሺም ይቅር፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
የዕቃቃ ጨዋታ የማስመሠል ፍቅር፤
.
ደገምኩት!ያንን ቃል
የላዩን መልዕክቴን የፊቱን ደብዳቤ፤
ሞኝ ነው ወረቀት
ምንም አልገባውም
ባሠፈርኩበት ቃል እንዲያ መንገብገቤ፤
.
ደግሜ መከርኩት
'አትመልከትብኝ የልቤን ስብራት'፤
ይልቅ እንዳልታመምኩ አስመስለህ ጥራት፤
ብዬ ብገስፀው
እያስተሳሰረ ከልቤ ሕመም ጋራ፤
እውነቴን መሸፈን
ክህደቴን መሸፈን ወረቀቴ ፈራ፤
.
እውነት ነው!
.
ሞኝ ነው ሞኝ ነው
ሞኝ ነው ወረቀት፤
እንዴት ብሎ አመነኝ
ባሰፈርኩበት ልክ በፃፍኩበት ርቀት፤
.
(ቲሽ!...ቀደድኩት!..)
.
(በቃ ትቼዋለሁ)
ለማስፈር ከበደኝ
ለዛኛው ደብዳቤ ማስተባበያ ቃል፤
ባስተባብለውም
የብዕሬ ቀለም ከልቤ እውነት ርቋል፤
.
ደጋግመሽ ብትጥይኝ
ያላንቺ ማትወጣ ጀምበር ታቅፌያለሁ፤
ይሄንን እያወቅኩ
አልወድሽም ብዬ እንዴት እፅፋለሁ?፤
ስለዚህ ሲደርስሽ
"ወረቀት ሞኝ ነው" የሚል ቃል አስታውሺ፤
ሞኝ አያጣላንም
ቀዳድደሽ ጣዪና ደግመሽ ተመለሺ፤
ታኅሳስ 5,2012 ዓ.ም.
@getem
@getem
@getem
👍1
ለውብ ቀን!
💚
#ትላንት በዚሁ በቻናላችን ቤተሰቦች የተዘጋጀ Hiking ተዘጋጅቶ ነበር ወዴት..? ካላቹኝ ሰሜን ሸዋ ከደብረብርሃን ወደ ደብረ ሲና በሚወስደው መንገድ የሚኒሊክ መስኮት የምትባል እጅግ እጅግ ውብ ቦታ እዚህ ቻናል ላይ ካሉት ቤተሰቦችና ሌሎች ሆንን ባልሳሳት 125 እንሆናለን ረጅምና ፈታኝ የእግር ጉዞ አድርገን ነበር በጣም የሚገርመው ልክ ቦታው ላይ ስትደርሱ ግን ያን ሁሉ ድካማቹን የሚያስረሳ ተአምር ታያላቹ ...ሀሴት ታደርጋላቹ ፣ ትፈነጥዛላቹ ብቻ የላያቹት ሂዱ ና እዩት እውነት ትወዱታላችሁ !
ትላትና ይሄንን ጉዞ አድርጌ ወደ ቤቴ ከመሸ ስመለስ አንዱ ወዳጅ ምን አለኝ አንተው መፈንጠዝ አበዛህሳ ቢለይኝ ጊዜ......የጫሌው ሼይኽ(ረዐ) ያሉትን ትዝ ቢለኝ ላኩለትና ረፍት ወሰድኩኝ....
*
*
*
እኔ ያየሁትን አይተኸው በነበር
አዳልቀኝ ሳልልህ ታዳልቀኝ ነበር
እንኳን ልለምንህ ትለምነኝ ነበር
ድምቅምቅ ያለ ሳምንት ይሁንልን !💚
@getem
@sunsethiking
@Nagayta
💚
#ትላንት በዚሁ በቻናላችን ቤተሰቦች የተዘጋጀ Hiking ተዘጋጅቶ ነበር ወዴት..? ካላቹኝ ሰሜን ሸዋ ከደብረብርሃን ወደ ደብረ ሲና በሚወስደው መንገድ የሚኒሊክ መስኮት የምትባል እጅግ እጅግ ውብ ቦታ እዚህ ቻናል ላይ ካሉት ቤተሰቦችና ሌሎች ሆንን ባልሳሳት 125 እንሆናለን ረጅምና ፈታኝ የእግር ጉዞ አድርገን ነበር በጣም የሚገርመው ልክ ቦታው ላይ ስትደርሱ ግን ያን ሁሉ ድካማቹን የሚያስረሳ ተአምር ታያላቹ ...ሀሴት ታደርጋላቹ ፣ ትፈነጥዛላቹ ብቻ የላያቹት ሂዱ ና እዩት እውነት ትወዱታላችሁ !
ትላትና ይሄንን ጉዞ አድርጌ ወደ ቤቴ ከመሸ ስመለስ አንዱ ወዳጅ ምን አለኝ አንተው መፈንጠዝ አበዛህሳ ቢለይኝ ጊዜ......የጫሌው ሼይኽ(ረዐ) ያሉትን ትዝ ቢለኝ ላኩለትና ረፍት ወሰድኩኝ....
*
*
*
እኔ ያየሁትን አይተኸው በነበር
አዳልቀኝ ሳልልህ ታዳልቀኝ ነበር
እንኳን ልለምንህ ትለምነኝ ነበር
ድምቅምቅ ያለ ሳምንት ይሁንልን !💚
@getem
@sunsethiking
@Nagayta