8.61K subscribers
14 photos
4 videos
9 files
11 links
The future starts here!
Download Telegram
በከንቱ አትጨነቅ!

አንዳንዴ አንተ ስለተጨነክ ብቻ የማትቀይራቸው ነገሮች አሉ፤ ሸክላው ራሱን ከሚያውቀው በላይ ጠፍጥፎ የሰራው ሸክላ ሰሪው ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ ካንተ በላይ የሚያውቅህና የሚያስብልህ አምላክ አለህ! በከንቱ መጨነቅ አቁም!

የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ ከዛ የሚገጥምህን መራራ ይሁን ጣፋጭ ነገር ለመቀበል ተዘጋጅ፤ ወዳጄ ጀግና እንዲህ ነው የሚያደርገው!

ብርታት የሞላው ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
እንደምትቀይረው እመን!

ጂም ሮን የተባለ ደራሲ ላንተ ብሎ ፑሽ-አፕ (ስፖርት) እንዲሰራልህ ሌላ ሰው አትቀጥርም ስለዚህ ከሌላ ሰው ብዙ አጠብቅ ይለናል። የኛን ሸክም ማንም አይሸከምልንም፣ እንደውም እኛ ከራሳችን አልፈን የሌሎችን ሸክም ማቅለል እንደምንችል ማመን አለብን።

አሪፍ ነገር ስናገኝ በልፋቴ እንደምንለው ከባድ ነገር ሲገጥመንም በጥፋቴ ማለት አለብን። የኛ ጥፋት መሆኑን ስናምን ለመፍትሄው ግማሽ መንገድ ተጉዘናል። ሰበብ እንደሚያበዛ ሰው ቆሞ የሚቀር የለም!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ራስን መቀየር!

የማትቆጣጠራቸው ነገሮች ላይ ጊዜህን ልታጥፋ ስትል ንፋስ ልትጨብጥ እየሞከርክ እንደሆነ አስብ፤ የሰዎችን ፀባይ፣ የሀገርህን ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነቱን፣ የአለቃህን ወይ የአሰሪዎችህን ፀባይ መቀየር አትችልም!

ግን እንደምትችለው እርግጠኛ የምትሆንበት አንድ ነገር አለ...ራስህን መቀየር ግን ትችላለህ! እመነኝ ወዳጄ አንተ ከተቀየርክ ነገሮች ሁሉ ይቀየራሉ፤ ካንተ የሚጠበቀው ለራሴ ያለሁት ራሴ ነኝ ብሎ ማመን እና የተግባር ሰው መሆን ነው።

@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ዳይ ወደ ስራ!

ከምታውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጠንክረህ የምትለፋው አንተ መሆን አለብህ፤ ዕድለኛ ስለመሆን አታስብ! ተዓምር የምትሰራው በማይቆም ጥረትህ ነው።

አሸናፊ መሆን ማለት ጥሩ ስሜት ላይ ባትሆንም እንኳን የጀመርከውን መቀጠል ነው። ጀግና ጥረቱን የማያቆም ነው! ዳይ ማቆም የለም!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ስንፍናን ማሸነፍ!

ሮኬት ወደ ህዋ ሲሄድ አብዛኛውን ጉልበት የሚጨርሰው እስኪነሳ ነው፤ የመሬትን ስበት አሸንፎ በሚገርም ፍጥነት ከፍ ማለት ከጀመረ በኋላ ያንን ፍጥነቱን ማስጠበቅ ቀላል ነው።

በህይወትም እንዲ ነው ራስህን ለመለወጥ ስትነሳ መጀመሪያ አካባቢ የሚገጥምህን ስንፍና እና መሰልቸት ካሸነፍከው በቃ የምትፈልገውን ነገር ከማግኘት የሚያቆምህ ነገር የለም!

ብሩህ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ተዓምር መስራት!

ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?!

በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው!

ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ፅናት!

"አሁን የምነግራችሁን የስኬት ሚስጥር ምንም ነገር አይተካውም። ጉብዝና አይተካውም! የአይምሮ ብስለት አይተካውም! እድለኛ መሆን አይተካውም! በቃ እሱን የሚተካ የለም....ፅናት ይባላል" ይለናል ካልቪን ኮሊጅ የተባለ የአሜሪካ መሪ።

በዚህ ምድር የተነሳ የትኛውንም ስኬታማና ታላቅ ሰው ብትመለከቱ ከየትኛውም ችሎታው ይበልጥ ለአላማው ያለው ፅናት የሚፈልግበት አድርሶታል። ምርጥ ውጤት ለማምጣት በየቀኑ በፅናት መዘጋጀት አለብህ!

ማራኪ ምሸት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ጥረትን መቀጠል!

ራሳችንን ለማሳደግ ከኛ የሚጠበቀውን በየቀኑ በትንሹ እያደረግን ከቀጠልን ሁላችንም ያሰብነው ከፍታ ላይ እንገናኛለን!

ትንሽ ጠብታ ልፋት ተጠራቅሞ ተዓምር ይሰራል። እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በሂደት እንጂ በድንገት አይደለም! ስለዚህ ጥረታችንን አናቆምም💪

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ለፈተና ምን ያህል ተዘጋጀህ?

ጊዜያዊ ስሜትህን ተቆጣጠር! አሁኑኑ ልደሰት ማለቱን አቁም! ከጥናት የሚያዘናጉህን ነገሮች እምቢ በል! ሁሉም ከፈተና በኋላ ይደርሳል፤ እንደልብህ ፈታ ትላለህ።

አሁን ግን በትኩረት አጥና፣ ብዙ ጥያቄ ስራ። ማትሪክ ማለት ብዙ ጥያቄ የሰራ ተማሪ የሚሰቅለው ፈተና ነው፤ አንተ ምን ያህል እየተዘጋጀህ ነው?

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
FutureX
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የትኛውን ትመርጣለህ?

በሰዎች መካከል ትልቁን ልዩነት የሚፈጥረው ለአንድ ተመሳሳይ ነገር የሚመርጡት ምርጫ ነው።

ነገን አስበህ አሁን ከለፋህ፤ የፈለከውን ሁሉ ታሳካለህ። አሁን የማይጠቅምህን በማድረግ ጊዜህን ካሳለፍክ ነገ በሌሎች ስኬት ትቀናለህ።

ተማሪ ከሆንክ አጥና! ፈተና ከደረሰ ብዙ ጥያቄ ስራ! ራስህን በአይምሮና በስነልቦና ለፈተና አዘጋጀው! ነገ ስታስበው የሚያኮራህን ነገር አሁን ምረጥ።

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
FutureX
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የምትችለውን ሁሉ አድርግ!

ሁልጊዜም ምርጫህ ህይወትህን ይወስነዋል፤ ዛሬ የምትወስነው እያንዳንዱ ውሳኔ ውጤቱን የሚያሳይህ ነገ ነው።

ትምህርት የዚህ አለም መጨረሻ አይደለም! ግን ጊዜህን ሰጥተህ እየተማርክ እስከሆነ ድረስ በደምብ ተማር! የምትችለውን ካደረክ ራስህንና የሚወዱህን ማስደሰት ትችላለህ።

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
በፈተና ደስ ይበልህ!

እውነተኛ ለውጥ በፈተናና በችግር የተሞላ ነው፤ ከንብ ማር መውሰድ የሚፈልግ ሰው ንድፊያዋን መታገስ አለበት። 

ወዳጄ ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ብታዝን፣ ብታማርር ወይ ራስህን ብትጎዳ ምንም አትፈጥርም! ትዕግስትህን በሚፈትኑ ችግሮች ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጠንካሮች ናቸው የሚፈተኑት!

ጣፋጭ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የማትሪክን ፍርሀት ማሸነፍ!

የማትሪክ ፈተና በተለይ ሲደርስ ውስጥህ በጣም ሊፈራ ይችላል፤ አንድ ቀላል መፍትሄ ልንገራችሁ።

ለፈተና ዝግጅት የምትችለውን ጥረት ሁሉ ካደረክ "ከፈጣሪ ጋር በደምብ ሰርቼ እወጣለው" ብለህ ጠዋት ስትነሳ፣ ማታ ልትተኛ ስትል እየደጋገምክ ለራስህ ንገረው፣ በወረቀት ፃፈው።

አይምሮህ የነገርከውን ስለሚያምን ፍርሀት ይጠፋል፤ በትኩረት ፈተናውን ሰርተህ ትወጣለህ።

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
በምትችለው ተዘጋጅ!

የፈተናውን ቀን መቀየር አትችልም! አንተ ግን ውስጥህን አሳምነህ ምርጥ ውጤት ለማምጣት ተዘጋጅ! ምክንያቱም ባትዘጋጅም ጊዜው እንደሆነ መሄዱ አይቀርም።

ጥቂቶች ስኬታማም ደስተኛም የሚሆኑት የተለዩ ስለሆኑ ወይ እድለኛ ሆነው አይደለም፤ ላመኑበት ጉዳይ በፅናት እና በትዕግስት ስለሚቆሙ ነው። አንተም ለዚህ አታንስም ወዳጄ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ትንሽ ታገስ

"ትዕግስት ይኑርህ ሁሉም ነገሮች ቀላል እስኪሆኑ ከባድ ነበሩ" ይለናል ፐርዢያዊው ገጣሚ ሰዓዲ።

የጎደለህ ትንሽዬ ትዕግስት ነው እንጂ የምትፈልገው ነገር ካንተ አያመልጥም! ታገስ ማለት ግን ቁጭ ብለህ ተመልከት አይደለም፤ ጥረትህን ሳታቆም ጠብቅ ነው።

ታላቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ወሳኙ ጥያቄ!

በየቀኑ ራስህን ማሻሻል፣ መጎበዝ ፈልገህ ነገር ግን ወደኋላ የሚጎትትህ ነገር ከበዛ ራስህን 1 ጥያቄ ጠይቀው፤ "ለውጡን ምን ያህል እፈልገዋለው?"
በልና መልሱን ለራስህ ንገረው።

ውሀ ቢጠማህ የትኛውንም ዋጋ ከፍለህ ውሀ ለመጠጣት ጥረት ታደርጋለህ፤ አየህ ራስህን መለወጥ እንደ ውሀው ያስፈልገኛል ብለህ ካመንክ በየቀኑ በፅናት ታጠናለህ፣ ታነባለህ፣ ራስህን ለነገ ታላቅ ህይወት ታዘጋጀዋለህ! አሁን ራስህን ጠይቀው!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
እንደምትቀይረው እመን!

ጂም ሮን የተባለ ደራሲ ላንተ ብሎ ፑሽ-አፕ (ስፖርት) እንዲሰራልህ ሌላ ሰው አትቀጥርም ስለዚህ ከሌላ ሰው ብዙ አጠብቅ ይለናል። የኛን ሸክም ማንም አይሸከምልንም፣ እንደውም እኛ ከራሳችን አልፈን የሌሎችን ሸክም ማቅለል እንደምንችል ማመን አለብን።

አሪፍ ነገር ስናገኝ በልፋቴ እንደምንለው ከባድ ነገር ሲገጥመንም በጥፋቴ ማለት አለብን። የኛ ጥፋት መሆኑን ስናምን ለመፍትሄው ግማሽ መንገድ ተጉዘናል። ሰበብ እንደሚያበዛ ሰው ቆሞ የሚቀር የለም!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
60 ቀን አለህ!

👉 ፈተና ሀምሌ ከሆነ ቢያንስ 60 ቀን አለህ።
👉 ከዛሬ ጀምረህ በየቀኑ ቢያንስ 6 ሰዓት መድበህ ለፈተና ተዘጋጅ!
👉 ከ 6 ሰዓቱ ውስጥ 4 ሰዓቱን አጥና 2 ሰዓቱን የማትሪክ ጥያቄ ስራ!

ፈተናው 1 ሳምንት እስኪቀረው ድረስ አሁን ያልኩህን በፅናት ካደረከው ማትሪክን ማለፍ ብቻ ሳይሆን ምናልባት ትልቁን ውጤት ታስመዘግባለህ። ዳይ ወደ ተግባር!

ጥረታችሁ እንዲሳካ ተመኘንላችሁ
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ትችላለህ!

የሰማይ አባትህ ለትልቅ አላማ ነው ሰው አርጎ የፈጠረህ! “አልችልም! አልረባም! የትም አልደርስም!” አትበል!

አንተ ባትሆን የማታልፋቸው ጊዜያት ነበሩ፣ አታልፍም የተባልከውን ከባድ ፈተና አልፈሀል፤ ይሄንንም ጊዜ በሚገርም ጥንካሬና ብርታት ማለፍ ትችላለህ!

የተለየ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ተዓምር ትሰራለህ!

አሸናፊ የሆንከው በፈጣሪ መመካት ስትጀምር ነው፤ ስለዚህ ምንም ነገር ብትሞክር ወይ ታሳካዋለህ ወይ የሚገርም የህይወት ትምህርት ትማርበታለህ። ምንም ነገር ለመጀመር አትፍራ!

ወዳጄ ህልም ካለህ፣ ጥረት ብትጨምርበት እና የአላማ ፅናት ብታዳብር ካሰብከው በላይ ተዓምር ትሰራለህ! አሸናፊ መሆን የሚፈልግ ሰው ይሄን ማድረግ ነው የሚጠበቅበት።

ተዓምረኛ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑በፅናት ማሸነፍ!

ሰነፍ የምትባለው ውጤትህ ዝቅ ሲል አይደለም፤ ምርጥ ውጤት ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት ስታቆም ነው።

አሸናፊዎች አያቆሙም፤ የሚያቆሙም አያሸንፉም!

@futureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!