ፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት (mana dilbata firee amentaa)
176 subscribers
239 photos
10 videos
23 files
44 links
በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታችንን እንድናውቅ የሚረዱ :-

፨ ከተለያዩ መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸውን መረጃዎች አናጋራቹሃለን።

፨ ጥያቄ አና መልስ አንጠያየቃለን።


፨ መንፈሳዊ መፃህፍትን በ አማርኛ ፣ Afaan oromoo አና English language እናካፍላቹሃለን።

ሐሳብ አስተያየት ካላቹ @ye_gebriel ላይ አሳውቁን።
Download Telegram
#የኔ_ትውልድ_ባለውለታውን_ያሳክማል

"ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ ታሟል"
ብዙዎቻችንን ወደ መንፈሳዊ መንገድ የመራን፣ በሐጢአት የገገረውን ዓለት ልባችንን በመንፈሳዊ መዝሙሮቹ ያቀለጠልን፣ ልንጠፋ ጫፍ ስንደርስ በሚስረቀረቅ ድምፁ የመለሰን፣ በአገልግሎቱ አዋጅ ነጋሪ የሆነ፣ መዝሙሩ ወደ ጸሎት ያደገለት ታላቁ አባታችን ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ ሕክምና ይፈልጋል።

ጠንካራ ቤተ ክህነት ቢኖረን ኖሮ ይህ የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ መታከሚያ ባላጣ ነበር። ዳሩ ግን...ሆድ ይፍጀው። እኛ የመዝሙራቱ ተጠቃሚዎች ግን ባለውለታችንን አንተውም። ዘማሪ ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስን ለማሳከም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ....እነሆ በረከት!
መርዳት የማትችሉ በማጋራት ተባበሩ።

ድጋፋችንን አድርገን ወዳጅነታችንን እንግለጥ

CBE
1000481007287
KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL
CMC Michael Branch
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር

በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን  ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም  ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡

ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡

ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡  በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ።

እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡

እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ።

ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
"የሰው ልጆች ሁሉ አዋቂ ናቸው የሚባለው ስህተት ነው። አዋቂ ማለት መጽሐፍትን ጠንቅቆ ያወቀ ሳይሆን ከኃጢአት በመቆጠብ ነፍሱን የማይጎዳ፣ አምላክን በማመስገን በማያወላውል በቅድስና ሥራ መልካም በመሥራት ነፍሱን የሚመግብ ያ ሰው እሱ ብቻ አዋቂ ተብሎ ይጠራል።"

#ታላቁ_ቅዱስ_እንጦንስ
"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡

የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡

የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡"

(ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ #ረቡዕ ይከፈታል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሔዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የግንቦት 2016 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነው፡፡

ይህ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚከፈት ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#ግንቦት_21

#ደብረ_ምጥማቅ

ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ።

እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል። አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ።

ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል ።

ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ።

ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር።

እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል።

እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ።


ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን አሜን::

(#ስንክሳር_ዘተዋሕዶ)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #EOTC

" የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው

ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።
 
የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው ምን አሉ ?

ቅዱስነታቸው ፥ " ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም  " ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናው ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ እንደሚከባትም አመልክተዋል።

" የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ " ያሉ ሲሆን " የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ሲሉ ገልጸዋል።

የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት እንደሆኑ አሳውቀዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " ከጥንት ጀምሮ የነበረ ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩ ፦
° ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤
° መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣
° ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን #ተሰሚነትና #ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው " ብለዋል።

" እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጥ ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል " ሲሉም አሳውቀዋል።

ቅዱስነታቸው፤ " በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም " ያሉ ሲሆን " ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም " ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት አስከፊ የሆነ በደል መፈጸሙን የገለጹት ቅዱስነታቸው " አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " ሲሉ ገልጸዋል።

" በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል " ሲሉም አስገንዝበዋል።

ጉባኤውም በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ወንድሞቼ!
ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡

እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን?

ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Forwarded from የስነ ፌለክ /Astronomical (Yonas)
#የአባቶች_ምክር

#ሀሜት :- ያለመሳሪያ ሰውን መግደል ነው።

#ማጉረምረም :- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።

#ቁጣ :-  ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው።

#ብስጭት :- የተበሳጨንበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የኃጢያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው።

#መዋሸት :-  እውነተኛን ሰው ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው።

#መርገም :- አቅም ሲያንስ ወደላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።

#መሳደብ :- ህሌናን የሚያቆስል ቁስሉ ተሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው።

#ዋዛ_ፈዛዛ :- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።

#የማይገባ_ሳቅ :- አላፊ አግዳሚውን የሚያጠምዱበት የአመንዝሮች ወጥመድ ነው።

#መሳለቅ :- በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘብቱበት  የመርገም ስንቁ ወግ ነው።

#ዘፈን :- ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ክፉ ፈላጻ ነው።

#ድንፋታ :- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ ነው።

#መንፈግ :- የሚለምነውን ሰው የሚወጉበት የስስታሞች ፈላጻ ነው።

#በክፉ_መንሾካሾክ :- ቀስ ብለው ሰውን የሚገሉበት የአሳባቂዎች ጩቤ ነው።

#ነገር_ማመላለስ :- የሚዋደዱትን የሚለዩበት የዲያብሎስ የግብር ልጆች መሳሪያ ነው።
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ …

በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ

የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል።

እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ነበረች ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣለች። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች።

በውጭም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ወገኖቼ  ያለኝን ጨርሻለሁ አሁን ላይ ያለኝን ቀሪ ነገር ኩላሊቴን ልስጠው ነውና ገንዘብ ያለው በገንዘቡ የሌለው በሃሳብና በጸሎት አግዙኝ ወንድሜን አድኑልኝ ስለፈጣሪ ተባበሩኝ የሰው ህይወት በማዳናችሁ በፈጣሪ ታገኙታላችሁ።

                   ፍሩታ አሻግሬ
             የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
              1000629004045

ለበለጠ መረጃ
➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929
➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689