FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
34 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የኢትዮጵያ መከላከያ ማርችንግ ባንድ በሩሲያ የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ለመሳተፍ ዛሬ ወደ ሩሲያ ይጓዛል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

ሩሲያ ባዘጋጀችው የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ መከላከያ ማርችንግ ባንድ ቡድን ዛሬ ወደ ሩሲያ እንደሚጓዝ የመከላከያ ሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን አሥታውቀዋል።

የመከላከያ ማርችንግ ባንድ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በዚሁ የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል የሚካፈለው ከሩሲያ በቀረበለት ጥሪ መሠረት መሆኑን የገለፁት ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ቡድኑ ሃምሳ አባላትን የያዘ ሆኖ በዛሬው ምሽት ወደ ሩሲያ እንደሚጓዝም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በሩሲያ የማርችንግ ባንድ ፌስቲቫል ላይ መሳተፏ የሁለቱን ወዳጅ ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና ወታደራዊ የልምድ ልውውጥን ለማድረግ እንደሚያግዝም ገልፀዋል።

በዚሁ ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፈው የመከላከያ ማርችንግ ባንድ ቡድን ከተጋባዥ የአፍሪካ ሀገራት ማርችንግ ባንዶች ጋርም የተሞክሮ እና የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ መልካም አጋጣሚ እንደሚሆንም ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው አሥገንዝበዋል።

የመከላከያ ማርችንግ ባንድ ቡድን በተለይ ባለፉት ሁለት ወራት ለፌስቲቫሉ ሊመጥን የሚችል ጠንካራ ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት ጄኔራል መኮንኑ በማርችንግ ባንዱ ብቻ ሙዚቃ መሥራት በሚያሥችል አግባብ በአዳዲስ ስራዎች ቡድኑ መዘጋጀቱንም አንስተዋል።

የተሻለ ብቃትና ሙያዊ አቅም ይዞ ወደ ሩሲያ የሚጓዘው ቡድን ከሁለት ሳምንታት በላይ የመቆየት ጊዜ እንዳለው የገለፁ ሲሆን ማርችንግ ባንዱ በፌስቲቫሉ መሳተፉ ከቡድኑ አልፎ ለመከላከያ ሠራዊት አንዱ የገፅታ ግንባታ በመሆኑ ሙያተኞች ወደ ሥፍራው የሚጓዙበትን ዓላማ በተገቢው አሳክተው እንዲመለሱ ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን አደራ ሠጥተዋል።

ዘጋቢ ውብሸት ቸኮል
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3525🔥3
መቻል ስፖርት ክለብ ወጣቱን ተጫዋች መሐመድ አበራን አስፈርሟል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

በፕሪምየርሊጉ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ መድህን ቤት ምርጥ ብቃታቸውን ካሳዩና ለዋንጫ ክብር እንዲበቃ ካስቻሉት ተጫዋቾች መካከል አንዱ እና ዋነኛው የሆነው ወጣቱ ኮከብ መሐመድ አበራ ወደ አሳደገው ክለብ መቻል በመመለስ ለቀጣይ ሁለት አመታት ለመቆየት ፈርሟል።

የመቻል እግር ኳስ ቡድን የቀደመ ስሙን ለመመለስ እንዲሁም ተቋሙን እና ደጋፊዎቹ  የናፈቁትን ውጤት ለማስመዝገብ ለ2018 የውድድር አመት ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ውላቸውን የጨረሱ በርካታ ተጫዋቾችን በማሰናበት በምትካቸው ወጣት እና ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች በማሥፈረም ላይ ይገኛል። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2213🔥3
የሠራዊቱን የሳይበር ግንዛቤ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

‎የሠራዊቱን የሳይበር ግንዛቤ በማሳደግ ለሚሰጠው ተልዕኮ ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጅ መሳሪያ በመጠቀም የመረጃ የበላይነትን በመውሰድ ግዳጁን በአሸናፊነት ለመወጣት አጋዥ መሆኑን የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ደረጀ ደመቀ ገልፀዋል ።

‎ጀኔራል መኮንኑ በሳይበር ደህንነት ፣ ምንነትና ሚዲያን መሠረት አድርገው ስለሚፈፀሙ አፍራሽ ፕሮፖጋንዳና ቅስቀሳ ዘመቻዎች እንዲሁም የሳይበር ደህንነቱ በጥንቃቄ ካልተመራ ስለሚያስከትለው ጉዳት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

‎በተለይም አሁን ካለው የውጊያ ቴክኖሎጅ ጋር ተያይዞ  የሳይበር ደህንነት አቅምን በማሳደግና በመገንባት ሃገርንና ተቋሙን ከጥቃት መከላከል እንዲቻል፣ የሠራዊቱን ንቃተ ህሊና በቀጣይነት ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎የሳይበር አውድ እንደ አንድ የጦርነት አውድ እየታየ የመጣ መሆኑን የገለፁት ጀኔራል መኮንኑ ለዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደቱ  የሳይበር ግንዛቤውን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

‎ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
‎ፎቶ ግራፍ ይህ አለም አታላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍10🔥5
በብርሸለቆ ማሠልጠኛ የ42ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
 
የብር ሸለቆ መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 42ኛ ዙር ምልምል ሰልጣኞች ከስልጠናቸዉ ጎን ለጎን በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ሲያካሂዱት የቆየው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቋል።

ስፖርታዊ ዉድድሩ ከሥልጠና ጎን ለጎን በተለያዩ የሥፖርት ዓይነቶች ፣በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ እንዲሁም በገመድ ጉተታ ለሦስት ወራት ሲካሄድ ቆይቶ ፍፃሜዉን ሊያገኝ ችሏል።

በፍፄሜዉ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ለአሸናፊ ቡድኖች ዋንጫ እና ሽልማት የሠጡት የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምክትል አዛዥ ለሰዉ ሃብት አስተዳደር  ኮሎኔል ጌታቸዉ ከበደ ስፖርታዊ ውድድሩ ሲዘጋጅ ዋና አላማዉ ሠልጣኙ እርስ በእርስ እንዲተዋወቅ፣ እንዲግባባ ፣አሃዳዊ ፍቅር እንዲኖረው እና ወታደራዊ ሙያውን እንዲገነዘብ በማሠብ መሆኑን ገልፀዋል።

የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ የሠራዊት ስነ - ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ሌተናል ኮሎኔል ፍቅሬ ዳመነ በበኩላቸው በ42ኛ ዙር ስፖርታዊ ክንዉን ምልምል ሰልጣኝ ተወዳዳሪዎች ስፖርታዊ ዲሲፕሊን ተላብሰው ውድድር ማካሄዳቸው እና በስፖርታዊ ጨዋነት በብርቱ ፍክክር መጨረሳቸው ለየት የሚያደርገው መሆኑን ተናግረዋል።

በውድድሩ በገመድ ጉተታ ሃያ አራተኛ ሻለቃ ሃያ ሁለተኛ ሻለቃን 2ለ0 በመረብ ኳስ ጨዋታ ሠላሳ አንደኛ ሻለቃ አሥራ አንደኛ ሻለቃን 3ለ2 እንዲሁም በእግር ኳስ ጨዋታ ሠላሳ ሁለተኛ ሻለቃ አሥራ አንደኛ ሻለቃን 3ለ2 በመርታት የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችለዋል።

ዘጋቢ ጥላሁን ጌታነህ
ፎቶ ግራፍ እንደግ አበዛው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
43👍8🔥1
የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስረከበ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

የማሰልጠኛ ማዕከሉ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመልካ ሰዲ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስገንብቶ በማጠናቀቅ ለአከባቢው ማህረሰብ አስረክቧል።

ሠራዊቱ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በማጠናከር ባለበት አከባቢው ሁሉ ለማህረሰቡ በመድረስ ምን ጊዜም የማይናወጥ አቋሙን በድጋፍ እያረጋገጠ ይገኛል ።

የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለበርካታ ዓመታት በማገልገል ለመማር ማስተማር ሂደቱ ፈታኝ የነበረውን በመልካ ሰዲ የሚገኝ ሲድሃ ፋጌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ሰርቶ ለአካባቢው ማህረሰብ አስረክቧል።

በቁልፍ ርክክብ ስነ ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉ የሜካናይዝድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል አየለ ወልደ ጊዮርጊስ ምን ጊዜም ለህዝብ እና ለሀገር ቅድሚያ የሚሰጥ ሰራዊታችን ከሚከፈለው የሕይወት መስዋእትነት ጎን ለጎን በእንዲህ ዓይነት በጎ ተግባር በመሳተፍ ለሀገር እድገት ስኬት ጉዞ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሲድሃ ፋጌ ቀበሌ መስተዳድር አቶ አብዱ አሊ ሰራዊቱ ከህዝብ አብራክ ወጥቶ ለህዝብ የሚያገለግል እውነተኛ ህዝባዊ ሰራዊት መሆኑን በተግባር አረጋግጧል ብለዋል ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍10🔥3👏2