Forwarded from የስነ ፌለክ /Astronomical (Yonas)
#የአባቶች_ምክር
#ሀሜት :- ያለመሳሪያ ሰውን መግደል ነው።
#ማጉረምረም :- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።
#ቁጣ :- ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው።
#ብስጭት :- የተበሳጨንበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የኃጢያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው።
#መዋሸት :- እውነተኛን ሰው ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው።
#መርገም :- አቅም ሲያንስ ወደላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።
#መሳደብ :- ህሌናን የሚያቆስል ቁስሉ ተሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው።
#ዋዛ_ፈዛዛ :- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።
#የማይገባ_ሳቅ :- አላፊ አግዳሚውን የሚያጠምዱበት የአመንዝሮች ወጥመድ ነው።
#መሳለቅ :- በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘብቱበት የመርገም ስንቁ ወግ ነው።
#ዘፈን :- ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ክፉ ፈላጻ ነው።
#ድንፋታ :- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ ነው።
#መንፈግ :- የሚለምነውን ሰው የሚወጉበት የስስታሞች ፈላጻ ነው።
#በክፉ_መንሾካሾክ :- ቀስ ብለው ሰውን የሚገሉበት የአሳባቂዎች ጩቤ ነው።
#ነገር_ማመላለስ :- የሚዋደዱትን የሚለዩበት የዲያብሎስ የግብር ልጆች መሳሪያ ነው።