Fidel Tutorial (ፊደል የጥናት አገልግሎት)
1.92K subscribers
824 photos
23 videos
192 files
170 links
* Professional Tutorial service
* Book online or via phone
* Kg to university
* Flashcards
* online Tutorials
Contact
+251979795154
+251979795468

Youtube: https://www.youtube.com/@FidelTutorial


To become a tutor
join https://t.me/fideltutores
Download Telegram
#MoE

• መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

• 200, 000  ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ  ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር )  በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ  እንደገለጹት መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ  ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች  በአንድ ጊዜ ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት  በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት አቶ ሰይድ " ይህ የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ  በመሆኑ ነው " ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)
#MoE

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ እንድታስተካክሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና #የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ ተማሪዎች (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች፣ ነፍሰጡር የሆናችሁ፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ያለባችሁ ተማሪዎች፣ ...) ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ ብቻ መላክ አለባችሁ፦ https://student.ethernet.edu.et

Source: @tikvahethiopia
#MoE

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያረጋገጠውና ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተላከ ደብዳቤ፦

➤ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን ነሐሴ አጋማሽ ላይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ታቅዷል።

➤ የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እስከ ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ ታሳቢ ተደርጓል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በመንግስት የኒቨርሲቲዎች የሚደለደሉትንና በራሳቸው ወጪ በመሸፈን በግል የሬሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን በተመለከተ፦

➤ የሬሚዲያል ፕሮግራም ለአራት ወራት ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ታቅዷል።

➤ የሬሚዲያል ፕሮግራም በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ በሁለት መስክ ተከፍሎ ከማዕከል በተዘጋጀ ይዘት መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች ተጨማሪ የሚያክሉትን በማካተት በተዘጋጀው መነሻ መሰረት ፕሮግራሙ እንዲከናወን ታቅዷል።

➤ የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 በመቶ እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70 በመቶ ተመዝነው በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ በቆዩበት ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል።

(ተጨማሪውን ከላይ ከተያያዘው ደብዳቤ ያንብቡ፡፡)

Source: @tikvahethiopia                                      
#MoE

የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ዛሬ የካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ይፋ ይደረጋል።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማወቅ ተከታዮቹን አማራጮች ይጠቀሙ፦

Website:  https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር ያሳውቃሉ ተብሏል።

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

Source: @tikvahethiopia
#NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

Credit : #MoE

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
👍1
#MoE #ይፋዊ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ #ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
👍2
#MoE

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

Via @tikvahuniversity
👍2
#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
👍2
#ExitExam

" ፈተናው የሚሰጠው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን " - ትምህርት ሚኒስቴር

በ2017 ዓ.ም በሰኔ ወር የሚሰጠው የመውጫ ፈተና መመዝገቢያ ጊዜ እስከ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ብቻ የተራዘመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

እስከ አሁን ያልተመዘገቡ የድጋሚ ተፈታኞች (resitters) ከዚህ በፊት ለምዝገባ በተከፈተውና በተገለጸው መመዝገቢያ ፕላትፎረም https://exam.ethernet.edu.et በኩል ገብተው ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ ብሏል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ለመውጫ ፈተና የሚቀመጡ ተፈታኞችም በተቋሞቻቸው በኩል መመዝገባቸውን እንዲያረጋግጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ፈተናው ከሰኔ 2-10/2017 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

ለመውጫ ፈተናው የሚያመለክቱ አመልካቾች ለመመዝገብ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ (ፋይዳ) ሊኖራቸው እንደሚገባና ፤ ከግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በኋላ ምዝገባ እንደማያስተናግድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE

@tikvahethiopia
👍1