8.71K subscribers
14 photos
4 videos
9 files
11 links
The future starts here!
Download Telegram
ከባዱን አሁን ስራ!

ታሪክ በአንድ ጀምበር አይሰራም! ሁሌም የማይቆም ጥረት ማድረግ አለብህ፤ የምትፈልጋቸው ነገሮች በነፃ አይገኙም ዋጋ ያስከፍላሉ ዋጋ ለመክፈል ራስህን አዘጋጅ!

ወዳጄ አሁን ከባዱን ካደረክ ህይወት ቀላል ትሆናለች፤ ቀላሉን ካደረክ ግን ህይወት ትከብድሀለች!

አጀብ የሚያሰኝ ስኬት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ስንፍናን ማሸነፍ!

በህይወት ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥሩት ትናንሽ ነገሮች ናቸው፤ ዝሆን ገጭቶት የሞተ ሰው ታውቃላችሁ? በትንሿ የወባ ትንኝ ግን ተነክሶ የሞተ ነፍ ነው። ታዲያ እንደ ቀላል የምታየው ቸልተኛ ፀባይህ ምን እንደሚያሳጣህ የምታውቀው ዘግይተህ ነው።

በቀን ውስጥ አደርጋለው ያልከውን ሳታደርግ ቀጣዩን ቀን አትጀምር! አለዛ ከነገ ላይ እየሰረክ ነው፤ ስንፍናን ማሸነፍ የምትችለው በየቀኑ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ በማድረግ ነው።

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ለራስህ ቃል ግባ!

ነገሮች በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብህ ይችላሉ፣ በዚህ አለም ለመኖር የሚያጓጉህን ነገሮች ሁሉ ልታጣ ትችላለህ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈን እናውቃለን ወደፊትም እናልፍ ይሆናል።

ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ቆርጠህ ጥረትህን እንደማታቆም ለራስህ ቃል መግባት ነው!

ተስፋ የሞላበት ምሽት ተመኘሁላችሁ🙏
@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ልክ ነህ!

ሁሌም የምትችለውን ሁሉ አድርግ! አሁን የዘራኸውን ነው ነገ የምታጭደው። አሁን ስትለፋ ወይ አላማህን ስታስቀድም እንደ ሞኝ ሊያዩህ ይችላሉ፤ አንተም ለጊዜው የተሸወድክ ይመስልሀል፤ ልክ ነህ አልተሳሳትክም።

ሰዎችን በብልጠት ሳይሆን በልፋትህ ብለጣቸው ምክንያቱም በልፋትህ ከፍ ስትል ብልጡን ሰው ቀጥረህ ታሰራዋለህ።

ደስ የሚል ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
አሁን ጀምር!

ምንም ነገር ቁጭ ባልክበት ሊሳካ አይችልም፤ ስልክህ ላይ ተጥደህ፣ ቲቪ ላይ አፍጥጠህ ወይ አልጋ ላይ ጋደም ብለህ ጣሪያ ጣሪያ እያየህ ምንም ነገር መጀመርም ሆነ መቀየር አትችልም!

ይህ ምድር ያንተን ላብ ይፈልጋል፤ ያንተን ጥረት ይፈልጋል፤ ለነገ መድረሻህ አሁን መዘጋጀት፣ ማቀድ እና ወደ ድርጊት መግባት አለብህ! ወዳጄ ለመጀመር ታላቅ መሆን አይጠበቅብህም፤ ታላቅ ለመሆን ግን አሁኑኑ መጀመር አለብህ!

የለውጥ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ትችላለህ!

ወዳጄ 'አልችልም' ካልክ ልክ ነህ አትችልም፤ 'እችላለሁ'ም ካልክ ልክ ነህ ትችላለህ! ሁሉም በመዳፍህ ነው! ውስጥህ ካመነበት የምትፈልገውን እንዳታገኝ የሚያስቆምህ ማነው?!

እንደምትችል ማንም እስኪነግርህ አጠብቅ! አንተ የምትችለውን ሁሉ ስታደርግ ፈጣሪ ደግሞ የማይቻል የሚመስለውን አድርጎ ያሳይሀል!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ቆራጥ ሁን!

የትም አያደርስህም እንጂ የስሜትህ ባሪያ መሆን ቀላል ነው፤ ጊዜያዊ ደስታ የሚሰጡህን ነገሮች በጥበብ እለፋቸው፤ ለእውነተኛ ደስታህ ስትል አሁን የማይጠቅሙህን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ሁኔታዎች፣ ቦታዎች ሁሉ ከህይወትህ አውጣቸው!

የተመረዘ እጅ ወይም እግር የሚቆረጠው ባለቤቱ ስለማያስፈልገው አይደለም ግን ሌሎቹን የሰውነት ክፍሎች ስለሚመርዝ ነው፤ ስኬትና ደስታ መስዋዕትነት ይጠይቃል! ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ ቆራጥ ሁን!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ያንተ ጥንካሬ!

አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል፤ ሀሳብህ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ።

ጨለማው ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም፤ ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ! አንተ ባትሆን የማታልፋቸው ብዙ ችግሮች ነበሩ፤ አንተ ግን ለዛሬ ደርሰሀል፤ ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበውን ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነው!

ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ጥረትህን አታቁም!

ከጓደኞችህ ወይ በዙሪያህ ካሉ ሁሉ ኋላ መቅረትህን አትጥላው፤ ምክንያቱም ረጅም ርቀት ለመወርወር ወደ ኋላ በደምብ መንደርደር ወሳኝ ነው።

እየታሸህ ያለኸው በደምብ እንድትበስል ነው፤ እድል ጓዟን ጠቅልላ እጅህ እስክትገባ ጥረትህን እንዳታቆም! የዚህ አለም እድለኞች አብዝተው የሚለፉ እንጂ አብዝተው የሚመኙ አይደሉም።

ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ተዓምር መስራት!

ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?!

በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው!

ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የተግባር ሰው ሁን!

"ስፖርት መስራት እጀምራለሁ፣ አንድ መፅሀፍ በሳምንት አነባለው፣ በጠዋት እነሳለው፣ ራሴን አሻሽላለው" ብለህ ካሰብክ ቆየህ ፤ ግን መቼ ነው ወደ ተግባር የምትገባው? ሁልጊዜ ሰኞ ሲመጣ ወይ ወሩ ሲያልቅ፣ ወይ አመቱ ሲፈፀም ማቀድ አልሰለቸህም?

ወዳጄ ምግብ የበላ እንጂ ለመብላት ያሰበ አይጠግብም እኮ! መድሀኒቱን የዋጠ እንጂ ስለ መድሀኒቱ አብዝቶ ያወቀ አይድንም እኮ! ማወቅ ማሰብ ማቀድ አሪፍ ቢሆንም ተግባር ከሌለው ግን በዜሮ ነው ሚባዛው! ስለዚህ አንዱን ዕቅድ አሁኑኑ ጀምረው! ዳይ ወደ ተግባር!

የተግባር ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ቆራጥ እና ፅኑ መሆን አለብህ!

ተመሳሳይ ሙቀት ጠንካራውን ድንች ልፍስፍስ ያደርገዋል፤ እንቁላል ደግሞ ያጠነክረዋል። በዚህ አለም ወሳኙ የገጠመህ ችግር አይደለም ያንተ ቆራጥነት እና ፅናት ነው!

ካልጠነከርክ ማንም አይፈልግህም፤ ከፈጣሪ በቀር ማንም እንዲሁ ሊወድህ ሊያከብር አይችልም፤ መበርታት ያለብህ ለዛ ነው። ስለዚህ ወዳጄ ተነስ እና ዘላለም እንደሚኖር ወጥረህ ስራ፤ ዛሬ እንደሚሞት ተደሰት!

የደስታ ጁምአ (አርብ) ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ፉክክሩን አቁም!

የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል፤ ራስህን ከሰዎች ጋር የምታወዳድር ከሆነ መቼም አትደሰትም፤ ደስ ቢልህ እንኳን ደስታህ ብዙ አይቆይም!

ከራሱ ጋር የሚወዳደር ሰውን ግን ማንም አያቆመውም። በራስህ ለውጥ ደስ ይበልህ፤ ዛፎች ሁሉ እኩል አያድጉም ግን ማደግ እስከሚችሉት ከፍ ይላሉ።

@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
አንድ መተማመኛ!

ፈጣሪ ባይረዳህ ፅናትና ትዕግስቱን ባይሰጥህ የማታልፋቸው ጊዜያት ነበሩ፤ አየህ ከዚህ በኋላ ለሚገጥሙህ ከባድ ፈተናዎች ሁሉ አንድ መተማመኛ አለህ!

ዝቅ ያልክ ሲመስልህ ከፍ የሚያደርግህ፤ ብታጎነብስም ቀና አርጎ የምትፈራውን ነገር ሁሉ በአሸናፊነት እንድታልፋቸው የሚረዳህ ፈጣሪህ አለና ተመስገን በል!

የምስጋና ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Futurexethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
የምትችለውን ሁሉ አድርግ!

ሁልጊዜም ምርጫህ ህይወትህን ይወስነዋል፤ ዛሬ የምትወስነው እያንዳንዱ ውሳኔ ውጤቱን የሚያሳይህ ነገ ነው።

ትምህርት የዚህ አለም መጨረሻ አይደለም! ግን ጊዜህን ሰጥተህ እየተማርክ እስከሆነ ድረስ በደምብ ተማር! የምትችለውን ካደረክ ራስህንና የሚወዱህን ማስደሰት ትችላለህ።

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
"ሁሉም ሰው ጂኒየስ ነው፤ ግን አሳ ከዛፍ ዛፍ በመዝለል ችሎታው ከተመዘነ እድሜ ልኩን የማይረባ እንደሆነ ያምናል" ይለናል አልበርት አንስታይን

ድክመታችንን ከሌሎች ጥንካሬ ጋር ካወዳደርነውማ ሁሌም የበታችነት ይሰማናል፤ ከሌሎች ዝቅ ያልን ይመስለናል። አንተ ጂኒየስ የምትሆንበትን የህይወት አላማህን እወቀው! ሌላው አያሳስብህ!

ደስ የሚል ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ከአንተ የሚጠበቀው!

በተግባር የምትገልጠው ማንነት ያስፈልግሀል፤ ከ 5 ዓመት ወይ ከ 10 ዓመት በኋላ መሆን የምትፈልገውን ሰው አሁን መሆን መጀመር አለብህ!

በቃ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርግ! በየቀኑ በጥረትህ የሚገነባ እንጂ ከሰማይ የሚወርድ ማንነት የለም!

የተለየ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ዳይ ማጥናት ጀምር!

ለእራት ሲያስቡን ለምሳ አረግናቸው እንደሚባለው የትም አይደርስም ብለው ለሚያስቡህ እንደተሳሳቱ ማሳየት አለብህ!

ያ የሚሆነው ደግሞ ማንም ሳይነግርህ ማጥናት ከጀመርክና ከበረታህ ብቻ ነው።

የለውጥ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ማትሪክን ከ 500 በላይ እናመጣለን!

የ 4 ዓመት ልፋትህን የሚወስነው የ 2 ሰዓት ፈተና ነው። ፈተና ክፍል ስትሆን የምታደርገው ነገር፤ ተረጋግተህ መስራትህ ወይ መደናበርህ ውጤትህን ይወስነዋል።

በዚህ ሰዓት በጣም ወሳኙ ነገር መረጋጋት ነው፤ በተለይ ፈተና አጭር ቀን ስለቀረው ያወጣሀቸውን ኖቶች ገለጥ ገለጥ እያደረክ እያቸው፤ በጣም ብዙ የማትሪክ ጥያቄ ስራ።

ስለ ፈተና ሳይኮሎጂ ይበልጥ ለማወቅ ኮርሳችንን ከፍተህ ማየት ነው። ከ 500 በላይ ታመጣለህ! ታመጫለሽ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 እነዚህን 3 ነገሮች ሁሌም አስባቸው

1. አላማ ይኑርህ አለበለዚያ ጊዜው ሲገፋ በዘፈቀደ የሚኖር ከንቱ ሰው እንደሆንክ ማሰብህ አይቀርም፤

2. ወደ አላማህ አንድ እርምጃም ቢሆን የሚያስጠጋህን ነገር በየቀኑ አድርግ፤ ስለዚህ በየቀኑ አጥና፣ ጥያቄ ስራ

3. በፈጣሪህ ታመን ከዛ ልበሙሉነት ፀባይህ ይሆናል ግን ሲሳካልህ አመስጋኝ እንጂ ጀብደኛ አትሁን!

ግሩም ምሸት ተመኘንላችሁ🙏
@futureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!