8.71K subscribers
14 photos
4 videos
9 files
11 links
The future starts here!
Download Telegram
50 Positive Study affirmation part 2.pdf
1.4 MB
አመለካከታችንን የሚቀይሩ ለራሳችን መናገር ያሉብን በጎ ንግግሮች (Positive Affirmations) እንድትጠቀሙበት አዘጋጅተናል።

@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ስንፍና ባንተ አያምርም!

አሁን ቆርጠህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው? ጊዜና አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም! ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ይሄን ወርቃማ ዕድሜዬን ተዓምር እሰራበታለው በል!

ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ሰዎች መቀየር አትፈልግም? እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ! ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ከምቾት ውጣ!

በየቀኑ ተመሳሳይ ነገር እያደረክ የተለየ ውጤት መጠበቅ ሞኝነት ነው። ከአልጋ ወርደህ፣ ስልክህን አስቀምጠህ ማጥናት ካልጀመርክ ውጤታማ አትሆንም!

አሁን የምትከፍለው ዋጋ፣ የምታደርጋት ትንሿ ጥረት ተጠራቅማ ነው ህልምህ የሚሳካው! የምትቀየረው ከምቾትህ ወተህ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ ስታደርግ ነው! ዳይ ተነስ!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
አታመንታ!

ቁጭ ብለህ እንዲህ ባደርግ እንዲህ ቢሆን አትበል! ተነስና አድርገው! ወደ ተግባር ግባ! ለማትሪክ ተዘጋጅ!

ከአልጋህ ውረድ! ፊልሙን አቁመው! መፅሀፉን አንብብ! አጥና! ጥያቄ ስራ! ጊዜህን ተጠቀምበት! ስትጨርስ ግን በደምብ ፈታ በል። ዳይ ተነስ አሁን!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Futurexethiopia
ሳትለወጡ አንላቀቅም!
🛑 በአጭር ጊዜ ጎበዝ ተማሪ መሆን

የትኛውም ተማሪ የሚያነሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች
👉 እንዴት ለፈተና አጥንቼ ልጨርስ?
👉 እንዴት ያጠናሁትንስ አስታውሼ ውጤታማ ልሁን?
👉 ጊዜዬን ምርጥ አድርጌ እንዴት ልጠቀም?
👉የፈተና ሳይኮሎጂ ገብቶኝ ይበልጥ ውጤታማ መሆን እፈልጋለው ምን ላርግ?

ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚገርሙ መፍትሄዎችን የያዘ ቪዲዮ ነው፤ አይታችሁ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትለወጡበት እርግጠኛ ነን። መልካም ቆይታ

ከታች ያለውን ሊንክ ነክታችሁ ቪዲዮውን ማየት ይቻላል።👇

https://youtu.be/K1sWhkN0Xd8?si=okULhtUFhmCN-dW7
ፈጣሪ አለህ!💪

ወዳጄ ከገጠመህ ችግር አንተ ትገዝፋለህ ምክንያቱም ጥሎ የማይጥል ፈጣሪና ወድቆ የማይቀር ማንነት ስላለህ!!

@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
መወሰን አለብህ!

ልብስህ አንዴ ወይ ሁለቴ ቢቀደድ ልብስ ሰፊ ጋር ልታሰፋው ትችላለህ፤ መቀደዱ ከበዛ ግን ደግመህ አትለብሰውም፤ ትቀይረዋለህ።

ችግሮች የሚደጋገሙ ከሆነ፤ ትላንት የሚስፈራህ ነገር ዛሬም ካስፈራህ፤ በቃ ትልቅ ለውጥ ህይወትህ ላይ ለመፍጠር መወሰን አለብህ ማለት ነው!

አሁን ቆራጥ ካልሆንክ ትላንት የገጠመህ ችግር ዛሬም ይገጥምሀል!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
አሸናፊ ነህ!

የጀመርከውን ጥናት ለማቆም ብዙ ምክንያቶችና ብዙ ፈተናዎች እየገጠሙህ ይሆናል ግን ወዳጄ እልኸኛ መሆን አለብህ!

የምፈልገውን ሳላሳካ፣ ለምወዳቸው ሳልደርስ ጥረቴን አላቆምም ማለት አለብህ!

አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም ግን ተስፋ ቆርጦ የማያቆም ነው። አንተ ደግሞ አሸናፊ ነህ! ትልቁ ቦታ ያንተ ነው!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የስኬት ሚስጥር

"ዛሬን ተጨነቅና ቀሪ ዘመንህን በደስታ ኑር እለዋለው ራሴን" ይለናል ታላቁ ስፖርተኛ መሀመድ አሊ

አንተም አሁኑኑ ልደሰት አትበል! ስኬትህ ማንነትህን እስኪመሰክር ድረስ ጠንክረህ ስራ! ጠንክረህ አጥና! የዚህ አለም ስኬት ትንፋሹን ለረጅም ጊዜ ተቆጣጥሮ ደስታውን ለሚያዘገይ ነው።

@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ዳይ ወደ ስራ!

ከምታውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጠንክረህ የምትለፋው አንተ መሆን አለብህ፤ ዕድለኛ ስለመሆን አታስብ! ተዓምር የምትሰራው በማይቆም ጥረትህ ነው።

አሸናፊ መሆን ማለት ጥሩ ስሜት ላይ ባትሆንም እንኳን የጀመርከውን መቀጠል ነው። ጀግና ጥረቱን የማያቆም ነው! ዳይ ማቆም የለም!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 1500 ቃላት (Vocabularies) በአጭር ጊዜ ማወቅ

ለ English እና SAT የኢንትራንስ ፈተና ብዙ ቃላት ማወቅ ወሳኝ ነው። እንዴት አድርገን በአጭር ጊዜ 800 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የኢንግሊዝኛ ቃላትን መያዝ እንደምንችል ይሄ ቪዲዮ ያስተምረናል።

ከታች ያለውን ሊንክ ነክታችሁ ቪዲዮውን ማየት ይቻላል።👇

https://youtu.be/VckSd-WSlkY?si=MwCQYZtwNLmwDGCr
ለውጡን ጀምረው!

አሁን ተነስተህ ካላጠናህ የሚቆጭህ ውጤት ሲመጣ ነው፤ ከምቾትህ ወጥተህ ውጤታማ ተማሪ ለመሆን ስትሞክር የተሻለ ነገር ወደ ህይወትህ ይመጣል።

የምትፈራው ወይ የምታመነታው እስክትጀምር ነው፤ ከጀመርክ በኋላ ግን በራስ መተማመንህ ይጨምራል። ዳይ አሁን ጀምር!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ትልቁ ህልምህን ፃፈው!

"በጣም የሚያበሳጭ ነገር በገጠመኝ ቁጥር ወረቀት አውጥቼ ትልቁ ህልሜን እፅፈዋለው፤ ከዛ እንደገና አዲስ ጉልበት እና ሀይል እሞላለሁ" ይለናል ግራንት ካርዶን የተባለ ሚሊየነር።

አይንህን ከትናንሾቹ ችግሮችህ ንቀልና ትልቁ መድረሻህ ላይ አድርግ! በህይወት ወሳኙ የገጠመህ ችግር አይደለም...ወሳኙ ያንተ ምላሽና ቆራጥነት ነው!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ከምቾት ውጣ!

ሁሌም ለውጥ የምትፈልግ ከሆነ ከማትፈልገው ነገር ጋር መጋፈጥ ተለማመድ፤ ምቾት ውስጥ ሆነህ ለውጥ የለም! አንተን የሚያሳድጉህ ነገሮች ያሉት ከምቾትህ ጀርባ ነው።

በጠዋት መነሳት ምቾት የለውም! ሁሌ በተመሳሳይ ሰዓት ማጥናት ምቾት የለውም! ስፖርት መስራት ምቾት የለውም! ግን በፅናት ካደረከው ራስህን ትልቅ ቦታ ላይ ታገኘዋለህ።

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🔥 ወሳኝ ኮርሶች ተለቀዋል!

SAT (Aptitude) እና Physics የ2014 እና 2015 ኢንትራንስ ፈተናዎችን እያንዳንዱን ጥያቄ ከነማብራሪያው ሰርተንላችኋል። English እና Maths ከዚህ በፊት ሰርተን ለቀንላችሁ ነበር።

ከእናንተ የሚጠበቀው እያንዳንዱን ጥያቄ አብራችሁን እየሰራችሁ መለማመድ ነው፤ ይሄን ካደረጋችሁ ኢንትራንስን ከ 500 በላይ ማምጣት ትችላላችሁ!! መልካም ዝግጅት!

👉 ማስታወሻ፡ አፕሊኬሽኑ ውስጥ ኮርሶቹን ማግኘት የሚችሉት የFutureX አባላት ብቻ ናቸው።

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ወደ ተግባር ግባ!

እንዳይቆጭህ ከፈለክ አሁን ካንተ የሚጠበቀውን አድርግ! ለነገ ህልምህ ዛሬ ዋጋ ካልከፈልክ ነገ አዲስ ነገር አይኖርም!

መዋኘት እየፈለክ መርጠብ ግን የማትፈልግ ከሆነ የሚዋኙ ሰዎችን እያየህ ስትቀና ትኖራለህ!

@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Parts_to_study_for_entrance_exam_Biology,_Physics,_Chemistry_and.doc
66 KB
ለኢንትራንስ ማጥናት ያሉብን ወሳኝ ቻፕተሮች

በ 50 ቀን ለፈተና መዘጋጀት በሚለው ቪዲዮ ላይ የተጠቀሰው፤ ለእያንዳንዱ ትምህርት በጣም ወሳኝ የሆኑ ማጥናት ያሉብን ቻፕተሮችን ይኸው በዚህ መልኩ አዘጋጅተንላችኋል።

👉 ለምታውቋቸው የ12 ክፍል ተፈታኞች ሼር አርጉላቸው።

መልካም ዝግጅት!
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ስንፍና ባንተ አያምርም!

ወጣት ሆነህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው?አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም፤ ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ ይሄን ወርቃማ ዕድሜዬን ተዓምር እሰራበታለው በል!

ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ቤተሰቦችህን መቀየር አትፈልግም? እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ!

ስለዚህ ተነስ! የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ቁጭ አትበል! የማይጠቅምህን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም!

@FutureX_Ethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
መፍራት የለም!

የምትፈራው ወይ የምታመነታው እስክትጀምር ነው፤ ከጀመርክ በኋላ ግን ወደኋላ አትይ።

በምታምንበት ጉዳይ ጨክኖ ራስን መለወጥ ህመም አለው ውጤቱ ግን አንጀት ያርሳል! ዳይ መፍራት የለም ወዳጄ!

@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!