FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.7K photos
33 videos
9 files
8.49K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እየተገነባ የሚገኘውን  የሠራዊት መኖሪያ ቤት ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስቴር  ሚኒስትር  ክብርት ኢንጂነር  አይሻ መሐመድ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን እየተገነባ የሚገኘውን ጋሻ የሰራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ሂደቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከጥቂት አመታት በፊት የአልሙኒየም ፍሬም ወርክ ቴክኖሎጂን መጠቀም የማይቻል እንደነበር አስታውሰው ዛሬ በአልሙኒየም ፍሬም ወርክ ቴክኖሎጂ የተሰራ የቤት ግንባታ ለማየት በቅተናል ብለዋል።

ሚኒስትሯ የአልሙኒየም ቴክኖሎጂ በዋጋ፣በጥራት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያለው አበርክቶ ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸው በፕሮጀክቱ እየተሳተፋ ለሚገኙ ሙያተኞች እና አመራሮች እየሠሩ ላለው ፈጣን እና ጥራት ያለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱን አስመልክተው ገለፃ ያደረጉት የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ደረጃ መገርሳ ጋሻ የሰራዊት የጋራ መኖሪያ ቤት በ26ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ 16 ህንፃዎችን የሚያካትት መሆኑን ገልፀው ግንባታው የሠራዊት መኖሪያ ፍላጎትን ከማሟላት በተጨማሪ ለሠራዊት የግዳጅ አፈፃፀም የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ስለ ግንባታው ሂደት ገለፃ ያደረጉት የፕሮጀክቱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ይርጉ አደራ የሰራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤት በውስጡ ባለ አንድ፣ባለ ሁለት እና ባለ ሶስት መኝታ ቤቶችን ያካተተ መሆኑን ገልፀው ግንባታውም በፍጥነት እና በጥራት እየተገነባ መሆኑን ገልፀዋል።
 
ዘጋቢ ደበላ ዲንሳ
ፎቶግራፍ እፀገነት ደቢሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
45👏5🔥3👍2
የማዕከላዊ ዕዝ ክፍለጦር የምስረታ በዓሉን አከበረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

‎በማዕከላዊ ዕዝ አብድሳ አጋ ክፍለጦር የተመሰረተበትን 3ኛ ዓመት በዓሉን ያከበረ ሲሆን በጀግንነት ሀገሩን ያፀና የሀገር ባለውለታ ክፍለጦር መሆኑ ተገልጿል።

‎በዕለቱ በክብር እንግድነት ተገኝተው አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ ክፍሎች እና አባላት ሽልማት ካበረከቱ በኋላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጄኔራል አብድሮ ከድር ክፍለጦሩ ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት ላስመዘገበው አንፀባራቂ ድል ምስጋና  አቅርበዋል።

‎በሰሜኑ ህግ የማስከበር ዘመቻ ተመስርቶ ከአጋር ክፍሎች ጋር በመሰለፍ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት በአመርቂ ገድል ተወጥቷል ያሉት ጄኔራል መኮንኑ የሌተናል ኮሎኔል አብድሳ አጋ ክፍለጦር የጀግና ስያሜ ወርሶ የኢትዮጵያን ጠላቶች ተጋፍጦ ያንበረከከ ጠንካራ አሀድ መሆኑን ገልፀዋል።

‎የአብድሳ አጋ ክፍለ ጦር የሰሜኑ ጦርነት በድል ከተቀለበሰ በኋላ ወደ ኦሮሚያ ክልል በማቅናት የኦነግ ሸኔን የሽብር ቡድን በመደምሰስና የቡድን መሳሪያውን በመማረክ በቄለም ወለጋ ዞን አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍንና የመሰረተ ልማት ተቋማት ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ችሏል ያሉት ሜጄር ጄኔራል አብድሮ ከድር ክፍለጦሩ አስተማማኝ የሰላም ዘብ ሆኖ መቀጠል እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።

‎ክፍለጦሩ በውጊያ መሀል ተፈጥሮ ሀገሩን ያሻገረ የጀግኖች መፍለቂያ ነው ያሉት የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ተገኝ አሊ ናቸው።

‎ከማዕከላዊ ዕዝ ኮሮች ፣ክፍለጦሮችና ከሰላም ማስከበር በተመለሱ አባላት የተቋቋመው  ክፍለጦሩ የተገነባበትን ሀገራዊና ተቋማዊ ተልዕኮ በድል አድራጊነት መወጣቱን ገልፀዋል።

‎በዕለቱ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሲሉ ህይወታቸውን ለሰጡ የዞንና የወረዳ ሚሊሺያ ቤተሰቦች የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን በባዕሉ ላይ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፣የፌዴራልና የክልል የፀጥታ አካላት፣ አባገዳዎች ፣ ሀደ ስንቄዎች እና የቄለም ወለጋ ዞን ነዋሪዎች በምስረታ ተገኝተዋል። ዘጋቢ መሀመድ አህመድ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
36👍10🔥2
ጤና ይስጥልን ጥቂት ሥለ ጤናዎ ሲጋራ ማጨስ ጤናን የሚፈታተን ስውር ጠላት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 11 ቀን 2017 ዓ.ም

ሲጋራ ማጨስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የሚዳርግ ሲሆን፣ ይህም በአማካይ በየ4 ሰከንዱ አንድ ሰው በትንባሆ ምክንያት ህይወቱን ያጣል ማለት ነው። ከዚህ ውስጥ ከ80% እስከ 90% የሚሆነው የሳንባ ካንሰር ሞት ከማጨስ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። አጫሾች በልብ ሕመም (stroke) የመያዝ እድላቸው ከማያጨሱት ከ2 እስከ 4 እጥፍ ይበልጣል፤ እንዲሁም ሥር በሰደደ የሳንባ ምች በሽታ (COPD) ከሚሰቃዩ 10 ሰዎች ውስጥ 8ቱ አጫሾች ናቸው።

በአማካይ፣ ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱት ቢያንስ 10 ዓመት ቀድመው እንደሚሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ (WHO FCTC 2023)። ይህ ከባድ የህብረተሰብ ጤና ቀውስ በተለይ ከፍተኛ አካላዊ ጥንካሬ፣ አእምሮአዊ ቅልጥፍና እና የስነ-ልቦና ጽናትን በሚጠይቀው የውትድርና ማህበረሰብ ውስጥ ሲታይ የሚያስከትለው መዘዝ የበለጠ ጥልቅ እና አሳሳቢ ይሆናል። በመሆኑም ሲጋራ ማጨስ የወታደሩን ግላዊ ጤና ከመጉዳት ባለፈ የመላው ሰራዊቱን የውጊያ ዝግጁነት እና ውጤታማነት አደጋ ላይ የሚጥል ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው።

የዚህ አውዳሚ ተጽዕኖ ሥር መሰረት ያለው በሲጋራ ጭስ ውስጥ በሚገኙ ከ7,000 በላይ ኬሚካሎች ውህድ ውስጥ ነው። ከእነዚህም መካከል እንደ ኒኮቲን፣ ካርቦን ሞኖክሳይድ እና ታር (ቅጥራን) ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች በወታደሩ አካል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት ይሰነዝራሉ። ለምሳሌ፣ ካርቦን ሞኖክሳይድ በቀይ የደም ሴሎች ውስጥ ኦክስጅንን በመተካት በሰውነት ውስጥ ያለውን የኦክስጅን መጠን በእጅጉ ይቀንሳል።

ይህ የልብ ምትንና የአተነፋፈስን ፍጥነት እንዲጨምር በማድረግ ልብና ሳንባ ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል። በዚህም ምክንያት የሚያጨሱ ወታደሮች በከፍተኛ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ወቅት ቶሎ የመድከም እና የትንፋሽ ማጠር ችግር ያጋጥማቸዋል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሲጋራ የሚያጨሱ የሰራዊት አባላት ከማያጨሱት ጋር ሲነፃፀሩ በሩጫ እና በሌሎች የአካል ብቃት መመዘኛዎች ላይ ያላቸው ብቃት ከ5-10% የቀነሰ ነው። ጉዳቱ በልብና በሳንባ ብቻ አያበቃም።

ሲጋራ ማጨስ ወደ ጡንቻዎች የሚደርሰውን የደም እና የኦክስጅን ፍሰት ስለሚቀንስ የጡንቻን ጥንካሬና ጽናት ያዳክማል። ከዚህም ባሻገር ኒኮቲን የአጥንትን እድገት እና ጥንካሬ የሚቆጣጠሩትን ህዋሳት ተግባር በማስተጓጎል የአጥንት ጥግግት እንዲቀንስ ያደርጋል። በዚህም ምክንያት የሚያጨሱ ወታደሮች በተለይም በስልጠና እና ከባድ እንቅስቃሰ ወቅት ለሚከሰቱ የአጥንት ስብራቶች (stress fractures) እና ሌሎች ጉዳቶች ያላቸው ተጋላጭነት ከማያጨሱት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው።

ከእነዚህ ቀጥተኛ አካላዊ ጉዳቶች ባሻገር፣ ሲጋራ ማጨስ የወታደራዊ ዝግጁነትን መሰረቶች በስርዓት ይሸረሽራል። የአንድ ወታደር አካል ዋነኛ መሣሪያው ሲሆን፣ ሲጋራ ማጨስ ግን የዚህን መሣሪያ ዋነኛ መከላከያ የሆነውን የበሽታ መከላከል አቅምን ያዳክማል። ይህም ወታደሮችን እንደ ብሮንካይተስ እና የሳንባ ምች ላሉ የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽኖች በስፋት ከማጋለጡም በላይ፣ የሰውነትን የመፈወስ ሂደት ስለሚያዘገይ ከጉዳት በኋላ የማገገሚያ ጊዜን ያራዝማል። አንድ ጥናት እንዳመለከተው የሚያጨሱ ወታደሮች ከማያጨሱት ጋር ሲነጻጸር በበሽታ ምክንያት ሆስፒታል የመታከም እድላቸው በ30% ይበልጣል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👏16👍8🔥2😁1