ግጥም ብቻ 📘
69.7K subscribers
1.51K photos
31 videos
61 files
166 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
Digital art exhibition

“Longing for the Unknown”! 🌌
Artist Fanuel Leul


Fendika Cultural Center
Opening on July 1st at 6 PM and running until July 15th.

@seiloch
ተጋፈጥኩ መከራዬን
ተፋላምኩ ፈተናዬን
ኃይሌን ጨረስኩ እንጂ መች አገኙሁ ውጤት
እኔ አለቅኩ እንጂ መች በቃሁ ለስኬት
ሩጫዬን ገታሁ አቆምኩ ትግሌን ላፍታ
ቃኘሁ ድክመቴን የሽንፈቴን ቃታ
ለካ
ብቻዬን ነው ምጓዝ እርቃኔን ወጥቼ
መከታ ጋሻዬን ረዳቴን ትቼ
ለካ
ውልክፍክፍ ስንኩልኩል ነበር አሯሯጤ
እውር ድንብር ነበር ሚወነጨፍ ውስጤ
ለካ
በዜሮ ተባዝቷል ሙከራ ጥረቴ
አንቺን ሳልይዝ ሂጄ ድንግል እመቤቴ

አፈገፈግኩ ወደ ኋላ
ተመለስኩ ወደ ቀልቤ
ሰአሊ ለነ እያልኩ ታጠቅኩሽ በልቤ

ይኸው ነጻ ጥርጊያው
ይኸው ቀና መንገዱ
ገና ሳልጠጋው
ሲያዘቀዝቅ አየሁ  የመከራ ቀንዱ

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
ሌላኛው ሊስት ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ ምርጥ 5 ውስጥ ያለ የክሪፕቶ ቢዝነስ ነው።

እድሎን ይሞክሩ!
https://t.me/tapswap_mirror_2_bot?start=r_454803628 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
ገጣሚ ታሮስ ዓለሙ

@getem
@getem
ይድረስልኝ ላንቺ ✍️በዔደን_ታደሰ
<unknown>
ይድረስልኝ ላንቺ.........
ገጣሚ እና አንባቢ ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
ቆንጆ የዕጅ ፅሁፍና የሀረግ አሰራር ለመማር ይሄን ገፅ ይመልከቱት!

https://youtube.com/@thelotrscribe?si=lzP8Ex6WV4W9OdHv
የተዘለለ የታሪክ ገጽ
(በእውቀቱ ስዩም)

ግዙፉ ጎልያድ፥ ያህዛብ ጀግና
-አስገመገመ
ዳዊትም ሰምቶ ፥ጎንበሰ አለና
-ጠጠር ለቀመ፤

እናም በእለቱ
ገበጣው ቀርቦ፤ ገጥመው ሁለቱ
ከግድግዳው ላይ፥ ሳይወርድ ወንጭፉ
ከየሰገባው፥ ሳይወጣ ሰይፉ
ተሸናነፉ;;


የቆፈሩትን፥ ጉድጓዱን ደፍነው
የገበጣውን ፥ጠጠር በትነው
ያወጁት አዋጅ ፥ አንድ ላይ ሆነው፥
ይሄ ነው ቃሉ ፦

“ የተከተልኸኝ ሰራዊት ሁሉ
ዋንጫህን አንሳ ፤ጦር ጋሻህን ጣል
የትኛው ሀገር
የትኛው ሀሳብ
ከህይወት በልጦ አንገት ያሰጣል?

@getem
@getem
@paappii
የሃሳብ መዲና የቀናቶች ወጉ
ማታ በእንቅልፍ ሰበብ ሸለብ ከማድረጉ
        ብቅ እልም...ብቅ እልም
       እውን አይሏት ወይ ህልም
   ዳበስ...ጨበጥ....ፈገግ...እቅፍ
               አይ እንቅልፍ
ታተራምሳለች ያረጋጋሁትን የቀልቤን ቀልበ ህግ
    ከተኛው በድኔ ምንድንነው ምትፈልግ
እየደጋገመች ሱስ ሆናብኝ ስትቀር በሌት ተ ሌት ድምር
መንቃቴን አቆምኩኝ ፈንጂ ቢፈነዳም ቢወርድብኝ ክምር
ትላንት ሆነ ዛሬ...
በህልም አያታለሁ እስኪበቃት ድረስ አይኗን እስክትሰብረው
በስመአብ.....እንዴት ነው ምታምረው።


ዮኒ
     ኣታን  @Yonatozz

@getem
@getem
@getem
/ስምኝማ እኔም ናፍቀሽኛል!/
እረፍት ባጣም እንኳን ካንቺ ሚያገናኘኝ
በቀናቶች መሀል ላንቺ ቀኖች አሉኝ፤
እመኚኝ የኔ ውድ አይጠፋም ለኛ ቀን
በአንድ አገናኝቶ በፍቅር ሚያዋድቀን፤
ናፍቆት አይሎብን ቢረዝም መገናኛችን
እውነት አንድ ቀን አለ የብቻ የሁለታችን፤
ሰመመን ነው ናፍቆት ከሃሳብ ይከታል
አይሎም ሲበረታ ለራስ ይታክታል፤
እናማ በመናፈቅ ብዛት ሳልታክት ደክሜ
በቅርቡ አይሻለው ሳይበረታ እመሜ
😍😍😍
# M.G


@getem
@getem
Forwarded from ሥዕል ብቻ © (Leul M.)
Exhibition titled, “መልክ”
By Surafel Alemneh

Artawi Gallery
opened for public.

The galley opened  until 20 July 2024 starting from 2 PM - 6 PM bole, around British international school or 250m in from Yod Abyssinia, Kkare Homes, 2nd Floor


@seiloch
...
ይሆንልሽ እንደሁ እንደሰርፍ
ቦታን አጥፎ ማንጠፍ
ጨረቃ ድንቡል ቦቃ
ከሰማይ ሳይሆን ከኩሬ ስትወጣ
ማየት እንቻል ፤
ልጅ ነፍሰ ጡር ሲያይ እንደሚለው
« በጣም ጠግባለች ማለት ነው »
እንባባል?
ልጅ አይነ ስውር ሲያይ እንደሚለው
« ዐይኑን በዱላ የሚፈልግ ሰው »
እንባባል?
ትችይ እንደሆነ ጊዜን ታግሎ መጣል
ትችይ እንደሆነ ልጅነትን መቻል
ነይ በጉሎ ጥላ ፥ ቼ! በጉቶ ፈረስ
ከኋላዬ ሁኚ ፣ ወደፊት እንድረስ
.....

መዘክር ግርማ

@getem
@getem
@paappii
አንጋፋው ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል። ነቢይ ተርጓሚ ፣ ገጣሚ ወግ አዋቂ የጥበብ ሰው ነበር🥀


በሰላም እረፍ ጋሽ ነብይ መኮንን

@getem
ግጥምም ዝም አለ። ጨዋታም ዝም አለ።
ሰው መውደድ ዝም አል። ትሕትና ዝም አለ።
ነቢይ ያልነው ዋርካ፥ በአገሩ የት አለ !!

ነፍስ ሄር ጋሼ ! በደግ እረፍ!

#ሰይፉ_ወርቁ

@getem
ገጣሚ ተሰፋሁን ከበደ እንዲህ ጋሸ ነብይን ተሰናብቷል!

ጋሽ ነባ ሳቅና ጨዋታህ ይናፍቀኛል
በብዙ ደግፈኸኛልና ስንብትህ ያጎድለኛል
አባቴም ጏደኛዬም መምህሬም ነህና እስከዘላለም በነፍሴ እድሜ ልክ እወድኻለሁ! አከብርኻለሁ!
መሰናበት እንኳን አልቻልኩም!
መልካም እረፍት
Rest in peace😢 farewell my friend
🙏😭🙏

እስረኛውና የሰጠመችው ፀሀይ
(ነቢይ መኮንን)

እድሜዬን በሙሉ
በአፌ ፈረስ ልጓም
እጄ ላይ ሰንሰለት
             ሲያኖሩ ስላየች
ፀሃይ ሰማይ በቅቷት
         ውሃ ሰጥማ ሞተች

ውሃ ውስጥ ተኝታ
ከኔ ትዋሳለች፣ ይኸው ብርሃን አጥታ።


@getem
ትንሽ ቦታ
....................
በዚህ ዓመት፣
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ትንሽ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ብቻ መሠደጃ።
ምናለበት፣
ለምን አልባት ብንተውለት?
ፍፁም መሆን ስለማንችል
ትንሽ ባዶ እንዋዋል፣በልባችን ደግ በኩል።
ለአንጎላችን መላወሻ
ትንሽ ቦታ እንተውለት
''ምናልባት'' የምንልበት !!
ልክ እንደ አምና - በዚህ ዓመት ።
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሰር ይቅር ማያ
ይቅር ብለን መታሰሪያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ
ጥግ ድረስ የለም ስራ፣ጥግ ድረስ የለም ፋታ።
በልባችን ደግ በኩል፣እንፈልግ ባዶ ቦታ፣
የጳጉሜ አይነት ትንሽ ቦታ
ለዘመን መለወጫ።

ነብይ መኮንን!

@getem
ነፍስ ደጃፍ ከርመው በድንን የረሱ
ጥቂት ሰዎች አሉ ከሞቱም ብሃላ
የሚተነፍሱ !
~~
ጋሽ ነብይ መኮንን ከጥቂቶቹ መሀል ነው በሰላም እረፍ የመንገዴ ሰው !!!

( ካሊድ አቅሉ)

@getem
@getem
@paappii
😭


በትዝታ ወደ ኋላ
ወደ አማልዕክት ገላ
ገብቶ ለመሸቅ
በላብ ለዠመዋዠቅ
አንድት ነጥብ መዞ
በጉም ተፈናጦ በትዝታ ጉዞ

ወደ አንድት ቅፅበት
ሲቃ ወደተሞላበት
ወደ ናርዶስ ጠረን
ወደ ብልግና መረን
ወደ ራቁት ገላ
ወደ ሸት ዘለላ
ወደ እኔ አማልዕክ
አንድ ቀን የመኖሬ ምልክት
ወደ ዛች ማስረጃ
በደመና መጋረጃ
ወደ ዛች አቅጣጫ


ያችኑ ቀን መርጦ
መጋረጃ ገልጦ
ከእግዜር ፍጥረት በልጦ
ጉዞ ወደ ኋላ
ወደ ሚሹት ገላ


ወደ ዛቹ ቅፅበት
ነፍሴ ካለችበት
በትዝታ ፈረስ
ወደዛው መገስገስ


አወዬው ተዝታ ከአሁን መብለጡ
የተዳፈነ እሳት ረመጥ መግለጡ



by kerim

@getem
@getem
@getem
ምን አይነት ውበት ነው

ዕፁብ ቁንጅናዋን እግዚሄሯ ሲፈጥራት
እንደ ፅጌረዳ አስውቦ ያሳመራት
የሀገር ቅብ ማዛን አላብሶ የሰራት
. ምን አይነት ውበት ነው
በውበቷ ድምቀት አዋፋት ተገርመው
በግቢዋ አጥር ላይ በደጇ በር ቆመው
ሀረጋትን ፅፈው መጥነው ቀመሩ
ለሷ ዜማን ሰርተው ለፍቅሯ ዘመሩ
ምን አይነት ውበት ነው
ጨረቃና ፀሀይ ኩባኩብት ጨምረው
ፍፁም አይደርሷትም ከሷ ተወዳድረው
መልኳ ፊደል ሰርቶ ጎልቶ ይነበባል
እልፍ ቅኔን ፅፎ ቃላትን ያዘንባል
ፊደልን ከፊደል
ሰምና ወርቅ አርጎ አዋዝቶ ያግባባል
ሰንደቅ አይሰቀል ትኑር በመቅደሷ
የሀገርን ቀለም
ጎልታ ለማሳዬት ትበቃለች እሷ
በሀገር ውብ ቀለም የተሰራው ልብሷ
ከሩቅ ጎልቶ ሚታይ ሰንደቋ ነው ለሷ

By @Habtishe01

@getem
@getem
@getem
-------

እዚህ ፎቶ ስር ሶስት ሰዎች ይታዩታኛል..
ገብሬ ፣ አብዬ መንግስቱ እና ጋሽ ነብይ!

አይ ማማር
አይ ውበት
አይ ግዜ
አይ ዘመን....

''They bared their brains to heaven..'' ይላል allen የታላላቆቹን ሞት ማለፍ ከሰሟ በኋላ!

የታላላቆቹ ማለፍ ምድር ላይ ለቀሩ ዋይታ
ለሰማይ ደግሞ ደስ የሚል ፈገግታ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።
ሚቀበሏቸውን ፣ ሚገናኟቸውን ማሰብ አካሄዳቸውን መከተል ያስመኛል።
እጆቻቸውን ይዞ ወደ ሚሄዱበት አብሮ መጎዝ...
ወደዛ ደስ ወደሚሉት ሰዎች...

የታላላቆቹ ማለፍ ታላቅ ሀዘን ብቻ ሳይሆን የሚጥልብን እነሱን የመከተል ፣ እነሱን የመፈለግ መሪር ናፍቆት ያሸክመናል።
ደጋጎቹ ሁሉ ጥለውን አንዲት ትንሽ ቦታ ይበሰባሉ።
እዚህ የኖሩትን ተሰብስበው ይደግሙታል።
ዘላለም የሚያምር ነገር መስራት አይደክማቸው እነሱ እንደሆነ...

እንደ ነብይ ያሉ ሰዎች በሰማይ እና በምድር መሀከል ያለውን ወግ የሚያገነኙ ድልድዮች ነበሩ።
ከእንግዲህ ስለ ትናንት ማን ይነግረናል?
ስለ ሚያማምሩት ሰዎች ማን ያጫውተናል?

በህይወት ያሉት በሞቱት ይቀናሉ! ማለት ይሄ ነው።

ነፍስ ይማር ጋሽ ነብይ!

#ይስሃቅ_አብርሃም

@getem
ለናዝሬት ( አዳማ ) ልጆች!
****
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

የናዝሬቱ ምልክት ፣ የአጼ ገላውዲዮሱ ጥበበኛ ነብይ መኮንን አዲስ አበባ ቢሆን የሚቀበረው ሥላሴ ይቀበራል።
የሚያውቀውም የሚያደንቀውም ይሄዳል። ራሱ ሰውየው ግን ናዝሬትን ፣ ማሪያም ቤተክርስቲያንን ፣ ከእናቱ አጠገብ ማረፍን መረጠ ። እኛን መረጠ ። እንግዲህ ነብይ ራሱ የለም። ቤተሰቦቹም የሉም። ታዛቢ የለም። ቀብሩ በክብሩ ልክ ላይደምቅ ይችላል። ከአዲስ አበባ ናዝሬት ለቀብር የሚሄደው ሰው በጣም ላይበዛ ይላል ( ከበዛ እሰየው )። እስቲ የናዝሬት ልጆች ፣ አዋቂ አዛውንቱ እንደ አፋር ዳጉ ስርዓት ተጠራሩና ወንድማችሁን ሸኙት ። እስቲ ተደዋወሉና 9:00 ሰዓት ማሪያም ቤተክርስቲያን ኑ ። አንድ ሰዓት አይወስድም ። ነብይን ብትወዱትም ፣ ባትወዱትም ፣ ብትቀርቡትም ባታውቁትም እስቲ ኑ ። እስቲ ተደዋወሉና " 9:00 ሰዓት ማሪያም ቤተክርስቲያን ነብይን እነሸኘው " ተባባሉ ።
እስቲ ኑ !!!!!!!!!

#SHARE በማድረግ ይህን መልዕክት ያዳርሱልን።

@getem
@getem
ጥቁር ነጭ ግራጫ
(ነብይ መኮንን)

...ሰው እያለ አጠገባችን
ቅንነቱን ማየት ሲያመን
ከኛ አብሮ በሕይወት ቆሞ ፤ መልካሙን ስምን
መጥራት ሲያንቀን
"ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም" እንላለን
እንዲህ እያልን፤
ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤
አበባውን ቀጥፈን ጥለን፤ አበባ (እ)ናስቀምጣለን።



@getem