Fidel Tutorial (ፊደል የጥናት አገልግሎት)
2.08K subscribers
857 photos
23 videos
192 files
185 links
* Professional Tutorial service
* Book online or via phone
* Kg to university
* Flashcards
* online Tutorials
Contact
+251979795154
+251979795468

Youtube: https://www.youtube.com/@FidelTutorial


To become a tutor
join https://t.me/fideltutores
Download Telegram
ተከፋይ Intern መሆን ይፈልጋሉ?

#ደረጃ_ዶት_ኮም መረጃ የሚሰበስቡ ተከፋይ ተለማማጅ ሰራተኞች/Interns እየፈለገ መሆኑን አሳውቋል።

አመልካቾች ከሚከተሉት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአንዱ ተመራቂ ተማሪዎች የሆኑናና በዚያው አካባቢ የሚኖሩ መሆን አለባቸው።

➤ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ

➤ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ

➤ ቀብሪ ዳር ዩኒቨርሲቲ

➤ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ

➤ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ

➤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

➤ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

➤ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው

ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም

ለማመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScCC2eEOQ8c8BkxkBGPXy2pKUpgofa1gR1EdzlHtovDDSc9qg/viewform
Fidel Educational Consultancy

-Fidel guides students to be innovative and opens up an opportunity to explore and try different Educational sectors.

-Ethical Children that are well mannered, decent, considerate and respectful.

-Confident children that communicate well and promote a healthy companionship with others.

call us.
0979795154
0979795468.
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች "ራስ ገዝነት"

ራስ ገዝ ሆነው የሚደራጁ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም አቀፍ ውድድር አዲስ ፕሬዝዳንቶችን እንደሚመርጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህ አሰራር በአገር ውስጥ ውድድር ተወስኖ የቆየውን የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ቅጥር ሂደት በማስፋት የውጭ ዜጎችም ጭምር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪነት እንዲወዳደሩ ዕድል የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 10 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ለማድረግ ዕቅድ ይዟል። በዚህ እቅድ ከተካተቱት ውስጥ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች ይገኙበታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው በጀት ዓመት የራስ ገዝ አስተዳደርን ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው የመንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን ይጠበቃል።

መንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶቻቸውን ከሀገር ውስጥ ካሉ ምሁራን አወዳድረው ሲቀጥሩ ቢቆዩም፤ በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች (በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በመቐለ ዩኒቨርሲቲዎች) ለተወሰኑ ዓመታት የውጪ ዜጎችም በፕሬዚዳንትነት ተመርጠው አገልግለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች “ራስ ገዝ” መሆናቸው የአስተዳደር፣ የአካዳሚ፣ የፋይናንስ እና የሰው ኃብት አስተዳደራቸው ላይ ነጻነት እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደር እና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር ተናግረዋል።

በተለያዩ አገራት በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ እና በአመራርነት የሚሰሩ ዳያስፖራዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎችን ቢመሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ ሲሉም አክለዋል። 

ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ሊኖራቸው የሚጠበቀው የትምህርት ደረጃ “ዶክትሬት ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የሚወክል ትምህርት እና ልምድ” መሆን እንዳለበት በመመሪያው ሰፍሯል። ሆኖም የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች “በልዩ ሁኔታ” ሊመረጡ እንደሚችሉ በመመሪያው ተቀምጧል። 

እስካሁን በነበረው አሰራር በትምህርት ሚኒስቴር ሹመት የሚያገኙ ፕሬዝዳንቶች የሥራ ዘመናቸው ስድስት ዓመት ሲሆን ለአንድ ተጨማሪ ጊዜ ሊመረጡ ይችላሉ። ምክትል ፕሬዝዳንቶች በአንጻሩ ሹመታቸው የሚጸድቀው በዩኒቨርስቲዎች ቦርድ ሲሆን አራት ዓመት የስራ ዘመን ይኖራቸዋል።

ራስ ገዝ እንደሚሆኑ የሚጠበቁ ዩኒቨርስቲዎች፤ ፕሬዝዳንቶቻቸውን የሚመርጡበትን መስፈርት፣ የአገልግሎት ዘመን እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚወስኑ ዝርዝር ድንጋጌዎች እንደሚኖራቸው ዋና ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ያለ ትምህርት ሚኒስቴር ጣልቃ ገብነት ፕሬዝዳንቶቻቸውን በቦርድ ማጽደቅ እንደሚችሉ ተገልጿል። #ኢትዮጵያኢንሳይደር
Aastu.Final.Exam.Collection.pdf
4.9 MB
📚Aastu University ‼️
📚All Final Exams
📚  ፈተና  በቀጣይ  ፉይናል ያለባቹ ሞክሩት

❗️የ ዘንድሮ ነው(2014) ፎቶ በእንደዚህ መልኩ አንስታችሁ ላኩልን። ለናንተም ውጤታችሁን ፎቶ ማንሳት በኋላ ውጤታችሁ ችግር ቢያጋጥመው መፍትሔ ይሆናል።
 
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተመረጡ የጤና መስክ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር አመልክታችሁ የተቀመጡ መስፈርቶችን ያሟላችሁ አመልካቾች ታህሳስ 17 18 2015 ዓ.ም በአካል በመቅረብ ምዝገባ እንድታከናውን ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አድርጓል።

@tikvahuniversty
📚AAU University ‼️
📚 Entrepreneurship Final Exams 2014 last weak
📚  ፈተና  በቀጣይ  ፉይናል ያለባቹ ሞክሩት

❗️የ ዘንድሮ ነው።
     
ለጓደኛዎ ሼር ያድርጉ🙏👇👇

@Fideltutorial
We are hiring!
Hawassa Branch


Fidel is Inviting University students, fresh graduates and Experienced tutors to assist children on their studies.

Please fill the form below :

Https://forms.gle/KsUieAxdTmejhAUs9

Hawassa 05, near to Lewi resort Round about.
0979795154/0979795468.
#Update #AddisAbaba

የ2ኛውን ዙር የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በ16 / 4 /2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ ዛሬ አሳስቧል።

የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።


🔔ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
@Fideltutorial
Do you want a Tutor?

Fidel Tutorial is in Hawassa to provide Quality Tutors for your Children.

-Private
-Group
-Weekend class
-Special need.

www.Fideltutorial.com
Hawassa 05, Lewi resort Round About.

0979795154
0979795468.
የ2ኛውን ዙር የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ለመፈተን #በአዲስ_አበባ ከተማ አስተዳደር የተመዘገቡ ተማሪዎች በክፍለ ከተማቸው በኩል በ16 / 4 /2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይንስና ቴክኖሎጂ 5 ኪሎ ካምፓስ እንዲገቡ የከተማው ትምህርት ቢሮ ዛሬ አሳስቧል።

የ2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ መግለፁ ይታወሳል።

@Fideltutorial
ፎቶ ፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

አንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቀናት በኃላ መሰጠት የሚጀምረውን 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምረዋል።

ተቋማቱ ከወዲሁ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ከገቡ በኃላ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከተፈቀደላቸው የተቋሙ ሰራተኞች እና ፈተና አስፈፃሚዎች በስተቀር ተፈታኞች ባሉባቸው ቦታዎች ማንኛውም አካላት እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

በተለያዩ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከታህሳስ 18 እስከ 21 ድረስ ባሉት ቀናት ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎች ፈተና ውጤት እስካሁን ይፋ ያልተደረገ እና ይፋ የሚደረግበት ትክክለኛ ቀን ያልታወቀ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት #ከሁለተኛ_ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

Photo Credit : ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ

Source
tikvahethiopia