FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.5K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ለ2017/18 የምርት ዘመን 95 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን አስታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦላይ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ2017/18 ዓ.ም የምርት ዘመን  እንደ በቆሎ፣ ስንደ፣ ሩዝ፣ ጤፍና የመሳሰሉትን የሰብል እህሎችን በማልማት የተሻለ ምርት ለማምረት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ትልቁ ተልዕኮ ማሰልጠን ቢሆንም ሀገራችን የያዘችውን የልማት ፖሊሲ ለመደገፍ በመከላከያም ይሁን በስልጠና ዋና መምሪያ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ሰልጣኙን የሠራዊት አባለቱንና የሠራዊቱን ቤተሰብ በኑሮ ለመደገፍ ታሳቢ ተደርጎ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
 
ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ከሰብል እህሎች በተጨማሪ የተለያዩ የፍራፍሬና የጓሮ አትክልት እንዲሁም የማር ምርትና የላም ወተትን ለሠራዊቱ ቤተሰብ በቅናሽ ዋጋ በማቅረብ የኑሮ ድጓማ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ሌተናል ኮሎኔል አሸብር በዛብህ በበኩላቸው ከሚሰጠው ሰልጠና ጎን ለጎን የሠራዊቱን ኑሮ ለመደገፍ ሰፊ የእርሻ ስራ እየሰራን እንገኛለን፤  በዚህም ሠራዊታችንም የሠራዊቱ ቤተሰብም ደስተኛ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል። 

ዘጋቢ ይትባረክ ፀዳሉ
ፎቶ ግራፍ ገነት ሙሌ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
20👍8🔥1
ወለጋ በአስደማሚ የሠላም አየር ላይ ናት ሚስጥሩ ምን ይሆን ?

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
 
ተፈጥሮ አብዝታ ፀጋዋን የቸረችው፤ በከርሠ ምድር እና ገፀ ምድር ሃብት የተንበሸበሸው የወለጋ ምድር ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮጉዱሩ ወለጋ በተሠኙ አራት ሠፋፊ ዞኖች ተዋቅሯል።

ይህ ከባቢ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለይም ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ በአሸባሪው ሸኔ የጥፋት ስትራቴጂ ትግበራ ምክንያት ሠላም ርቆት ቆይቷል። ብቻም ሳይሆን በንፁሃን ላይ ኢ-ሠብዓዊና  ድርጊቶች ተፈፅመውበታል። ንፁሃን ተገድለውበታል፤ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ሆሮጉድሩ ወለጋም የዚህ አስከፊ የታሪክ ገፅታ ሠለባ ብቻም ሳይሆን ዋና ማዕከል ሆኖ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች በሚባል ደረጃ  የአሸባሪው የሸኔ ቡድን እንዳሻው ሲፈነጭ እና የህዝቦችን በጋራ የመኖር እሴት ለማጥፋት ማድረስ የሚችለውን ጥፋት ሁሉ የፈፀመበት አካባቢ እንደነበር ከማንም የተሠወረ አይደለም። የህዝብን ዘመን ተሻጋሪ እሴቶች ጥላሸት ለመቀባትና የህዝቡን የመልማትና የመበልፀግ ጉዞ በማምከን ብሎም ዘልዓለማዊ እድሜ ለመስጠት የጥፋት ቡድኑ ብዙ ርቀቶችን ተጉዟል። ግን አልተሳካለትም።

ወለጋ ዛሬ በአስደማሚ የሠላም አየር ስር በማንሠራራት ጉዞ ውስጥ ይገኛል። በአራቱም የወለጋ ዞኖች ዛሬ የሠላም፣ የተስፋ፣ የልማትና የአብሮነት መልካም መዓዛ ማወድ ጀምሯል። በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ሻምቡ ከተማ በነበረን ቆይታ ይህንኑ መታዘብ ችለናል። የአካባቢው አገር ሽማግሌዎችና የአስተዳደር አካላትንም በአካባቢው ስለተፈጠረው ሠላምና ምክንያቱ ጠይቀን ሚስጥሩ ምን ይሆን ያስባለንን ቋጠሮ ፈተናል።
ሚስጥሩ ምን ይሆን ይቀጥላል...

በሲሳይ ደመቀ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
26👍12🔥1
ማሠልጠኛው የዕዙን አመራር የብቃት ደረጃ የሚያሳድጉ ሥልጠናዎችን እየሠጠ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የደቡብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል አድማሱ አለሙ የዕዙን የአመራር አቅም በየጊዜው በማሳደግ ዕዙ የሚሰጠውን ተልዕኮ በጀግንነት የሚፈፅም በጠንካራ ስልጠና የተፈተነ አመራር ማፍራትና መገንባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ሜጀር ጄኔራል አድማሱ የዕዙን የሠራዊት አባላት በተለያዩ የመሬት ገፅና የአየር ፃባይ ማሰልጠን ፅኑ እምት  ያለው ከአላማው ዝንፍ የማይል እንደ ወርቅ በስልጠና የተፈተነ ግዳጅን ጀምሮ በድል የሚያጠናቅቅ አመራር ለመፍጠር የሚያስችል እንደሆነም ገልፀዋል።

ሰልጣኝ አመራሩ ከግል እስከ ቡድን የነገን ተልዕኮ ታሳቢ ያደረገ ውጤታማ ሥልጠና እየወሰደ እንደሆነም  ተናግረዋል።
     
የማሰልጠኛው ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ቦጋለ ተገኔ በበኩላቸው ማዕከሉ በማሰልጠን የብዙ ጊዜ ተሞክሮ  ያለው በመሆኑ በትኩረት ሰውንና ንብረትን በማቀናጀት ውጊያን መምራት የሚችል ሃይል እያፈራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ዘጋቢ በላይ ታደለ
ፎቶ ግራፍ ቦጋለ አዲሴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
18👏8👍5🔥1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ መከላከያ ማርችንግ ባንድ በሞስኮ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

ሩሲያ ባዘጋጀችው የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ማርችንግ ባንድ ቡድን በሞስኮ የሙዚቃ እና ባህል ትርዒቱን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

ዛሬም የመጀመሪያ ሥራውን ተመልካቹን ባስደመመ ብቃት እና ቀልብን የመያዝ ስሜት አቅርቧል። የሩሲያው የዜና ወኪል ስፑትኒክ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ባህሏን እና ሙዚቃዎቿን በታዋቂው ቀዩ አደባባይ በማስተዋወቅ በሞስኮ ደምቃ ታይታለች፡፡

ኢትዮጵያ በሩሲያ የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ላይ መሳተፏ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና ወታደራዊ የልምድ ልውውጥን ለማሳደግ የሚያግዝም ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
53🏆12🔥3🥰3
የመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ
ውጤታማ ሥራ ማከናወኑን አሥታወቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የ2017 በጀት አመት የሥራ አፈፃፀም ከማዕከል እና ከዕዞች የሰው ሃብት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ የሰው ሃብት አመራር የሰው ሃይሉን በመመልመል በማሰልጠንና በማብቃት በማንኛውም ሁኔታ የሚሰጡ ግዳጆችን በሙሉ አቅም መወጣት የሚያስችል ቁመና የተላበሰ ሠራዊት መገንባት መቻሉን ገልፀዋል።

ሌተናል ጀኔራል አጫሉ ሸለመ የምንሰራቸውን ስራዎች ነጥበን በማስቀመጥ የሚጎድሉትን ክፍተቶች በመለየት እና በተጠያቂነት እዲሁም በታማኝነት መንፈስ በመስራት በበጀት አመቱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ይህንን አቅማችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ በኩልም ለተገልጋዩ የተጣራ መረጃ በመስጠት እና የሰው ሃይል በመቆጣጠር ዳታን በማደራጀትና ሠራዊቱ በግዳጅ ላይ ደስተኛ እንዲሆን በማድረግ በኩል ሁሉም የሰው ሃይል ሙያተኛ በላቀ ደረጃ ስራውን በመስራት ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ  ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ገልፀዋል።                          

በመከላከያ የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ የእድገትና ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል አምሳሉ ኩምሳ በበኩላቸው የሰው ሃብት አመራር ሙያተኞች የተሰጣቸውን ተግባራት በሚገባ ለመወጣት ሁሌም በጥረት እንደሚሠሩ እና ውጤት ማምጣት እንደቻሉ ገልፀው በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ በተቋሙ የተወሰኑ ክፍሎች ላይ የተሳካ ኢንስፔክሽን መደረጉን ተናግረዋል።

በመጨረሻም በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየት የሠራዊቱን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ተችሏል።

ዘጋቢ ትግስት ሙላት   
ፎቶ ግራፈር ዮዲት በዛወርቅ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍3🔥2