❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካች #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለመንፈስ_ቅዱስ (ለጰራቅሊጦስ) በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና ደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሉ ሉያ "ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ኅምዝ ወይወውዑ አድባር ወአውግር ወኵሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዐባይ ፍሥሓ በሰማያት #ወምድርኒ_ትገብር_ፋሲካ_ተሐጺባ_በደመ_ክርስቶስ። ትርጉም፦ ምድርና ሰማይ ይደሰቱ፣ ቀርነ መለከትም ይነፋ፤ ተራሮችና ኮረብቶችም የዱር ተክሎችም ይደሰቱ፤ ዛሬ በሰማያት ታላቅ ደስታ ሆነ፣ #ምድርም_በክርስቶስ_ደም_ታጥባለችና_ፋሲካ (ደስታን) ታደርግ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #ጰራቅሊጦስ፦ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኃጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጉምን ይሰጣል መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ፤ ከትንሣኤ በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠርጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
❤ "እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ" አላቸው። ሁለተኛም "ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል" አላቸው።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው "እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናስበውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ"። ይህንንም ሲነግራቸው እንሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደ ርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ። የተከፋፈለ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ። በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ።
❤ ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ "በዓለ ኃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ። ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ መላው የተከፋፈለ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀምጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየአገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና። ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ። "እንሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ፣ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን። በሁለት ወንዝ መካከል በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣ በፍርግያም በጽንፍልያም፣ በግብጽም፣ በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እንሆ እንሰማቸዋለን። ሁሉም ደግጠው የሚናገሩትን አጡ። እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው "ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል" አሉ።
❤ ቅዱስ ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው "የይሁዳ ሰዎቼ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደለም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና። ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለውነው፦ "እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ መንፈሴ አሳድራለሁ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁ ሕልምን ያልማሉ። ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ። ደግሞ እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሓይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል"።
❤ ዳዊትም እንዲህ አለ "ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ድኅነትህንም ስጠኝ። በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው"። ሁለተኛም "መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ" አለ። ደግሞ "ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ" አለ። ደግሞም "በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ"።
❤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ"።
❤ ጌታችንም እንዲህ አለ "ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ። ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። እኔ ሰላም እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣች። እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም። እኔ እሔዳለሁ ወደ እናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ"።
❤ ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ "እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይምሰክራል። እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ። እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና። ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሰዋል። ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንዲህም አታዩኝም ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና" አላቸው። "የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ። ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና"።

❤ ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ "ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁ የሚለን"። ጌታ ኢየሱስ ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐውቀባቸው እንዲህ አላቸው "ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ። እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል"።
❤ ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ "ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ። ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ። ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ" አላቸው ። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋራ ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የግንቦት18 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን"። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ"። መዝ 77፥65-66። የሚነበቡት ወንጌላት ማቴ 28፥1-ፍ.ም፣ ማር16፥1-ፍ.ም፣ ሉቃ 24፥1-13።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር። ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ። ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።" መዝ117፥24-25 ። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥20-41፣ 1ጴጥ 1፥1-13 እና የሐዋ ሥራ 2፥1-21 ወይም 2፥22_37። የሚነበው ወንጌል ዮሐ 20፥1-19 ወይም 14፥1-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጰራቅሊጦስ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ #ግንቦት ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ #ከእናቱ_ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል ማርያም #ከአረጋዊው_ቅዱስ_ዮሴፍና #ከቅድስት_ሰሎሜ ጋራ ወደ #ግብጽ_ምድር_በስደት_ለወረዱበት ዓመታዊ በዓል፣ #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቅ_ነቢያት አንዱ ለሆነው #ለነቢዩ_ዕንባቆም_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ #ለአሮን_ልጅ #ለካህኑ_ለቅዱስ_አልዓዛር ለዕረፍት በዓልና #ከእንጽና_አገር ለሆነ ለከበረ ለቀሲስ #ቅዱስ_አብቊልታ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ ከቅዱሳን አርከሌድ፣ ከቴፍላስና ከማርዩ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን፡ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #በዚች_ቀን_የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋራ ወደ ግብጽ ምድር ወረደ።
❤ ያን ጊዜም እርሱ ጌታ የሁለት ዓመት ሕፃን ነበር። ወንጌላዊ እንዳለ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ "ተነሥተህ ሕፃኑና እናቱ ን ይዘህ ወደ ግብጽ ምድር ሽሽ ተመለስ ብዬ እስምነግርህም በዚያው ኑር"።
❤ ጌታችንም ወደ ግብጽ መምጣት ስለ ሁለት ሥራዎች ነው። አንዱ ኄሮድስ ቢያገኘው ሊገድለው እንደአይችል። ስለዚህ ሌሎች ትስብእቱ ምትሐት ነው ብለው አንዳያስቡ። ሁለተኛው የግብጽ ሰዎች በመካከላቸው በመመላለሱ ጸጋውን እንዲያገኙ ጣዖታትንም ቀጥቅጦ ለማጥፋት "እንሆ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል ጣዖታትም በፊቱ ይወድቃሉ" ያለው የነቢይ ኢሳይያስ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ ሸሸ በመጀመሪያም የደረሰበት አገር ስሙ በስጣ ይባላል አልተቀበሏቸውም በዚያም የውኃ ጒድጓድ ቆፈሩ ያቺም ውኃ ለሩቆች ፈዋሽ ስትሆን ለዚያች አገር ሰዎች ግን መራራ ሆነች። ከዚያም በጉምኑዲ መንገድ ተጒዘው ወንዝ ተሻግረው ወደ ምዕራብ ደረሱ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ተረከዙን በአለት ላይ አደረገ በተረከዙም አምሳል በአለቱ ላይ ተቀረጸች እስከ ዛሬ ያም ቦታ የጌታችን የተረገዝ ቅርጽ ተባለ። ጌታችንም እመቤታችን ድንግል ማርያምን "እናቴ ሆይ በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ይሠራ ዘንድ እንዳለው ዕወቂ። በውስጡም ድንቅ ተአምራትን አደርጋለሁ ስሙም ደብረ ምጥማቅ ይባላል" አላት።
❤ ከዚያም ወደ ፀሐይ መግቢያ ወዳለ ባሕር ሔዱ የአስቄጥስንም በረሀ ዱር ከሩቅ አዩ። ጌታም በላዩ ባረከ እናቱንም "እናቴ ማርያም ሆይ በዚህ ዱር ውስጥ ብዙዎች ሰዎች መነኰሳትን ሁነው በገድልም ተጸምደው በመላእክት አምሳል ያገለግሉኛል"።
❤ ከዚያም በፀሐይ መውጫ በኵል ወደአለ ተራራ ሒዱ ዮሴፍም የሚመረኰዘው በትር በእጁ ነበር ጌታችንም "ይህ ቦታ የሚቃጥል በረሀ ነውና እንቀመጥ" አለ። ጌታችንም የዮሴፍን በትር አንሥቶ ሰበራት ጥቃቅን ስብርባሪዎች አድርጎ በዚያ ቦታ ተከላቸው። በከበሩ እጆቹ ጒድጓድ ማሰ መዓዛው የሚጣፍጥ ውኃ ፈልቆ ፈሰሰ ከእዚያ ውኃም በመሐል እጁ እየዘገነ የተከላቸውን ስብርባሪዎች አጠጣቸው። ወዲያውኑ በቀሉ አድገውም ታላላቅ ዛፎች ሆኑ ከእርሳቸውም ጣፍጭ ሽታ ሸተተ። እርሱም ከሽቱዎች ሁሉ እጅግ የሚጣፍጥ ነው በለሳንም ብሎ ጠራቸው። እናቱን ድንግል እመቤታችንንም "እናቴ ሆይ ይህ የተከልኩት በለሳን እስከ ዓለም ፍጻሜ ከዚህ ይኖራል የክርስትና ጥምቀትንም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ለሚጠመቁ ከእርሱ ቅባት ይገኛል" አላት የዚያም ቦታ ስም መጠሪያ ነው።
❤ ከዚያም ብንህሳ ወደሚባል አገር ሔዱ ትርጓሜው ቤተ ኢየሱስ የሆነ በይሱስ ወደሚባልም ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በሽታውን ደዌውን ሁሉ የሚፈውስ የጒድጓድ ውሃ አደረገ። ሁለተኛም በአንዲት የጒድጓድ ውኃ ምልክትን በየዓመቱ አደረገ ይኸውም ከቀኑ እኵሌታ በማዕጠንትና በጸሎት ጊዜ ለእግዚአብሔር በዚያች ውኃ ጒድጓድ ዕጣንን ሲያሳርጉ የከበረ የወንጌል ንባብም ሲፈጸም በዚያች ጒድጓድ ውስጥ ያለ ውኃ ወደ ላይ ወጥቶ እስከ ጒድጓዱ አፍ ይደርሳል። ከእርሱም ይባረካሉ ከዚያም በኋላ እንደ ቀድሞው ወደ ቦታው ይመለሳል። ውኃው ከነበረበት እስከ ደረሰበት ይሰፍሩታል። ሃያ ክንድ የሆነ እንደሆነ የጥጋብ ዘመን ይሆናል ዐሥራ ሰባት ክንድ ከሆነ ግን በግብጽ አገር ታላቅ ረኃብ ይሆናል።
❤ ከዚያም ወደ እስሙናይን አገር ሔዱ በዚያ ያሉ ጣዖታትም ወድቀው ተሰባበሩ። እነርሱም ስሙ አፍሎን ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጡ። በዚያም የእሸ እንጨት ዛፎች አሉ ለጌታችንም ሰገዱ እስከ ዛሬም እንደ ሰገዱ ናቸው። ከዚያም ወደ ደብረ ቊስቋም ሒደው በውስጧ ስድስት ወር ተቀመጡ በዚያም በሽታን ሁሉ የሚያድን የጉድጓድ ውኃ አደረገ።
❤ ጌታችንም የፈቀውን በግብጽ የሚኖርበት ወራት በፈጸመ ጊዜ ይኸውም ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ነው። ኄሮድስም ከሞተ በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ "የሕፃኑን ነፍስ የሚሹት ሙተዋልና ተነሣ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ተመለስ" አለው። ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት። ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ። ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች። ከዚያም ጌታችን የተከለው የክርስትና ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚመጣው ነው። በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅዱሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከበርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው።
❤ በጌታችን መመለስም "ልጄን ከግብጽ ጠራሁት" ያለው የኦዝያን ትንቢት ተፈጸመ። ስለዚህም ተአምራትን በግብጽ ድንቅ ሥራንም በጣኔዎስ በረሀ ያደረገ በማለት እየዘመርን በዚች ዕለት መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል። ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ስለ እኛ ለተሰደደ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታውና ምሕረቱ ይሁን። አምላክን የወለደች የተባረከች የድንግል እመቤታችን ማርያም በረከቷ የቅዱስ ዮሴፍና የቅድስት ሰሎሜም በረከታቸው ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ነቢዩ_ቅዱስ_ዕንባቆም፦ ይህም ቅዱስ በአንዲት ዕለት እህሉን ለሚያጭዱለት ምሳቸውን አዘጋጅቶ ተሸክሞ ሲሔድ መልአክ ተገልጾለት "ይህን መብል በባቢሎን አገር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ ላይ ለነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ውሰድ" አለው። ዕንባቆምም "ጌታዬ ሆይ ባቢሎንን አላየኋት ጒድጓዱንም አላውቀው" አለው። የእግዚአብሔር መልአክም በራሱ ጠጉር ያዘው ምግቡን በእጁ እንደያዘ ወሰደውና ጒድጓዱ እንደተዘጋ አስገባው ምግቡንም ሰጥቶ መገበው ወዲያውኑ ዕንባቆምን ወደ ይሁዳ አገር መለሰው።

❤ በአረጀና በሸመገለም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ከተማረኩበት ተመልሰው ቤተ መቅደስን ሠሩ። ቅዱስ ዕንባቆምም ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በታላቅ ደስታም ተቀበሉት ትንቢቱንም ሊሰሙ ወደርሱ ተሰበሰቡ አፉንም ከፍቶ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለ "አቤቱ ድምፅህን ሰማሁ ሰምቼም ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ" አለ። ስለ መድኃኒታችንም መውረድና በይሁዳ ክፍል በሆነች በቤተ ልሔም ስለመወለዱ ሲናገር "የተመሰገነ እግዚአብሔር ግን ከፋራን ተራራ ከቴማን ከይሁዳ አውራጃ ይመጣል" ብሎ እስከ መጨረሻው ተናገረ ከነቢያት መጻሕፍትም ጋራ ደመርዋት።
❤ ከዚህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች አንዲት ሴት ወደርሱ መጣች እያለቀሰችም እንዲህ አለችው "ሁለት ልጆች ነበሩኝ ጣዖት እንዲአመልኩ ፈለጉአቸው እምቢ በአሉ ጊዜም ገድለው በጐዳና ላይ ጣሉአቸው"። ተገድለው ወደአሉበትም አብሮዋት ሔደ ነፍሳቸውንም ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው ልመናውንም ተቀብሎ በሕይወት አነሣቸው"።
❤ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ዘመዶቹን ጠራቸው። እንደሚሞትም ነገራቸውና አንዲት ሰዓት ያህል ወደላይ እየተመለከተ ተቀመጠ። እንሆ እንደ ሰው ክንድ ያለች ታላቅ ክንድ የቤቱን ጣሪያ ሠንጥቆ ወረደች ወደ አፉም ተዘርግታ ነፍሱን ወሰደች ያን ጊዜም ዐረፈ። በክርስቲያን ንጉሥ በአንስጣስዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ ገድሉን በአነበበ ጊዜ አድንቆ በግብጽ ደቡብ ቀርጣስ በሚባል ቦታ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሠራለት እርሷም በዚች ቀን ከበረች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የነቢዩ ቅዱስ ዕንባቆም በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቀሲስ_ቅዱስ_አብቊልታ፦ ይህ የእንጽና አገር የሆነ ባለ መድኃኒት ነው በሽተኞችን በጎ ሥራ በመሥራት ያለ ዋጋ ያክማቸዋል ደግሞም የሚበሉትን፣ የሚጠጡትን፣ የሚለብሱትን የሚሹትን ሁሉ ይሰጣቸዋል።
❤ በዚያም ወራት ወደ ሰዒዲ አውራጃ ወደ መኰንኑ አርያኖስ ዲዮቅልጥያኖስ ላከ የዚያችን አገር ሰዎች ለጣዖታት እንዲሰግዱ ያስገድዳቸው ዘንድ። በዚያንም ጊዜ ይህን ቅዱስ ያዙት ወደ እስሙናይንም ወስደው በመኰንኑ ፊቱ አቆሙት መኰንኑም ወደርሱ ይመልሰው ዘንድ በጎ ቃልን ተናገረው ሊመለስም ባልቻለ ጊዜ ቆዳው እስቲሠነጣጠቅ እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ በሕይወት እያለ በእሳት አቃጠሉት ገድሉንም በዚህ ፈጸመ ምዕመናን ወጥተው በድኑን ወሰዱ ከከተማው ደብባዊ በሆነ ተራራ ላይ ገንዘው በክብር ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የቅዱስ አብቊልታ በረከቱም ከእኛ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ምንጭ፦ #የግንቦት_24 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለአልዓዛር_ወፊንሐስ ካህናት ዐበይት እለ ቅቡዓን በቅብዐ ዕረፍት"። ትርጉም፦ በጣፈጠ ቅብዐ ክህነት ለተቀቡ ለታላላቆች ካህናት አልዓዛር ና ፊንሐስ ሰላምታጨይገባል። #ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወየአም እግዚአብሔር ፍኖተ ንጹሐን። ወለዓለም ውእቱ ርስቶሙ። ወኢይተሐፈሩ በመዋዕለ እኩያት"። መዝ 36፥18-19። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥40-ፍ.ም።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦"ዘገብረ ተአምረ በግብጽ። ወመንክረ በሐቅለ ጣኔዎስ። ወረሰየ ደመ ለአፍላጊሆሙ"። መዝ 77፥43-44። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 4፥4-13፣ ራእ.ዮሐ 12፥13-ፍ.ም ወይም 1ኛ ጴጥ 1፥8-13 እና የሐዋ ሥራ 12፥20-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ማቴ 2፥13-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል፣ የነቢዩ ዕንባቆም የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለሐዋርያት_ለሰኔ_ጾም እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ጾም_ትፌውስ_ቁስለ_ነፍስ ወታጸምም ኲሎ ፍትወታተ ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና እስመ #ሙሴኒ_ጾመ_በደብረ_ሲና"። ትርጉም፦ #ጾም_የነፍስን ቁስል ታድናለች የሥጋ ፍትወትንም ታስወግዳለች ለጎልማሶችም ደህንነትን (መታገስን) ታስተምራለች #ሙሴም_በሲና_ተራራ_ጾሟልና፡፡ #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው_ላይ።
✝️ ጾመ ሐዋርያት ✝️
❤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለጾም ሥርዓትና ደንብ አውጥታ ዕድሜው ከሰባት ዓመት ጀምሮ ክርስቲያን እንዲጾመው ካወጣችው ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ አንዱ ከ0ቢይ ጾም ቀጥሎ የሚጾመው ጾመ ሐዋርያት /የሰኔ ጾም/ በመባል የሚታወቀው ነው፡፡
❤ ይህ ጾም ለምን ይጾማል?
❤ ጌታችን ለመዋዕለ ስብከቱ መነሻ ጾምን እንዳደረገ ሐዋርያትም አምላካቸውን አብነት በማድረግ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው የወንጌልን ቃል ለማዳረስ ወደ ዓለም ከመሄዳቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ቤተክርስቲያን (ምእመናን) እነርሱን አብነት አድርገው ይጾሙታል ፡፡
❤ ቤተክርስቲያንም ጳጳሳት ቀሳውስት ዲያቆናት ሥልጣነ ክህነትን ካገኙ በኋላ ወደ አገልግሎት ከመሠማራታቸው በፊት አርባ ዕለት እንዲጾሙ የምታደርገውም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከሐዋርያት ያገኘችውን አብነት መሠረት አድርጋ ነው፡፡
❤ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ይህ ጾም በአንዳንድ ምዕመናን ዘንድ የተሳሳተ አመለካከትና ስያሜ ይዟል፡፡ ይህ የቄስ ጾም ነው ለምዕመናን አይደለም የሚል የተሳሳተ አመለካከት ሲሆን እውነታው ግን ቤተክርስቲያናችን ለቄስ ለዲያቆን ለምዕመናን ወዘተ ብላ ለይታ ያወጀችው ጾም የለም፡፡ ክርስቲያኖች እንደ ውዴታቸው የሚጾሙት የፈቃድ ጾም አለ ነገር ግን ከአዋጅ ጾም ጋር አይዛመድም ይህ ጾም የአዋጅ ጾም ስለሆነ ቤተክርስቲያን ዕድሜው ከሰባት ዓመት ጀምሮ ክርስቲያን ሁሉ እንዲጾም ታዛለች፡፡
❤ በአጠቃላይ ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን የምታዘውን ሥርዓት በመቀበል ሊጾሙት ያስፈልጋል፡፡ ሐዋርያት አባቶቻችን አብነት አድርገን መንፈሳዊ ሆነ ሥጋዊ ጉዞአችንን ሁሉ መነሻ መድረሻውን በጾምና በጸሎት ማድረግ ይገባናል፡፡ ዕብ 13፥7 "የእግዚአብሔር ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው" እንዲል፡፡ እንግዲህ እኛም ይህን ጾም ጾመን ሐዋርያት ያገኙትን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን እንድናገኝ የአምላካችን ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ ምንጭ፦ ✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ።
❤ ጾሙ ለአገራችን ኢትዮጵያና ለኦርቶዶክስ ተሐዋሕዶ ሃይማኖታችን ሰላም፣ ፍቅር አንድነትንና መተሳሰብን የሚያመጣ ይሁንልን። መልካም የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

❤ #ግንቦት ፳፭ (25) ቀን።
❤ እንኳን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_የዮሴፍን_በትሮች በአረንጓዴ ቦታ ላይ ተክሎ ወዲያውኑ #ዛፎች_ላደረገበት ዓመታዊ በዓል (ይህ በዐል #ከእመቤታችን_ከ33_በዐላት አንዱ ነው)፣ #ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም #ለአክስት_ልጅ #ለብፅዕት_ቅድስት_ሰሎሜ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ ስብስጣ ከሚባል ለሆነ በዕረፍቱ ጊዜ ጌታችን ተገልጦ ብዙ ቃል ኪዳንን ለሰጠው #ለአባ_ኄሮዳና #ከእንዴናው_አገር አገር ለሆነ ለከበረ በቀን መቶ እንዲሁ በሌሊትም መቶ ጸሎታትን ይጸልይ ለነበረ #ለቅዱስ_ኮጦሎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት #ለዕረፍቱ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡት፦ #ከአባ_ኄሮዳ_ማኅበረ_ሰማዕታት #ከሠላሳ_ሺህ_አምስት_መቶ ሰዎች፣ #ከከበሩ_ቅዱሳን_በላኖስ_ከእሎንትራን_ከራምኔሳ፣ከ#መቶ_ኃምሳ_ሰማዕታት፣ #ከቈስጠንጢኖስና ከእናቱና #ከሔላም ከመታሰብያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #የእመቤታች_የአክስት_ልጅ_ቅድስት_ሰሎሜ፦ እርሷም የማጣት ልጅ የሌዊ ልጅ የሚልኪ ልጅ የካህኑ አሮን ልጅ ናት። ለማጣት ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱ ስማ ቅድስት ማርያም ነው የሁለተኛዪቱ ስም ቅድስት ሶፍያ የሦስተኛዪቱ ስም ቅድስት ሐና ነው ይቺም ቅድስት ማርያም ቅድስት ሰሎሜን ወለደቻት ቅድስት ሶፍያም ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት ቅድስት ሐናም ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለጀቻት።
❤ እመቤታችንም ድንግል ስትሆን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወለደችው ጊዜ ይቺ ቅድስት ሰሎሜ የእመቤታችንን አወላለድ እንደ ሴቶች ሁሉ አወላለድ መስሏት ተጠራጠረች ከዚህም በኋላ የድንግል እመቤታችንን ገላዋን ዳሠሠቻት ያን ጊዜ እጇ ተቃጠለ ሕፃኑን በዳሠሠችው ጊዜ ደግሞ ዳነች። በዚህም በኅቱም ድንግልና አምላክን እንደወለደችው አወቀች።
❤ ከተረገመ ኄሮድስ ፊት እመቤታችን በሸሸች ጊዜ ከቅዱስ ዮሴፍ ጋራ በመሆን አብራ በመሰደድ የእመቤታችንን ድካሟን ተካፍላ አገለገለቻት ከስደት እስከ ተመለሱ ድረስ ሕፃኑን ታዝለዋለች የምታጥብበት ጊዜ አለ። መድኃኒታችን ሰው በሆነበት ወራት ሁሉ አልተለየችም በመከራውም ቀን ከእመቤታችን ጋራ ከከበሩ ሁሉ ሴቶች በትምህርቱ ወራት ከተከተሉት ጋራ እያለቀሰች ነበር። በተነሣባት ዕለት ወደ መቃብር ገሥግሣ ከሐዋርያት ቀድማ ያየች ናት።
❤ በኃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከባልንጆሮቿ የከበሩ ሴቶች ጋራ ሰማያዊ ሀብትን ተቀብላ በክብር ባለቤት መድኃኒታችን ስም ሰበከች ብዙዎችንም አሳመነች። ከአይሁድም ብዙ ስድብና ሽሙጥ አገኛት ከዚያም ግንቦት25 ቀን ዐረፈች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሰሎሜ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከሁላችን ጋራ ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱስ_ኮጦሎስ፦ የዚህም ቅዱስ እናትና አባቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ናቸው አባቱም የእንዴናው ገዥ መኰንን ነው ልጅ አልነበረውም ይህን ቅዱስ ልጅ እስከ ሰጠው ድረስ ጌታችንን አዘውትሮ ይለምነው ነበር የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት አስተማረው። ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ሆነ ለራሱም ሥርዓት በመሥራት በቀን መቶ እንዲሁ በሌሊትም መቶ ጸሎታትን ይጸልያል። ጥቂት በአደገ ጊዜም ወላጆቹ ሊአጋቡት ፈለጉ እርሱ ግን አልፈቀደም። ነገር ግን ከእርሱ በኋላ የተወለደች ሴት ልጅ ነበረቻቸውና እርሷን ከአርያኖስ ጋራ አጋቧት። አባቱም ከሞተ በኋላ ለስደተኞች የእንግዳ መቀበልን ጀመረ።
❤ ከዚህም በኋላ የጥበብ መጽሐፍን ተምሮ ሐኪም ሆነ። በሽተኞቹ ሁሉ ወደ ርሱ ይመጣሉ እርሱም ያለዋጋ ይፈውሳቸዋል። ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ አርያኖስ ስለ ሹመቱ ከንጉሡ ጋራ ተስማምቶ ሰማዕታትን የሚያሠቃያቸው ሆነ። ይህም ቅዱስ ሰማዕት ለመሆን ይተጋ ነበር ወደ ፍርድ አደባባይም ሒዶ አርያኖስን ንጉሡንም አለቆቹን ሁሉ ረገማቸው ጣዖታቱንም ሰደበ። አርያኖስ ስለ እኅቱ በእርሱ ክፋ ሊአደርግበት አልቻለውም ወደ እኅቱ ላከው እንጂ። እርሷም ከመታሠር አዳነችው።
❤ ከአርያኖስም በኋላ ሌላ መኰንን ተሾመ የዚህ የቅዱስ ኮጦሎስን ዜና ነገሩት። ጭፍራ ልኮ ወደርሱ አስመጣውና በርሱ ላይ በመቆጣት "ለአማልክት ካላጠንክ ይህ ካልሆነ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይሃለሁ" አለው። ቅዱሱም "እኔ ለረከሱ አማልክት ዕጣን አላቀርብም ለክብር ባለቤት ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹሕ መሥዋትን አቀርባለሁ እንጂ" ብሎ መለሰለት። በዚያን ጊዜም መኰንኑ ተቆጥቶ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። የእግዚአብሔር መልአክም ወደ ርሱ መጥቶ ይፈውሰው ያጽናናውና ያረጋጋው ነበር።
❤ ጌታችንም በእጆቹ ታላቅ የሆነ ድንቆች ተአምራትን አደረገ። ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ በሰይፍ ራሱን ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። የሰማዕትነትንም አክሊል ግንቦት25 ቀን ተቀበለ ቤተሰቦቹም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሩት። ከሥጋውም እጅግ ብዙ ድንቆች ተአምራት የሚታዩ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ኮጦሎስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ኄሮዳ፦ ይህም አባት ስብስጣ ከሚባል አገር የሆነ ነው። ከከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ የስደት ወራት በሆነ ጊዜ ይህ ቅዱስ አባ ኄሮዳ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ይፈራ ነበር።
❤ በአንዲት ሌሊትም በአልጋው ተኝቶ ሳለ እርሱም ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ በማሰብ "በኃላፊው ዓለም ውስጥ መኖር ምን ይጠቅማኛል። በከበረ ወንጌል የተናገረውን የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ይህን ዓለም ያልካደ ሊያገለግለኝ አይችልም ያለውን ሰምቻለሁና አሁንም ተነሥቼ ሒጄ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ደሜን አፈሳለሁ" አለ። ይህንንም በልቡ ሲያስብ እንሆ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደርሱ መጥቶ "የከበርክና የተመሰገንህ ኄሮዳ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ እግዚአብሔር የክብር ዙፋን አዘጋጅቶልሃልና እኔም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነኝ። እኔም ወደ ፍርድ አደባባይ ከአንተ ጋራ እሔዳለሁ በከበረ ሥጋህም ላይ ምንም የሚበረታብህ የለም" ብሎት ሰላምታም ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ።
❤ ከዚህም በኋላ ብፁዕ አባ ኄሮዳ ወደ ምዕራባዊ አገር ወጣ። ፊቱንም ወደ ምሥራቅ መልሶ እንዲህ ብሎ ጸለየ "ልዩ ሦስት አንድ አምላክ ሆይ ጌትነት በረከት ክብር ገንዘብህ የሆነ ለአንተም ለብቻህ ስግደትና አምልኮት የሚገባህ የተሳልኩትን እስከምፈጽም ታጽናኝ ዘንድ እለምንሃለሁ"። ይህንንም ብሎ ወደ ፍርድ ሸንጎ ሔዶ "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በግልጥ ጮኸ። መኰንኑም "ክርስቲያንስ ሁነሃል አገርህ ወዴት ነው? አንተ ማነህ? ስምህስ ማነው? ወገንህስ ምንድነው? አለው። የከበረ ኄሮዳም "በብህንሳ አውራጃ ስብስጣ ከሚባል አገር ነኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ለምድራዊ ሟች ለሆነ ንጉሥ ሳገለግል ኖርኩ እንግዲህስ ሕያው ለሆነ ሰማያዊ ንጉሥ አገለግላለሁ" ብሎ መለሰለት።

❤ ሉክያኖስ መኰንንም "ብዙ ገንዘብ ሰጥቼህ ከጭፍሮቹ ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ከፍ አድረግህ ዘንድ ለአማልክት ለአጵሎንና ለአርዳሚስ ለመሠዋት ተዘጋጅ" አለው። ቅዱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "ልብ የሌለህ ደንቆሮ ሆይ እምነቱን በሰው ላይ ላደረገ ሰው ወዮለት ግን እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ የሆነ የተመሰገነ ነው የሚል በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፏል። እኔም ለረከሱ አማልክት አልሠዋም አለኝታዬ እግዚአብሔር ስለሆነ ለእርሱ ብቻ እሠዋለሁ"። ያን ጊዜም መኰንኑ ተቆጥቶ እንዲገርፉትና እሾህ ባላቸው በብረት ዘንጎችም እንዲደበድቡት ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ጌታችንም በመልአኩ እጅ አጽንቶ አዳነው ጤነኛም ሆነ። ሕዝቡም ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ። ቊጥራቸውም ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ ነው። መኰንኑም መሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ።
❤ እንሆ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጸለትና እንዲህ አለው "ብፁዕ ኄሮዳ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን አትፍራ እኔ ፈጣሪህ ክርስቶስ ነኝ እንሆ መቀመጫህን ከቅዱሳን ጋራ በሰማያት አዘጋጅቼልሃለሁ። በእውነት እነግርሃለሁ በመታሰቢያህ ቀን መከራ ድካምህን አስቦ መሥዋዕት፣ ለሚያቀርብ ለድኃ ምጽዋትን ለሚሰጥ በእንስሶቹ ውስጥ ርባታ ይሆናል። በቤቱም የተባረከ ልጅ አይታጣም። ሰይጣንም በእርሱ ላይ በሥራውም ሁሉ ሊበረታበት አይችልም። የገድልህን መጽሐፍና ስምህን የሚጽፈውንም እኔ በሕይወት መጽሐፍ ስሙን እጽፋለሁ የዕዳ ደብዳቤውን እደመስሳለሁ። ደግሞ በችግር በመከራ ውስጥ ስምህን ጠርቶ የሚለምነኝን ከመከራው ሁሉ እኔ አድነዋለሁ። መታሰቢያህንም ለሚያደርግ ሁሉ በደሉን ሁሉ እተውለታለሁ ሰላሜም ከአንተ ጋራ ይሁን" ይህንንም ብሎ መድኃኒታችን ከእርሱ ዘንድ ዐረገ።
❤ የከበረ አባ ኄሮዳም ፍጹም ደስታን ተደሰተ። ተጋድሎውንም በሚፈጽምበት ጊዜ በዚያ ወደ አሉት ሕዝቡ ተመልሶ "ከውስጣችሁ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ያለ ከሆነ ሥጋዬ በጎ በረከትን እስከሚያደርግለት ድረስ ሥጋዬን ወስዶ በእርሱ ዘንድ ያኑረው" አላቸው። ያን ጊዜም አንገቱን ዘረጋላቸው በሰይፍም ቆረጡት የምስክርነቱ አክሊልንም በግንቦት ወር በሃያ አምስት ቀን ተቀበለ።
❤ ከሦስት ወር በኋላም ዘመዶቹ መጡ ሥጋውንም ወሰዱ ተሸክመውም ወደ አገሩ ስብስጣ አድርሰው በአነፁለት ቦታ አኖሩት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ ለድውያን ፈውስ ተገኘ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኄሮዳ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ #የግንቦት_25_ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለኄሮዳ_እግዚአብሔር_ዘሐወጾ። ከመ የሀቦ ኪዳነ በኢሐስዎ ወዐምፆ። ለዝ መዋዒ ትግርምት መኰንን ኢያደንገፆ። በብልሐ ቅትራት አመ ገቦሁ ደጐፆ። በአእዳወ ኀፂን ካዕበ እንዘ ይጸፍዕ ገጾ። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የግንቦት_25።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አድኅነኒ እምደም እግዚአብሔር አምላክ መድኃኒትየ። ይትፌሣሕ ልሳንየ በጽድቀ ዚአከ እግዚኦ። ትከሥት ከናፍርየ ወአፉየ ያየድዓ ስብሓቲከ። መዝ 50፥14-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 9፥20-ፍ.ም።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ዘአቀመ ስምዐ ለዮሴፍ። አመ የሐውር ብሔረ ግብጽ። ወሰምዐ ልሳነ ዘኢየአምር"። መዝ 80፥5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 2፥8-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥12-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥8-15። የሚነበበው ወንጌል ማር 15፥40-42። የሚቀደሰው ቅዳሴ የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል፣ የቅድስት ሰሎሞ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።