FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
32 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የሠራዊቱን የጤና ተደራሽነት ሥርዓት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እና በኮሌጁ የሚማሩ ከፍተኛ መኮንኖች የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ግሩፕና ዲያግኖስቲክስ ማዕከል ጎብኝተዋል።

በዕለቱ የተገኙት የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል ጥጋቡ ይልማ፤ የሠራዊቱን ተልዕኮ ከሚያሳልጡና ለድል ከሚያበቁ መሰረታዊ ነገሮች ዋናው ሠራዊቱ ጤናው የተጠበቀ ሆኖ መገኘት እንደሆነ ተናግረዋል።

በሁሉም አቀፍ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት አገልግሎት አሠጣጥን ለማሳደግ በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ የህክምና ቴክኖሎጂ ማሣደግ ዋና ጉዳይ መሆኑን ገልፀው በዚህም የተሻለ ሥራ እንደተቋም መሠራቱን አንስተዋል።

የሠራዊቱን ጤንነት መከታተል እና ስነ-ልቦናዊ ሁኔታ ማሣደግ እንደሚገባ ያመላከቱት ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ተቋሙ በህክምና ቴክኖሎጂው ዘርፍ አሁን የደረሰበትን ደረጃ ማወቅ ተገቢ እንደሆነም አሥረድተዋል፡፡

በየደረጃው የጤና ተደራሽነት በማስፋፋት እና የጤና ሙያተኞችን አሠልጥኖ በማብቃት ረገድ ብዙ ሥራዎች ተግባራዊ ሥለመሆናቸውም አንስተዋል። ዘገባው የማዕከሉ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1513👏5🔥1
ዕዙ የጥገና ሙያተኞችን አሰልጥኖ አስመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ ጥገና ክፍል ከሁሉም ኮሮች፣ክፍለጦሮችና ሬጅመንቶች የተውጣጡ የጥገና ሙያተኞችን በሁለገብ የሙያ ዘርፍ ለ6 ወራት አሰልጥኖ አስመረቀ።

በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት የዕዙ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ብርጋዲየር ጀኔራል መኮንን በንቲ ዕዙ የተሰጠውን ተልዕኮ በተፈለገው ጊዜና ቦታ ያለምንም እንከን በአሸናፊነትና ድል አድራጊነት መፈፀም እንዲችል የጥገና ክፍሉን አቅም ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የዕዙ ጥገና ክፍል ሃላፊ ኮሎኔል ከበደ ንጋቱ በበኩላቸው ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው በመካኒክ፣በኤሌክትሪሻል ፣በብየዳ፣በመሳሪያ በዳቦ ማሽንና በጀኔሬተር በተግባርና በንድፈ ሃሳብ የተደገፈ ስልጠና ወስደው በቀጣይ መስራት የሚያስችላቸውን በቂ ሙያዊ አቅም ፈጥረው ለምረቃ መብቃታቸውን አብራርተዋል።

ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ይህ አለም አታላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏1615👍11🔥3
የጥገና ክፍሉ ችግር ፈቺና መፍትሄ አምጭ የፈጠራ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለፀ።

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

‎የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል ሎጀስቲክስ በውጊያና በተለያዩ ግዳጆች ደጀን በመሆን ከፍተኛ የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት እንደሚሠጥ ተናግረዋል። የጥገና ክፍሉም በውጊያ ቦታም ሆነ በሌሎች ዘርፎች አሥፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የማይተካ ሚና የሚጫወት ችግር ፈቺ  መፍትሄ አምጭ መሆኑንም አንስተዋል።

‎በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሜንቴናንስ መምሪያ ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል በርሄ ገብረ መድህን ሜንቴናንስ መምሪያ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን በራስ አቅም በመፍጠር ተቋሙን ከበጀት ብክነት መታደግ  የቻለ ሥለመሆኑ ተናግረዋል።

‎የተቋሙን ትጥቅና የተኩስ አቅም በማዘመን የሠው ሃይል በማብዛት ተተኪ ሙያተኞችን በማፉራት ችግር ፈቺ እና ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሠራታቸውን የገለፁት የመምሪያ ሃላፊው ቆራጥ እና ብቃት ያለው በራሱ የሚተማመን በተግባር የተፈተነ ባለሙያ መፍጠር መቻሉንም ገልፀዋል።

‎በዕለቱ በሥራ አፈጻጸማቸው የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ የመምሪያው አባላት የምስጋና እና የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

‎ዘጋቢ ወርቅነህ ተስፋው
‎ፎቶግራፍ በድሩ መሀመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
47👍21🔥3👏3
ዓለም-ዓቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ለሴት መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖች ስልጠና ሠጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 09 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ለመከላከያ ሴት መስመራዊ እና ከፍተኛ መኮንኖች በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ለ3 ቀናት ያሠለጠናቸውን ሰልጣኞች አስመርቋል።

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ከዓለም-አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በጋራ በመስራታችን ደስተኞች ነን ብለዋል። ዛሬም ከፆታዊ እና ከወሲባዊ ጥቃት አንፃር ራስን ለመከላከል ምን ማድረግ አለብን በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ጥሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሥጠታቸው አመሥግነዋል።

ከመከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች እና እዞች የተውጣጡት ሰልጣኞቹ በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ በተለይም በጦርነት ጊዜ ሴቶች እና ህፃናት ራሳቸውን ከፆታዊ እና ወሲባዊ ጥቃት መከላከል በሚችሉባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና መውሰዳቸው ከሙያቸው ባህሪ አንፃር ጠቃሚ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከሰልጣኞች መካከል ሻምበል እመቤት ጌታቸው እንደ አንድ ሴት የመከላከያ አባል ይህን ስልጠና በመካፈሌ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለሌሎች ጓዶች ለማከፈልም ፈቃደኛ ነኝ ብለዋል።

ሰልጣኞቹ ከየዕዞች እና ከመከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊዎች ሲሆኑ ስልጠናውን የወሰዱት ሰልጣኞች ሰልጠናው የሚያሰልጥኑ አሰልጣኞች ናቸው። ሰራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ስልጠናው እንዲዳረስ ስልጠኞች አስተዋፅኦቸው የጎላ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ ዕፀገነት ዴቢሰ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27👍7🔥2